FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.6K photos
32 videos
9 files
8.48K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ጠንካራ ወታደራዊ ሥልጠና ግዳጅን በድል ለመወጣት እንደሚያሥችል ሌተናል ጀኔራል ይመር መኮነን ገለፁ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 08 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ሃላፊ  ሌተናል ጀኔራል ይመር መኮንን በደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል በስልጠና ላይ ለሚገኙ አመራሮች ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
   
ጄኔራል መኮንኑ በየደረጃው የሚገኘውን የሠራዊታችንን አመራሮች በተደጋጋሚ በማሰልጠን የአመራር ችሎታውን ማሳደግ ተችሏል ብለዋል። ጠንካራ ወታደራዊ ስልጠና ግዳጅን በድል ለመወጣት እንደሚያስችል ገልፀው በዚህም የሃገርን ሰላምና የአሃድን ደህንነት ማስጠበቅ  እንደተቻለ ተናግረዋል።
  
አሁን ላይ የሃገራችንን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ በስልጠና የበቃ የመከላከያ ኃይል መገንባቱን የተናገሩት ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮነን አመራሩ ተልዕኮውን  የሚረዳና ግዳጅን በአግባቡ የሚወጣ የተሰጠውን  ንብረትና የሰው ኃይል አቀናጅቶ በመምራት ደህንነትን በመጠበቅ በታጠቀው መሳሪያ የመጠቀም ችሎታ ያለው አዋግቶ ድል ማምጣት የሚችል ሥለመሆኑም አስገንዝበዋል።
   
ተቋሙ የዘመኑን ቴክሎጂ ውጤቶች የሚጠቀም ከዘመኑ ጋር የሚራመድ ፕሮፌሽናል ሠራዊት መገንባቱን የገለፁት ጄኔራል መኮንኑ በወታደራዊ ስነ-ምግባር  የታነፀና በዓላማው የፀና ሥለመሆኑም አንስተዋል።
    
ሠራዊታችን ለማንኛውም ግዳጅና ሁኔታ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ ወታደራዊ አቅሙን ለማሣደግ በንድፈ ሃሳብና በተግባር በማሰልጠን የማድረግ ችሎታውን ከፍ ማድረግ እንደተቻለም አስረድተዋል።

ፈጣንና ተነቃናቂ ተልዕኮውን በብቃት መወጣት የሚችል በአካል ብቃት፣ በስነ- አዕምሮው የዳበረ ፣ሞራል ያለው ኃይል መገንባቱን የገለፁት ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮነን በቀጣይም ዘመናዊ ሠራዊት የማፍራቱ ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል፡፡

ዘጋቢ በላይ ታደለ
ፎቶ ግራፍ ቦጋለ አዲሴ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
27👏13👍6👎1
የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ ለሠራዊቱ አቅም ግንባታ  ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 08 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ አመራሮችና የአካዳሚ ስታፍ አባላት በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ከባለድርሻ አካላት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ እያካሄዱ ይገኛሉ።

በውይይቱ የየክልሉ ከተማ አስተዳደሮች የፀጥታ ተቋማት የዕዝ አመራሮች የመከላከያ ሠራዊት አባላት ተገኝተዋል።

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ አላማና ተልዕኮውን ለማሳካት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

ባለድርሻ አካላት የኮሌጁን ቁመና የማስተማር አቅም  መረዳት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የኮሌጁ አመራሮችና የአካዳሚ ክፍሉ አባላት በሲዳማ፣ በአፋር  በሀረሪ፣ በዲ
ድሬዳዋ ፣በጋምቤላ፣ በአማራ ክልሎች በመዘዋወር ለክልል አመራሮችና ለከተማ መስተዳድሮች እንዲሁም ለዕዝ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጡ ይገኛሉ።

አጠቃላይ ወደ ኮሌጁ የሚመለመሉና ተምረው ሲመረቁ ባገኙት የአመራር ብቃት ሀገራቸውን ማገልገል በሚያስችል የአመራር ጥበብ ተክነው እንዲወጡ ኮሌጁ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በአለማቀፋዊና አህጉራዊ እንዲሁም ቀጠናዊ  ጆኦ-ፖለቲካ የኢትጵያን  ጥቅም ማስጠበቅ በሚያስችል መንገድ መቃኘት እንዳለበትም ተገልጿል።

ዘመናዊ ሰራዊት መገንባት የሠራዊታችንን አቅም ከማሳደጉም ባሻገር  ለሀገራዊ ጥቅም አስቻይ ሁኔታ በመፍጠር ሀገረ-መንግስትን ማፅናት የሚችል አመራር መፍጠር እንደሚቻልም ተነስቷል። 

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ የመከላከያ ዋር ኮሌጅ የመከላከያ ስትራቴጂክ አመራሮችን ከማስተማርና ከማስልጠን በተጨማሪ ከየክልሉ ተመልምለው የሚመጡ የሲቪል አመራሮችን  አስተምሮ በማስመረቅ ሀገራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ ያለ ኮሌጅ እንደሆነ አስረድተዋል። ዘጋቢ አሰፉ ግርማይ ናት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
37👍16
የሠራዊቱን የጤና ተደራሽነት ሥርዓት ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 08 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች እና በኮሌጁ የሚማሩ ከፍተኛ መኮንኖች የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ግሩፕና ዲያግኖስቲክስ ማዕከል ጎብኝተዋል።

በዕለቱ የተገኙት የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል ጥጋቡ ይልማ፤ የሠራዊቱን ተልዕኮ ከሚያሳልጡና ለድል ከሚያበቁ መሰረታዊ ነገሮች ዋናው ሠራዊቱ ጤናው የተጠበቀ ሆኖ መገኘት እንደሆነ ተናግረዋል።

በሁሉም አቀፍ የጤና አጠባበቅ ሥርዓት አገልግሎት አሠጣጥን ለማሳደግ በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ የህክምና ቴክኖሎጂ ማሣደግ ዋና ጉዳይ መሆኑን ገልፀው በዚህም የተሻለ ሥራ እንደተቋም መሠራቱን አንስተዋል።

የሠራዊቱን ጤንነት መከታተል እና ስነ-ልቦናዊ ሁኔታ ማሣደግ እንደሚገባ ያመላከቱት ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ ተቋሙ በህክምና ቴክኖሎጂው ዘርፍ አሁን የደረሰበትን ደረጃ ማወቅ ተገቢ እንደሆነም አሥረድተዋል፡፡

በየደረጃው የጤና ተደራሽነት በማስፋፋት እና የጤና ሙያተኞችን አሠልጥኖ በማብቃት ረገድ ብዙ ሥራዎች ተግባራዊ ሥለመሆናቸውም አንስተዋል። ዘገባው የማዕከሉ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።
 
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍1513👏5🔥1
ዕዙ የጥገና ሙያተኞችን አሰልጥኖ አስመረቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 08 ቀን 2017 ዓ.ም

የ6ኛ ዕዝ ጥገና ክፍል ከሁሉም ኮሮች፣ክፍለጦሮችና ሬጅመንቶች የተውጣጡ የጥገና ሙያተኞችን በሁለገብ የሙያ ዘርፍ ለ6 ወራት አሰልጥኖ አስመረቀ።

በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው የስራ መመሪያ የሰጡት የዕዙ ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ብርጋዲየር ጀኔራል መኮንን በንቲ ዕዙ የተሰጠውን ተልዕኮ በተፈለገው ጊዜና ቦታ ያለምንም እንከን በአሸናፊነትና ድል አድራጊነት መፈፀም እንዲችል የጥገና ክፍሉን አቅም ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።

የዕዙ ጥገና ክፍል ሃላፊ ኮሎኔል ከበደ ንጋቱ በበኩላቸው ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው በመካኒክ፣በኤሌክትሪሻል ፣በብየዳ፣በመሳሪያ በዳቦ ማሽንና በጀኔሬተር በተግባርና በንድፈ ሃሳብ የተደገፈ ስልጠና ወስደው በቀጣይ መስራት የሚያስችላቸውን በቂ ሙያዊ አቅም ፈጥረው ለምረቃ መብቃታቸውን አብራርተዋል።

ዘጋቢ ደባልቅ አቤ
ፎቶ ግራፍ ይህ አለም አታላይ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👏1615👍11🔥3