FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.6K photos
32 videos
9 files
8.48K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች የሎጀስቲክስ ክፍሎችን ጎበኙ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 07 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ትምህርታቸውን በኮሌጁ እየተከታተሉ የሚገኙ ከፍተኛ መኮንኖች በሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ ቆሬ የሚገኘውን የጥገና መምሪያን፣ የገመኔ ትራንስፖርትን እና የመልካ ቃሊቲ የሎጅስቲክስ ክፍሎችን ጎብኝተዋል።

ጀግኖችን መፍጠር የማይታክታት ታላቅ ሀገር እንዲሁም የግዙፍና ጠንካራ ተቋም ፍሬዎች በመሆናችሁ ልትኮሩ ይገባል ሲሉ በዕለቱ የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጀነራል አብዱራህማን እስማኤል ተናግረዋል።

የዋና መምሪያ ሃላፊው ሎጀስቲክስ የተቋማችንን ሀብት አቅቦ በመንከባከብ እያሻሻለና እያዘመነ የሚያስታጥቅ፤ እንዲሁም በሳይንሳዊ መንገድ እያቀደ ስራውን የሚያሳካ ክፍል እንደሆነ ተናግረዋል።

የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ሙሉጌታ አምባቸው በበኩላቸው የማዕከላቱ ግንባታ የተቋሙን ዝግጁነት እንደሚያሳድግ ጠቅሰው፤ ሎጀስቲክስ በተቋም የሚገኝ የሃገር ሀብት ነው ብለዋል።

በምግብ ራስን የመቻል ተቋማዊ ዕቅዳችንን በሚያፋጥን መልኩ በአሳ፣ በማር፣ በዶሮ እንዲሁም ስንዴና በሚበሉ ፍራፍሬዎች በዋና መምሪያው አመርቂ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

የማዕከላቱን የቀድሞ ገፅታ ያሥታወሱት ኮሎኔል ድንበሩ ደጀኔ አሁን መከላከያን የሚመጥን የሎጀስቲክስ ማዕከል መገንባቱ ስራን ለማቀላጠፍ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብላዋል።

ሌተናል ኮሎኔል አብርሃም ቻሌ በበኩላቸው የኮሊደር ልማቱን አርአያ ተከትለው የተገነቡት ለትውልድ የሚተላለፉ ድንቅ ስራዎች መሆናችውን አንስተዋል።

ዘጋቢ ዳዊት ብርሃኑ
ፎቶግራፍ ወንድሙ መድህን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
35👍9🔥3👏2
ተልዕኮ ተኮር የመስክ ላይ ሥልጠናዎች ለላቀ ግዳጅ አፈፃፃፀም ጉልህ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 07 ቀን 2017 ዓ.ም

በዩናሚስ ሴክተር ኢስት ግዳጁን እየፈፀመ ለሚገኘው የ20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ሲሰጥ የነበረው ተልዕኮ ተኮር የመስክ ላይ ስልጠና ልምምድ ተጠናቀቀ።

የመስክ ላይ ስልጠና ልምምዱን የመሩት በደቡብ ሱዳን የሴክተር ኢስት አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል ራዛቅ አህመድ በዩናሚስ የሚሰጡ ተልዕኮ ተኮር ስልጠናዎች በማንኛውም ወቅት የሚኖሩ ግዳጆችን በብቃት ለመፈፀም ጉልህ ሚና አላቸው በማለት ተናግረዋል።

የተሰጠው ስልጠና እንደ አንድ ዓለም አቀፍ የሰላም አስከባሪ ሠራዊት ተልዕኮን በአስተማማኝ መንገድ ለመፈፀም የሚያስችል አቅምን ለመገንባት ይረዳል ያሉት የሴክተር ኢስት አዛዡ ብርጋዲየር ጀነራል ራዛቅ አህመድ በተለይ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሠራዊት በቀጠናው ያለውን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ እያበረከተ ያለውን ጉልህ ድርሻ የበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥል የመስክ ስልጠና ልምምድ ለቀጣይ ሥራ ተደማሪ አቅምን እንደሚፈጥርም አስገንዝበዋል።

የ20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ሰጥየ አራጌ በበኩላቸው ሥልጠናው በተያዘው ዕቅድ መሠረት መከናዎኑን ጠቅሰው እንደ አንድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የተሰጠው ሥልጠና ከተልዕኳችን ጋር በቀጥታ ተያያዥነት ያለው ሲሆን በሥልጠና የተገኘውን አቅም ይበልጥ በመጠቀም ግዳጅን በውጤት ለመፈፀም ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል በማለት  አጽንኦት ሰጥተዋል።  ዘጋቢ አንዋር ሁሴን ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
32👍10🔥2
ሚስጢራዊነቱ የተጠበቀ ግንኙነት ለመመስረት የግንኙነት ስርዓቱን ማዘመን ተገቢ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 07 ቀን 2017 ዓ.ም

ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ ስታፍ ከፍተኛ መኮንኖችና መስመራዊ መኮንኖች ሚስጥራዊነቱን የጠበቀ የግንኙነት ዘዴ መጠቀም በሚያስችሉና በተቋሙ በበለፀጉ መተግበሪያዎች የግንኙነት ሲስተም ዙሪያ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል።

ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ የግንኙነት ስርዓትን ለመመስረት የግንኙነት ስርዓቱን ማዘመንና ዲጂታላይዝድ ማድረግ እንደሚገባ ነው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ መገናኛና ኢንፎርሜሽን መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ወርቅነህ ነዳሳ የገለፁት።

አንድ መልዕክት ለብዙ ባለድርሻ አካላት ፈጣንና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ሚስጥራዊነቱ ተጠብቆ እንዲደርስ የሚያስችሉ የግንኙነት ዘዴዎች ላይ አመራሩ ግንዛቤ እንዲያገኝ የሚያስችል ስልጠና ስለመሆኑም ኮሎኔል ወርቅነህ ነዳሳ ተናግረዋል።

በአውት ሉክና በሰርኩኒ የሚደረጉ የግንኙነት ዘዴዎች የግንኙነት ስርዓታችንን ከአናሎግ ወደ ዲጅታል ሲስተም የሚያሻግር ነው ያሉት ኮሎኔል ወርቅነህ ነዳሳ የእነዚህ አፕልኬሽኖች ፋይዳ ተቋሙ ባበለፀገው ዌብሳይት የምንጠቀም በመሆኑ ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀና አስተማማኝም ነው ብለዋል።

ዲጅታል የግንኙነት ስርዓትን መመስረትና መጠቀም መልዕክቶቹ በሰከንዶች ለባለ ድርሻ አካላት  ከመድረሳቸውም ባሻገር ወጪ ቆጣቢ ፣ደህንነቱ የተጠበቀ፣ጊዜና ጉልበትን የሚቆጥብ ፈጣንና አስተማማኝ ስለመሆኑም በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ ተገልጿል።

በተቋሙ የተፈቀደላቸው አካላት የጋራ መልዕክቶችን ለመላክ ለመቀበል እና በአንድ ጊዜ ለብዙ ባለድርሻ አካላት የፅሁፍ፣የድምፅና የቪዲዮ መልዕክቶችን ለመለዋወጥ የሚያስችሉ አፕልኬሽኖች ስለመሆናቸውም በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተጠቁሟል።

ስልጠናው ከንድፈ ሃሳብ ባሻገር በተግባር ልምምድ የተደገፈና በአጭር ጊዜ ወደ ትግበራው ለመግባት በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ነው።
ዘገባው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
47👍20🔥3
ክፍለጦሩ ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ በርካታ መሳሪያዎች መማረኩን አሥታወቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 07 ቀን 2017 ዓ.ም

የማዕከላዊ ዕዝ አይበገሬ ክፍለጦር በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ቶሌ ወረዳ በርካታ የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎችን እና ተተኳሾችን መማረኩን የክፍለጦሩ ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ሌተናል ኮሎኔል ወልደ ገርማ ብርሃኔ ገልፀዋል።

ክፍለጦሩ በተሠማራባቸው ቀጠናዎች የሽብር ቡድኑን እግር በእግር ተከታትሎ በመደምሰስ ለዘረፋ ሲጠቀምበት የነበረውን መሳሪያና ተተኳሽ በመማረክ ቡድኑን ከጥቅም ውጪ ማድረግ መቻሉንም አሥረድተዋል።

ሠራዊቱ በየጊዜው በሚያደርገው የተቀናጀ ዘመቻ የአሸባሪውን የዘረፋ ተግባር በማክሸፍ እና ከህዝቡ ነጥሎ በመምታት በርካቶችን ሙትና ቁስለኛ ማድረጉንም ምክትል አዛዡ ተናግረዋል።

ዘጋብ ፍቃዱ አበራ
ፎቶግራፍ ዘውዱ አቡኔ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
62👍29👏5🔥4🕊3
የኢትዮጵያ ሠራዊት ለሀገር እና ለህዝብ ክብር ራሱን አሳልፎ የሠጠ ነው።
    ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 08 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሠራዊት ለህዝቦችና ለሀገር እንዲሁም ለሠንደቅ ዓላማው ክብር ራሱን አሳልፎ የሠጠ በጠንካራ ሀገራዊ ፍቅር የተገነባ መሆኑን የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ገልፀዋል።

አዛዡ ዕዙ የአቅም ግንባታ ስልጠና አየሠጣቸው ለሚገኙ የሻምበልና የሬጅመንት አመራሮች በሠራዊት ግንባታ ሂደትና አቅጣጫ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል።

የማይሸነፍ ዘመናዊና ጠንካራ ሠራዊት መሠረቱ የጠንካራ አመራር የግንባታ ስራ ውጤት መሆኑን የገለፁት አዛዡ እያንዳንዱ መሪ ይህንን ተገንዝቦ የማያቋርጥ እና ከዕለት ዕለት አየዳበረ የሚሄድ የሠራዊት ግንባታ ስራን መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ሠራዊቷን የምትገነባበት የራሷ የሆነ መልካም ዕሴት ያሉት ሀገር መሆኗን የገለፁት ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ የዜጎችን ክብርና ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅና ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ የሆነ ሠራዊት መገንባት የመሪው የዘወትር ስራ መሆኑን አስረድተዋል።

አዛዡ በአንድ ሀገር ዴሞክራሲያዊ ስርአት ስር ሰዶ የሚያብበው ጠንካራ ሠራዊት ሲኖር መሆኑን ጠቁመው ይህ ከልሆነ ግን አምባገነኖችና የባዕዳን ተፅዕኖ ያረፈባቸው ተላላኪዎች የህዝብን የስልጣን ባለቤትነት በመቀማት መከራን እንደሚዘሩ ሩቅ ሳንሄድ ጎረቤቶቻችን አስረጅ ናቸው ብለዋል።

የሀገሩንና የህዝቡን ፍላጎትና ብሔራዊ ጥቅም ጠንቅቆ የሚያውቅ ሊመጡ የሚችሉትን አደጋዎች ተረድቶ በላቀ ሀገራዊ ፍቅር የኢትዮጵያንና የህዝቦቿን ብሔራዊ ጥቅም የሚጠብቅ ፕሮፌሽናል ሰራዊት የመገንባቱ ስራ አጠናክሮ መቀጠል በየደረጃው የሚገኝ አመራር ሃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።

በስልጠና ላይ የሚገኙ የክፍሉ አመራሮችም ተቋሙ እየሠራ ያለውን የፕሮፌሽናል ሠራዊት ግንባታን በማጠናከር የለማች ኢትዮጵያንና በትውልድ ቅብብሎሽ  ለቀጣዩ ትውልድ ለማሸጋገር ያለመታከት እንደሚሠሩ በመድረኩ አረጋግጠዋል። ዘገባው የአብዱራህማን ሀሰን ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
39👍15👏10🔥2👎1