FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.6K photos
32 videos
9 files
8.48K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ምስራቅ ዕዝ የሀገር ሉዓላዊነትን የማስጠበቅና ሰላምን የማረጋገጥ ግዳጅን አጠናክሮ ቀጥሏል።
   ሌተናል ጀነራል መሐመድ ተሰማ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሐሴ 06 ቀን 2017 ዓ.ሞ

የምስራቅ ዕዝ 48ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በሐረር ከተማ ኢማም አህመድ ስታድዬም በስፖርት ፌስቲቫል መከበር ጀምሯል።

በበዓሉ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የዕለቱ የክብር እንግዳ ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ተሰማ ምስራቅ ዕዝ ለሀገር ሉዓላዊነትና ለህዝቦች ደህንነት መከበር ከፍተኛ ተጋድሎ ካደረጉ ዕዞች መካከል አንዱ መሆኑን አውስተው ዕዙ የ48ኛ የምስረታ በዓሉን ለመዘከር ዋዜማው ላይ ይገኛል ብለዋል።

ምስራቅ ዕዝ ከሌሎች ዕዞች ጋር በመሆን ህዝባዊ ባህሪያቶቹንና እሴቶቹን በመጠበቅ ኢትዮጵያን ከውስጥም ሆነ ከውጪ ጥቃቶች በመከላከል አገርና ተቋሙ የሰጡትን ተልዕኮ በውጤት እየፈፀመ ይገኛል። በቀጣይም  የሀገር ሉዓላዊነትን የማስጠበቅና ሰላምን የማፅናት ተግባራችንን እናጠናክራለን ብለዋል።

ሰራዊቱ የኢትዮጵያዊነት እሴቶችን ተላብሶ የፈፀማቸው ተልዕኮዎች በህዝባችን ዘንድ የክብር ካባ ያጎናፀፈውና ላስመዘገባቸው ውጤቶች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉን ተናግረዋል።

የምስረታ በዓሉን "ህገ መንግስታዊ ተልዕኳችንን በድል እየተወጣን የሀገራችንን ሰላም እናፀናለን" በሚል መሪ በተለያዩ መረሃ ግብር እንደሚከበር ያበሰሩት  የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለውጊያ አገልግሎት ድጋፍ ሜጀር ጀነራል ፍቃዱ ፀጋዬ በዓሉ ስፖርታዊ ፌስቲቫል፣ በወታደራዊ  ትርዒቶች፣ በፓናል ውይይት፣ በመጽሐፍ ምረቃና በሌሎች ፕሮግራሞች ይከበራል ብለዋል።

ሜጀር ጀነራል ፍቃዱ ፀጋዬ የዕዙን የግዳጅ አፈፃፀም የሚያሳዩ ዘጋቢ ፊልምና የፎቶ ዐውደ ርዕይ ለእይታ እንደሚቀርብም የገለፁ ሲሆን ምስራቅ ዕዝ ከተልዕኮው ጎን ለጎን በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና ሁሉ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር  ከህዝቡ ጋር  በመሆን ችግኝ በመትከልና በመንከባከብ ሰፋፊ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።

በመርሃ ግብሩ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር፣ በብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ፣ ጀነራል መኮንኖች፣ የሰራዊቱ አመራሮችና አባላት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የሀረሪ ክልሉ የፖሊስ አባላትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች  ታድመዋል።

ዘጋቢ ሳምሶን ባህሩ
ፎቶ ግራፍ ኪሶ ኢቲቻ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
47👍10🔥3
ዕዙ በየጊዜው የሚሰጡትን ግዳጆች በብቃት የተወጣና በመወጣት ላይ የሚገኝ ነው።
    ሌተናል ጄኔራል አሰፋ ቸኮል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 06 ቀን 2017 ዓ.ም

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አሠፋ ቸኮል በቡርቃ ማሰልጠኛ ማዕከል ተገኝተው በስልጠና ላይ ለሚገኙ ፣ለሻምበል እና ለሻለቃ አመራሮች እንዲሁም ለልዩ ልዩ የሙያ ሰልጣኞች የግንዛቤ ማሥጨበጫ ሰጥተዋል።

ዕዙ በየጊዜው የሚሰጡትን ግዳጆች በብቃት የተወጣ እና በመወጣት ላይ የሚገኝ አስተማማኝ ሀይል መሆኑን አሁን ላይም ማንኛውንም ሀይል በብቃትና በቁርጠኝነት መመከት በሚያስችል የዝግጁነት ደረጃ እና ቁመና ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

ዋና አዛዡ የዕዙ የሠራዊት አባላት ሀገርን ለማፍረስ ቀን ከሌሊት የሚኳትኑ ባንዳዎችን እና ፅንፈኞችን ህልም በማክሰምና እኩይ አላማቸውን በማክሸፍ እያደረጉት ያለው የጀግንነት ተግባር የሚመሰገን መሆኑን ገልፀው ይህ የሰራዊቱ በመስዋዕትነት የደመቀ የድል ተግባርም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የሰራዊቱን ሁለንተናዊ አቅምና ብቃት የማሳደግ ሂደትና ብቁ አመራሮችን ማፍራት የስልጠናው ዋና አላማ መሆኑን በማስገንዘብ ይህ ተግባር ዕንደ ዕዝ ብሎም እንደተቋም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የገለፁት ዋና አዛዡ በስልጠናው ሂደትም የሚሰጡ ስልጠናዎችን በትኩረት መከታተልና በግዳጅ አፈፃፀም ወቅት አኩሪ ድል ማስመዝገብ ከሰልጣኞች የሚጠበቅ ተግባር ነው ብለዋል።

የማሰልጠኛ ማዕከሉ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ግርማ ስዩም በበኩላቸው በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ በሚሰጡ ስልጠናዎች የአመራሩን ብቃት የሚያሳድጉ ልዩ ልዩ ሰልጠናዎች እየተሰጡ የቆዩ መሆናቸውን ገልፀው በአሁኑ ሰአትም አመራሩን ማዕከል ያደረገ ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል ያሉ ሲሆን ማዕከሉ ብቁና ተኪ አመራሮችን በማፍራት ረገድ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን ገልፀዋል። ዘገባው የንጉሴ ውብሊቀር ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
36👍12👏3🔥2🥰2
መቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን ተጨማሪ ተጫዋች አስፈረመ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 06 ቀን 2017 ዓ.ም

በኢንስትራክተር መሠረት ማኔ የሚመራው የመቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቿን ቤዛዊት ንጉሴን አስፈርሟል።

በዝውውር መስኮቱ በንቃት እየተሳተፈ የሚገኘው መቻል ያለፈውን አመት በሲዳማ ቡና ውጤታማ ጊዜን ማሳለፍ የቻለችውን በመስመር ስፍራ እና  በአጥቂነት መጫወት የምትችለውን ቤዛዊት ንጉሴን ማሥፈረም ችሏል።

የመቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን ለ2018 የውድድር አመት ከዋና አሰልጣኝ ቀጠራ ጀምሮ ምክትል አሰልጣኝ ፣ የግብ ጠባቂ  እንዲሁም አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን በማሥፈረም ወደ ዝግጅት መግባት ችሏል። ዘጋቢ ገረመው ጨሬ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
37👍12🔥3😁1
በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤሊያስ ወረዳ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ተካሄደ።

‎የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 06 ቀን 2017 ዓ.ም

‎በምሰራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ ለግዳጅ የተሰማራው እና ፅንፈኛውን በማፅዳት ሰላም እያረጋገጠ የሚገኘው ክፍለ ጦር አመራሮች ከማህበረሰቡ ጋር በወቅታዊ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ  ውይይት አድርገዋል።

"ህብረታችን ለሰላማችን" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ውይይት ላይ የተገኙት የክፍለ ጦሩ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አለም ሰገድ ተስፋዬ ሠራዊት ህዝብና መንግስት የሰጡትን ተልዕኮዎች ለማሳካት በተለያዩ አካባቢዎች የፅንፈኛውን ቡድን በመደምሰስ ህዝባዊ ሃላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

‎ክፍለ ጦሩ በፈፀመው ግዳጅ ባስመዘገበው ድል ሰላም ከተረጋገጠባቸው ቀጠናዎች መካከል የደብረ ኤልያስ ወረዳ አንዱ እንደሆነ ያወሱት አዛዡ ለተገኘው ሰላም የማህበረሰቡ ሚና ከፍተኛ እንደሆነም ጠቁመዋል።

‎ከጦርነት ኪሳራ እንጅ ትርፍ ታይቶ አንደማይታወቅ ያስረዱት ከፍተኛ መኮንኑ የወረዳው ነዋሪዎችም  የተረጋገጠውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል ከሰራዊቱ ጎን ሊሰለፉ እንደሚገባም ተናግረዋል።

‎የወረዳው ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሙላት ሙንዬ በበኩላቸው የተገኘው ሰላም በመከላከያ ሰራዊቱ መስዋዕትነት የመጣ መሆኑን ገልፀው ለሰራዊቱ ምስጋና አቅርበዋል።

‎የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በፅንፈኛው ይደርስባቸው የነበረውን የዘረፋ፣የመፈናቀል፣ የመሰረተ ልማት እና ተቋማት ውድመት መኖር የማይቻልበት ሁኔታ ደርሰው እንደነበር በምሬት አስታውሰው ሰራዊቱ አሁን ላረጋገጠልን ሰላም ለተገኘው ውጤት ምስጋናችን የላቀ ነው ለዘላቂ ሰላም አብረን ለመስራት ቁርጠኛ ነን ሲሉ አረጋግጠዋል ።

‎ዘጋቢ አዲሱ ታዬ
‎ፎቶ ግራፍ አለባቸው ዳኘ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
43👍6🔥5
ሠላም አሥከባሪ ሻለቃው ህዝባዊነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 06 ቀን 2017 ዓ.ም

በደቡብ ሱዳን ዌስት ኢኳቴርያ ቀጠና በያምቢዮ እና ፓዙ ካምፖች የሚገኙ የ21ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አባላት በያምቢዮ ስቴት ሆስፒታል ለሚገኙ ታካሚዎች የመድሃኒት እና የምግብ ድጋፍ አድርገዋል።

በደቡብ ሡዳን የዌስተር ኢኳቴሪያ ስቴት ጥብቅ አስተዳዳሪ ሚስተር ዳንኤል ባግደቡ ሪምባሳ የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት ተልዕኮውን በብቃት እየፈፀመ እንደሆነ መስክረው ከፀጥታ አካላት እና ከማሕበረሰቡ ጋር በመናበብ የቀጠናው ሠላም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እንዲመጣ አበክረው እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል። ለተቸገሩ ወገኖች የሚያደርጉት ልዩ ልዩ ድጋፎቾም የሚደነቅ እንደሆነ አብራርተዋል።

የዩናሚስ የመሰክ ኦፊሠር  ወይዘሮ ጄይን ኮኒ በበኩላቸው ሠላም አስከባሪው የአከባቢው የፀጥታ ችግሮች በሚገባ በመረዳት በሠላም ግንባታ ሂደቶች ውጤታማ ተግባራት ከማከናወኑ በተጨማሪ በየወቅቱ መሠል ድጋፎች ማድረጋቸው መልካምነታቸውን ያመላከተ ተግባር መሆኑንም ገልፀዋል።

የ21ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አሥከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል እንዳለ እሸቱ ሠላም አስከባሪ ሠራዊቱ የቀጠናውን ሠላም እና ፀጥታ ከማረጋገጥ ባሻገር ከራሱ የሚጠቀመውን መድሀኒት እና ምግብ ቀንሶ በህክምና ላይ ለሚገኙ ታካሚዎች ድጋፍ ማድረጉ ህዝባዊነቱን ያሳያ እንደሆነ ገልፀው  በቀጣይም መሠል ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የ21ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ ደረጃ አንድ ሆስፒታል ሲኒየር ሜዲካል ኦፊሰር ሻለቃ ዶክተር ተክለወይኒ ተስፋይ ሰላም አስከባሪ አባላቱ ሀላፊነታቸውን በዲሲፕሊን ከመወጣት አልፈው በዌስት ኢኳቴርያ ስቴት ከሚገኙ የጤና ሙያተኞች ጋር በቅንጅት የሕብረተሰቡን ችግር ለመፍታት እየሰሩ እንደሆነ ገልፀዋል። 

በዌስተርን ኢኳቴሪያ የያምብዮ ስቴት ሆስፓታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ሳሙኤል ኮንጅ ሰላም አስከባሪ ሻለቃው በየወቅቱ ከየአካባቢው የማሕበረሰብ ተወካዮች በጋራ ተቀራርቦ በመስራት ሕዝቡ ውስጥ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያከናውነት በጎ ተግባራት የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው አሁን ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናችን የላቀ ነው ብለዋል።

ዘጋቢ ፍፁም ተካ
ፎቶ ግራፍ ግርማቸው አብረሀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
38👍6🔥5