FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
34 videos
9 files
8.49K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ታላቅ ሀገርን እና የታላቅ ሀገርን ህዝብ በውትድርና ሙያ ማገልገል ክብርም መታደልም ነው።
    ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 01 ቀን 2017 ዓ.ም

ታላቅ ሀገርንና የታላቅ ሀገርን ህዝብ በውትድርና ሙያ ማገልገል ክብርም መታደልም ነው ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ተናገሩ።

የመቆያ ጊዜያቸውን አጠናቀው በስራ አፈፃፀማቸው የላቀ ብቃት ላስመዘገቡ ከፍተኛ መኮንኖች ማዕረግ ያለበሱት ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ በተከበረው የውትድርና ሙያ ሀገርን በፅናት በማገልገላችን ብንኖርም ብንሰዋም ስማችን ሁሌም በክብር ሲታወስ የሚኖር ነው ብለዋል።

የውትድርና ሙያ በባህሪው የቡድን ስራ የሚጠይቅ ፕሮፌሽን ነው ያሉት ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ
በእያንዳንዳችን የማዕረግ ዕድገት ውስጥ የራስ ጥረትና ስኬት መኖር እንደተጠበቀ ሆኖ የቡድን ስራና የጓዶቻችን ክቡር መስዋዕትነት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል ስለሆነም በተልዕኮዎቻችን ሁሉ ለእኛ መኖርና ስኬት ዋጋ የከፈሉ ጀግኖቻችንን ማሰብ እንደሚገባም አመላክተዋል።

ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ጀግኖች አባቶቻችን ብዙ ኪሎ ሜትሮችን በእግራቸው ተጉዘው ወራሪዎችን በመደምሰስ መስዋዕትነት የከፈሉት መጪው ትውልድ በነፃነት እንዲኖር ስለመሆኑ አስታውሰው  እኛም ለመጪው ትውልድ ሀገርን በክብር የማስረከብ ዕድል ነው ያገኘነው ብለዋል።

የማዕረግ ዕድገት ለበለጠ ስራና ኃላፊነት መታጨት መሆኑን መገንዘብና ተልዕኮን በላቀ ብቃት ለመፈፀም መዘጋጀት እንደሚገባ ያሳሰቡት ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ የጀግኖች የመስዋዕትነት ውጤት የሆነውን የኢትዮጵያን ክብርና ከፍታዋን የማስቀጠል ጉዞ ለማሳካት ጠንክረው መስራት እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል።

እንደ ዕዝም እንደተቋምም አገራዊ ኃላፊነት ተቀብለን በውጤታማነት እየሰራን ነው ያሉት ዋና አዛዡ የተሰጠንን ህገ-መንግስታዊ ተልዕኮ በላቀ ጀግንነት በመፈፀም በቀጣይ ለሚኖሩን ግዳጆችም የበለጠ መዘጋጀት ይጠበቅብናል ሲሉም አሳስበዋል።

የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሰው ሃብት አመራር ኃላፊ ኮሎኔል ደረጄ ነዳሳ በበኩላቸው ተሿሚዎች የተቋሙን የማዕረግ ዕድገት  መመልመያ መስፈርት ያሟሉና በስራ አፈፃፀማቸው ውጤታማ ስለመሆናቸው ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ገልፀዋል።
ዘገባው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
33👍11👏2🔥1
ክፍለ ጦሩ ተልዕኮውን በድል እየተወጣ እንደሚገኝ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሐሴ 01 ቀን 2017 ዓ.ም

በማዕከዊ ጎንደር ዞን ግዳጁን እየተወጣ የሚገኘው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ክፍለ ጦሩ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡን የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሌተናል ኮሎኔል በንድር በደድ አስታወቁ።

ምክትል አዛዡ ከአካባቢው ማህበረሰብ አና የፀጥታ ሀይል ጋር በመቀናጀት ፅንፈኛውና ዘራፊው ቡድን ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ ደርሷል ብለዋል ።

የማዕከላዊ ጎንደር የአለፋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በጋሻው ይመር ሠራዊቱ ህዝባዊነቱን በተግባር ያረጋገጠበትን ተልዕኮ እየተወጣ በመሆኑ ለህዝባችን ተስፋ ሰጪ ውጤት መመዝገቡን ገልፀዋል።

በፕሮግራሙ ላይ በአመቱ በስራ አፈፃፀማቸው ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ የወረዳው አሰተዳዳሪና የሠራዊቱ አመራሮች ተሸላሚ ሆነዋል።

ዘጋቢ መንግስቱ ተፈሪ 
ፎቶ ግራፍ ያደታ ወዬሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
28👍7👏3🔥1
የለመለመች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስረከብ ችግኝ መትከልና መንከባከብ ይገባል
     አቶ ጌታቸው ሀይለ ማርያም

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 01 ቀን 2017 ዓ.ም

በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ኤሌክትሮኒክስ ኢንጅነሪንግ እንዱስትሪ በለገዳዲ ባዘጋጀው የችግኝ መትከያ ስፍራ የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታቸው ሀይለ ማርያምን ጨምሮ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጅነሪንግ እንዱስትሪ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ሲቭል ሰራተኞች፣ በሪፐብሊካን ጥበቃ ሀይል የክፍለ ጦር የሠራዊት አመራሮችና አባላት፣ በሸገር ከተማ የኩራጅዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የመንግስት የስራ ሀላፊዎች የተሳተፉበት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተካሂዷል፡፡

የችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩን ያስጀመሩት የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታቸው ሀይለ ማርያም የዚህ ትውልድ የታሪክ አሻራ የሆነውን የአረንጓዴ ልማት መርሀ ግብር በመላው ህዝባችንና በሠራዊታችን የነቃ ተሳትፎ በየአመቱ የሀገሪቱ የደን ሽፋን በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

በዚህም በአረንጓዴ የለመለመች ሀገር ለትውልድ  ለማስተላለፍ በችግኝ ተከላ መርሀ ግብር  እየተከናወነ ያለው ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በሪፐብሊካን ጥበቃ ሀይል የክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ፍቃዱ ጥላሁን በበኩላቸው ሠራዊታችን የሀገርንና የህዝብን ሰላምና ደህንነት ከመጠበቅ ጎን ለጎን ከህዝባችን ጋር በመቀናጀት በአረንጓዴ አሻራና በተለያዩ የልማት ስራዎች በትኩረት እየተሳተፈ ይገኛል ብለዋል፡፡

በሸገር ከተማ የኩራጅዳ ክፍለ ከተማ አሰተዳደር አቶ ተማም ሁሴን ዛሬ ከህዝብ አብራክ ከወጣው ሠራዊታችን ጋር ሆነን ችግኝ በመትከላችን የበለጠ ተነሳሽነት ፈጥሮልናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሠራዊታችን በሰፋፊ የልማት ስራዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆኑን አንስተው የሀገርን ልዕልና በሁሉም መስክ ለማስከበር ሁላችንም የድርሻችን ልንወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው  ብዝሀ ሕይወትን በዘላቂነት ለመጠበቅና ሁለንተናዊ ልማትን ለማሳደግ ችግኝ መትከል አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው አረንጓዴ አሻራ ህዝባዊ ትስስርንና አንድነትን የሚያጠናክር የጋራ የልማት ውጤት መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ዘጋቢ ያሬድ ጥላዬ
ፎቶግራፍ አበረ አየነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
37👍7👏3🔥1
ተተኪ መኮንኖች የአባቶቻችሁን ታሪክ በመውረስ የኢትዮጵያ መለያና አርማ መሆን ይገባችኋል፡፡
    ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮነን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 01 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮነን በሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለ26ኛ ዙር ንስር ኮርስ ዕጩ መኮንኖች የአውደ ውጊያ ተሞክሮ አስተላልፈዋል፡፡
 
ጠንካራ እና ዘመናዊ ሠራዊት ለመገንባት  ብቁ መኮንኖች መኖር አለባቸው እነዚህ መኮንኖች የሚገኙት ደግሞ ከብቁ ማሰልጠኛ ማዕከል ነው፤ እናንተ ልክ እንደ ጥቁር አንበሳ ኮርስ ሀገር በፈለገቻቸው ሰዓት ተገኝተው ደማቅ ታሪክ እንደፃፉት ሁሉ የነሱን ፈለግ መከተል አለባችሁ ብለዋል፡፡

የጀግንነትና አልደፈር ባይነታችን ሲነሳ ሁሌም  አርበኞቻችንና ጀግኖቻችን እናስታውሳለን አሁንም በዚህ ትውልድ ጀግኖች እየተፈጠሩ ነው፤በፈተናዎች ተፈትነው ድል በማድረግ ፈንጥቀው የወጡ በከፍተኛ ጀብዱነት ሀገርን ያዳኑ የሀገር ባለውለታዎች ተፈጥረዋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ 

ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮንን እናንተ ተኪ መኮንኖች የባንዳነት ተግባር የምትጠየፉና የኢትዮጵያ መለያ፤ አርማና አምባሳደር ናችሁ ሲሉም ገልፀዋል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ምክትል ሀላፊ ለአመራር ስልጠና ሜጄር ጄኔራል ሰለሞን ቦጋለ
አያት ቅድመ አያቶቻችን ዳር ደንበሯ ሳትደፈር ከነ ሙሉ ክብሯ ያስረከቡን ሀገር አያሌ መስዋዕቶችን በመክፈል መሆኑን ገልፀው በተለያዩ ጊዚያት የተካሄዱት አውደ ውጊያዎች በኢትዮጵያ አሸናፊነት የተጠናቀቁ ቢሆንም ባንዳዎች ግን ነበሩ ብለዋል።

አሁንም እዚህም እዚያም የጠላት ተልዕኮ በመቀበልና ፍርፋሪ ለማግኘት ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጭምር በማበር የባንዳነት ስራ እየሰሩ ያሉትን የሀገራችን ልጆች የታሪክ ተወቃሽ አትሁኑ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁሌም አሸናፊ ነች ሲሉም ተናግረዋል።

ዘጋቢ ፊሊሞን ገብረእግዚሀብሔር 
ፎቶግራፍ ሩሚያ ዮሱፍ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
24👍19👏5
ለጥፋት ተዘጋጅተው የነበሩ የሸኔ አባላት በሠራዊቱ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 01 ቀን 2017 ዓ.ም

በተለያዩ አካባቢዎች የጥፋት ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ምስራቅ ወለጋ ዞን የገቡት የአሸባሪው የሸኔ አባላት  ጥፋት ከማድረሳቸው በፊት በመከላከያ ሠራዊቱ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።

በምስራቅ ወለጋ ዞን በአሞሮ ወረዳ ልዩ ቦታው አፈሊ በሚባል አካባቢ የምዕራብ ዕዝ ባሩድ ክፍለጦር ሬጅመንት የሽብር ቡድኑን ሴራ አክሽፏል።

የሬጅመንቷ ምክትል አዛዥ መቶ አለቃ ታጠቅ ወንድፍራው በአካባቢው በመንቀሳቀስ እና  የህብረተሰቡን ሰላም ለማወክ የጥፋት ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ቀጠናው ሰርገው እንዲገቡ የተደረጉት የኦነግ ሸኔ ቡድን በህብረተሰቡ ድጋፍ መያዛቸውን ገልፀዋል።

ሃያ ዘጠኝ የአሸባሪው ሸኔ አባላት በህብረተሰቡ ውስጥ ሰርጎ በመግባት ተመሳስለው ለማለፍ ሲሞክሩ የሬጅመንቷ አባላት ባደረጉት ክትትል አንድ የሸኔ አባል በመግደል ሃያ ዘጠኙን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን መቶ አለቃ ታጠቅ ወንድፍራው ተናግረዋል።

በተደረገው አሰሳና ፍተሻ የአካባቢው ህብረተሰብ ያደረገው ድጋፍ ሰላም ፈላጊነቱን በተግባር ያረጋገጠ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ዘጋቢ ዘላለም ሽመልስ
ፎቶግራፍ ወንድወሰን ፍቃዱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
40👍36👏11🥰4🔥1