FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.6K photos
32 videos
9 files
8.48K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ጤና ይስጥልን ጥቂት ሥለጤናዎ የሳንባ ካንሰር ዋና ዋና አጋላጭ ሁኔታዎች ምንድናቸው?

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም

የሳንባ ካንሰር ማለት በሳንባ ውስጥ የሚገኙ ህዋሳት ከመደበኛ ዕድገታቸውና ቁጥራቸው ውጪ ጤናማ ባልሆነ መልኩ መባዛት ነው፡፡

የሳንባ ካንሰር ከሳንባ ተነስቶ ወደ አንጎል እንዲሁም ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ሊሰራጭ ይችላል፡፡ ለመሆኑ የሳንባ ካንሰር ዋና ዋና አጋላጭ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?

ማጨስ፡- ለሳንባ ካንሰር ዋነኛ አጋላጭ ሁኔታ ነው፤ የትምባሆ ምርቶችን መጠቀም ለሳንባ ካንሰር የመጋለጥ ዕድልን ይጨምራል፡፡

ደባል አጫሾችም (ሲጋራ በሚያጨሱ ሰዎች አካባቢ የሚገኙ) ለሳንባ ካንሰር የተጋለጡ ናቸው፡፡ ማንኛውም የዕድሜ ክልል ማጨስን ማቆም በሳንባ ካንሰር የመጋለጥ ዕድልን ሊቀንስ ይችላል፡፡

- የስራ ቦታ፡- በብዛት ከሚታወቁ የስራ ቦታ አጋላጭ ሁኔታዎች ውስጥ እንደ አስቤስቶስ፣ ሲሊካ፣ ራዶን፣ ከባድ ብረቶች፣ ፖሊሳይክሊክ እና ሃይድሮካርቦን የመሳሰሉ ኬሚካሎች ያሉባቸው የስራ ቦታዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

- የአየር ብክለት፡- በቤት ውስጥ እንዲሁም ከቤት ውጪ የሚኖር የአየር ብክለት ለሳንባ ካንሰር ተጋላጭ ያደርጋል፡፡
በተለይም በቂ አየር በሌላቸው ቤቶች ውስጥ ከሰል፣ እንጨት እና ሌሎች ለማገዶ የምንጠቀማቸው ነገሮች የሚያወጡት ጭስ ሴቶችን ይበልጥ ተጋላጭ ያደርጋቸዋል፡፡

- የቤተሰብ ሁኔታ፡- የሳንባ ካንሰር በቤተሰብ ውስጥ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍ ያለ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

- የጨረር ህክምና፡- በተደጋጋሚ በደረት ላይ የሚደረግ የጨረር ምርመራ በሳንባ ካንሰር የመጋለጥ ዕድልን ከፍ ያደርጋል፡፡

በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩትን አጋላጭ ሁኔታዎች መቀነስ ወይም ማስወገድ የሳንባ ካንሰርን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

የሳንባ ካንሰር ዋና ዋና ምልክቶች ምንድናቸው?

ለረጅም ጊዜ እየተባባሰ የሚሄድ ወይም በቀላሉ የማይጠፋ ሳል፣ የደረት ህመም፣ የትንፋሽ ማጠር፣ ስንተነፍስ ድምጽ መኖር፣ ደም የቀላቀለ አክታ፣ በብዛት የሚሰማ የድካም ስሜት፣ ባልታወቀ ምክንያት ክብደት መቀነስ፣ በተደጋጋሚ ለሳንባ ምች መጋለጥ ይጠቀሳሉ፡፡

የሳንባ ካንሰር ሕክምና:-

የሳንባ ካንሰር እንደ ካንሰር አይነቱ እንዲሁም እንደሚገኝበት የስርጭት ደረጃ በብዙ መንገዶች ይታከማል፡፡

በዚህም በቀዶ ሕክምና፣ በኬሞቴራፒ፣ በጨረር ሕክምና እና በሌሎች ዘመናዊ ህክምናዎች ወይም በእነዚህ ሕክምናዎች ጥምረት መታከም ይችላል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
33👏9👍5🔥3
የፅንፈኛውን እኩይ ሴራ የተረዱ አባላቱ ለሠላም እጅ መሠጠታቸውን ቀጥለዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 27 ቀን 2017 ዓ,ም

በሰሜን ሽዋ ዞን መርሀ-ቤቴ ወረዳ የፅንፈኛውን እኩይ ሴራ የተረዱ55  አባላቱ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ለአየር ወለድ ክፍለጦር እጃቸውን መስጠታቸውን የክፍለ ጦሩ  አዛዥ ኮሎኔል ማቲዎስ ማደቦ ገልፀዋል።

የፅንፈኛው ሀይል ከጠላቶቻችን የሚሰጠውን ተልዕኮ በመያዝ በሀሰት ፕሮፖጋንዳ ለአማራ ነው የምታገለው በማለት ጫካ ገብቶ የነበረ ቢሆንም በአሁን ስአት ግን እውነታውን እየተገነዘበ እጅ እየሰጠ ይገኛል።

በቀጣይም ሌሎች ጫካ የሚገኙ ፅንፈኞች እጃቸውን እንደሚሠጡ ቢታሠብም አሻፈረኝ ባለው ላይ ግን ክፍለጦሩ እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ እንደምቀጥልበት አዛዡ ተናግረዋል።

እጅ የሠጡ አባላቱ እስከዛሬ ተታለን ህዝባችንን ለዕፍረት እና ለጉስቁልና አጋልጠነዋል፤ የተጀመሩ መሰረተ ልማቶች እንዳይጠናቀቁ እንቅፋት ሆነን ቆይተናል፣ በቀጣይ ግን ከህዝባችን እና ከመንግስት ጎን በመሆን አካባቢያችንን ወደነበረበት ሰላም ከመመለስ ጎን ለጎን አሁንም በስህተት ጫካ ያሉ ጓደኞቻችንን መክረን እንመልሳለን ሲሉ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

ዘጋቢ ታከለ ታለ
ፎቶ ግራፍ ሚኪያስ ጌታቸው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
39👍16🔥2
የሠራዊቱን እና ቤተሠቡን ማህበራዊ ኑሮ ለመደገፍ እየሠራ መሆኑን ዳይሬክቶሬቱ አሥታወቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ መደብሮችና መዝናኛ ክበቦች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በበጀት አመቱ አዳዲስ ስኬቶችን ጭምር ያስመዘገበበት ስኬታማ የስራ አፈፃፀም እንደነበረ ዳይሬክቶሬቱ አስታውቋል።

ዳሬክቶሬቱ የባለፈውን አመት የስራ አፈፃፀም መነሻ በማድረግ በ2017 በጀት አመት  የስራ አፈፃፀሙን በማዘመን ለሠራዊቱ አባላትና ለቤተሰቡ ፣በጡረታ ለተሠናበቱ የሠራዊት አባላት እንዲሁም ለተቋሙ ሲቪል ሰራተኞች የመሠረታዊ የፍጆታ እቃዎች አቅርቦት፣ ሸቀጣሸቀጦች፣የክበብ አገልግሎትና የግብርናና የኢንዱስትሪ ውጤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ መቻሉን የመከላከያ መደብሮችና ክበቦች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል አንተነህ ተፈራ ገልፀዋል።

አመራሩና አባላቱ በበጀት አመቱ ስራዎችን ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀትና ተገቢውን ትስስር በመፍጠር በሙሉ ሀላፊነት በመስራታቸው አጥጋቢ ውጤት መገኘቱንም ኮሎኔል አንተነህ ተናግረዋል።

ዳይሬክቶሬቱ በየደረጃው ለሚገኙ የመደብርና የመዝናኛ ክበብ ሙያተኞች አቅማቸውን ለማሳደግ  ለዕዞች፣ ለማሰልጠኛዎች፣ለመምሪያዎችና ለኮሌጆች ስልጠናዎችን የሰጠ ነው።

ዕዞችን ከመደገፍ አኳያም የሚመለስ ከ100 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ሸቀጣሸቀጦችን በመስጠት የመደገፍ ስራና በስልጠና ዋና መምሪያ ስር ለሚገኙ ኮሌጆችና ማሰልጠኛዎች ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ኮሎኔል አንተነህ ተፈራ አሥታውቀዋል።

በአመቱ የተሻለ የስራ አፈፃፀም ለነበራቸው ክፍሎችና አጋር ተቋማት እውቅናና ሽልማት ያበረከተው ዳይሬክቶሬቱ የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ እና የተሻለ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አባላቱም ማዕረግ አልብሷል።

ዘጋቢ ልደት አስረስ
ፎቶ ግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
33👍9🔥2
ዕዙ ለሀገርና ለህዝብ ጋሻና መከታ መሆኑን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት ተናገሩ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም

ምዕራብ ዕዝ የተሰጠውን ተልዕኮ በድል እየተወጣ ለህዝብ ጋሻና መከታ መሆኑን አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት ተናግረዋል።

ጄኔራል መኮንኑ ይህንኑ የተናገሩት በዕዙ ማሰልጠኛ ማዕከል ዴዴሳ፤ ከኮሮች፣ክፍለ ጦሮች የተወጣጡ ስልታዊ አመራሮች እና  የቡድን መሳሪያ ሰልጥኖ አሰልጣኞች  ለሁለት ወር በነበራቸው የስልጠና  ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው በዕለቱም በስልጠና ቆይታ ብልጫ ለነበራቸው ክፍሎችና አባላት የሽልማትና የእውቅና መርሀ ግብር ተከናውኗል።

ሀገራችን ታፍራና ተከብራ ትኖር ዘንድ ዕዙ ታሪካዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ያሉት ሌተናል ጀኔራል መሰለ መሰረት ዕዙ አሸባሪውን የሸኔ ቡድን እና የፅንፈኛውን ሃይልን ከመደምሰስ ባሻገር ለዘመናዊ ሰራዊት ግንባታ በሚያግዙ ስልጠናዎች በመታጀብ  የአፈፃፀም ብቃቱን በማሳደግ አስተማማኝ የሰላም ሀይል ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል።

ሠራዊት ዘመናዊና ፕሮፌሽናል ነው የሚባለው በስልጠና መሀል እያለፈ በታጠቀው መሳሪያ በቂ እውቀት ኖሮት ግዳጁን መፈፀም ሲችል ነው ያሉት አዛዡ ይህ ስልጠና ስልታዊ አመራር ሙሉ አቅም የፈጠሩበት በመሆኑ ለውስጥ ፀረ-ሰላም ቡድኖች ብቻ ሳይሆን ሉዓላዊነታችን ለመዳፈር ለሚቃጣቸው ውጫዊ ሀይሎችም ጭምር ዝግጁነታችንን የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

ስልታዊ አመራሩ የጠላትን አስተሳሰብና አሰላለፍ በውል ተገንዝቦ ራሱን ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በማስማማትና አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት በማድረግ አባላቱን በራሱ ልክ አስተካክሎ እንዲቀርፅ ያደርጋል ነው ያሉት ጄኔራል መኮንኑ ።

የዕዙ የሰራዊት አባላትና አመራሮች በአሁን ሰዓት የተበታተነውን የአሸባሪውን የሸኔ ቡድን ለቅሞ የመምታት እና የፅንፈኛውን ሃይል የመደምሰስ ስራዎችን እያከናወኑ እንደሚገኙ ያነሱት ዋና አዛዡ እናንተም ወደየ ክፍላችሁ በመሄድ የወሰዳችሁትን ስልጠና በተግባር በመቀየር አመርቂ ውጤት ማምጣት ይገባችኋል ሲሉ ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት አሳስበዋል።

የስልጠናውን ሪፖርት ያቀረቡት  የዕዙ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ኮሎኔል ጀንበሬ ማሞ በበኩላቸው የስልጠናው ዓላማ በክህሎትና በዲስፕሊን የታነፀ ስልታዊ አመራሮችን እና የቡድን መሳሪያ ሰልጥኖ አሰልጣኞችን መፍጠር መሆኑን ጠቁመው  ስልጠናው አመርቂ ከመሆኑም በላይ  የአመራሩ ድጋፍ የታከለበት በንድፈ ሀሳብና በተግባር ለሁለት ወር የተሰጠ እና ተጨባጭ አቅም የፈጠረ ስልጠና መሆኑን አብራርተዋል።

ዘጋቢ ፍፁም ከተማ
ፎቶግራፍ ሽመልስ እሸቱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
29👍18🔥2