FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.6K photos
32 videos
9 files
8.48K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
በሰሜን ሸዋ ዞን ፅንፈኛው ቡድን የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ እጅ እየሠጠ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም

በሰሜን ሽዋ ዞን መርሀ-ቤቴ ወረዳ ታች ቤት ንዑስ ወረዳ በፕሮፖጋንዳ ተሰብከው ጫካ ገብተው የነበሩ የፅንፈኛው ቡድን አባላት በየዕለቱ የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ላይ መሆናቸውን የአየር ወለድ ክፍለ-ጦር አዛዥ ኮሎኔል ማቲዎስ ማዴቦ ተናግረዋል። 

የአየር ወለድ ክፍለጦር አዛዡ ዛሬም 79 የፅንፈኛ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ለአየር ወለድ ሠራዊት እጅ መስጠታቸውን በመግለፅ ለዚህ ሰላማዊ ስኬት መሳካት የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የመርሀ-ቤቴ ህዝቦች እና የጥምር ጦሩ ከሠራዊቱ ጋር በመሆን ያበረከቱት አሥተዋፅኦ ሠፊ ነው ብለዋል።

ኮሎኔል ማቲዎስ አሁንም በጫካ ለሚገኙ የቡድኑ አባላት ኢትዮጵያዊ ወንድሞቻችን ናችሁ ኑ የሀገር ሰላምን በማስፈን ኢትዮጵያን እንገንባ ልዩነቶቻችንን በሰላማዊ በሰለጠነ መንገድ መፍታትን እንለማመድ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአየር ወለድ ክፍለጦር ዘመቻ ሀላፊ ሌተናል ኮሎኔል መኩሪያ ሙሉነህ በበኩላቸው የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል እጃቸውን ለሰጡ ለታጠቁ ሀይሎች በሙሉ ሠራዊቱ በክብር በመቀበል ወደቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ አስፈላጊውን ህጋዊ ጥበቃ እያደረገ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

ዘጋቢ ፈለቀ ዋሲሁን
ፎቶ ግራፍ ሚኪያስ ጌታቸው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
53👍31👏6🔥1
ሬጅመንቱ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ቡድን ላይ እርምጃ ወስዷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም

የማዕከላዊ ዕዝ የአይበገሬ ክፍለጦር ሬጅመንት በምዕራብ ሸዋ ዞን ቶሌ ወረዳ ጉለሌ ቀበሌ በአሸባሪው ቡድን ላይ በወሰደው የተጠና እርምጃ የጥፋት ቡድኑን በመደምሰስ የተለያዩ መሣሪያዎችን እና ተተኳሾችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

የሬጅመንቱ አዛዥ ሻምበል ምስጋናው ተሾመ የሬጅመንቱ ሠራዊት በየጊዜው በሚያደርጋቸው የተቀናጀ ዘመቻ በዘራፊው ቡድን ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሰ መምጣቱን ተናግረዋል። ዘጋቢ ፍቃዱ አበራ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
45👍16🔥1
ወደ ሠላም ማስከበር ተልዕኮ ለሚሰማሩ ከፍተኛ መኮንኖች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም

በእንግሊዝ መንግስት የገንዘብ ድጋፍና በመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል የአለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በጋራ ያዘጋጁት በተባበሩት መንግስታት የሠላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ስታፍ ኦፊሰር ለሚሰማሩ ከፍተኛ መኮንኖች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

የስልጠናው አስተባባሪ ሌተናል ኮሎኔል ቴዎድሮስ አስማማው እንደገለፁት ለሁለት ሳምንት የተሰጠው የስታፍ ኦፊሰር ስልጠና በተባበሩት መንግስታት የሠላም ማስከበር ተልዕኮ መርሆና ህጋዊ መሰረቶች፣ በግጭት ወቅት ለማህረሰቡ ስለሚደረጉ ጥበቃዎች፣ ሰብአዊ መብት አያያዝ እና ድጋፎች፣የፆታ እኩልነት፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ስለሚደረግ የተቀናጀ ግዳጅ አፈፃፀም የሠላም ግንባታ ተግባራቶች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ የትምህርትና ስልጠና ዲን አቶ ከድር አባቡልጉ በንድፈ ሀሳብና በተግባር በተደገፈ የተሰጣችሁ ስልጠና በቂ ዕውቀትና ግንዛቤ ከመፍጠር ባሻገር በተባበሩት መንግስታት የስታፍ ኦፊሰር የአለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ስራዎች ብቁ እንድትሆኑ ሚናው የላቀ ነው ብለዋል፡፡
  
በስልጠናው የገንዘብ ድጋፍ ላደረገው የእንግሊዝ መንግስትና ስልጠናውን ለሰጡ ላስተባበሩ አካላት በማዕከሉ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
ዘጋቢ ተፈራ ጥላዬ
ፎቶግራፍ ፍሬህይወት ተፈራ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
31👏7👍6🥰4🔥1
ልዩ የጋብቻ ስነ-ስርዓት በምዕራብ ዕዝ ዴዴሳ ማሰልጠኛ ማዕከል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም

በምዕራብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል በዴዴሳ ከኮሮች፣ ክፍለ ጦሮች የተወጣጡ ስልታዊ አመራሮች እና  የቡድን መሳሪያ ሰልጥኖ አሰልጣኞች የምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ በአይነቱ ለየት ያለ የጋብቻ ስነ-ስርዓት ተከናውኗል።

የመቶ አለቃ ቢያዝንልኝ ይቴ እና የወይዘሪት ሀገሬ ቢተው የጋብቻ ስነ-ስርዓት የተካሄደው የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት በክብር እንግድነት በተገኙበት የዕዙ ስልታዊ አመራሮች እና የቡድን መሳሪያ ሰልጥኖ አሰልጣኞች የምርቃት መርሃ-ግብር ላይ ነው።

የዕለቱ የክብር እንግዳ ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት በዕዙ ማሰልጠኛ ማዕከል ለመጀመሪያ ጊዜ በእንደዚህ አይነት በወታደራዊ ስነ-ስርዓት የተደረገ የጋብቻ ስነ-ስርዓት መሆኑን ጠቁመዋል።

ለተጋቢዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ጄኔራል መኮንኑ ዕዙ ለተጋቢዎቹ ለመቶ አለቃ  ቢያዝንልኝ ይቴ እና ለወይዘሪት ሀገሬ ቢተው የአንድ መቶ ሺህ ብር ሽልማት መሰጠቱን አብስረዋል።

ለዕዙ ስልታዊ አመራሮችና የቡድን መሳሪያ ሰልጥኖ አሰልጣኞች የምረቃ መርሃ ግብርም የጋብቻ ሥነ-ሥርዓቱ  ድምቀት ሆኗል።

ዘጋቢ ፍፁም ከተማ
ፎቶግራፍ ሽመልስ እሸቱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
62👏12👍8🥰4👎3🔥1
የዕዙ ስታፍ የሠራዊት አባላት ለሠራዊት ልጆች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ስታፍ እና የመከላከያ መሀንዲስ ኮንስትራክሽን ሠመራ ቅርንጫፍ የሠራዊት አባላት  ለሠራዊት ልጆች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

በኮምቦልቻ ከተማ ደረቅ ወደብ ካምፕ ለሚኖሩ መስዋዕት ለከፈሉ የሠራዊት ልጆች 55 ሺህ ብር በማሠባሠብ ለ26 ተማሪዎች ደብተር እስክርቢቶና ፓርሳ እንዲሁም የትምህርት ማስመዝገቢያ ገንዘብ ድጋፍ መደረጉን የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ኃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል እሸቱ አስማማው ገልፀዋል።

የጓዶቻችን ልጆች በገንዘብ እና በቁሳቁስ መደገፍ እና ማበረታታት ከእኛ የሠራዊት አባላት የሚጠበቅ ነው ያሉት ጄኔራል መኮንኑ ተማሪዎች ለትምህርታችሁ ትኩረት በመስጠት ትልቅ ደረጃ ላይ በመድረስ ሀገር ተረካቢ መሆን ይጠበቅባችኋል ሲሉ አሥገንዝበዋል።

ሠራዊቱ ያደረገው ድጋፍ ለ3ኛ ጊዜ  መሆኑን የጠቆሙት ብርጋዲየር ጄኔራል እሸቱ አሥማማው በቀጣይነትም አሥፈላጊውን ድጋፍ አቅም በፈቀደ ልክ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።

ድጋፍ ከተደረገላቸው መካከል ወሮ ሀያት ሰይድ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የሠራዊት አባላት በተለያዬ ጊዜ አሥፈላጊውን ድጋፍ በማድረግና የስራ እድል ቅድሚያ በመስጠት ለሚደረግልን ድጋፍ ሁሉ ከልብ እናመሠግናለን ብለዋል። ዘጋቢ ጌትነት አምሳሉ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👏2016👍5🔥4🥰1