FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
33 videos
9 files
8.49K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ዋና መምሪያው በበጀት ዓመቱ ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል
     ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ማጠቃለያን አስመልክቶ የዕውቅና፣ የማዕረግ ማልበስ ፣ የተማሪዎች ድጋፍ እና የሽኝት መርሃ-ግብር አካሂዷል።

ዋና መምሪያው የሰው ሃብት ፖሊሲዎች ፣ስትራቴጂዎችና ስታንዳርዶችን በመንደፍ የሰው ሃብት ቅጥር ልማት እድገትና ስንብት ስርዓት በመዘርጋት ፣ወቅታዊነቱን የጠበቀ የመረጃ ሥርዓት በማዘጋጀት እና በሌሎችም በርካታ ተግባራት ውጤታማ ሥራ መፈፀሙን የመከላከያ ሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ ተናግረዋል።

ጠላት ፕሮፖጋንዳ በመንዛት የተቋሙን ገፅታ ለማጠልሸት ቢጥርም ጥረቱን በመመከት ረገድ ትኩረት የተሠጠው ሥራ መሠራቱን ያነሱት ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ የመከላከያ ሠራዊቱ ህግና መመሪያን መሰረት በማድረግ ተልዕኮውን በብቃት እየፈፀመ መሆኑን አስምረውበታል።

ተቋሙ ሠራዊቱን በተለያዩ ማህበራዊ ዘርፎች፣ በፋይናንስ ፣ የቤት ባለቤት እንዲሆን በማድረግ እና በሌሎች ተግባራት ውጤት ያለው ሥራ ተግባራዊ እያደረገ ሥለመሆኑም ተናግረዋል።

ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ ሁሉም አባላት የተገኘውን ውጤት አጠናክረው ማስቀጠል እንደሚገባቸው ገልፀው ለዋና መምሪያው ተልዕኮ ስኬት ትብብርና እገዛ ላደረጉ የተቋሙ ክፍሎች ምስጋና አቅርበዋል።

የመከላከያ ሠው ሀብት አመራር ዋና መምሪያ በጡረታ ለተሠናበቱ የክፍሉ አባላት የክብር አሸኛኘት ያደረገ ሲሆን የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑና ጥሩ የሥራ አፈፃፀም ላላቸው አባላቱም በየደረጃው ማዕረግ አልብሷል።

ዘጋቢ ቃለእግዚአብሔር ፍቃዱ
ፎቶግራፍ አበረ አየነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
51👍8🔥5
ጤና ይስጥልን ጥቂት ሥለጤናዎ የሳንባ ካንሰር ዋና ዋና አጋላጭ ሁኔታዎች ምንድናቸው?

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም

የሳንባ ካንሰር ማለት በሳንባ ውስጥ የሚገኙ ህዋሳት ከመደበኛ ዕድገታቸውና ቁጥራቸው ውጪ ጤናማ ባልሆነ መልኩ መባዛት ነው፡፡

የሳንባ ካንሰር ከሳንባ ተነስቶ ወደ አንጎል እንዲሁም ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ሊሰራጭ ይችላል፡፡ ለመሆኑ የሳንባ ካንሰር ዋና ዋና አጋላጭ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?

ማጨስ፡- ለሳንባ ካንሰር ዋነኛ አጋላጭ ሁኔታ ነው፤ የትምባሆ ምርቶችን መጠቀም ለሳንባ ካንሰር የመጋለጥ ዕድልን ይጨምራል፡፡

ደባል አጫሾችም (ሲጋራ በሚያጨሱ ሰዎች አካባቢ የሚገኙ) ለሳንባ ካንሰር የተጋለጡ ናቸው፡፡ ማንኛውም የዕድሜ ክልል ማጨስን ማቆም በሳንባ ካንሰር የመጋለጥ ዕድልን ሊቀንስ ይችላል፡፡

- የስራ ቦታ፡- በብዛት ከሚታወቁ የስራ ቦታ አጋላጭ ሁኔታዎች ውስጥ እንደ አስቤስቶስ፣ ሲሊካ፣ ራዶን፣ ከባድ ብረቶች፣ ፖሊሳይክሊክ እና ሃይድሮካርቦን የመሳሰሉ ኬሚካሎች ያሉባቸው የስራ ቦታዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

- የአየር ብክለት፡- በቤት ውስጥ እንዲሁም ከቤት ውጪ የሚኖር የአየር ብክለት ለሳንባ ካንሰር ተጋላጭ ያደርጋል፡፡
በተለይም በቂ አየር በሌላቸው ቤቶች ውስጥ ከሰል፣ እንጨት እና ሌሎች ለማገዶ የምንጠቀማቸው ነገሮች የሚያወጡት ጭስ ሴቶችን ይበልጥ ተጋላጭ ያደርጋቸዋል፡፡

- የቤተሰብ ሁኔታ፡- የሳንባ ካንሰር በቤተሰብ ውስጥ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍ ያለ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

- የጨረር ህክምና፡- በተደጋጋሚ በደረት ላይ የሚደረግ የጨረር ምርመራ በሳንባ ካንሰር የመጋለጥ ዕድልን ከፍ ያደርጋል፡፡

በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩትን አጋላጭ ሁኔታዎች መቀነስ ወይም ማስወገድ የሳንባ ካንሰርን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

የሳንባ ካንሰር ዋና ዋና ምልክቶች ምንድናቸው?

ለረጅም ጊዜ እየተባባሰ የሚሄድ ወይም በቀላሉ የማይጠፋ ሳል፣ የደረት ህመም፣ የትንፋሽ ማጠር፣ ስንተነፍስ ድምጽ መኖር፣ ደም የቀላቀለ አክታ፣ በብዛት የሚሰማ የድካም ስሜት፣ ባልታወቀ ምክንያት ክብደት መቀነስ፣ በተደጋጋሚ ለሳንባ ምች መጋለጥ ይጠቀሳሉ፡፡

የሳንባ ካንሰር ሕክምና:-

የሳንባ ካንሰር እንደ ካንሰር አይነቱ እንዲሁም እንደሚገኝበት የስርጭት ደረጃ በብዙ መንገዶች ይታከማል፡፡

በዚህም በቀዶ ሕክምና፣ በኬሞቴራፒ፣ በጨረር ሕክምና እና በሌሎች ዘመናዊ ህክምናዎች ወይም በእነዚህ ሕክምናዎች ጥምረት መታከም ይችላል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
33👏9👍5🔥3
የፅንፈኛውን እኩይ ሴራ የተረዱ አባላቱ ለሠላም እጅ መሠጠታቸውን ቀጥለዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 27 ቀን 2017 ዓ,ም

በሰሜን ሽዋ ዞን መርሀ-ቤቴ ወረዳ የፅንፈኛውን እኩይ ሴራ የተረዱ55  አባላቱ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ለአየር ወለድ ክፍለጦር እጃቸውን መስጠታቸውን የክፍለ ጦሩ  አዛዥ ኮሎኔል ማቲዎስ ማደቦ ገልፀዋል።

የፅንፈኛው ሀይል ከጠላቶቻችን የሚሰጠውን ተልዕኮ በመያዝ በሀሰት ፕሮፖጋንዳ ለአማራ ነው የምታገለው በማለት ጫካ ገብቶ የነበረ ቢሆንም በአሁን ስአት ግን እውነታውን እየተገነዘበ እጅ እየሰጠ ይገኛል።

በቀጣይም ሌሎች ጫካ የሚገኙ ፅንፈኞች እጃቸውን እንደሚሠጡ ቢታሠብም አሻፈረኝ ባለው ላይ ግን ክፍለጦሩ እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ እንደምቀጥልበት አዛዡ ተናግረዋል።

እጅ የሠጡ አባላቱ እስከዛሬ ተታለን ህዝባችንን ለዕፍረት እና ለጉስቁልና አጋልጠነዋል፤ የተጀመሩ መሰረተ ልማቶች እንዳይጠናቀቁ እንቅፋት ሆነን ቆይተናል፣ በቀጣይ ግን ከህዝባችን እና ከመንግስት ጎን በመሆን አካባቢያችንን ወደነበረበት ሰላም ከመመለስ ጎን ለጎን አሁንም በስህተት ጫካ ያሉ ጓደኞቻችንን መክረን እንመልሳለን ሲሉ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

ዘጋቢ ታከለ ታለ
ፎቶ ግራፍ ሚኪያስ ጌታቸው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
39👍16🔥2