FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.6K photos
33 videos
9 files
8.48K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የመከላከያ አይሲቲ ማዕከል በዘርፋ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ አይሲቲ ማዕከል ስራ ከጀመረ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደ ሃገር የዲጅታል ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ እየተሰራ ባለው ስራ ማዕከሉ በተቋማችን ታላላቅ ፕሮጀክቶችን በሃላፊነት ተረክቦ በመስራት የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

መከላከያ እንደ ሃገር ከፍተኛውን የቴክኖለጂ ተጠቃሚ መሆኑን የገለፁት የአይሲቲ ማዕከል ኋላፊ ብርጋዲየር ጀኔራል ጥላሁን አሸናፊ በተቋሙ ውስጥ እስካሁን የነበሩ የወረቀት ስራዎችን ወደ ዲጅታል መቀየር፣ በራስ አቅም ልዩ ልዩ ሶፍትዌሮችን አበልፅጎ ወደ ስራ ማስገባት፣ አሁን በዕቅድ በመሰራት ላይ ነው ብለዋል።

መከላከያ የራሱ ፕራይቬት ኔትወርክ እንዲኖረው ትልቅ ፕሮጀክት ይዘው በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራ እንደሚገኝ እና ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ተቋሙ ደህንነቱ የተጠበቀ ኔትዎትክ እንዲኖር የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ከቴክኖለጂ ጋር ለመራመድ ክፍሎችን በስልጠና ማሳደግና ሙያዊ ድጋፍ ጭምር እየሰጡ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ዘጋቢ ደጀኔ አሳይቶ
ፎቶግራፍ ሳሙኤል መንገሻ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
26👍8🔥1
ሠራዊታችንን የሚደግፍ በራሱ ተነሳሽነት የሚሠራ ሙያተኛ ተፈጥሯል፡፡
ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የጥገና ሙያተኞችን አሠልጥኖ አሥመርቋል። በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ ሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል ግዳጅን ተቀብሎ የሚወጣ ብቻ ሳይሆን በሚሰጠው ስልጠና መሰረት ጨምሮና ፈጥሮ ጥራት ባለው መንገድ የሚሠራ ጀግና ሙያተኛ እንደተፈጠረ ገልፀዋል።

ሙያተኞች የሠለጠናችሁትን ሙያ በመጨመር ወደ አሃዳችሁ ስትመለሱ ዘርፈ ብዙ ችግር ፈቺ ስራዎችን በተሻለ በመስራት የሠራዊታችንን ሁለንተናዊ ዝግጁነት ማረጋገጥ ይጠበቅባችኋል ብለዋል።

በመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የሜንተናንስ መምሪያ የታንክና ጦር መሳሪያ ሜንተናንስ ቡድን መሪ ኮሎኔል መስፉን ሐይሉ ሰልጣኞቹ ከእዞችና ክፉለ ጦሮች የተውጣጡ የሠራዊት አባላት ሲሆኑ በከባድ የጦር መሳሪያ፣ በታንኮች እና በሮኬቶች የንድፈ ሀሳብ እና የተግባር ስልጠና ለአስር ወራት ሲሠለጥኑ የቆዩ ሙያተኞች መሆናቸውን ገልፀዋል ። ዘጋቢ ወርቅነህ ተስፉዉ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
24👍6👏2🔥1
የመከላከያ ክፍሎች የመቆያ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ አባላቱ ማዕረግ አልብሷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ዘመቻ ዋና መምሪያ የመቆያ ጊዜያቸውን አጠናቅቀው የላቀ የስራ አፈፃፀም ለነበራቸው የዋና መምሪያው አባላት የማዕረግ ማልበስ ስነ-ስርዓት አከናውኗል።

የዋና መምሪያው ኃላፊ ሌተናል ጀኔራል በላይ ስዩም በማዕረግ ማልበስ ስነ-ስርዓቱ ላይ በመገኘት ለተሿሚዎች የማዕረግ ማልበስ ስነ-ስርዓት በማከናወን የስራ መመሪያም ሰጥተዋል።

ተሿሚዎች የማዕረግ ዕድገት ማግኘት ተጨማሪ ግዳጅና ኃላፊነትን መቀበል መሆኑን አውቃችሁ ህዝብና መንግስት የሰጣችሁን አደራ ከዚህ በፊት ከነበረው በላይ ስራዎችን መፈፀም ይጠበቅባችኃል ብለዋል።

በተያያዘ የመከላከያ ሠላም ማሥከበር ማዕከል የተሻለ የስራ አፈፃፀም ለነበራችውና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ የማዕከሉ የሠራዊት አባላት የተፈቀደላቸውን ማዕረግ አልብሷል።

የሠላም ማስከበር ማዕከሉ አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ ተሿሚዎች ዛሬ የምታገኙት የማዕረግ ሹመት ለቀጣይ ስራ መነሳሳት የሚፈጥር እና ለከፍተኛ ሃላፊነት የሚያዘጋጃችሁ የዕድገት መሰላል በመሆኑ በታታሪነት ልትሠሩ ይገባል ብለዋል።

ለረጅም ዓመት ተቋሙን ስያገለግሉ የቆዩ እና በክብር በጡረታ ለተሰናበቱ የሠራዊት አባላት ምሰጋና በማቅረብ ቀሪው ዘመን ጥሩ እንዲሆንላቸውም ለተሰናባች የሠራዊት አባላት መልካም ምኞታቸውን አቅርበዋል፡፡

በተመሳሳይ የስትራቴጂክ መሳሪያዎች ኮር በስራ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አመራር እና አባላት ማዕረግ አልብሷል።

በዕለቱ ማዕረግ ያለበሱት የኮሩ ዋና አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ግርማ ከበበው የእለቱ ተሿሚዎች ከአሁን ቀደም ባሳዩት መልካም ስነ-ምግባርና በግዳጅ አፈፃፀማቸው የተሻሉ በመሆናቸው ለሹመት እንዲበቁ ተደርጓል ብለዋል።

ተሿሚዎች የተሰጣቸው ሹመት ጊዜያቸው ስለደረሰ ብቻ ሳይሆን ባሳለፉት የአገልግሎት ዘመን በስነ-ምግባራቸው የተመሰገኑና በተቀመጠው መመዘኛ ተመዝነው ያለፉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
50👍20🔥1
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል የተሻለ የስራ አፈፃፀም ላላቸው ሙያተኞች እውቅና ሰጠ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም

ሆስፒታሉ ለሠራዊቱ ለሚሰጠው ቀልጣፋ አገልግሎት  የበኩላቸውን ሚና የተወጡ እና በሥራ አፈፃፀም መመዘኛ ውጤታማ ለሆኑ ሙያተኞች ሽልማት ያበረከቱት የሆስፒታሉ አዛዥ ኮሎኔል ክበበው ወጊ የተሠጣችሁ እውቅናና ሽልማት ለቀጣይ ስራችሁ ይበልጥ መነሳሳትን እና ሞራልን የሚፈጥር በመሆኑ ይበልጥ ልትበረቱ ይገባል ብለዋል፡፡

ቀጣይ በራሱ የሚተማመን እና ሙያዊ ግዴታውን በአግባቡ መወጣት የሚችል ሙያተኛ የማፍራት ሂደት ላይ አሥተዋፆ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው ዛሬላይ እውቅናና ሽልማት የተሰጣችሁ የሆስፒታሉ ሙያተኞችና አመራሮች ለተጨማሪ ሀላፊነት የሚዘጋጁበት እና ተቋሙን በታማኝነት የሚያገለግሉበት መሆን እንዳለበትም አብራርተዋል። 

ዘጋቢ አይናዲስ ደሳለኝ
ፎቶግራፍ አይናዲስ ደሳለኝ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
35👍13🔥4👏1
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን አባላት በጋራ ችግኝ ተክለዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ አመራሮች እና አባላት እንዲሁም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሰራተኛች በጋራ በመሆን አዲስ እየተገነባ በሚገኘው የእዙ ጠቅላይ መምሪያ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል ከአስር ሺህ በላይ የፍራፍሬ እና የደን ችግኞችን ተክለዋል።

በመርሃ ግብሩም የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ዮናስ አያሌዉ እና ሌሎች የዕዙ እና የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዉ አሻራቸዉን አሳርፈዋል።

በሰባተኛዉ አመት የ700 ሚሊየን የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት አሻራቸዉን ያሳረፉት ሌተናል ጀኔራል ሹማ አብደታ ችግኝን መትከል የትውልድን ቀጣይነት ማረጋገጥ መሆኑን ገልፀው አዲስ በሚገነባዉ የዕዙ ጠቅላይ መምሪያ የተካሄደው የችግኝ ተከላ ታሪካዊ መሆኑንና የተተከሉ ችግኝች በአብዛኛዉ ለምግብነት የሚዉሉ በመሆናቸዉ የፍራፍሬ ችግኝ መተከል አለበት ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ዮናስ አያሌዉ በበኩላቸዉ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ዉጤታማ ስራዎችን እየሰራች መሆኑን ጠቅሰዉ በዕለቱም በልዩ ዘመቻዎች ዕዝ አዲሱ ጠቅላይ መምሪያ 10 ሺህ ለምግብነት የሚዉሉ የፍራፍሬ ችግኞችን መተከሉን ተናግረዋል። በተለይ ደግሞ በውጊያ ብቻ ሳይሆን በላቀ የልማት ተሳትፎ ከሚታውቁ የመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን ይህንን ታሪካዊ ተግባር በመፈፀማችን ከፍተኛ ኩራት ይሰማናል ብለዋል፡፡

ዘጋቢ ምህረት ስመኝ
ፎቶ ግራፍ አብዱራህማን ሃሰን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
25👍7👏6🔥1