FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
34 videos
9 files
8.49K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሠራዊታችን የተልዕኮው አንዱ አካል ነው።
      ሌተናል ጄኔራልብርሃኑ በቀለ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሠራዊታችን  አንዱ የተልዕኮው አካል መሆኑን የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ተናገሩ።

ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ የአንድ ጀምበር የሰባት መቶ ሚሊየን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር  በጎንደር ከተማ በተከናወነበት ወቅት እንደተናገሩት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ ሠራዊታችን ከህዝባችን ጋር ሆኖ የተጠናከረ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛልም ብለዋል ።

ዘንድሮም "በመትከል ማንሰራራት"በሚል መሪ ቃል እንደ ዕዝ ቀደም ብለን ጀምረናል ያሉት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ዛሬም እንደ ሀገር 7 መቶ ሚሊዮን ችግኝ  የመትከል ፕሮግራሙንም ከህዝባችን ጋር ሆነን በመትከል ላይ እንገኛለን ብለዋል።

ሠራዊቱ ዋነኛ ተልዕኮው የሆነውን ሠላምና ፀጥታን የማረጋገጥ ተግባሩን እያከናወነ በአረንጓዴ አሻራም ሆነ በሌሎች የልማት ስራዎች ላይ የሚያደርገውን ተሳትፎ አጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ችግኞችን ከመትከል ባሻገር  እንዲፀድቁ ክትትልና እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው በበኩላቸው በዘንድሮው "በመትከል ማንሰራራት"  የአንድ ጀምበር የ7መቶ ሚሊየን የችግኝ  ተከላ መርሃ ግብር  ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን በከተማው ከ60 ሺ በላይ የሚሆኑ ሀገር በቀል ችግኞችን ተክለናል ብለዋል።

ሠራዊቱ ከፀጥታ ማስከበሩ ጎን ለጎን በአረንጓዴ አሻራ እያሳየ ያለው ስራ ምስጋና የሚገባው ነው ያሉት አቶ ቻላቸው ችግኝ ተከላው ምህዳሩን ለመጠበቅ ያግዛል፤ የአካባቢውን ልምላሜ በመጠበቅ የከተማውን የሙቀት መጠን የሚያስተካክል በመሆኑ መንከባከብ የሁላችንም ኃላፊነት ነው ብለዋል።

በተመሳሳይ የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጄር  ጄኔራል ግዛው ኡማ በተገኙበት በባህርዳር ከተማ መኮድ ካምፕ ተካሂዷል።

"በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ የተጀመረው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ሠራዊታችን ከተልዕኮው ጎን ለጎን ችግኞችን በመትከል  የአረንጓዴ አሻራውን አኑሯል ብለዋል።

ሠራዊታችን ከአረንጓዴ አሻራ ባሻገር በሁሉም የልማት ስራዎች ላይ የሚሳተፍ ነው ያሉት የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጄር ጄኔራል ግዛው ኡማ ይህ የልማት ተሳታፊነቱ የሠራዊታችን መገለጫ ባህሪው ነው ሲሉም ተናግረዋል።  ዘገባው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
21👍7🔥4
ሠራዊቱ በአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ላይ ያለውን ተሳትፎ እያሳደገ መጥቷል።
       አቶ አረጋ ከበደ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም
         
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ኮር የሰራዊት አባላት በኮምቦልቻ ከተማ ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር ባካሄዱት የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር የተገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ሰራዊቱ በአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ላይ ያለውን ተሳትፎ ከዓመት ዓመት እያሳደገ እና ውጤት እየታየበት የመጣ መሆኑን ተናግረዋል።
         
የዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ ለየት የሚያደርገው በሃገራችን ውስጥ የታቀደው የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ በከፍተኛ ሁኔታ የተሳካ ከማድረግ ባለፈ  በሁሉም ዘንድ የጋራ መተባበር እና መረዳዳት የሚፈጥርበት እንዲሁም አንድነታችን በይፋ የምናጠናክርበት መድረክ ነው ብለዋል። 

ችግኞችን ከመትከል ጎን ለጎን ከሰው እና ከእንስሳት ንክኪ መጠበቅ ስለሚያስፈልግ ከማህበረሰቡ ጋር በመነጋገር እና በመግባባት እንክብካቤ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ የገለፁት አቶ አረጋ ከበደ መንግስት የጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከግብ ለማድረስ የኮሩ የሰራዊት አባላት ከ 83ሺህ በላይ ለምግብነት የሚውሉ እና የዛፍ ችግኞችን ተክለዋል ብለዋል። ዘጋቢ አይናዲስ  ደሳለኝ ናት።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
22👍5🔥3🥰1
የመከላከያ ሠራዊት አባላት በዛሬው ዕለት የችግኝ ተከላ-መርሃ ግብር አከናውነዋል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ባህር ሃይል  ከፍተኛ  መኮንኖች አባለትና የመከላከያ ክብር አባላት  በተገኙበት ቢሾፍቱ ከተማ እየተገነባ ባለው የባህር ሃይል መሰረታዊ ባህርተኞች  ማሰልጠኛ ቅጥር ግቢ የችግኝ ተከላ  መርሃ ግብር  አከናውነዋል።

የችግኝ ተከላ መርሐግብር ላይ ተገኝተው ንግግር  ያደረጉት የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ምክትል አዛዥ እና የውጊያ አገልግሎት ድጋፍ ሃላፊ ኮሞዶር ተገኝ ለታ ሰራዊታችን የቆየ ችግኝ የመትከል ልምድ ያለው መሆኑን አስታውሰው የዛሬ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም በሀገር አቀፍ ደረጃ በመትከል ማንሰራራት በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሃ ግብር አንድ አካል ነው ብለዋል።

በተመሳሳይ የጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የሠራዊት አባላት ከቦቶር ጦላይ ወረዳ አመራሮችና ከዋዩ ከተማ ማህበረሰቦች ጋር ሁለተኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናውነዋል።

የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ጡምሲዶ ፊታሞ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ የመንግስትን እቅድና ፕሮግራም ለመደገፍና የራሳችንን አስተዋፅኦ ለማበርከት ከወረዳው አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን ሀገር በቀል ችግኞች መትከሉን ገልፀዋል በቀጣይም ሠራዊቱ አሥፈላጊውን እንክብካቤ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

በተያያዘ የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ አመራሮች እንዲሁም የስታፍ አባላት በተገኙበት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

መርሃ-ግብሩን የዕዙ የስነ-ልቦና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ወንዶወሰን አስፋው ችግኝ በመትከል ያስጀመሩ ሲሆን ሠራዊታችን የተሰጠውን ተልዕኮ እያስቀጠለ እንደሚገኝ በመግለፅ ዛሬ የምንተክላቸው ነገ በሀገራችን የተስተካከለ የአየር ንብረት እንዲኖር  ያስችላልም ብለዋል። ዘገባው የየክፍሉ ሪፖርተሮች ነው


የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
13👍4🔥3
የማይተካ ነፍሱን ለሚሰጥ ወታደር የሚተካ ደም መለገስ መታደል ነው
     የኢንዱስትሪ ግሩፑ ደም ለጋሾች

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሠራዊት አባላትና ሲቪል ሠራተኞች ደም ለግሰዋል።
ኢንዱስትሪ ግሩፑ በሥሩ ባለው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አስተባባሪነት በግንባር ግዳጁን እየተወጣ ያለው ሠራዊት በሚያጋጥመው ጉዳት የደም ዕጦት እንዳያጋጥመው በማሰብ በርካታ በጎ ፈቃደኞች ደም ለግሰዋል።

ደምን መለገስ  ከጥቅሙ ውጭ አንዳች ጉዳት የለውም ያሉት የቤላ ደም ባንክ ሜዲካል ዳይሬክተር ኮሎኔል ዶክተር ጌታቸው አምባው በየሦስት ወር የሚተካውን በበጎነት ለዜጎች በመለገስ ሕይወትን ማዳን እንደሚገባ ተናግረዋል።

የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ በየዓመት የደም ልገሳን ጨምሮ የተለያዩ የክረምት በጎ አድራጎት ተግባራትን እንደሚያደርግ የገለፁት የኢንዱስትሪ ግሩፑ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ሻምበል እመቤት ጌታቸው ከየክፍሎች የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ለማበርከት መሰብሰቡን ተናግረዋል።

ለሠራዊታችን ደም መለገስ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ያነሱት የዕለቱ የደም ለጋሾችም የማይተካ ነፍሱን ለሚሰጥ ወታደር የሚተካ ደም በመለገስ ሕይወትን ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

ዘጋቢ ውብሸት አንበሴ
ፎቶግራፍ አብርሃም ዘርጋው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
10🔥7👍3