FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.8K photos
36 videos
9 files
8.51K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የሀገራችንን ልማትና ብልፅግና ለማረጋገጥ በተግባር  የተገለጠ ስራዎችን መስራታችን ተጠናክሮ ይቀጥላል።
    ክብርት ወይዘሮ ሐና አርዓያስላሴ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ፣የፍትህ ፣ የሰላም ሚኒስትሮች እና ተጠሪ ተቋማት በመተባበር ባዘጋጁት የክረምት የበጎ ፍቃደኝነት ተግባር ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ላይ  የተገኙት የፍትህ ሚንስትሯ ክብርት ወይዘሮ ሐና አርዓያስላሴ ፣ የክረምት የበጎ ፍቃድና የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴው የሀገራችንን ብልፅግናና ልማት ለማረጋገጥ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

የተተከሉት ችግኞች በወረዳው የተጀመሩትን የግብርና ስራዎች ከማገዝ ባለፈ ለመጪው ትውልድ ጥሩ መሰረትን የሚጥሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል የኑስ ሙሉ በበኩላቸው ከመከላከያ ጋር በተለያዩ ዘርፎች በጋራ እንደሚሰሩ ገልፀው ፣በወረዳው በተከናወነው የችግኝ ተከላና የበጎ ተግባር ስራ በመሳተፋቸው ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል።

በምስራቅ ሸዋ ዞን በሎሜ ወረዳ በተካሄደው ዝግጅት ላይ  አምስት ሺህ የተለያዩ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን  ለ1500 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍና የአስራ ስድስት የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ተጀምሯል።

በዝግጅቱ ላይ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኢንጂነር ሀይሻ መሃመድ ፣ የሎሜ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ታዬ ዶሪን ጨምሮ ሚኒስትር ዲኤታዎች ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች ፣ የምስራቅ ሸዋና የወረዳው የስራ ሀላፊዎችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👏2120🎉1
ኮሌጆች እና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶች የተቋሙን ዝግጁነት የሚያጠናክር ውጤታማ ስራዎችን ሠርተዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የበጀት ዓመቱን የስራ አፈፃፀም ውይይት አድርጓል። በውይይቱ በዋና መምሪያው ስር ያሉ ኮሌጆችና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶች የተገኙ ሲሆን የስራ አፈፃፀም ሪፖርቶችን በማቅረብ በጠንካራ እና በእጥረቶች የታዩ አፈፃፀሞች ላይ ውይይት አድርገዋል።

ከውይይቱ በኋላ በአዲሱ 2018 በጀት ዓመት እንደ መከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ሊተገበሩ የታቀዱ ዕቅዶች ላይ በዝርዝር ውይይት የስራ መመሪያ እንደሚሰጥ የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮንን አመላክተዋል።

በዛሬ ውሎው በቀረበው የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በሁሉም ኮሌጆች እና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶች የተቋሙን ዝግጁነት በማጠናከር በርካታ ውጤታማ ስራዎች እንደተሰሩ ተገልጿል።

በተቋሙ ኮሌጆችና ማሰልጠኛ ተቋማት ቁጥራቸው ከመቶ በላይ የሆኑ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ወታደራዊ አመራሮች ሰልጥነው መመረቃቸው በወታደራዊ ዲፕሎማሲው መስክ እና በሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ዲፕሎማሲ እንደሚያጠናክር ተገልጿል።

ዘጋቢ አባቱ ወልደማሪያም
ፎቶግራፍ አበረ አየነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2117🤩1
የዩናሚስ ሴክተር ሳውዝ አዛዥ የ21ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አሥከባሪ ሻለቃን ጎበኙ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም

አዛዡ ብርጋዲየር ጄኔራል ዲነሽ ሲንግ ኢትዮጵያዊያን የአድዋን ታሪክ እንደ ስንቅ ወስዳችሁ በሠላም ማስከበር ተልዕኮ ያላችሁን የፀና መሠረት በማጠናከር   ግዳጃችሁን በብቃት በማጠናቀቅ ለቀጣይ ሠላም አስከባሪ አባላት እንደምታስረክቡ እምነቴ የፀና ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በፍጥነት ነገሮችን በመረዳት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አርማና የሠላም ማስከበር ሰማያዊ ሄልሜንት አላማን በማሳካት እንደ ወትሮው ሁሉ ያሀገራችሁን ስም ማስጠራት አለባችሁ ብለዋል።

የ21ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል እንዳለ እሸቱ በቀጠናው አሁን ያለው የሠላም ሁኔታ ይበልጥ እንዲሻሻል የተሠጠንን ተልዕኮ በትኩረት እንወጣለን ሲሉ ተናግረዋል።

ጄኔራል መኮንኑ ሻለቃው ያለበትን ቁመና እና ወትሮ ዝግጁነት በምልከታ ከማረጋገጥ በተጨማሪ ገላፃ ተደርጎላቸዋል። በመጨረሻም በሁሉም የሙያ ዘርፍ በግዳጅ አፈፃፀም ምሳሌ ለሆኑ አባላት ሰርተ-ፊኬት አበርክተዋል። ዘጋቢ ፍፁም ተካ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
30🔥16👍15👏6👎2💘2
ተቋሙን የሚመጥን ሎጀስቲክሳዊ ስራ ከምንጊዜውም በላይ እየተሠራ ነው፡፡
ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምን ለአራት ቀናት ተመልክቷል።

የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ  ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል የዘንድሮው የእቅድ አፈፃፀም ውይይት ከወትሮው ለየት የሚያደርገው ሀገራችን ባከናወነቻቸው ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ተግባራት በዓለምአቀፍ እና አህጉራዊ መድረኮች ያላት ተቀባይነት እና ተደማጭነቷ እያደገ በመምጣቷ በተቋማችንም በወታደራዊ ዘርፉ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የሚደረጉ የወታደራዊ ጉዳዮች ትብብር እያደገ ሀገራት ከእኛ ጋር በትብብር ለመስራት የተነሱበት ወቅት መሆኑ ነው ብለዋል፡፡

በዋና መምሪያው ስር የሚገኙ የመምሪያ እና የክፍል ሃላፊዎች በተሰጣቸው ተልዕኮ እና በእቅዱ መሰረት አፈፃፀማቸውን በማስመልከት ባቀረቧቸው ሪፖርቶች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ እንደተቀመጠው በበጀት ዓመቱ ዋና መምሪያው የሠራዊቱን ሁለንተናዊ ዝግጁነት በማረጋገጥ ረገድ በሁሉም ዘርፍ የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት ሰፊ ስራ ተሠርቷል።
 
የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል በመርሐ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ አፈፃፀማችን የተቋማችንን ፈጣን ለዉጥ ታሳቢ በማድረግ፣ ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጡ ትጥቆች በውስጥ አቅም በማዘጋጀት ወጪን በመቀነስ፣ አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን እና ወጤታማነትን በማሳደግ ሁለንተናዊ ዝግጁነታችንን ያረጋገጥንበት የአፈፃፀም ብቃት ከፍ ብሎ የታየበትና አዳዲስ የስራ ባህል የተላመድንበት አመት ነው ብለዋል።

የሰራዊቱን የዕለት ተዕለት ቀለብ፤ አልባሳት፣ ትጥቅ እንዲሁም ሞብሊቲን በማረጋገጥ የውጊያ ድጋፍ አገልግሎት አሰጣጡን እያሳለጠ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በልማቱ ዘርፍም በተቋማችን እንዲተገበሩ የታቀዱ የልማት ስራዎች ውስጥ የማዕከሎች የግንባታ ስራ በማጠናቀቅ እና በማልማት አመራሩና ሙያተኛው የተሰጡትን ተልዕኮዎች በአግባቡ አሳክቶ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያደርስ፤ የሥራ ተነሳሽነቱ ይበልጥ እንዲጨምር መደረጉንም አንስተዋል።

በአዳዲስ ሀሳቦች ችግር ፈቺ ወጪ ቆጣቢ አሰራሮች ላይ አተኩሮ እንዲሰራ ማዕከላቱን ውብ፣ ፅዱ እና ለስራ የተመቹ የማድረግ ስራ መሠራቱን ገልፀዋል።

ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን ኢስማኤል በተቋማችን የተጀመረውን የሪፎርም ትግበራ የሚያሳኩ፣ የአመራሩንና የሙያተኛውን የመፈፀም አቅም የሚያሳድጉ የሰነ-ልቦና ግንባታዎች፣ ስልጠናዎች በተከታታይ በመከናወናቸው አሁን ላይ በሙያዊ ስነ-ምግባር የታነፀ ወታደራዊ ባህል እና ጨዋነትን ያከበረ የተቋቋመበትን ተልእኮ እና የሚሰጠውን ግዳጅ ታሳቢ ያደረገ አባላት መፍጠር መቻሉን አንስተዋል።

በሰላምም ሆነ በውጊያ የሚኖር ተልዕኮን በማገናዘብ፣ ሃብትን በአግባቡ የሚያስተዳድር፣ ቀልጣፋ፣ የማይቋረጥ፣ ወጪ ቆጣቢና ውጤታማ የውጊያ አገልግሎት ድጋፍ በተፈለገው ጊዜና ቦታ በፍጥነትና በጥራት መስራት የሚያስችል የሎጀስቲክስ አቅም የተፈጠረ መሆኑ በውይይቱ ተገልፃል፡፡ ዘገባው የወርቅነህ ተስፋው ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
34👍3
የመከላከያ ሚኒስቴር ተጠሪ ክፍሎች በበጀት ዓመቱ የእቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት እያደረጉ ነው፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ የውይይቱ ዋና ዓላማ የእቅድ አፈፃፀማችንን የጋራ ለማድረግ፣ ጠንከራ ጎኖቻችንን ይዘን ለመዝለቅ እና ክፍተቶች ካሉ የበለጠ በማሻሻል ተግባራቶቻችን ሁሉ የተቋማችን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ ፋይዳ ያላቸው እንዲሆኑ ማድረግ ነው ብለዋል፡፡

ሁሉም ተጠሪ ክፍሎች በተመደበላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የስራ አፈፃፀማቸውን እንደሚያቀርቡ እና በቀረቡት ላይ ውይይት ተደርጎ በመጨረሻም በ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ገለፃ እንደሚደረግ የሚኒስቴሩ እቅድ እና ሪፖርት ዝግጅት ክትትል ዳይሬክተር ኮሎኔል ፈይሳ ታደሰ ገልፀዋል፡፡

የመከላከያ ፋይናንስ ሥራ አመራር ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጅ የተቋሙን የሰው ሃይል፣ የውስጥ ገቢ፣ የግብዓት፣ የአግልግሎት አሰጣጥ እና የኢንስፔክሽን ስራዎች አቅምን ለማሳደግ መልካም ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልፀዋል፡፡ በተለይም ደግሞ የፋይናንስ ስርዓት፣ የግዥ አፈፃፀም፣ የንብረት አያያዝ ስርዓት በመመሪያ እና በአሰራር ተግባራዊ እንዲሆኑ በማድረግ በኩል አበረታች ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

የፋይናንስ ስርዓቱን በቴክኖሎጅ ማዘመን፣ የሴቶችን አቅም በማሳደግ እና ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ፣ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የሰራዊት አባላት እና የማህበረስብ ክፍሎች የበጎ አድራጎት ተግባራትን መከወን፣ የተመደበውን በጀት በአግባቡ ስራ ላይ ማዋል የበጀት ዓመቱ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫ ሆነው ሲተገበሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ
ፎቶግራፍ ድምሩ ህሩይ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2619