FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.8K photos
36 videos
9 files
8.51K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
በተሳሳተ ፕሮፖጋንዳ ተታለው ጫካ የገቡ 100 የፅንፈኛው አባላት እጅ ሰጡ። 

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

በሰሜን ሽዋ ዞን ሚዳ ወረዳ  ህብረተሰቡን ሲያሸብሩ የነበሩ 01 ሴትን ጨምሮ 100 አመራርና ተዋጊ እጅ መስጠታቸውን የአየር ወለድ ሬጅመንት አዛዥ ሻለቃ ኢብራሂም ሀጅ ተናግረዋል።

ሻለቃ ኢብራሂም ሀጅ ራሱን ፋኖ ብሎ የሚጠራው ፅንፈኛ ቡድን አማራን ነፃ እናወጣለን በሚል ፕሮፖጋንዳ ተታልለው ወደ ጫካ ከገቡ በኋላ የፅንፈኛው ሀይል የውሸት ፕሮፖጋንዳ ሲገባቸው እና የሠራዊቱ የህዝብ ወገንተኝነትና ተከታታይ የህዝብ መድረክ በመሰራቱ መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ በመቀበል እጃቸውን ለሠራዊቱ ሰጥተዋል ብለዋል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰይድ ኢብራሂም  በበኩላቸው የሰላም እጦቱ በወረዳው ተፈጥሮ መቆየቱን ገልፀው ከቅርብ ጊዚ ወዲህ የህዝብ በደል እና እንግልት እንዲሁም የፅንፈኛውን ቡድን የውሸት ፕሮፖጋንዳ ተረድተው ወደ ሰላም በመመለሳቸው አመሥግነዋል።

በቀጣይም ከጥምር ጦሩ ጋር በመሆን ወረዳውን አልፎም ዞኑን ወደ ቀደመ ሰላሙ እንመልሳለን ሲሉ ተናግረዋል።

በሰላም የገቡት የፅንፈኛው አባላትም ጫካ ያለው ሀይል ለህዝብ የቆመ ሳይሆን የውጪ ተላላኪና ለዘረፋ የቆመ ሀይል መሆኑን በመረዳት እጅ መሥጠት መቻላቸውን ተናግረው የምናውቃቸው በፅንፈኛው የተታለሉት በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል።

ዘጋቢ ታከለ ታለ
ፎቶ ግራፍ መኮንን አባይ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍3731😁2🔥1🏆1
የ6ኛ ዕዝ ማሠልጠኛ በየደረጃው ያለ አመራርን እያበቃ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ማረጋገጥ እና ጦርነትን ማስቀረት የሚቻለው የሠራዊቱን የጀግንነት ቁመና ማረጋገጥ ሲቻል በመሆኑ ስልጠና የማያቋርጥ የሠራዊቱ የዕለት ተዕለት ተግባር መሆኑን የ6ኛ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሸናል ሜጄር ጄኔራል ነገሪ ቶሊና ገልፀዋል።

ጄኔራል መኮንኑ በ6ኛ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ተገኝተው ሰልጠናቸውን እየተከታተሉ ለሚገኙ ሰልታዊ አመራሮች ተሞክሯቸውን አካፍለዋል።

የጦርነት አውድ መረዳት የሚችል ሠራዊት መገንባት ለነገ የማንለው ጉዳይ በመሆኑ ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ በክህሎት ልቀን መገኘት ሁሌም በስልጠና ማዳበር ነው ያሉት ሜጄር ጄኔራል ነገሪ ቶሊና ሠራዊት ተለዋዋጭ የውጊያ ዘዴዎችን ተረድቶ የስልጠና አቅሞችን በመጠቀም ተልዕኮውን በብቃት እየፈፀመ መሆኑን ተናግረዋል።

በክህሎት ደረጃ ከፍተኛ ሙያዊ ልህቀት ያለው በዘመናዊ የጦርነት ሰልቶች የበቃ ሰትራቴጅካዊ አስተሳሰብ የታጠቀ ሁሌም ራሱን በማሻሻልና በማብቃት የተዘጋጀ ተዋግቶ ሌሎችን ማዋጋት የሚችል አመራር ለመፍጠር ስልጠና ከፍተኛ አቅም መሆኑን አብራርተዋል።

ማሰልጠኛ ማዕከሉ የሠራዊቱ ታክቲካልና ሰነ-ልቦናዊ ዝግጁነት የሚጎለብትባቸው አቅሞች በመሆናቸው ተደማሪ የእውቀት ማዕከላት ናቸው ያሉት ምክትል አዛዡ ሠራዊቱ በአግባቡ ሊገለገልባቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ዘጋቢ አዲሱ አራጋው
ፎቶግራፍ ሌሊሴ አራርሜ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
41👍5🏆4
በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ የልማት ስራዎች እንዲስፋፉ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ16 ቀን 2017 ዓ.ም

በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ የተሻለ ሰላምና መረጋጋት በመኖሩ ያለስጋት የልማት ስራዎች እንዲሰሩ የሴክተር 3 የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሴክተር 3 ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ተክሉ ሁሪሳ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ አባላት የደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ የፀጥታ አካላትን በመደገፍና በጋራ በመጣመር የክልሉ የስራ ሃላፊዎችና ህብረተሰቡ ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሶ ያለስጋት የሰላምና የልማት ስራዎችን እንዲሰሩ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ብርጋዲየር ጀኔራል ተክሉ ሁሪሳ በከተማ ይሁን በገጠር አካባቢዎች የተጀመሩትን የልማት ስራዎች አልሸባብ በማደናቀፍ ትንኮሳ እንዳያደርግና የአካባቢውን ሰላም እንዳያውክ የሰላም አስከባሪ አባላቱ ቀድሞ አካባቢውን ቅኝት የማድረግና የእጀባ ስራዎችን በመሥራት ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ደንብና መመሪያን በማክበር የሰላም አስከባሪ አባላቱ በጨዋነት ግዳጁን እየፈፀመ ይገኛል ያሉት የሴክተሩ አዛዥ ሠራዊቱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ ንቁ ሆኖ ባህልና ጨዋነቱን ጠብቆ የቀጣዩን ተልዕኮ መፈፀም እንደሚጠበቅበትም አስገንዝበዋል፡፡  

ዘጋቢ ሰመረ እሸቱ
ፎቶግራፍ አይናለም ተክለፃዲቅ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
44👏11🏆3👍2
በመደበኛ ሠራዊት ምልመላ ስራ ቢሮው ሃላፊነቱን በሚገባ መወጣቱን አሥታወቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 17 ቀን 2017 ዓ.ም

የብሔራዊ ተጠባባቂ ኋይል ማደራጃና ማስተባበሪያ ቢሮ በበጀት ዓመቱ የተሰጠውን ኃላፊነት ከባለድርሻ አካላት ጋር ሆኖ በውጤት መፈፀሙን የቢሮው ኃላፊ ሜጄር ጄኔራል ጀማል መሃመድ ገልፀዋል።

በበጀት ዓመቱ የአንደኛና የሁለተኛ ዙር የመደበኛ ሠራዊት መልመላ ስራ ከተቋሙ በተሰጠን አቅጣጫ መሠረት በተሟላ መንገድ ማሳካት ችለናል ያሉት ኃላፊው ይህን ለማሣካት በየደረጃው ካለ አመራርና ሙያተኛ ጋር ተናበን መሥራት ችለናል በተፈለገው ልክም ሄደናል ብለዋል።

ለሀገራቸው ሠላም ሲሉ በጀግንነት በክብር የተሰው የሠራዊት አባላት ቤተሰቦች በህግ የተፈቀደላቸውን ድጎማ የወራሽ አበልና የዘላቂ ጡረታ ስራዎች ተደራሽ በማድረግ በኩል ትኩረት በመስጠትና በሃላፊነት መንፈስ የማከናወን ተግባር በበጀት ዓመቱ መከናወኑንም ሃላፊው አሥረድተዋል።

በ2018 በጀት ዓመት ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ በመቀጠል ብሎም በአዳዲስ ዕቅዶች ተቋም ተኮር ውጤታማ ተግባራት ለማከናወን አመራሩ እና አባላቱ ይበልጥ መዘጋጀት እንዳለባቸውም አመላክተዋል። ዘገባው የቢሮው የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
41👍16🔥4