FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.7K photos
35 videos
9 files
8.51K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የመከላከያ ማርችንግ ባንድ የሙዚቃ ሥራዎችን በሩሲያ ሞስኮ ለህዝብ አቅርቧል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠረዊት ነሃሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
34👍12🔥3
የመከላከያ ሚኒስትሯ የጦር ኃይሎች ኮንፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታከሚዎችን ጎበኙ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

‎እንኳን ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ በሰላም አደረሳችሁ በሚል በዛሬው ዕለት የመከላከያ ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ እና ስታፋቸው ከመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ጋር በመጣመር ለሆስፒታሉ የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር አካሂደዋል።

በዚሁ ወቅትም ሚኒስትሯ ‎ ለሀገር ክቡር ዋጋ ከከፈላችሁ ውድ ጀግኖቻችን ጋር ማዕድ በመጋራታችን ኩራት ተሰምቶናል ብለዋል።  ኢትዮጵያ  በሁለንተናዊ እድገቷ ቀዳሚ ከሚባሉ ሀገራት ተርታ የምትመድበበት ቀን ሩቅ አይሆንም ያሉት ሚኒስትሯ ለዚህ ደግሞ  የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና አመራሮች  የሀገሪቱን ሰላም እና ሉአላዊነት በማስጠበቅ በኩል ቀዳሚውን ስፍራ ስለሚይዙ  ኢትዮጵያ  እና ኢትዮጵያዊ  ሁሉ ሲያመሰግናቸው ይኖራል ብለዋል።

‎የመከለከያ ጤና ዋና መምሪያ ሌተናል ጀኔራል ጥጋቡ ይልማ በበኩላቸው ጤና ዋና መምሪያው በበጀት ዓመቱ በርካታ ተግባራት ማከናወኑን ገልፀው ከእነዚህ ውስጥም  የውጭ ህክምናን በሀገር ውስጥ ህክምና እንዲተካ ጥረት ማድረግ እና የታካሚዎችን ፍላጎት ማርካት ቀዳሚ ተግባር መሆኑን አንስተዋል።

ለታከሚዎቹ እንኳን ለአዲሱ ዓመት እና ለፅናት ቀን ዋዜማ በሰላም አደረሳችሁ ያሉት ጀኔራሉ ለሀገር ዋጋ የከፈሉ እና በመክፈል ላይ የሚገኙ ጀግኖችን ማክበር ኢትዮጵያን  ማክበር በመሆኑ ከእናንተ ጋር መዓድ በመጋራታችን ደስታችን ከፍ ያለ ነው ብለዋል።

በተመሳሳይ በወይራ  በሚገኘው የጦር ሀይሎች ሆስፒታል የታከሚዎች ጊዜያዊ ማገገሚያ ማዕከል የታከሚዎች ጉብኝት እና የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር የተከናወነ ሲሆን ጤና ዋና መምሪያው እየገነባቸው የሚገኙ የመሰረተ ልማት ስራዎችም ተጎብኝተዋል።

ስራዎቹ አበረታች መሆናቸውን ጠቅሰው ወደፊት የበለጠ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ክብርት ሚኒስትሯ መልዕክት አስተላልፈዋል።

‎ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ
‎ፎቶግራፍ ዕፀገነት ዴቢሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
25👍6🔥2😁2👏1
እኛ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እያለን ኢትዮጵያን መበተን አይታሠብም፦
     ጄኔራል አበባው ታደሠ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

በምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር 4ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ለመታደም ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ የገቡት  የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር እኛ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የቁርጥ ቀን ልጆች እያለን ኢትዮጵያን መበተን አይቻልም፤ አይታሠብምም ብለዋል።

በውጭ ያሉ ጠላቶቻችን እና ውስጥ ያሉ ጠላቶቻችን ተሰባስበው እንመጣለን እያሉ ሲመክሩና ሲፎክሩ ይሰማል።  እኛም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከመላ ህዝባችን ጋር ሆነን ምን ሊያደርጉ እንደሚመጡ ስለምናስብና ስለምናውቅ ተዘጋጅተን እንጠብቃቸዋለን፤ ያኔ የተለመደውን ዋጋ ከፍለን ኢትዮጵያን ካሰቡላት ጥፋት እንደ ትናንቱ እንታደጋለን ብለዋል።

በህጋዊ መንገድ በህዝብ የተመረጠ መንግስትን ህገ ወጥ በሆነ መንገድ በአፈሙዝ ለማስወገድ የሚደረግ ማናቸውም ሙከራ ጀግናው ሠራዊታችን እያለ አይሳካም ያሉት ጄኔራል አበባው ታደሠ ለህዝብ የሚጠቅም አማራጭ ሃሳብ ያለው ማንኛውም አካል ህጋዊ እና ሠላማዊ መንገዶችን ተጠቅሞ ምኞቱን ለማሳካት መስራት እንደሚችል እና የዘመኑ ብቸኛ አማራጭም ይህ ብቻ እንደሆነ  አስገንዝበዋል።

ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ በዕለቱ ባደረጉት ንግግር 4ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ያከበረው የ401ኛ ቴዎድሮስ ኮር በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች የተሠጠውን ወታደራዊ ግዳጅ እንደሌሎች የጦር ክፍሎች በድል መጨረስ የቻለ መቺ የጦር ክፍል መሆኑን ተናግረዋል።

ቴዎድሮስ ኮር በሠሜኑ ህግ የማስከበር ተልዕኮ ግዳጁን በላቀ ውጤት ከፈፀመ በኋላም አሁን ተሰማርቶበት በሚገኘው የሆሩ ጉድሩ ወለጋ ዞን፤ አሸባሪውን የሸኔን ቡድን በመምታት እና ተገዱ ወደ ሰላም እንዲገባ በማድረግ ለአካባቢው ህዝብ አንፆራዊ ሰላም ማስፈን የቻለ ኮር ነው በማለት የኮሩን የላቀ ግዳጅ አፈፆፀም ገልፀውታል።

ጄኔራል አበባው ታደሠ በመጨረሻም የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ህዝብና አስተዳደር በአሸባሪው ሸኔ የነበረበትን ከባድ ጫና ተቋቁሞ ከሠራዊታችን ጋር በፅናት በመቆም ላሳየው ቁርጠኝነትና ለከፈለው መስዋዕትነት ሁሉ በመከላከያ ሠራዊት ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

በዕለቱም ጄነራል አበባው ታደሠ እና ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አባገዳዎች እና ሃደስንቄዎች ፤ የሃገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች የተበረከተላቸውን  የፈረስ ፤ ጋሻና ጦር ስጦታ ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምሬሳ ፊጤ እና ከአባገዳዎች እጅ ተቀብለዋል።

ዘጋቢ ሲሳይ ደመቀ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
24👍18👏10👎1