FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.7K photos
35 videos
9 files
8.51K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ዕዙ በላብራቶሪ እና በረዳት ፋርማሲ ያሰለጠናቸውን የጤና ሙያተኞችን አስመረቀ፣

የኢፌዴሪ መከሊከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ/ም

የ6ኛ ዕዝ ጤና መምሪያ ለአምስት ወራት በላብራቶሪና በረዳት ፋርማሲ ሙያ ያሰለጠናቸውን የጤና ሙያተኞች አስመርቋል።

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፋትና የስራ መመሪያ የሰጡት የዕዙ ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ብርጋዲየር ጀኔራል መኮንን በንቲ ዕዙ የሚሰጠውን የትኛውንም ግዳጅ በአስተማማኝ ብቃት እንዲወጣ ለማስቻል የጤና ዝግጁነትን ማረጋገጥ ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

ዕዙ በሃገራችን ላይ በየትኛውም አቅጣጫ በማንኛውም  ቦታና ጊዜ ሊቃጡ የሚችሉ ትንኮሳዎችን በብቃት መመከት በሚያስችለው የተሟላ ዝግጁነት ላይ ይገኛል ያሉት ጀኔራል መኮንኑ የዕለቱ ተመራቂዎችም ይህንን የዕዙን የማድረግ አቅም የበለጠ ለማጎልበት ባገኛችሁት ስልጠና ተጠቅማችሁና በየጊዜው አቅማችሁን በማዳበር የዕዙን የጤና ዝግጁነት በማረጋገጥ ተደማሪ አቅም መፍጠር ይጠበቅባችኋል ብለዋል።

የዕዙ ጤና መምሪያ ሃላፊ ኮሎኔል ፈንታሁን ተሾመ በበኩላቸው የዕዙ ጤና መምሪያ የአገልግሎት አሰጣጡ በማሻሻልና የጤና ተደራሽነቱን በማስፋፋት ተልዕኮውን በላቀ ብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀው የእለቱ ተመራቂዎችም የሆስፒታሉን ሁለንተናዊ አቅም ለማጠናከርና የጤናሙያተኞችን ሙያዊ ብቃት ለማሳደግ እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማሳካት አጋዥ እንደሚሆኑም ተናግረዋል።

በእለቱም  በስልጠናው  የተሻለ ውጤት ለአስመዘገቡ ተመራቂዎች ፣ ለስልጠናው መሳካት ትብብርና ድጋፍ ለአደረጉ አካላት እና የስታፍ ክፍሎች እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ዘጋቢ ደባልቅ አቤ
ፎቶ ግራፍ ይህአለም አታላይ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
23👍10🔥3👏2👎1
የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር የተሠጠውን ተልዕኮ በአስገራሚ ጀግንነት መፈፀም የቻለ ኮር ነው
    ሜጄር ጄኔራል ሙላት ጀልዱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም

በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ በሚገኘው የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር 4ኛ ዓመት የምስረታ በዓል መድረክ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ሜጄር ጄኔራል ሙላት ጀልዱ ቴዎድሮስ ኮር በዕዙ የተሠጠውን ውስብስብ ተልዕኮ በፅናትና ቁርጠኝነት መፈፀም የቻለ የምዕራብ ዕዝ አስተማማኝ ክንድ ነው ብለዋል።

ሜጄር ጄኔራል ሙላት ጀልዱ የምዕራብ ዕዝ የኢትዮጵያ ጋሻ በመሆን ተቋሙ የሚሠጠውን ማናቸውንም ግዳጅና ተልዕኮዎች በጀግንነት በመፈፀም አንፀባራቂ ድሎችን የማስመዘገብ አኩሪ ታሪክ ባለቤት መሆኑን አውስተው በዕዙ ስር ያሉ ኮሮች እርስ በእርስ ባላቸው ጥልቅ ቁርኝትና መናበብ ምክንያት ጠላትን መውጫ መግቢያ በማሳጠት መደምሰስ መገለጫቸው ነው ብለዋል።
 
የምስረታ በዓሉን በማክበር ላይ የሚገኘውና የምዕራብ ዕዝ አስተማማኝ ክንድ የሆነው ቴዎድሮስ ኮርም በማናቸውም ግዳጆች ወታደራዊ ብቃቱንና ጀግንነቱን አስመስክሯል ብለዋል። ይህንኑ አይበገሬነቱን አጠናክሮ ማስቀጠል እና ለላቀ ድል መዘጋጀት እንዳለበት ያሳሰቡት ጄኔራል መኮንኑ ለኮሩ አመራርና አባላት የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውንም ገልፀዋል።

ዘጋቢ ሲሳይ ደመቀ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
23🔥11👏4🥰2👍1
በጋዜጠኛ ሌተናል ኮሎኔል ፈይሳ ናኔቻ የተፃፈው የወታደር ውሎ አዳር መፅሀፍ ተመረቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም

የወታደር ውሎ አዳር የተሰኘው መፅሀፍ፣ የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማን ጨምሮ፣ ጄኔራል መኮንኖች ፅሀፊያን እና ደራሲያን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በአደዋ ድል መታሰቢያ ሁለገብ አዳራሽ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።

የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ ታሪኮች የሀገር ሀብት በመሆናቸው፣ሰንዶ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ጠቁመው የጋዜጠኛው መፅሃፍም የመከላከያ ሠራዊቱን ሁለንተናዊ የግዳጅ ውሎ አስገራሚ የኋላ ታሪኮች የሚያትት በመሆኑ አመሥግነውታል።

በመከላከያ ስነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት የሚዲያ ስራዎች ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል አስፋው ማመጫ፣ ለምርቃት የበቃውን መፅሀፉ ዳሰሳ በማድረግ የሰራዊቱን ህይወት በሚገባ የሚገልፅ እና የሚያሳይ መሆኑን አመላክተው በመፅሀፉ ውትድርና እና ኢትዮጵያዊነት ያላቸውን ግንኙነት፣ በግልፅ፣ማሳየት እንደተቻለም አብራርተዋል።

በመፅሀፉት ምርቃቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር  ፕሬዚዳንት፣ ደራሲ አበረ አዳሙ፣በመፅሀፉ ላይ የመመዘኛ ዳሰሳ አድርገዋል። በዚህም መፅሀፉ የመፅሀፍ መመዘኛ መስፈርትን በጥሩ ሁኔታ ማሟላቱን ገልፀው ወታደራዊ ታሪኮች ሀገርን በሚመጥን መልኩ ተሰንደው እና በመፅሃፍ ተዘጋጅተው ለትውልድ መተላለፍ እንዳለባቸው አመላክተዋል። ለሀገር መስዋዕት እየከፈለ ሠላምን እያረጋገጠ  ለሚገኘው የመከላከያ ሠራዊትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዘጋቢ ቢያድግልኝ መሪ
ፎቶ ግራፍ አበረ አየነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
33👍25👏8🔥2🏆2🥰1
ጤና ይስጥልን ጠቂት ሥለጤናዎ ታይፈስ ልብስ በመልበስ የሚመጣ በሽታ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

የሀገራችን  የብዙ ጤና ጣቢያዎች ደረጃ "ሀ" የበሽታ አይነት ተደርጎ መቆጠር ከጀመረ ሰነባብቷል። ይኸ ጉዳይ እየቆየ የመጣና ዛሬ ላይ ታይፈሴ ተነሳብኝ ፤ ታይፎይዴ ወደ ታይፈስ ተቀየረብኝ ወደ ሚል ሰፊ እና ሊቀለበስ ወደ ማይችል አስቸጋሪ የማህበረሰብ እሳቤ ሊደርስ ችሏል።

ታካሚዎች ወደ ህክምና ቤት የሚመጡት ለመመርመር ሳይሆን የተቀሰቀሰባቸውን ታይፈስ ለማከም የሚውል መድሐኒት ለመውሰድ ነው የሚመጡት ቢባል ይቀላል። ይኽ ሊሆን የቻለው በተደጋጋሚ ታይፈስ ነው እየተባሉ በመመለሳቸው ነው። ትልቁ ችግር ከኛው ባለሙያው ጋር ነው።

ታይፈስ አደገኛ እና ተላላፊ በሽታ ነው። በአለም ላይ በወረርሺኝ ደረጃ ከሚከሰቱ ቀዳሚ ነው። የብዙ ሚሊዮኖችን ህይወት ቀጥፎ  አልፏል። ታይፈስ ተስቦ በሚል ይተጠራል። ዛሬ ታይፈስን ከመኖር ብቻ አይደለም ከታሪክ ማህደራቸውም ያጠፉ ሀገራት ሞልተዋል። ምክነያቱም ታይፈስ የሰው ልጅ ስብዕና የሚነካ ፀያፍ ህመም ነው ብለው በማሰባቸው ነው።

ታይፈሰን ከሰው ወደ ሰው የሚያዛምቱት አካላት በሚለበስ ልብስ ውስጥ ምሽግ ሰርተው በሚኖሩ ነው። የግል እና የልብስ ንፅህና ባለመጠበቅ ተስቦን የሚፈጥር ጀርም ተሸካሚዎች የሚፈጡረበት እድል ስለተመቻቸ ነው። የታይፈስ መከላከያ ንፅህና መጠበቅ ነው። ሌላ ተዓምር የለም።

በተለይ ቀዝቃዛ አካባቢ ታይፈስ ይከሰታል። ለዚህ ትልቁ ምክነያት ቅዝቃዜን ለመከላከል ሰው ያለ የሌለውን ልብስ ደራርቦ በመልበሱና ቅዝቃዜን በመፍራት ልብስን አውልቆ ለማጠብ በሠስነፉ ነው። ታይፈስ ከገንዘብ እና አስተሳሰብ ድህነት ጋር የተቆራኘ ገዳይ እና አሳፋሪ ህመም ነው። ልብስን ከገላ አርቆ ቢያንስ ለ24ሰዓት ካስቀመጡ ጀርም ተሸካሚ አካላት ይሞታሉ።

ትክክለኛው ታይፈስ ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት ያለው ነው። ሙቀት የሌለው ሰውን ምንም አይነት ምልክት ቢኖረው ታይፈስ ነው ማለት ያስቸግራል። የሙቀት ልኬቱ ትክክልኛ የሆነን ሰው ታይፈስ ነው ከማለት ይቆጠቡ። በተረፈ ለታይፈስ የሚውል ምርመራ ለታካሚ የሚጠቅም ሳላልሆነ አይዘዙ ፤ ሌሎች ችግሮችም ውጤቱን እንዳለ አሳይተው ሊያሳሳቱ በመቻላቸው ነው።

ሌላው የታይፈስ የቅርብ ጓደኛ ታይፎይድ ነው። ሁለቱን መነጣጠል አቅቶናል። ታይፈስ ታይፎይድ ተባልኩኝ
የማይል የመኪና አደጋ ገጥሞት የሔደ ብቻ ይመስለኛል። ታይፈስን ወደ ታይፎይድ ፤ ታይፎይድን ወደ ታይፈስ ማቀያየር የተለመደ ክስተት ሆኗል። ይኸ ማለት ላምን ወደ በግ ፤በግን ወደ ላም እንደመቀየር ነው። ሁለቱ በፍፁም የተራራቁና አንዱ ወደ ሌላ ሊቀያየሩ የማይችሉ ናቸው። ሁለቱ ህመሞች ግን በአንድ ሰው ላይ ሊከሰቱ ይችላሉ። አንድ ሰው ብዙ አይነት ህመሞች ሊኖሩበት እንደሚችሉት ማለት ነው።

ታይፎይድ በምግብና ውሐ መበከል የሚመጣ ውሐና ምግብ ወለድ በሽታ ነው። የምግብ ንፅህናን የውሐ ንፅህናን መጠበቅ ሁነኛ መፍትሔ ነው። ሁለቱን የሚያመሳስላቸው በንፅህና ጉድለት መከሰት መቻላቸው ነው። የአኗኗር ደረጃን ፍትው አድርገው የሚያሳዩ የአንድ ሰው አኗኗር ማሳያ መስተውቶች ናቸው።

በሌላ መንገድ ታይፈስና ታይፎይድን የሚያዛምቱት የምግብና መኝታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ናቸው። ብዙ የሀገራችን የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡ ሆቴሎች ታይፈስ ቀጣይ ሆኖ እንዲቀር  እየሰሩ ያሉ ይመስላል። በዚህም ብዙ የግል ንፅህና የሚጠብቁ ሰዎች በሆነ አጋጣሚ ሆቴል ሲያድሩ ለታይፈስ የሚጋለጡ እንዳሉ ልብ ይበሉ። ምናልባትን ታይፈስ ሊሆን ይችላል ለማለትም የማይጠረጠርበት የአኗኗር ደረጃ ላይ ያለ ሰው በዚህ በሽታ ህይወቱ አደጋ ላይ ሊደርስ ይችላል።

ችግሩ ከግለሰብ አልፎ የማህበረሰብ ነው። የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ብዛት ያላቸው ሆቴሎች ከደረጃ በታች መሆን ብቻ አይደለም የተባይና የበሽታ አምጪ ነፍሳቶች መገኛና መፈልፈያም ጭምር ናቸው። ተቆጣጣሪ አካላት የበሩን ቀለም ብቻ ከማየት አንሶላና ብርድለብሱንም አየት አየት ማድረግ አለባቸው። በእውነቱ አሳፋሪ አገልግሎት የሚሰጡ ሰው ከመግደል ወንጀል በላይ ስብዕናን የሚነኩ በሚል መጠየቅ አለባቸው። ትክክለኛው ታይፈስ ገዳይና አጣዳፊ እንዲሁም ወረርሺኝ የሚያስነሳ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
17👍3🔥1