FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.7K photos
35 videos
9 files
8.51K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ጄኔራል አበባው ታደሠ የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር የምስረታ በዓልን ለመታደም ሻምቡ ከተማ ገቡ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ እና ሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች  የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር የምስረታ በዓል ላይ ለመታደም ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ ገብተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ እና ሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በስፍራው ሲደርሱ የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች የዞንና የወረዳ አስተዳደሮችን ጨምሮ የሻምቡ ከተማ ከንቲባና የአካባቢው አባገዳዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጄኔራል አበባው ታደሠ  በቴዎድሮስ ኮር የተዘጋጀውን የፎቶ አውደ ርዕይን እና የኮሩን ሎጎ  መርቀዋል። በተጨማሪም  ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ ቴዎድሮስ ኮር በራስ ወጪ የሠራውን የአቅመ ደካማ እናት መኖሪያ ቤትን መርቀው በመክፈት ቁልፍ አስረክበዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው እናትም ረዳት አልባ በመሆናቸው እና አቅማቸው በመድከሙ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠው የቆዩ መሆናቸውን ተናግረው ዛሬ ሠራዊቱ ሠርቶ ላስረከባቸው ቤት ምስጋና አቅርበዋል።

አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች በሠጡት አስተያየትም እኝህ አቅመ ደካማ እናት  ከዚህ በፊት በፈራረሠ ቤት ውስጥ ብርድ እና ዝናብ ሲፈራረቅባቸው መቆየቱን ገልፀው ሠራዊቱ ባደረገው የበጎ አድራጎት ተግባር መደሠታቸውን ተናግረዋል።

የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር 4ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ ኩነቶች ማክበሩን ቀጥሏል።

ዘጋቢ ሲሳይ ደመቀ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
42👍4🔥1
የምዕራብ ዕዝ  ቴዎድሮስ ኮር 4ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ማጠቃለያ እየተካሄደ ነው።
 
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

" የጀግኖች መፍለቂያ ፤ የድል ምልክት " በሚል መሪ ቃል እየተከበረ በሚገኘው በዚሁ የቴዎድሮስ ኮር 4ኛ ዓመት ምስረታ በዓል ማጠቃለያ ላይ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ ፣ ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና ፣ የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔሬል ዘውዱ በላይ ፣ የምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሠለ መሠረት፣ የሆሮጉዱሩ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ  ምሬሳ ፊጤ ጄኔራል መኮንኖች ፣ የምዕራብ ዕዝ አመራሮችን ጨምሮ የቴዎድሮስ ኮር የሠራዊት አባላት እና የሻምቡ ከተማ ነዋሪዎች ታድመዋል።

በምስረታ በዓሉ ማጠቃለያ የተለያዩ መርሃ - ግብሮች እንደሚከናወኑ አና ልዩ ልዩ መልዕክቶች እንደሚተላለፉ ይጠበቃል።

ዘጋቢ ሲሳይ ደመቀ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2016🔥1
መቻል ቦሌ ክፍለ ከተማን 4ለ1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ከጀግኒት ፕሮሞሽን ጋር በጋራ በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው የአዲስ አበባ ጀግኒት ዋንጫ (ሲቲ ካፕ) ሀሉተኛ ጨዋታ መቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን ቦሌ ክፍለ ከተማን አራት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸንፏል።

መቻል አሸናፊ የሆነበትን አራት ግቦች  ትግስት ወርቄ ሶስት እና ቱፊት ካዲዮ  ቀሪውን ከመረብ አሳርፈዋል።

የዛሬውን ድል ተከትሎ መቻል እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራት አራት ነጥብ በመያዝ በጎል ተበላልጠው አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን ወደ ሩብ ፍፃሜ ተቀላቅለዋል።

በጨዋታው ላይ ለመቻል ሶስት ግቦች ያስቆጠረችው አጥቂዋ ትግስት ወርቄ የጨዋታው ኮከብ ተብላ ከክብር እንግዳው ሽልማት ወስዳለች።

በስድስት የከተማዋ ክለቦች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ የጀግኒት ዋንጫ ውድድር ላይ በሁለት ምድብ ተከፍሎ እየተካሄደ ይገኛል።

በቀጣይ ለዋንጫ ለማለፍ መቻል ከምድብ ሁለት ከተደለደሉት ከኢትዮ ኤሌክትሪክና አዲስ አበባ ከተማ አሸናፊ ከሆነው ቡድን ጋር የሚገናኝ መሆኑን የወጣው ፕሮግራም ያመለክታል።

ዘጋቢ ገረመው ጨሬ
ፎቶግራፍ እስክንድር ሰለሞን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍1613👏6🔥1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የመከላከያ ማርችንግ ባንድ የሙዚቃ ሥራዎችን በሩሲያ ሞስኮ ለህዝብ አቅርቧል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠረዊት ነሃሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
35👍13🔥3
የመከላከያ ሚኒስትሯ የጦር ኃይሎች ኮንፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታከሚዎችን ጎበኙ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

‎እንኳን ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ በሰላም አደረሳችሁ በሚል በዛሬው ዕለት የመከላከያ ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ እና ስታፋቸው ከመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ጋር በመጣመር ለሆስፒታሉ የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር አካሂደዋል።

በዚሁ ወቅትም ሚኒስትሯ ‎ ለሀገር ክቡር ዋጋ ከከፈላችሁ ውድ ጀግኖቻችን ጋር ማዕድ በመጋራታችን ኩራት ተሰምቶናል ብለዋል።  ኢትዮጵያ  በሁለንተናዊ እድገቷ ቀዳሚ ከሚባሉ ሀገራት ተርታ የምትመድበበት ቀን ሩቅ አይሆንም ያሉት ሚኒስትሯ ለዚህ ደግሞ  የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና አመራሮች  የሀገሪቱን ሰላም እና ሉአላዊነት በማስጠበቅ በኩል ቀዳሚውን ስፍራ ስለሚይዙ  ኢትዮጵያ  እና ኢትዮጵያዊ  ሁሉ ሲያመሰግናቸው ይኖራል ብለዋል።

‎የመከለከያ ጤና ዋና መምሪያ ሌተናል ጀኔራል ጥጋቡ ይልማ በበኩላቸው ጤና ዋና መምሪያው በበጀት ዓመቱ በርካታ ተግባራት ማከናወኑን ገልፀው ከእነዚህ ውስጥም  የውጭ ህክምናን በሀገር ውስጥ ህክምና እንዲተካ ጥረት ማድረግ እና የታካሚዎችን ፍላጎት ማርካት ቀዳሚ ተግባር መሆኑን አንስተዋል።

ለታከሚዎቹ እንኳን ለአዲሱ ዓመት እና ለፅናት ቀን ዋዜማ በሰላም አደረሳችሁ ያሉት ጀኔራሉ ለሀገር ዋጋ የከፈሉ እና በመክፈል ላይ የሚገኙ ጀግኖችን ማክበር ኢትዮጵያን  ማክበር በመሆኑ ከእናንተ ጋር መዓድ በመጋራታችን ደስታችን ከፍ ያለ ነው ብለዋል።

በተመሳሳይ በወይራ  በሚገኘው የጦር ሀይሎች ሆስፒታል የታከሚዎች ጊዜያዊ ማገገሚያ ማዕከል የታከሚዎች ጉብኝት እና የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር የተከናወነ ሲሆን ጤና ዋና መምሪያው እየገነባቸው የሚገኙ የመሰረተ ልማት ስራዎችም ተጎብኝተዋል።

ስራዎቹ አበረታች መሆናቸውን ጠቅሰው ወደፊት የበለጠ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ክብርት ሚኒስትሯ መልዕክት አስተላልፈዋል።

‎ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ
‎ፎቶግራፍ ዕፀገነት ዴቢሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
26👍7🔥2😁2👏1