የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት አካሄደ ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
በዚሁ የፓናል ውይይት ላይ የጀግናው ሠራዊታችን ዘመን ተሻጋሪ ገድሎች ተዘክረዋል። በተለይም የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር ፅናት ፤ ቁርጠኝነት እና ህዝባዊነት መሠረቶች በፅሁፍ ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
የፓናል ውይይቱን የመሩት የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር ስያሜውን ከጀግናው አፄ ቴዎድሮስ መውረሡ ለጠላቶቻችን እጅ የማንሠጥ ፤ የማንጨበጥ የእሳት ነበልባል ትውልድ ዛሬም ኢትዮጵያ እንዳላት የሚጠቁም መሆኑን ታሪክን አጣቅሠው አስገንዝበዋል።
ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ቴዎድሮስ ኮር "የጀግኖች መፍለቂያ ፤ የድል ምልክት "የሚል መሪ ቃል ያነገበ ሲሆን በእርግጥም ኮሩና የኮሩ መስራች ክፍለጦሮች በሠሜኑ የህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻ በሠሩት ድንቅ ጀብዱ በሃገር ደረጃ የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ እንደነበሩ አስታውሰው ቴዎድሮስ ኮርም ጀግኖች የሚፈልቁበት አሃድ ነው ብለዋል።
የፓናል ውይይቱ ተጋባዥ እንግዳ የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምሬሳ ፊጤ በበኩላቸው ካለፉት ሁለት እና ሶስት ዓመታት በፊት ምዕራብ እና ቄለም ወለጋን ጨምሮ በአራቱም የወለጋ ዞኖች ፅንፈኛ እና አሸባሪ ቡድኖች በንፁሃን ላይ ሲያደርሡት የነበረው ሁለንተናዊ ሠቆቃ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ክፉኛ ያሳዘነ እንደነበር አውስተዋል። ከማንም በላይ የወለጋ ህዝብ ደግሞ የመጀመሪያው ገፈት ቀማሽ በመሆኑ ያንን ወቅት ዛሬም ድረስ የጨለማ ዘመን እያለ እንደሚጠራው ተናግረዋል።
የምዕራብ ዕዝ በቀጠናው በተሠማራ አጭር ግዜ ውስጥ ታሪክ ሲዘክረው በሚኖር ጀግንነትና ወታደራዊ ብቃት የወለጋ አካባቢን ከጨለማ ወደ ብርሃን አሸጋግሯል ያሉት አቶ ምሬሳ ፊጤ የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞንም እንደ ሌሎቹ የወለጋ ዞኖች ለዓመታት የራቀውን ሠላም መልሶ እንዲጎናፀፍ አስችሏል ብለዋል።
ለዚህ ስኬት ደግሞ በተለይ የዕዙ ቴዎድሮስ ኮር ያደረገው ተጋድሎ በወለጋ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ለዘለዓለም ታትሞ ሲዘከር ይኖራል ብለዋል።
የፓናል መወያያ ፅሁፉን ያቀረቡት ዕጩ ዶክተር ደረጄ ገቢሳ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለአንድ ሀገር የጀርባ አጥንት ፤ የሉዓላዊነት፤ የብሔራዊ ክብርና ጥቅም ዋልታ ምሰሶ መሆኑን ገልፀው የጀግናው ሠራዊታችን ተልዕኮዎች ሁሉ ከዚሁ መርህ የመነጩ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።
ዕጩ ዶክተር ደረጄ ገቢሳ የምዕራብ ዕዝ በወለጋ እና አዋሳኝ አካባቢዎች በአጭር ግዜ ውስጥ ያስመዘገበው ድል ሠራዊቱ የተገነባበትን ህዝባዊነት እና አይበገሬነት ፍንትው አድርገው ያሳዩ ስለ መሆናቸው አብራርተዋል። የቴዎድሮስ ኮርም ለዚህ አባባል ሁነኛ ማረጋገጫ የሆኑ ተጨባጭ ድሎችን ማስመዝገቡንም ጠቅሠዋል።
የፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች በሠጡት አስተያየትም። ዛሬ እንዲህ የሠላም አየር መተንፈስ የቻልነው በእናንተ በውድ ልጆቻችን ደምና መስዋዕትነት በመሆኑ እናከብራችኋለን፤ እንወዳችኋለን የተገኘው አንፃራዊ ሠላም ተጠናክሮ ቀጥሎ አካባቢያችን የተቸረውን የተፈጥሮ ፀጋ በማልማት ለራሳችንም ለሃገራችንም የሚተርፍ እድገትና ብልፅግና እንዲመጣ በማናቸውም ሁኔታ ከጎናችሁ አንለይም ሲሉ ተናግረዋል።
ዘጋቢ ሲሳይ ደመቀ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

YouTube
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
# የመከላከያ ሠራዊት ቁልፍ እሴቶች፡-
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
❤23👍7🔥2🥰1
መሰረተ ልማትን ለማደናቀፍ በሞከሩ ሃይሎች ላይ እርምጃ ተወሰደ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ክፍለጦር በማዕከላዊ ጎንደር ግዳጁን እየተወጣ ባለበት ቀጠና ህዝብ ጠል የሆኑ ልማትን ለማደናቀፍ በተሰማሩ ሃይሎች ላይ እርምጃ ተወስዷል።
በተወሰደው ርምጃም በጠላት ላይ ሰብዓዊና ማቴሪያላዊ ኪሳራ የደረሰ ሲሆን ክላሽ፣ ኋላ ቀር መሳሪያ የተለያዩ ዓይነት ጥይቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል
ዘጋቢ ሱማፍ ብርሃኑ
ፎቶግራፍ እንዳልካቸው ሃጂ

❤24👍14🔥2👏1😁1
ዕዙ በላብራቶሪ እና በረዳት ፋርማሲ ያሰለጠናቸውን የጤና ሙያተኞችን አስመረቀ፣
የኢፌዴሪ መከሊከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ/ም
የ6ኛ ዕዝ ጤና መምሪያ ለአምስት ወራት በላብራቶሪና በረዳት ፋርማሲ ሙያ ያሰለጠናቸውን የጤና ሙያተኞች አስመርቋል።
በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፋትና የስራ መመሪያ የሰጡት የዕዙ ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ብርጋዲየር ጀኔራል መኮንን በንቲ ዕዙ የሚሰጠውን የትኛውንም ግዳጅ በአስተማማኝ ብቃት እንዲወጣ ለማስቻል የጤና ዝግጁነትን ማረጋገጥ ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።
ዕዙ በሃገራችን ላይ በየትኛውም አቅጣጫ በማንኛውም ቦታና ጊዜ ሊቃጡ የሚችሉ ትንኮሳዎችን በብቃት መመከት በሚያስችለው የተሟላ ዝግጁነት ላይ ይገኛል ያሉት ጀኔራል መኮንኑ የዕለቱ ተመራቂዎችም ይህንን የዕዙን የማድረግ አቅም የበለጠ ለማጎልበት ባገኛችሁት ስልጠና ተጠቅማችሁና በየጊዜው አቅማችሁን በማዳበር የዕዙን የጤና ዝግጁነት በማረጋገጥ ተደማሪ አቅም መፍጠር ይጠበቅባችኋል ብለዋል።
የዕዙ ጤና መምሪያ ሃላፊ ኮሎኔል ፈንታሁን ተሾመ በበኩላቸው የዕዙ ጤና መምሪያ የአገልግሎት አሰጣጡ በማሻሻልና የጤና ተደራሽነቱን በማስፋፋት ተልዕኮውን በላቀ ብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀው የእለቱ ተመራቂዎችም የሆስፒታሉን ሁለንተናዊ አቅም ለማጠናከርና የጤናሙያተኞችን ሙያዊ ብቃት ለማሳደግ እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማሳካት አጋዥ እንደሚሆኑም ተናግረዋል።
በእለቱም በስልጠናው የተሻለ ውጤት ለአስመዘገቡ ተመራቂዎች ፣ ለስልጠናው መሳካት ትብብርና ድጋፍ ለአደረጉ አካላት እና የስታፍ ክፍሎች እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ዘጋቢ ደባልቅ አቤ
ፎቶ ግራፍ ይህአለም አታላይ

❤17👍5👏2👎1🔥1
የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር የተሠጠውን ተልዕኮ በአስገራሚ ጀግንነት መፈፀም የቻለ ኮር ነው
ሜጄር ጄኔራል ሙላት ጀልዱ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ በሚገኘው የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር 4ኛ ዓመት የምስረታ በዓል መድረክ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ሜጄር ጄኔራል ሙላት ጀልዱ ቴዎድሮስ ኮር በዕዙ የተሠጠውን ውስብስብ ተልዕኮ በፅናትና ቁርጠኝነት መፈፀም የቻለ የምዕራብ ዕዝ አስተማማኝ ክንድ ነው ብለዋል።
ሜጄር ጄኔራል ሙላት ጀልዱ የምዕራብ ዕዝ የኢትዮጵያ ጋሻ በመሆን ተቋሙ የሚሠጠውን ማናቸውንም ግዳጅና ተልዕኮዎች በጀግንነት በመፈፀም አንፀባራቂ ድሎችን የማስመዘገብ አኩሪ ታሪክ ባለቤት መሆኑን አውስተው በዕዙ ስር ያሉ ኮሮች እርስ በእርስ ባላቸው ጥልቅ ቁርኝትና መናበብ ምክንያት ጠላትን መውጫ መግቢያ በማሳጠት መደምሰስ መገለጫቸው ነው ብለዋል።
የምስረታ በዓሉን በማክበር ላይ የሚገኘውና የምዕራብ ዕዝ አስተማማኝ ክንድ የሆነው ቴዎድሮስ ኮርም በማናቸውም ግዳጆች ወታደራዊ ብቃቱንና ጀግንነቱን አስመስክሯል ብለዋል። ይህንኑ አይበገሬነቱን አጠናክሮ ማስቀጠል እና ለላቀ ድል መዘጋጀት እንዳለበት ያሳሰቡት ጄኔራል መኮንኑ ለኮሩ አመራርና አባላት የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውንም ገልፀዋል።

❤16🔥10👏3🥰1