ዳይሬክቶሬቱ የፋይናንስ ስርዓቱን ወደ ዘመናዊ የአሰራር ሲስተም በመቀየር ውጤታማ መሆኑ ገለፀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም
በኢፌዴሪ አየር ኃይል የፋይናንስ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት እያከናወነ ባለው የስራ አፈፃፀም ዙሪያ ከተቋሙ የፋይናንስ አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በኢፌዴሪ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለኤር ኦፕሬሽን ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ ለገሰ በውይይቱ ማጠቃለያ አየር ኃይል ባለፉት ሰባት ዓመታት ካስመዘገበው ስኬቶቹ መሀል የፋይናንስ ስርዓት ለውጡ አንዱ ተጠቃሽ መሆኑን አውስተው ይህም በአመራሩና የፋይናንስ ሙያተኛው ተናቦ ከመስራት የተገኘ ውጤት እንደሆነም ገልፀዋል።
በቀጣይም ለፋይናንስ ሴኩሪቲው ለህግና ኦፕሬሽን ተግባራት ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡና ዘርፉን ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ይበልጥ በማሳደግ የተጀመሩ አበረታች ተግባራትን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ ለገሰ አሳስበዋል።
የአየር ኃይል ፋይናንስ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል በሻ ደገፋ ተቋሙ በፋይናንስ በኩል ያለውን የአሰራር ሲስተም በፊት ከነበረው ወደ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የቀየረ መሆኑን ገልፀው በዚህም በፋይናንስ በግዢ እንዲሁም በንብረት አስተዳደር ክፍሎች ቀልጣፋ ተደራሽና ውጤታማ አሰራር መዘርጋቱን ተናግረዋል።
ከውይይቱም በተጨማሪ በኤሌክትሮኒክስ ግዢ በእቅድ አዘገጃጀትና በሌሎችም የፋይናንስ አሰራሮች ዙሪያ አጭር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በሲነር ዋረንት ኦፊሰር ዮሐንስ ሲሳይ አማካኝነት ተሰጥቷል።
ዘጋቢ ፍቅሬ በቀለ
ፎቶግራፍ አሰፋ ብርሃኑ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

YouTube
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
# የመከላከያ ሠራዊት ቁልፍ እሴቶች፡-
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
❤29👍29🔥2
መከላከያ ከራሱ መደበኛ በጀት ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ገንብቶ እያጠናቀቀ ነው።
ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም
በኮንስትራክሽን ግንባታ ዘርፍ እየተከናወኑ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች መካከል ግንባታቸው ወደ መጠናቀቁ የተቃረቡት የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ እና የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮዎች እንዲሁም የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተጎብኝተዋል።
የኢፌዲሪ መከላከያ ከለውጡ በኋላ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የቀጣዩን መከላከያ ዕድገት እና ዘመናዊነት ታሣቢ ባደረገ አግባብ በመሰረተ ልማት ግንባታ ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መገኘቱን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ተናግረዋል።
መከላከያ ለቀጣዩ ትውልድ በሚመች መልኩ የተሻለ እና ዘመኑን የዋጀ ተቋም ለማሥረከብ በሚፈለገው ልክ ጥራት እና ፍጥነት ፕሮጀክቶችን እየገነባ መገኘቱን ያነሱት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለተቋሙ የተመደበውን መደበኛ በጀት ያለ ምንም ብክነት በማብቃቃት ጥቅም ላይ በማዋል በርካታ ዘርፈ ብዙ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ መገንባት እየተቻለ ሥለመሆኑም አንስተዋል።
ከለውጡ በፊት ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የመተው ተቋም እና ሀገር ጎጅ ስራ ምክንያታዊነቱ የተመደበውን በጀት በአግባቡ ያለመጠቀምና ለብክነት መዳረግ እንደነበረም አውስተዋል።
አሁን ላይ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ መተው አይታሠብም ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በየጊዜው ተቋማዊ ድጋፍና ክትትል በማድረግ በራስ አቅም በመደበኛ በጀት ከመቶ ያላነሱ ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ እየተገነቡ ለአገልግሎት እየበቁ ሥለመሆናቸውም አንስተዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ መከላከያ አዳዲስ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ከመገንባት በዘለለ የነበሩትን ካምፖች እና የተቋሙን ልዩ ልዩ ማዕከላት በማደሥ እና በማሥፋፋት በርካታ ተግባራትን አከናውኗል እያከናወነም ይገኛልም ነው ያሉት።
በ2018 በጀት ዓመት የተጀመሩትን መጨረስ እንደአሥፈላጊነቱ አዲስ መጀመር ያሚያሥችል ሥራ ላይ ትኩረት መሥጠት እንደሚገባ ያመላከቱት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ጠቅላይ መምሪያ እና የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮዎች ጥራታቸውን በጠበቀ አግባብ ተገንብተው ወደ መጠናቀቁ መድረሳቸውን በጉብኝታቸው አረጋግጠዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በጎበኟቸው ሦስቱም ቦታዎች ችግኝ በመትከል የአረንጓዴ ልማት አሻራቸውን አኑረዋል።
ዘጋቢ ውብሸት ቸኮል
ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ

❤34👍14🔥2
የኢትዮጵያ አየር ኃይል አሁን ባለው ተቋማዊ ግንባታ በአለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊ ሆኗል።
ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም
የአየር ኃይል አካዳሚ ለ3ኛ ዙር እጩ መኮንን ሰልጣኞች የትከሻ ምልክት ማልበስን ጨምሮ የአጫጭር ኮርሶችና የደረጃ 7 ሰልጣኝ የአውሮፕላን ጥገና ባለሙያዎችን አስመርቋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለታላቅ ሀገር ታላቅ ተቋም ከሚል እሳቤ ተነስተን ለሀገራችን በሚመጥን ደረጃ መገንባት በመቻላችን ማንም ተነስቶ የሚያስፈራራት ሳይሆን የሚያከብራትና ከአካባቢያችን አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃም ጭምር ተፈላጊ የሆነ ተቋም መሆኑንም አውስተዋል።
በተለይም ለሰው ኃይል ግንባታ በተሰጠው ልዩ ትኩረት በአየር ኃይል አካዳሚ በኩል ጠንካራ በራሪዎች ብቁ የአውሮፕላን ጥገና ባለሙያዎችንና ተተኪ የአየር ኃይል መሪዎችን ተቋሙ በብቃት እያፈራ መሆኑንም ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ ገልፀዋል።
የዕለቱ ተመራቂ ሰልጣኞች በየሙያ መስካቸው ጠንካራ ሊሆኑ እንደሚገባና ዘመኑን በሚመጥን የአቅም ደረጃ ላይ እራሳቸውን ማብቃት እንዳለባቸው የጠቆሙት ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ ይህም ከተቋሙ አልፎ በሁሉም አቅጣጫ ተወዳዳሪ እንደሚያደርጋቸውም ገልፀዋል።
ተመራቂዎቹ በመልካም ስብዕና ታንፀው ቀጣይ በየተሰማሩበት ኃላፊነታቸውን በተግባር እንዲወጡም ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ አሳስበዋል።
ምክትል አዛዥ ለአየር ኃይል አካዳሚ ኮሎነል ገዛኸኝ ነጋሽ አካዳሚው ለተቋሙ ተልዕኮ ስኬታማነት በትኩረት እየሰራ መሆኑን እና በተለይም ባሳለፍነው ዓመት ከመደበኛ ስልጠናዎች ጎን ለጎን ለነባሩ ሰራዊታችንም አጫጭር የአመራርነት ስልጠና መስጠት መጀመሩን አውስተው በዚህም የተቋሙን የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎት ለማሟላት በትጋት ሲሰራ መቆየቱንም አውስተዋል።
ሰልጣኞቹ በየዲፓርቲመንቱ በተግባር እና በንድፈ ሀሳብ የተቀመጠውን የስልጠና ሰዓት በብቃት ያለፉ መሆናቸውንም ኮሎነል ገዛኸኝ ነጋሽ አያይዘው ገልፀዋል።
በዕለቱ ለሰልጣኝ እጩ መኮንኖች በአየር ኃይል ዋና አዛዥ አማካኝነት የትከሻ ምልክት የማልበስ ስነ ስርዓት የተከናወነ ሲሆን በዲፓርቲሜን የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ሰልጣኞችም ሌሎች ጄነራል መኮንኖቹ አበርክተዋል።
ዘጋቢ ፍቅሬ በቀለ
ፎቶግራፍ መድኃኒት ምስክር

❤36🏆5👍4🔥2
ኮሩ በአማራ ክልል ሰላምን በማረጋገጥ ህዝቡ ስራውን እንዲያከናውን ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል
ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም
ኮሩ ሰላምን በማረጋገጥ ህዝቡ ተረጋግቶ የልማት ስራውን እንዲያከናውን ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ ይገኛል ሲሉ የ6ኛ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን ገለፁ።
ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን ከዕዝ ስታፍ መምሪያ ሃላፊዎች ጋር በመሆን በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን ተልዕኮውን በስኬት እየፈፀመ የሚገኘውን ሠራዊት የግዳጅ ሁኔታ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ዋና አዛዡ የቀጠናውን አሁናዊ የሰላም ሁኔታ አስመልክተው ከኮሩ የሠራዊት አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይም የፅንፈኛው ቡድን የአካባቢውን ሰላም በማወክና ህዝቡ ወቅቱን ጠብቆ አርሶና አምርቶ እንዳይጠቀም መዳበሪያ በመዝረፍ ለግል ጥቅሙ በማዋል መንግስትና ህዝብን ለመለያየት እርካሽ የፓለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲፍጨረጨር የቆየ ስብስብ መሆኑን ገልፀዋል።
አሁን ላይም ሠራዊቱ በወሰደው ጠንካራ ምት አከርካሪው ተሰብሮ አጉል ምኞቱ ቅዠት ሆኖበት ቀርቷል ብለዋል።
የሠራዊቱን የማድረግ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተና ከፍተኛ ልምድና ብቃትን እያዳበረ እንደሚገኝ አረጋግጠናል ያሉት ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን በመስዋዕትነት የተገኘውን ሰላም በዘላቂነት ለማፅናት አሁንም ኮሩ የሚሰጠውን ማንኛውንም ግዳጅ በነበረው ልምድና ተሞክሮ ተመስርቶ ምንጊዜም የድል ባለቤትነቱን ደግሞ ደጋግሞ ማስመስከር እንዳለበትም አፅንኦት ሰጥተዋል።
ሠራዊቱ ሃገርን ለማፅናት የተሰጠውን ግዳጅ በድል እየተወጣ በመምጣቱ የህዝብ አገልጋይነቱን በፈፀማቸው የጀግንነት ገድሎች በተግባር እያስመሰከረ ይገኛል ያሉት ዋና አዛዡ የትኛውም ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ መሰናክል ሳይበግረው ተልዕኮውን በፅናትና በውጤት የሚወጣ በአካል ብቃት ብቻም ሳይሆን በስነ ልቦና የዳበረ ፣ለቆመለት አላማ ጠንቅቆ የተረዳ እንደሆነም ተናግረዋል።
ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን ለኮሩ የሠራዊት አመራርና አባላትም ህዝብና መንግስት የጣለባችሁን አደራ በታላቅ ጀግንነት በመፈፀማችሁም ልትኮሩ ይገባልም ብለዋል።
የኮሩ የሠራዊት አመራርና አባላት በቀጣይም ባስመዘገቧቸው ድሎች ሳይዘናጉ የትኛውንም ግዳጅ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመፈፀም በሚያስችላቸው ወታደራዊ ቁመና ላይ እንደሚገኙ ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ ደባልቅ አቤ
ፎቶ ግራፍ ሰው መሆን ሃብቱ

❤35👍10🔥2👏2