FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
34 videos
9 files
8.49K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የሜጀር ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ሙያተኞች አስመረቀ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም

የሜጀር ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ዘርፎች በደረጃ አምስት በአጭር ኮርስ ያሰለጠናቸውን የፌዴራል ፖሊስ አባላት በዛሬው እለት አስመርቋል፡፡

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ምክትል ሃላፊ ለአመራር ስልጠና ሜጀር ጄኔራል ሰለሞን ቦጋለ ተቋማችን እያደረጋቸው ከሚገኙ የሪፎርም ስራዎች ውስጥ በዋነኝነት የሰው ሀይልን ማደራጀት እና ማብቃት አንዱ መሆኑን ገልፀው በልዩ ልዩ ሙያዎች አሰልጥነው የሚያበቁ ማሰልጠኛዎችን እና ኮሌጆችን በማጠናከር ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ኮሌጁ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለውና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በበርካታ የቴክኖሎጂ ሙያዎች ሙያተኞችን እያፈራ የሚገኝ አንጋፋ ኮሌጅ መሆኑን ገልፀዋል። የዛሬ ተመራቂዎችም በዚህ አንጋፋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰልጥናችሁ በመመረቃችሁ ደስተኛ ሆናችሁ ቀጣይ ማንኛውንም ተልዕኮ በውጤት መፈፀም አለባችሁ ብለዋል።

የኮሌጁ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል አበበ ዋቅሹማ በበኩላቸው ተቋማችን እያከናወነ የሚገኘውን የፕሮፌሽናል ሠራዊት ግንባታ ከግብ ለማድረስ የትምህርት ፖሊሲውን በመከተል ከዘመኑ ጋር የሚሄድ ቴክኖሎጂን በመታጠቅ የተሟላ ሙያዊ ብቃት ያለው ሙያተኛን እያፈራን እንገኛለን ብለዋል።

የምረቃ ስነ-ስርዓቱን በማስመልከት በኮሌጁ የሚገኙ የሰራዊት አባላት "ትውልድ ይማር" በሚል መሪ ቃል በሆለታ ከተማ ለሚገኙ የኢኮኖሚ ዕጥረት ላለባቸው ተማሪዎች ከ168 ሺህ ብር በላይ በሚሆን ወጪ የመማሪያ ቁሳቁስ እና አልባሳት ድጋፍ በማድረግ ህዝባዊነታቸውን አሳይተዋል፡፡

የከተማው አስተዳደር ከንቲባ አቶ እሸቱ በቀለ ሰራዊቱ ህይወቱን ለግሶ ሀገሩን ከመጠበቅ ጎን ለጎን እያደረገ ላለው የበጎ አድራጎት ስራ በከተማው አስተዳደር ስም ምሰጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ኮሌጁ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ ለመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች እንዲሁም ለባለ ሌላ ማእረግተኞች ማዕረግ አልብሷል፡፡ በበጀት አመቱ የላቀ የስራ አፈጻጸም ላሳዩ አባላትም ማበረታቻ ሽልማት አበርክቷል፡፡ ዘጋቢ አፈወርቅ በቀለ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
34👏8🔥3👍2
የኮማንዶ ሬጅመንት በሰሜን ሸዋ ዞን ኢፍራታና ግድም ወረዳ የፅንፈኛውን አባላት በቁጥጥር ስር አውሏል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም

የኮማንዶ ሬጅመንት በሰሜን ሸዋ ዞን ኢፍራታና ግድም ወረዳ ፈረዳ ውሀ እና ካራ ለጎማ ቀበሌ የፅንፈኛው አባላትን በቁጥጥር ስር አውሏል።

የኮማንዶ ሬጅመንት አዛዥ ሻምበል መልካሙ ገነት እንደገለፁት ሬጅመንቱ ባካሄደው ኦፕሬሽን በኢፍራታ ግድም ወረዳ ካራ ሎጎማ እና ፈረዳ ውሀ ቀበሌ በስውር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፅንፈኛው አመራርና አባላትን ከነትጥቃቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

አቶ ጋሻው እና አቶ በለጠ የተባሉ የፅንፈኛው ቡድኑ ሎጀስቲክስ ሀላፊዎች ከነግብረአበሮቻቸው እና አራት ክላሽ አንድ ብሬን ተማርኳል።

ህብረተሰቡ አሥፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እያደረገ ነው  ያሉት ሻምበል መልካሙ ገነት ሬጅመንቱ በፅንፈኛው ላይ የሚወሰደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል ዘጋቢ ዮሴፍ አስመላሽ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
45👍12👏7🔥2
ዋና መምሪያው በበጀት ዓመቱ ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል
     ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ማጠቃለያን አስመልክቶ የዕውቅና፣ የማዕረግ ማልበስ ፣ የተማሪዎች ድጋፍ እና የሽኝት መርሃ-ግብር አካሂዷል።

ዋና መምሪያው የሰው ሃብት ፖሊሲዎች ፣ስትራቴጂዎችና ስታንዳርዶችን በመንደፍ የሰው ሃብት ቅጥር ልማት እድገትና ስንብት ስርዓት በመዘርጋት ፣ወቅታዊነቱን የጠበቀ የመረጃ ሥርዓት በማዘጋጀት እና በሌሎችም በርካታ ተግባራት ውጤታማ ሥራ መፈፀሙን የመከላከያ ሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ ተናግረዋል።

ጠላት ፕሮፖጋንዳ በመንዛት የተቋሙን ገፅታ ለማጠልሸት ቢጥርም ጥረቱን በመመከት ረገድ ትኩረት የተሠጠው ሥራ መሠራቱን ያነሱት ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ የመከላከያ ሠራዊቱ ህግና መመሪያን መሰረት በማድረግ ተልዕኮውን በብቃት እየፈፀመ መሆኑን አስምረውበታል።

ተቋሙ ሠራዊቱን በተለያዩ ማህበራዊ ዘርፎች፣ በፋይናንስ ፣ የቤት ባለቤት እንዲሆን በማድረግ እና በሌሎች ተግባራት ውጤት ያለው ሥራ ተግባራዊ እያደረገ ሥለመሆኑም ተናግረዋል።

ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ ሁሉም አባላት የተገኘውን ውጤት አጠናክረው ማስቀጠል እንደሚገባቸው ገልፀው ለዋና መምሪያው ተልዕኮ ስኬት ትብብርና እገዛ ላደረጉ የተቋሙ ክፍሎች ምስጋና አቅርበዋል።

የመከላከያ ሠው ሀብት አመራር ዋና መምሪያ በጡረታ ለተሠናበቱ የክፍሉ አባላት የክብር አሸኛኘት ያደረገ ሲሆን የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑና ጥሩ የሥራ አፈፃፀም ላላቸው አባላቱም በየደረጃው ማዕረግ አልብሷል።

ዘጋቢ ቃለእግዚአብሔር ፍቃዱ
ፎቶግራፍ አበረ አየነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
51👍8🔥5