FBC (Fana Broadcasting Corporate)
187K subscribers
55.5K photos
436 videos
23 files
51.6K links
This is FBC's official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com
Download Telegram
ትውልዱ በሀገረ መንግስት ግንባታ የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ትውልዱ በሀገረ መንግስት ግንባታው ላይ የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ሲሉ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) አመላከቱ፡፡ “የምሁራንና ወጣቶች ሚና ለሀገረ መንግስት ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት በመካሄድ ላይ ነው፡፡ በብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ዋና ጽ/ቤት በተዘጋጀው 2ኛ ዙር የፓናል ውይይት፤ የመስኖና ቆላማ አካባቢ…

https://www.fanabc.com/archives/244400
በአማራ ክልል ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት የህግ ማእቀፍ ተዘጋጅቶለት ይሰራበታል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትህ ሰርዓቱን ለማገዝ እና ለማጠናከር እንዲሁም ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት የህግ ማእቀፍ ተዘጋጅቶለት ይሰራበታል ሲሉ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ተናገሩ፡፡ በደሴ ከተማ በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ የሚገኙ አካላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ እና ፍትህ ጉዳይ ላይ…

https://www.fanabc.com/archives/244403
ለአርብቶ አደሩ የጤና ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ35 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት የሚተገበርና ለአርብቶ አደሩ የጤና ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ። ፕሮጀክቱ በ4 ክልሎች ውስጥ የሚገኙ 35 የአርብቶ አደር ወረዳዎችን ያቀፈ መሆኑ ተገልጿል። በስነ ተዋልዶ ጤና፣ በስርዓተ ምግብ፣ የእናቶች እና የህፃናት፣ የአፍላ ወጣቶች ጤና፣ የጨቅላ ህፃናት ጤና እንዲሁም የቤተሰብ…

https://www.fanabc.com/archives/244406
Live stream finished (36 minutes)
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለኢትዮጵያዊያን የኩራት ምንጭ የሆነ ታላቅ ተቋም ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለለመላው ኢትዮጵያዊያን የኩራት ምንጭ የሆነ ታላቅ ተቋም ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። በከንቲባዋ የተመራ የአስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች በኢፌዴሪ አየር ኃይል ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝቱ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ አየር ኃይል ከተጣለበት ሀገራዊ ተልዕኮ ባሻገር በግብርናው ልማት በኩል ቀድሞ…

https://www.fanabc.com/archives/244409
በቻይና በአውራ ጎዳና መደርመስ የ19 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ለቀናት የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በጉዋንግዶንግ ግዛት በአውራ ጎዳና ላይ በደረሰ የመደርመስ አደጋ የ19 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሌሎች 30 ሰዎች ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው የተገለጸ ሲሆን ለህይወታቸው አስጊ ነገር እንደሌለም ተመላክቷል፡፡ የግዛቱ አስተዳደር 500 የሚሆኑ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ሰጪ ሰራተኞችን ማሰማራቱም…

https://www.fanabc.com/archives/244413
ስራ ፈጠራን በማበረታታት የኢኮኖሚ ነጻነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ስራ ፈጠራን በማበረታታትና የተረጂነት አመለካከትን በመቀየር የምግብ ዋስትና እና የኢኮኖሚ ነጻነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኋላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ። የብልጽግና ፓርቲ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እንደቀጠለ ነው። መድረኩ ሶስተኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን በዛሬው ዕለትም…

https://www.fanabc.com/archives/244417
የሰራተኞችን መብትና ጥቅም የማስከበር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሰላምን የማረጋገጥ፣ ምርታማነትን የማሳደግ፣ የሥራ ላይ ደህንነትንና የሰራተኞችን ጥቅም የማስከበር ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። የዓለም የሠራተኞች ቀን በኢትዮጵያ ለ49 ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ135 ጊዜ “ለሠላምና ለኑሮ ውድነት መፍትሔ እንሻለን” በሚል መሪ ሐሳብ እየተከበረ ይገኛል። በአዲስ አበባ…

https://www.fanabc.com/archives/244424
ማስታወቂያ!
እንኳን አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 482/2013 የተቋቋመ ሲሆን፣ ዓላማውም ለገንዘብ አስቀማጮች የመድን ዋስትና ወይም ኢንሹራንስ ሽፋን በመስጠት ለፋይናንስ ዘርፉ ጤናማነት አስተዋጽኦ ማበርከት ነው፡፡ በዚህም መሠረት አይበለውና አንድ ባንክ ወይም ማይክሮፋይናንስ ተቋም ኪሳራ አጋጥሞት ለገንዘብ አስቀማጮች ገንዘባቸውን መመለስ ቢያቅተው፣ ፈንዱ ኪሳራ ያጋጠመውን እና የወደቀውን ባንክ ወይም ማይክሮፋይናንስ በመተካት ለእያንዳንዱ አስቀማጭ እስከ መቶ ሺህ ብር በፍጥነት የመመለስ ሃላፊነት አለው፡፡ ለገንዘብ አስቀማጮች የሚመለሰው ገንዘብም ከፋይናንስ ተቋማት የሚሰበሰብ ሲሆን፣ ለዚህም ሲባል እስካሁን ባለው ሁኔታ ከብር 4.6 ቢሊዮን በላይ አረቦን (premium) ተሰብስቧል፡፡

ፈንዱ የራሱን የፋይናንስ አቅም ለማሳደግና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት፣ በየጊዜው የሚሰበስበውን አረቦን በሕግ አግባቡ መሠረት በመንግስት ግመጃ ቤት ሰነድ ላይ ኢንቨስት እያደረገ ይገኛል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251115571597 እና +251115578534 መደወል ይቻላል፡፡
ከ80 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለሚያደርግ የውሃ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በሃዋሳ ከተማ ከ80 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የውሃ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡ አቶ ደስታ ሌዳሞ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በክልሉ በከፍተኛ ደረጃ ተግባራዊ ከሚደረጉ ፕሮጀክቶች አንዱ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ነው። ዛሬ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የፋራ ሂጠታ ንፁህ የመጠጥ…

https://www.fanabc.com/archives/244428
በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 46 በርሚል ነዳጅ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 46 በርሚል ነዳጅ መያዙን የሚዛን አማን ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ረ/ኢንስፔክተር አዳነ አለማየሁ እንደገለጹት÷ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ከተያዘው ነዳጅ ውስጥ 35 በርሚሉ ናፍታ ሲሆን 11 በርሚሉ ደግሞ ቤንዝል ነው፡፡ በተሽከርካሪ ተጭኖ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ በተያዘው ነዳጅ ላይ ምርመራ እየተደረገ…

https://www.fanabc.com/archives/244433
በሻምፒየንስ ሊጉ ግማሽ ፍፃሜ ዶርትመንድና ፓሪስ ሴንት ጀርሜይን ይፋለማሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመኑ ቦርሺያ ዶርትመንድና የፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ጀርሜይን በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን ዛሬ ምሽት ያካሂዳሉ፡፡ ጨዋታው ከምሽቱ 4 ሰዓት በዶርትመንድ ሜዳ ሲገናል ኤዱና ፓርከ የሚካሄድ ሲሆን÷ የመልሱ ጨዋታ ደግሞ በፓሪስ ፓርክ ደ ፕሪንስ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ ትናንት ባየርን ሙኒክ እና ሪያል ማድሪድ በአሊያንዝ…

https://www.fanabc.com/archives/244436
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ሲምፖዚዬም በዘርፉ ያላትን ተሞክሮ አካፈለች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዶሚኒካን ሪፐብሊክ በተዘጋጀው የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ሉላዊ የአፈፃፀም ድጋፍ ሲምፖዚዬም ላይ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ልምድ አካፍላለች፡፡ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ሲምፖዚዬም ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡ አለሙ ስሜ(ዶ/ር) ÷ በሲምፖዚዬሙ የአቪዬሽን ዘርፉን በሚያሳድጉ እና በሚያዘምኑ ጉዳዮች ላይ…

https://www.fanabc.com/archives/244439
ክልሉ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ926 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ926 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታወቀ።

የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ እሸቱ ጎዴቶ እንደገለጹት÷ የክልሉ የይቅርታ ቦርድ በይቅርታ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ታራሚዎችን ከመንግስት፣ ከህዝብና ከታራሚ ጥቅም አኳያ ሲመረምር ቆይቷል።

በተደረገው ምርመራም በአጠቃላይ የይቅርታ ጥያቄ ካቀረቡ 978 ታራሚዎች መካከል መስፈርቱን ያሟሉ 926 ታራሚዎች ጥያቄያቸው ለክልሉ መንግስት ቀርቦ የይቅርታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን ተናግረዋል።https://www.fanabc.com/archives/244441
ከዳያስፖራው 3 ቢሊየን ዶላር በሬሚታንስ ወደ ሀገር መላኩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዳያስፖራው የሚገኘውን ሬሚታንስ ለማሳደግ በተደረገ ድጋፍና ክትትል 3 ቢሊየን ዶላር የሬሚታንስ ገቢ መገኘቱን የዳያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ በዳያስፖራ ዘርፍ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ላይ ከኢፌዴሪ ሚሲዮኖች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱም ባለፉት 9 ወራት ከ197 ሺህ በላይ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላትን ያሳተፈ ወቅታዊና ሀገራዊ የልማት ጉዳዮች የተዳሰሱባቸው ከ730…

https://www.fanabc.com/archives/244452
ሐረር ከተማን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ አበረታች ሥራዎች ተከናውነዋል- ቢሮው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሐረር ከተማንተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ አበረታች ሥራዎች መከናወናቸውን የክልሉ ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ÷ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የክልሉን ባህል ፣ ቅርስና ቱሪዝም ከማስተዋወቅ አንጻር ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል። በተለይም ከተማዋ ሙዚዬሞችን ያቀፈች ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የቱሪዝም ሎጎ ተቀርጾ…

https://www.fanabc.com/archives/244457
በ300 ሚሊየን ብር ለሚገነባ የመድሃኒት ማከማቻ መጋዘን የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅግጅጋ ከተማ በ300 ሚሊየን ብር ወጪ የመድኃኒት ግብዓት ማከማቻ መጋዘን እና የአስተዳደር ህንጻ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ፡፡ የመሰረት ድንጋዩን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሃመድ እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ አስቀምጠዋል፡፡ አቶ ሙስጠፌ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ፕሮጀክቱ በክልሉ የጤና አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነትን ለማሳደግ…

https://www.fanabc.com/archives/244460
Live stream finished (1 hour)
የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገቡ ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡ የብልጽግና ፓርቲ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል፡፡ በዛሬው ዕለትም የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት፣ ከስራ ዕድል ፈጠራ እና የተረጂነት አመለካከትን ከመለወጥ አኳያ በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡…

https://www.fanabc.com/archives/244465