FBC (Fana Broadcasting Corporate)
198K subscribers
60K photos
732 videos
23 files
53.7K links
This is FBC's official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com
Download Telegram
ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መጪውን የትንሣዔ በዓል ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ማዕድ አጋሩ፡፡

የማዕድ ማጋራቱ ዝቅትኛ ገቢ ካላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች በተጨማሪ ጽሕፈት ቤቱ የሚያሳድጋቸው አሳዳጊ የሌላቸው ሕጻናትንም ያካተተ ነው፡፡
የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ 11 ግለሰቦች በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀና

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራንስፖርት ስምሪትና የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር ሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ 11 ግለሰቦች በስር ፍ/ቤት የተሰጠውን ዋስትና አፀና። ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ ከሀገር እንዳይወጡ እግድ እንዲጣል ትዕዛዝ ሰጥቷል። ተጠርጣሪዎቹ የቀድሞ የህዝብ ትራንስፖርት የተሽከርካሪ ዘርፍ ኃላፊና የትራንስፖር ሎጂስቲክ ሚኒስትር አማካሪ የነበሩት ከድልማግስት ኢብራሂም፣ የትራንስፖርት ማህበራት አመራርና…

https://www.fanabc.com/archives/244333
ማስታወቂያ!

እንኳን አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 482/2013 የተቋቋመ ሲሆን፣ ዓላማውም ለገንዘብ አስቀማጮች የመድን ዋስትና ወይም ኢንሹራንስ ሽፋን በመስጠት ለፋይናንስ ዘርፉ ጤናማነት አስተዋጽኦ ማበርከት ነው፡፡ በዚህም መሠረት አይበለውና አንድ ባንክ ወይም ማይክሮፋይናንስ ተቋም ኪሳራ አጋጥሞት ለገንዘብ አስቀማጮች ገንዘባቸውን መመለስ ቢያቅተው፣ ፈንዱ ኪሳራ ያጋጠመውን እና የወደቀውን ባንክ ወይም ማይክሮፋይናንስ በመተካት ለእያንዳንዱ አስቀማጭ እስከ መቶ ሺህ ብር በፍጥነት የመመለስ ሃላፊነት አለው፡፡ ለገንዘብ አስቀማጮች የሚመለሰው ገንዘብም ከፋይናንስ ተቋማት የሚሰበሰብ ሲሆን፣ ለዚህም ሲባል እስካሁን ባለው ሁኔታ ከብር 4.6 ቢሊዮን በላይ አረቦን (premium) ተሰብስቧል፡፡

ፈንዱ የራሱን የፋይናንስ አቅም ለማሳደግና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት፣ በየጊዜው የሚሰበስበውን አረቦን በሕግ አግባቡ መሠረት በመንግስት ግመጃ ቤት ሰነድ ላይ ኢንቨስት እያደረገ ይገኛል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251115571597 እና +251115578534 መደወል ይቻላል፡
አማራ ክልልን ከጎበኙ ቱሪስቶች ከ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከሀገር ውስጥና ከውጭ ጎብኚዎች 2 ቢሊየን 445 ሚሊየን 9 ሺህ 550 ብር ገቢ መገኘቱን የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ክልሉን ከ5 ሚሊየን 914 ሺህ በላይ ሰዎች መጎብኘታቸውን የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡ በክልሉ ያጋጠመው የጸጥታ ችግር በቱሪዝም እንቅስቃሴው ላይ አሉታዊ…

https://www.fanabc.com/archives/244344
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች እና ጽሕፈት ቤቱ ለሚያሳድጋቸው ሕጻናት ያጋሩት ማዕድ
ቦምብ ለሸኔ የሽብር ቡድን ሊያቀብሉ ነበር ተብለው የተከሰሱ 2 ግለሰቦች በእስራት እንዲቀጡ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 50 የእጅ ቦምብ ለሸኔ የሽብር ቡድን ሊያቀብሉ ነበር ተብለው የተከሰሱ አማንኤል ግርማ እና አብዶ መላኩ በ3 ዓመት ከ7 ወራት እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ። የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ህገ መንግስታዊና በህገ መንግስት ስርዓት ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ችሎት ነው። ቀደም ሲል…

https://www.fanabc.com/archives/244352
ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ”ጽዱ ኢትዮጵያ” ንቅናቄን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ”ጽዱ ኢትዮጵያ ”ንቅናቄን ተቀላቅለዋል። ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶችን በመገንባት ክብርን ጠብቆ የመፀዳዳት ባህልን ለማዳበር የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የ “ጽዱ ኢትዮጵያ ” ንቅናቄን በመቀላቀል የ 10 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን…

https://www.fanabc.com/archives/244365
የሰራተኞችን መብቶች የማስከበር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰራተኞችን ጥቅምና መብቶች የማስከበር እንዲሁም ደህንነታቸውን የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ተናገሩ። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እና የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ካሣሁን ፎሎ ዓለም አቀፉን የሠራተኞች ቀን በማስመልከት የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። የሰራተኛውን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ በየጊዜው የሚነሱ ጥያቄዎችን በጥናት…

https://www.fanabc.com/archives/244370
Live stream finished (1 hour)
ባለሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ ለ"ጽዱ ኢትዮጵያ "ንቅናቄ የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ በላይነህ የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶችን በመገንባት ክብርን ጠብቆ የመፀዳዳት ባህልን ለማዳበር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ይፋ የተደረገውን የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄን በመቀላቀል 2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ "ጽዱ ኢትዮጵያ " ንቅናቄን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ "ጽዱ ኢትዮጵያ " ንቅናቄን በመቀላቀል የ10 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ንቅናቄውን ሌሎች አካላትም እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የማር የጤና በረከቶች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማር ከዕፅዋት አበባ በማር ንቦች የሚሰራ ፈሳሽ ውህድ ሲሆን በንጥረ-ምግቦች እና አንቲኦክሲዳንትስ የበለፀገ ፥ ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪይ አለው፡፡ ማር በርካታ የጤና ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ፥ በቤት ውስጥ ለሚደረግ የህክምና እና የምግብ አማራጭ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ማር ፕሮቲን፣ ፋይበር እንዲሁም በውስጡ አነስተኛ መጠን ያላቸው ንጥረ ነገሮችን የያዘ በመሆኑ…

https://www.fanabc.com/archives/244361
ማስታወቂያ

#CashGo
ከውጭ ሀገራት ገንዘብ መላኪያ የሞባይል መተግበሪያ
==================
በሞባይል ስልክዎ አማካኝነት ቪዛና ማስተር ካርድዎን በመጠቀም
ከውጭ ሀገር በቀጥታ ወደ ወዳጅ ዘመድዎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ገንዘብ በነፃ መላክ ይችላሉ::
*****************
የሞባይል መተግበሪያውን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ ይጠቀሙ።

• ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo&hl=en&gl=US

• ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/cashgo/id1559346306

#ከውጭ #ሀገራት #ገንዘብ #cbe #CashGo #visa #mastercard #moneytransfer
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕና የሶማሌ ክልል የእርሻ መሳሪያዎች ሽያጭ ውል ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕና የሶማሌ ክልል ግብርና ቢሮ የእርሻ መሳሪያዎች ሽያጭ ውል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በስምምነቱ መሰረት ግሩፑ ዋይቲኦ ትራክተር፣ ማረሻ፣ መከስከሻ እና ኮምባይነሮችን አምርቶ ለክልሉ እንደሚያቀርብ ጠቁመዋል።

በዚህም በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስር የሚገኘው የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ 50 ዋይቲኦ ትራክተር፣ 50 ማረሻ፣ 50 መከስከሻ እና አምስት ኮምባይነሮችን አምርቶ እንደሚያቀርብ ገልጸዋል።

በተጨማሪም የድህረ ሽያጭ አገልግሎት ለመስጠት ስምምነት መደረጉን ጠቅሰው፤ ግሩፑ ላቀረባቸው የግብርና ማሽነሪዎች ሉብሪካንቶችንና መለዋወጫዎችን በማቅረብ የጥገና አገልግሎት የሚሰጥበት ማዕከል በክልሉ ይገነባል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ‘ጽዱ ኢትዮጵያ’ ንቅናቄን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ‘ጽዱ ኢትዮጵያ’ ንቅናቄን ተቀላቀለ። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ ተደርጎ “ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ያለውን የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን በመደገፍ 50 ሺህ ብር ገቢ አድርጓል። ንቅናቄው ለከተማ ውበት እና ለኅብረተሰቡን ጤና መጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ…

https://www.fanabc.com/archives/244386
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በእርስዎ አስተዋፅዖ ብዙ መፀዳጃዎችን መገንባት ይቻለናል - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

ብሩህ ቀን ኢትዮጵያ! ''የፅዱ ጎዳና-ኑሮ በጤና'' መፀዳጃ ቤቶችን ዝርዝር ይዞታ በዚህ ናሙና ይመልከቱ። የህዝባዊ መፀዳጃ ቤቶቹ ዲዛይን እንደየሚመረጡ ስፍራዎች ተስማሚነት ተዛምዶ ይሰራል። በእርስዎ አስተዋፅዖ ግን ለብዙዎች የሚያገለግሉ ብዙ መፀዳጃዎችን መገንባት ይቻለናል።
የአፍሪካ ህብረት በሀሰተኛ ሰነድ ከባንክ ሂሳቡ ገንዘብ ለማውጣት የተደረገውን ሙከራ አወገዘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት በፈረንጆቹ ሚያዝያ 15 ቀን 2024 በዋና መስሪያ ቤቱ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀሰተኛ ሰነድ ገንዘብ ለማዛወር የተደረገውን ሙከራ አውግዟል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኞች እና የህብረቱ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ምንም ገንዘብ እንዳይወጣ በማድረግ የተቃጣውን የማጭበርበር ሙከራ ለማክሸፍ ለወሰዱት ፈጣን እርምጃም አድናቆቱን…

https://www.fanabc.com/archives/244392
በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የጋራ መግባባትን መፍጠር ይገባል – አቶ ብናልፍ አንዷለም

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው ውይይትና የጋራ መግባባትን መፍጠር ይገባል ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም ተናገሩ። የፌዴራልና የክልል ምክር ቤቶች በሀገር ግንባታ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የስልጠና እና የንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው። በሰላም ሚኒስቴር በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር…

https://www.fanabc.com/archives/244396