FBC (Fana Broadcasting Corporate)
183K subscribers
44.8K photos
204 videos
23 files
45K links
This is FBC's official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com
Download Telegram
በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ የህወሓት ወታደራዊና ሲቪል አመራሮች ክስ ተቋረጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ የህወሓት ወታደራዊና ሲቪል አመራሮች ክስ መቋረጡን የፍትህ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በፌዴራል መንግስት እና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረት ከግጭቱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ወንጀሎች ተጠያቂነት በተመለከተ ያለውን ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ ሊታዩ እንደሚገባ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

ስለሆነም በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮችን ክስ በማቋረጥ ጉዳያቸው በቀጣይ በሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ እንዲታይ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱ ተጠቁሟል፡፡

ስለዚህ በተገለፀው አግባብ ከዚህ ጋር በተያያዘ ክስ ቀርቦባቸው በክርክር ሂደት ላይ ይገኙ የነበሩ የወንጀል ክሶች በአዋጅ 943/2008 አንቀጽ 6 (3) (ሠ) መሰረት የተነሱ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና ብሔራዊ ባንክ ህገወጥ የውጭ ምንዛሪና የገንዘብ ዝውውር ተዋናዮችን በጥናት በመለየት ቀጣይ እርምጃ እንደሚወስዱ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና ብሔራዊ ባንክ ህገወጥ የውጭ ምንዛሪና የገንዘብ ዝውውር ተዋናዮችን በጥናት በመለየት ቀጣይ እርምጃ እንደሚወስዱ አስታውቀዋል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ እንቅስቃሴ ዙሪያ ያካሄደው ሰፋ ያለ ጥናት ዛሬ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

በመድረኩ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት፣ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት የሥራ ሃላፊዎች፣ ኮሚሽነሮች እንዲሁም የደኅንነት እና የፀጥታ ተቋማት ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው÷የውይይት መድረኩ የቀረበው ጥናት በዘርፉ ያሉትን ችግሮች እንዲሁም የተለያዩ የውጭ ሀገራትን ተሞክሮም ጭምር በጥልቀት የዳሰሳ ነበር።

የጥናቱን ግኝቶች መነሻ በማድረግ ህገወጥ የውጭ ምንዛሬና የገንዘብ ዝውውርን ሰንሰለት ለመበጠስ እንዲሁም የድርጊቱ ተዋናዮች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል የፖሊስ፣ የሥርዓትና የተጠያቂነት መፍትሄዎችን የሚጠቁሙ ምክረ ሐሳቦችን እንዲሁም በቀጣይ ሊወሰዱ የሚገባቸውን ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎችንም አመላክቷል።

በጥናቱ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ህገወጥ የውጭ ምንዛሬ ገበያዎች የሀገርን ኢኮኖሚ በማዳከም፣የኑሮ ውድነትን በማናርና ሙስናን በማስፋፋት ሀገርን ለከፋ አደጋ እያጋለጡ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/186857
በጦርነት የተጎዱ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም ዘላቂ ሰላም ለማስፈን መረባረብ እንደሚገባ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜኑ ጦርነት የተጎዱ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ።

የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመልሶ ግንባታ ዙሪያ በባህር ዳር እየመከረ ነው፡፡

https://www.fanabc.com/archives/186896
ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በመኖሪያ ቤታቸው የአፍጥር ዝግጅት አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በመኖሪያ ቤታቸው የአፍጥር ዝግጅት አካሂደዋል፡፡

በሥነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼክ ሃጂ ኢብራሂም፣ የምክር ቤቱ አባላትና የእምነቱ አባቶች ተገኝተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ባለፈው ዓመትም በመኖሪያ ቤታቸው የአፍጥር ዝግጅት ማካሄዳቸው ይታወሳል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍን ለአንባቢያን ተደራሽ የሚያደርግ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍን ለአንባቢያን ተደራሽ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ መርሐ-ግብር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተካሄደ ይገኛል።

የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ከመጽሐፍ የሚገኘው ገቢ ደረጃውን ለጠበቀ የባህል ሙዚየም ግንባታ የሚውል ይሆናል፡፡

የመደመር ትውልድ መጽሐፍን ስፖንሰር በማድረግ እና በመግዛት ሁሉም ዜጋ በትውልድ ግንባታ ሂደት የበኩሉን እንዲወጣም ርዕሰ-መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።https://www.fanabc.com/archives/186897
የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠል መንግስት በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በለውጡ ሂደት በሁሉም መስክ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠል መንግስት በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት እንደሚሰራ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ ገለጹ፡፡

አቶ ተስፋዬ በለውጡ ሂደት ባለፉት አምስት ዓመታት በፖለቲካው መስክ የተከናወኑ ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/186918
ትራምፕ የወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው የመጀመሪያው የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነዋል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀድሞዋን የወሲብ ፊልም ተዋናይ ስቶርሚ ዳንኤልስን ዝም ለማሰኘት 130 ሺህ ዶላር ከፍለዋል በሚል ክስ ሊመሰረትባቸው መሆኑ ተሰማ።

ትራምፕ በፈረንጆቹ 2016 በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ ከመሆናቸው ቀደም ብሎ ለግለሰቧ የከፈሉት ገንዘብ አለ በሚል በኒውዮርክ ጠበቆች ምርመራ ሲደረግባቸው ቆይቷል።

ምርመራው ትራምፕ ከቀድሞዋ የወሲብ ፊልም ተዋናይ ጋር የፈጸሙት ጾታዊ ግንኙነት ይፋ እንዳይሆን ገንዘብ ከፍለዋል በሚል ነው ሲካሄድ የቆየው።https://www.fanabc.com/archives/186931
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኮሞሮስ ሕብረት ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኮሞሮስ ሕብረት ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፕሬዚዳንቱን በቢሯቸው ተቀብለው እንዳነጋገሩ አስፍረዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በሁለትዮሽ፣ በክልላዊ እና በባለ ብዙ ወገን ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከኮሞሮስ ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ እና በተለያዩ መስኮች ያለውን ትብብር ለማጠናከርም እንደምትሰራ አረጋግጠዋል።
ለግድቡ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ ፈጠራ በታከለበት ሁኔታ ሊጠናከር ይገባል - አቶ ደመቀ መኮንን
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኅብረተሰቡ ለታላቁ ሕዳሴ ግድቡ ያለውን ጽኑ ድጋፍ በሚመጥን ደረጃ የማስተባበር ስራን ፈጠራ በታከለበት ሁኔታ ሊጠናከር ይገባል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡
በ12ኛው ዓመት ዋዜማ የታላቁ የኅዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሳባ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
በመድረኩም የህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ የስድስት ወራት አፈፃፀም ተገምግሞ አስተያየት እና የቀጣይ ስራ አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል፡፡
አቶ ደመቀ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በታላቅ ንቅናቄያችን "እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን" በሚል ወኔ የተረባረብንበት ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ከተጀመረ እነሆ 12 አመታት ሆነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
12 የጥረት እና የስኬት ብሎም የፈተና ጉዞ የታየባቸውን አመታት አሳልፈን በስተመጨረሻ የድል ዘመናት ላይ ደርሰናል ነው ያሉት።
በዚህ ጉዞ ከሁሉ በላይ ህዝባችን በእውቀቱ፣ በችሎታው፣ በገንዘቡ፣ በጉልበቱ ሳይሰሰት ለታላቁ የባንዴራ ፕሮጀክት አስተዋጽኦ አድርጓል ያሉት አቶ ደመቀ÷ በየደረጃው ያለው አመራርም ወደር የለሽ ርብርብ ማድረጉን አውስተዋል።
በህዝባዊ ተሳትፎም ሆነ በመሬት ላይ ያለው የፕሮጀክቱ አፈፃፀም በጥሩ ሁኔታ እየተጓዘ መሆኑ አበረታች መሆኑን ጠቅሰው፥ ይሁንና ኅብረተሰቡ ለግድቡ ያለውን ፅኑ ድጋፍ በሚመጥን ደረጃ የማስተባበር ስራን ፈጠራ በታከለበት ሁኔታ ሊጠናከር እንደሚገባ አስረድተዋል።
ከአረንጓዴ አሻራ ስራ ጋር በማያያዝ የተፋሰስ ልማቱን እንቅስቃሴ ከፍተኛ ትኩረት ልንሰጠው ይገባልም ነው ያሉት።
አቶ ደመቀ መኮንን ለዲፕሎማቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ማህበረሰብ የአፍጥር ፕሮግራም አካሄዱ


አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ማህበረሰብ የአፍጥር ፕሮግራም አካሄዱ።

ፕሮግራሙ በስካይላይት ሆቴል የተካሄደ ሲሆን፥ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።