ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
242K subscribers
289 photos
1 video
16 files
237 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
📕ታምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_አርባ_ሶስት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ሁለቱ ፍቅረኛሞች ከአካባቢው ተነስተው የተንቀሳቀሱት ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ነበር…እያመሩ ያሉት ወደመኝታ ቤት ነበር..ልብስ ቀይረው ራት ለመብላት እና ምሽቱን ዘና ብለው ለማሳለፍ ወደ ሬስቶራንት ለመሄድ..ግን  መንገድ ላይ ያላሰቡት ሰው በዛፎችና በጭለማ የተሸፈነውን  ጠባብ  የእግር መንገድ ዘግቶ ሽጉጥ ደቅኖ ጠበቃቸው… መላኩ ቶሎ ብሎ የሰሚራን ክንድ ጨምድዶ ያዘና ጎትቶ ከጀርባው በማድረግ አሱ የግንብ ግድግዳ ሆኖ ከፊቷ ተገተረ…..
‹‹አይ አይ ….ካንተ በፊትማ እሷን ነው መግደል  የምፈልገው››
‹‹አይ እንደጀመርከኝ እኔኑ ጨርሰኝ….››
‹‹አይ መጀመሪያማ እንደህጻን ያታለለቺኝን ይቺን ጊንጥ ፊትህ ደፋትና አንተን አስከትላለሁ..››
‹‹ለመሆኑ እዚህ ድረስ እንዴት ተከትለኸን መጣህ..?››መላኩ  ነው ድንጋጤውን እንደምንም   ተቆጣጥሮ  በጣም የገረመውን እና ያልጠበቀው ነገር እንዴት ሊሆን እንደቻለ ለማወቅ የጠየቀው፡፡

‹‹እግዜር ነው እጄ ላይ የጣላችሁ..እኔማ ሀገር ሰላም ነው ብዬ ልዝናና ነበር እዚህ የመጣሁት
…ግን ሞቶ አልቅሼ በእጄ አፈር
አልብሼ ቀብሬዋለሁ ያልኩት ወንድሜ እዚህ ዘና ብሎ አለሙን ሲቀጭ አገኘሁት…..ለዛውም ገደልኩልህ ብላ 6መቶ ሺ ብሬን ቅርጥፍ አድርጋ ከበላች ቀጣፊ ሴት ጋር…››መለሰለት ሰሎሞን
መላኩ እየተንቀጠቀጠ መናገር ጀመረ‹‹ገራሚ ነህ …አንደኛ በዚህ አፍህ የእግዜያብሄርን ስም ማንሳትህ ትልቅ ድፍረት ነው..እግዚያብሄር እኮ ፍትህ ነው..እግዚያብሄር ፍቅር ነው..እግዜያብሄር የበጎነት የመጨረሻው ጥግ ነው…ታዲያ በምን ስሌት  እግዚያብሄር አንትን ረድቶህ እኛን አንተ እጅ ላይ ይጥለናል ብለህ ታስባለህ …..?ማይሆነውን…..!!!ደግሞ ገንዘቤን የምትለው…ገንዘቡ እኮ የእኔው ነው…ደግሞ እሷ እንደአንተ እና እንደዛች ሴት ከንቱ አትምሰልህ….ገንዘቡን የእኔ መሆኑን በመረዳት ሳትሰስት ሰታኛለች…››
‹‹በቃ ከዚህ በላይ ልፍለፋህን ልስማ  አልፈልግም …..አሁን አይኔ እያየ ሁለታችሁም በአንድ ሳጥን ተዳብላችሁ ትቀበራላችሁ..እዚህ የጀመራችሁት ፍቅር እዛ ያለከልካይ ትኮመኩሙታላችሁ…››ብሎ ወደነሱ የቀሰረውን ሽጉጡን ቀጭ ቀጭ አድርጎ አቀባበለ….ይሄ ቅጭልጭልታ ቀድሞ የተሰማው ለሰሚራ ጆሮ ነበር..ያው ሴት ከወንድ በላይ ንቁ አይደለች….ከሰማችው ድምጽ ጋር እኩል ተሸከርክራ መላኩን  ገፍታር ከፊቱ ተደቀነች.. ሞቱን ቀድማ ልትሞትለት….ተሳካላት…..በዛ ቅፅበት   ዶ..ዶ..የሚል አደንቋሪ ድምጽ ተሰማ  …ወዲያው የብዙ ሰው ጩኸት እና  የሚሮጡ የሰው ኮቴ …ከዛ ሰሚራ ዝልፍልፍ ብላ መላኩ  እጁ ላይ ገንደስ ስትል ይዟት ወደመሬት ሲወርድ ..ሁሉ ነገር የሚሆነው በደመነፍስ ነበር….
…ሰሚራ ድንገተኛ እና ያልታሰበ ከነበረው ከዛ አደጋ ከወራት  ህክምና በኃላ ዳነች…መላኩም ወንድሙንና  እና የበፊት ሚስቱን በግድያ ሙከራ እና በእምነት ማጉደል ከሶ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ  ወህኒ እንዲወረወር አድርጎ ንብረቱን መልሶ ተቆጣጥሯል….አዎ እዚህ ድረስ ያሉ ነገሮች ጥሩና መልካም የሚመስሉ ነገሮች ነበሩ…እንግዲህ ይህ  ድርጊት የተከወነው ከአምስት አመት በፊት ነበር…

በመላኩ ወንድም በሰለሞን  ሽጉጥ ተተኩሶባት ፍቅረኛዋን ቀድማ በተመታችበት ወቅት ከተተኮሱባት ሁለት ሽጉጦች መካከል አንዱ ሽጉጥ በደረቷ ሌላው ደግሞ በጭነቅላቷ ነበር የገባባት…እና በወቅቱ በደረቷ የገባቸውን የጥይት ቀላሀ በቀላሉ ማውጣት ቢቻልም የጭንቅላቷን ማውጣት ግን በጣም አስቸጋሪ ሆኖ ነበር…፡፡
አስቸጋሪነቱ ጭንቅላቷን ቀዶ ጥይቷን  መዞ ማውጣቱ አይደለም….የከበደው ጥይቷ የተቀረቀረችበት ቦታ እንጂ… ጥይቷ ከወጣች የሰሚራ የጤና ሁኔታ በቋሚነት እንደሚበላሽ ….ትውስታዋ ሙሉ በሙሉ ሊጠፋ ከዛም አልፎ የማሰብ አቅሞንም እንደሚጎዳው ከፍተኛ ስጋት ስለጣለባቸው….ለጊዜው  ባለበት እንዲቆይ… በየጊዜው የቅርብ የህክምና ክትትል እንድታደርግና በሂደት የሚሆነውን ለማድረግ ተወሰኖ ነበር..
ለአንድ አመት  በየወሩ እየተማመላለሰች ህክምናዋ በመከታል በጥንቃቄ  ካሳለፈች በኃላ ምንም የሚሰማት እና የሚለወጥ ነገር ስላልነበረ ቀስ በቀስ እየተዘናጋችና ምንም አይፈጠረም በሚል እምነት ክትትሉን አቆመች ….
በዛን የጊዜ ክፍተት ውስጥ…መላኩ በንግዱ አለም ከበፊቱ የበለጠ ተሳክቶለት ከሰሚራ ጋር ያየነበረው የፍቅር ትስስር ይበልጥ እየጎመራ ሄዶ ወደጋብቻ ሊሸጋገር ወራቶች ሲቀሩት….ግን ከሁለት አመት ቆይታ በኃላ ድንገት ወድቃ  ሀኪም  ቤት ዳግመኛ ለመግባት ተገደደች…  ምርመራ ባደረገችበት ጊዜ በጭንቅላቷ መሀከላዊ ስፍራ የተቀረቀረችው ጥይት ብቻ ሳትሆን በፊት ያልነበረ ጎን ላይ  አስደንጋጭ እጢ ተፈጥሮ  ታየ..ሀኪሞቹ ተደናገጡ ..ተስፋ እንደሌላት እና ማድረግ የሚችሉት ብዙም ነገር እንደሌለ ለመላኩ ሲነግሩት አንጠልጥሎ ወደውጭ ሀገር ይዞት ሄደ….ግን የረፈደ ውሳኔ ነበር…ጥይቷ እንዲወጣላት ማድረግ ተቻለ ..እጢውም በጨረር ህክምና እንዲሞሞ ማድረግ ብዙም ከባድ አልነበረም…ይ ሁሉ ቢሆን ግን በህይወት ልትቆይ የምትችለው በዛ ቢባል ለቀጣዩ አንድ ወይም ሁለት አመት እንደሆነ አስምረው ነገረዋቸዋል…ከዛ በኃላ ወይ ትሞታለች ወይ ደግሞ በድን ሆና በህይወት እና በሞት መካከል ተንጠልጥላ ለአመታት ትኖራለች…..ሚሻለው ግን ወዲያው ብትሞት ነው…. የሀኪሞቹ ምክር ነበር፡፡ …የምርመራው ወጤቱ ለሁለቱም  ሰቅጣጭ ነበር…

እንግዲህ እነዚህ ፍቅረኛሞች …ሳቃቸው ከእንባ የተቀላቀለ፤ደስታቸው ከፍራቻ የተጋባ፤ተስፋቸው ጨለማ የገደበው ከሆነ እና በዚህ ሰቀቀን ውስጥ መኖር ከጀመሩ አመት አልፏቸዋል እና ንስሯ ባመጣላት ታሪክ መሰረት በቀደም የዋና ገንዳ ውስጥ ያገኘችው ፤የፈተነችው እና የፎከረችበት ወጣት ታሪክ እንደዚህ ነው…ታማኝ የሚሆነውም ለዚህች ፍቅረኛው ነው…..አግቢኝ እና ውለጂልኝም የሚላት ይችኑ በጀርመናዊዎቹና በአሜሪካኖቹ ሀኪሞች የ አመት ጊዜ ብቻ የተቆረጠላትን ወጣት  ነው….
ኬድሮን አሰበች‹‹እና ምን ላድርግ ….?እንዳለች ልተዋት….? ትውለድለትና ትሙት…. ከዛ እኔ ለእሱ ሚስት ለልጁ ደግሞ እናት ልሁን…..?ነው ወይስ ላድናት……..?›ከህሊናዋ ጋር ከባድ ፈተና ገባች፡፡በእርግጠኝነት   ንስሯ ከረዳት ለእሷ መዳኛ የሚሆን መድሀኒት ሌላ የአለም ጥግ ማሰስ ሳያስፈልጋት …ከዚህችው ከቅድስቲቷ የኢትዬጵያ ምድር  ቆፍር ቆፈር አድርጋ  ስር ማስ ማስ ፤ ቅጠል በጠስ በጠስ በማድረግ  ልታድናት ትችላለች..፡፡ግን  ለምን ታደርገዋለች…..?ለማንኛወም ጊዜ ወስዳ ልታሰብበት ከራሷ ጋር ተስማማች….

ይቀጥላል….

#ክፍል 44,,እንዲለቀቀ (15) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18