😎ጠላፊዎቹ
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ
፡
#በኬንፎሌት
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
..ለአስር ደቂቃ ያህል ከተጓዙ በኋላ አንድ ከእንጨት የተሰራ ቤት አገኙና ጥልቅ አሉ፡፡ ናንሲ ስልኩ አጠገብ ያለ ወንበር ላይ ተቀምጣ እጇ እየተንቀጠቀጠ የስልኩን እጀታ አነሳችና ‹‹ናንሲ ሌኔሃን ነኝ›› አለች፡፡
ኦፕሬተሩም ‹‹የቦስተን ስልክ ፈላጊ መጥታለች ስልኩን አትዝጉት›› አለ።
ትንሽ ቆይቶ ‹‹ናንሲ ነሽ?›› አለ ከወዲያኛው አገር የመጣ ድምጽ ስልኩን የደወለው ማክ መስሏት ስለነበር የሰማችው ድምጽ የዳኒ ሪሌይ መሆኑን ለማወቅ ትንሽ ጊዜ ወስዶባታል ‹‹ዳኒ ሪሌይ ነህ?,,
‹‹ናንሲ ችግር ውስጥ ውድቄልሻለሁ እባክሽ እርጂኝ›› አለ፡
የስልኩን እጀታ አጥብቃ ያዘች፡፡ የሸረበችው ሴራ ግቡን ሊመታ ይመስላል፡፡ የዳኒ ስልክ የረበሻት ለመምሰል በተሰላቸና ረጋ ባለ ድምፅ
‹‹የምን ችግር ዳኒ?›› አለችው፡፡
‹‹ሰዎች በቀድሞ ጊዜ ላጠፋሁት ጥፋት ከዚህም ከዚያም ስልክ እየደወሉ አስቸገሩኝ››
ይሄማ ጥሩ ብስራት ነው፡፡ ማክ ዳኒ ላይ ሽብር ነዝቷል ማለት ነው› አለች ሆዷ በደስታ እየሞቀ፡፡ ዳኒ ድምፁ ይንቀጠቀጣል፡ እሷም ይህን ነው
የፈለገችው፡፡ ነገር ግን እንዳያውቅባት ስለምን እንደሚያወራ እንደማታውቅ
አስመስላለች፡ ‹‹የምን ችግር ነው? ምንድን ነው እሱ?››
‹‹በስልክ ልነግርሽ አልችልም››
‹‹ታዲያ ጉዳዩ በስልክ የማይነገር ከሆነ ለምን ደወልክልኝ?››
‹‹ናንሲ እንደ ቆሻሻ አትቁጠሪኝ ከጉድ እንድታወጪኝ ነው
የደወልኩልሽ››
‹‹እሺ ተረጋጋ›› በሚገባ ተሸብሯል፡፡ ይህን ፍርሃቱን ደግሞ ልትጠቀምበት ወስናለች፡ ‹‹የሰው ስምና አድራሻ ሳትገልፅ የሆነውን ብቻ ንገረኝ የምትፈልገውን ነገር መገመት አያቅተኝም››
‹‹የአባትሽ ሰነዶች በሙሉ አንቺ ጋ ናቸው?››
‹‹አዎ እኔ ቤት ካዝና ውስጥ ናቸው››
‹‹ሰዎቹ ሰነዶቹን ማየት ሳይፈልጉ አይቀሩም››
ዳኒ ራሷ የቀመረችውን ታሪክ እየነገራት ነው፡ ሴራው እስካሁን በዕቅዱ መሰረት እየተከናወነ ነው፡፡ ለጉዳዩ ትኩረት የሰጠች በማይመስል ሁኔታ ‹‹እነዚያ ሰነዶች ውስጥ አንተን የሚያስጨንቁህ ነገሮች ያሉ
አይመስለኝም››
‹‹እንዴት እርግጠኛ ሆንሽ?›› ሲል አቋረጣት በንዴት።
‹‹እኔ እንጃ››
‹‹ሰነዶቹን በሙሉ አይተሻቸዋል?››
‹‹አይ ብዙ ሰነዶች ነው ያሉት››
‹‹ምን እንዳለ ማንም አያውቅም፡፡ ሰነዶቹን ገና ድሮ አቃጥለሻቸው
ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር፡››
‹‹ልክ ነህ የሆነስ ሆነና ሰነዶቹን መመርመር የፈለገው ማነው?››
‹የጠበቆች ማህበር ነው፡፡ እነሱ ሰነዶቹን ለማየት መብት አላቸው››
‹‹የላቸውም፡፡ ነገር ግን እኔ አልሰጥም ካልኩ ጥሩ አይመጣም››
‹‹አንቺ ጠበቃ አይደለሽ ሊያስገድዱሽ አይችሉም››
ናንሲ ንግግሯን ትንሽ ቆም አደረገች ልቡን ልትሰቅለው፡ ‹‹ስለዚህ ችግር አይኖርም›› አለችው
‹‹አልሰጥም ትያቸዋለሽ?››
‹‹ከዚያም በላይ ማድረግ እችላለሁ። ነገ አሜሪካ ስመጣ አቃጥላቸዋለሁ››
ዳኒ ሳግ እየተናነቀው ‹‹ናንሲ አንቺ እውነተኛ ጓደኛ ነሽ›› አለ፡፡
ከልቧ ልትረዳው እንዳልሆነ ህሊናዋ እየነገራት ‹‹ሌላስ ምን ላድርግልህ?››
‹‹ይሄ ይበቃኛል እንዴት አድርጌ እንደማመሰግንሽ አላውቅም››
‹‹አንተ ካነሳኸው ደግሞ ውለታ ልጠይቅህ ነው›› አለችና ከንፈሯን
በጥርሷ ነከሰችው::
‹‹መቼም ለምን እንዲህ
እንደፈለግኩ ሳታውቅ አትቀርም››
እንዲህ በአስቸኳይ ወደ አሜሪካ ለመመለስ
‹‹አላውቅም ምንድን ነው?›› አላት፡
ፒተር ኩባንያውን እኔ ሳላውቅ ሊሸጥ ተዘጋጅቷል››
ዳኒ ፀጥ አለ፡፡
‹‹ዳኒ አለህ?››
‹‹አለሁ አንቺ እንዲሸጥ አትፈልጊም?››
‹‹እኔ እንዲሸጥ አልፈልግም፡፡ ለግዥ የቀረበው ዋጋ በጣም ዝቅ ያለ ነው፡፡ ከተሽጠ እኔም ቦታ የለኝም: ስለዚህ እንዲሸጥ የማልፈልገው ለዚህ ነው ፒተር ኩባንያው የሚሸጥበት ዋጋ በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ ያውቃል፡
ነገር ግን እኔን ለመጉዳት ስለሆነ ቢሸጥ ግድ የለውም:፡››
‹‹የሚሸጥበት ዋጋ ጥሩ አይደለም? ኩባንያው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ
አክሳሪ እየሆነ እኮ ነው››
‹‹ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? አታውቅም››
‹‹አንድ የምገምተው ነገር አለ››
‹‹ታውቃለህ፡፡ ምክንያቱን ተናገረው እና ይውጣልህ፡ ፒተር የማይረባ ማኔጀር ስለሆነ ነው››
‹‹እሺ››
‹‹ኩባንያውን በርካሽ ዋጋ ከምንሸጠው ለምን ከኃላፊነት አናነሳውም፡፡
እኔ የኃላፊነቱን ቦታ ልውሰድና ወደ ቀድሞው ስሙ ልመልሰው፡፡ እንደ
ምመልሰውም ታውቃለህ፡፡ ኩባንያው ደህና ደረጃ ላይ ሲደርስ በከፍተኛ ዋጋ
እንሸጠዋለን ከፈለግን››
‹‹እኔ አላውቅም››
‹‹ዳኒ አሁን በድፍን አውሮፓ ጦርነት እየተቀጣጠለ ነው፡ ይህ ማለት አቅርቦት ጥያቄ ይጎርፍልናል፡፡ ሁለት ሶስት ዓመት ብንቆይ ደግሞ
ቢዝነስ ይጧጧፋል ማለት ነው፡፡ ከምናመርተው ጫማ በላይ የጫማ ኩባንያውን አሁን ከተሰጠው በሁለት ሶስት እጥፍ ዋጋ መሸጥ እንችላለን፡›››
‹‹ነገር ግን ከናት ሪጅዌይ ጋር የፈፀምኩት የጥብቅና ውል ለኔ ጠቃሚዬ ነው›› አለ ዳኒ፡፡
‹‹ጥቅም የምትለውን ተወው፡፡ እኔ እንድትረዳኝ ነው የጠየኩv››
‹ይህን ሁሉ የምትጠይቂኝ ለራስሽ ጥቅም አይደለም?›
አንተ እልም ያልክ ውሸታም ነክ አንተስ ስለራስክ ጥቅም አደለም የምታወራው? ልትለው ፈልጋ ላለመናገር ከራሷ ጋር ታገለችና ‹አባባ ጋ ያሉትን ሰነዶች እንዳትረሳ›› አለችና ትንፋሿን ያዝ አደረገች
‹‹ምንድን ነው ያልሽው?››
‹‹ባጭሩ እንረዳዳ ነው የምልህ፡፡ እንዲህ ያለ ነገር መቼም የሚገባህ
ይመስለኛል››
‹‹አዎ ገብቶኛል ይሄ ዛቻ ይባላል››
እያደረገችው ያለችው ነገር በሙሉ የሚያሳፍር ነው፡፡ ነገር ግን ከማን ጋር እንደምትወያይ አስታወሰችና ‹‹አንተ አስመሳይ ሽማግሌ! እንደዚህ ያለ ነገር ህይወትህን ሙሉ
ስትፈፅም ኖረሃል››
ዳኒ ሳቀና ‹‹ዛሬ እጅሽ ላይ ወድቂያለሁ፡›› ይህን ተናግሮ ሲያበቃ አንድ
ነገር አዕምሮው ውስጥ አቃጨለና ‹‹እኔ ላይ ግፊት ለማድረግ ብለሽ ራስሽ
ሳትሆኚ አትቀሪም ይህን የጠነሰስሽው›› አላት፡፡
አሁን ወደ እውነቱ ተጠግቷል፡፡
‹‹አንተ ብትሆን እንዲህ
እንደምታደርግ አውቃለሁ፡፡ ከዚህ በላይ አትመርምረኝ፡፡ አንድ ማወቅ የሚገባህ ነገር በነገው የቦርድ ስብሰባ እኔን ከደገፍክ ከችግር ነጻ ነህ ካልደገፍከኝ ግን አለቀልህ›› ስትል ቁርጡን ነገረችው:፡ አሁን በግልጽ
ማስፈራራቱን ተያያዘችው፡፡ እሱ ደግሞ የሚገባው ቋንቋ እንዲህ ያለው ነው፡፡ ከዚህ በኋላ እግሯ ስር ይወድቃል ወይስ ዞር በይ› ይላል?
‹‹እኔን እኮ እንዲህ ልትናገሪኝ አትችይም! እኔ ቂጥሽን ያልጠረግሽ ልጅ
ሳለሽ ጀምሮ ነው የማውቅሽ››
ናንሲ ድምጿን ለስለስ አድርጋ ‹‹ታዲያ እኔን ለመርዳት ይሄ ምክንያት
ሊሆን አይችልም›› አለች፡፡
ትንሽ ቆየና ዳኒ ‹‹ሌላ ምን ምርጫ አለኝ!›› አለ፡፡
‹‹ያለህ አይመስለኝም እኔ ያልኩህን ከማድረግ ውጭ።››
‹‹እሺ›› አለ በገነገነ ሁኔታ፡ ‹‹ነገ ለአንቺ ድምፅ እሰጣለሁ አንቺ
እነዚያን ሰነዶች የምታጠፊ ከሆነ፡፡››
ናንሲ ያሰበችው በመሳካቱ ልታለቅስ ምንም አልቀራትም፡፡ ዳኒን
ከእግሯ በታች አዋለችው፡ አሁን ድሉ የእሷ ሊሆን ነው፡፡ የብላክ የጫማ
ኩባንያ በእሷ ቁጥጥር ስር ሊገባ ነው፡፡

📕ተአምረተ_ኬድሮን
#ተከታታይ ልቦለድ
#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
በማግስቱ….
ከምሽቱ 1 በሰዓት አካባቢ ነው ሰሚራም ሆነች ዶ/ር እስክንድር የእለቱ የማታ ተረኛ ሆነው ስራቸው ላይ ተስማርተዋል፡፡
ሰሚራ ለመላኩ ዘመዶች ደወለችላቸው…ሰሎሞን ነበር ስልኩን ያነሳው
‹‹ሄሎ››
‹‹ሄሎ..ሰላም ነሽ?››
‹‹አዎ ሰላም ነኝ …እንድትመጡ ፈልጌ ነው››
‹‹ማን…..? ››
‹‹እናንተ ናችሁ…. ሁለታችሁም››
‹‹ለምን…..? ምን ተፈጠረ…..?››
‹‹ላደርገው ነው…ማድረግ የምፈልገው ደግሞ እያያችሁ ነው..እናንተ ባላችሁበት››
‹‹አረ ችግር የለውም ..ሁሉን ነገር ካጠናቀቅሽ በኃላ ብትደውይልን ይሻላል››
‹‹እንደዛ አላደርግም…በቃ አሁን በነፍስ ነው ብዬ እንደደወልኩላችሁ አስቡትና እቤትም ሆነ መንገድ ላይ ለገኛችሁት ሰው እንዲሁም ለሌሎች ዘመዶቻችሁ እየደወላችሁ በነፍስ ነው ተብሎ ተደውሎልናል እያላችሁ ንገሩ ፣እናንተም በ20 ደቂቃ ውስጥ ድረሱ›
‹‹አዎ… በቃ ገባኝ እንመጣለን..ትክክል ነሽ››ስልኩ ተዘጋ
ሁለቱ ብቻ ሳይሆኑ በሌሎች ከስድስት በማያንሱ ሰዎች ታጅበው ለመምጣት ከ15 ደቂቃ በላይ አልፈጀባቸውም…..ሰላም ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ሆስፒታሉን አተረማመሰችው….ሰሎሞንም እንባውን እየዘራ ወንድሜን እያለ በማጎራት ግቢውን መዞር ጀመረ…
ለስድስት ቀን በኮማ ውስጥ የሰነበተው መላኩ ምን እንደነካው ከዶክተሩና ከሰሚራ ውጭ ማንም በማያውቀው ምክንያት በጣር ነፍስ ጊቢ ነፍስ ውጭ እያቃተተ ነው…ዶ/ር እስክንድር ሲስተር ሰሚራ እና ሌሎች ሁለት ነርሶች ዙሪያውን ከበው ሊረዱት እየሞከረ ነው..
‹‹ሲስተር ሰሚራ ቶሎ ብለሽ ይሄንን መድሀኒት ውጊው ››ብሎ በወረቀት ላይ የመድሀኒቱን ስም ጽፎ ሰጣት… እሷም ተቀብላ ቶሎ ብላ ወጥታ ሄደችና በሶስት ደቂቃ ውስጥ ይዛ መጣች… መዳሀኒቱን በተንጠለጠው ግሉኮስ ከረጢት ውስጥ በስሪንጅ መጣ ለቀቀችበት ..ቀስ እያለ በቱቦ ውስጥ በመንጠባጠብ ከደም ስሩ ተቀላቀለ…. ከደቂቃዎች በኃላ የበሽተኛው ጣር እየቀነሰ …መንፈራገጡም እያቆመ መጣ….ከዛ ፀጥ አለ …ሰው ሲሸነፍ ወይም ሲያፈገፍግ ፀጥ ይል የለ….ዶ/ር እስክንድር በማዳመጫ ትንፋሹ አዳመጠው…እጆቹና እያወናጨፈ አንገቱና ቀብሮ በብስጭት ክፍሉን ለቆ ወጣ …ኮሪደር ላይ እነ ሰሎሞን እና አጃቢዎቻቸው ከበቡት.
‹‹ዶክተር..እንዴት ነው በሽተኛው…..?››
‹‹ዶክተር ይሻለዋል ..ፍቅሬ ይድናል…..?››
ለበራካታ ሰከንዶች ተገትሮ ሰላምን አፍጦ ከማየት ውጭ ምንም መናገር አልቻለም፣‹‹….….ይቺን ላየ ሰው እነ ሰላም እና መሀደር ምኑን አክተር ተባሉት ?››ሲል በውስጡ አሰበ…መለስ ብሎም ስለራሱ አሰበ …ወየው ጉድ እኔም ለካ ሌላ ተዋናይ ሆኜያለሁ…አለም ሰፊ መድረክ እኛም ኑሪዎቾ ተዋናዬች ነን ያለው ማን ነበር …..? ለካ እውነት ነው…›አለና ወደቀልብ በመመለስ ለእነሱ ጥያቄ መልስ መስጠት ጀመረ
‹‹አዝናለሁ የተቻለንን አድርገናል…ግን አልተሳካልንም..አርፏል ››ብሎ በተገተሩበት ጥሎቸው እግሮቹን አንቀሳቀሰ … ግቢውን በጩኸት እና በለቅሶ ሲያደበላልቁት በውስጡ እየተጠየፋቸው እና እየረገማቸው ጥሎቸው ወደ ቢሮው ሄደ
ሰላም…
..ፍቅሬ ፍቅሬ…
እንጋባለን ብለሀኝ አልነበረ ወይ…
ሙሽራዬ ነሽ አላልከኝም ነበር ወይ..
ለማን ተውከኝ..ለማን ተውከኝ
ሰሎሞን……
ወንድም ጋሻዬ ….ወንድም ጋሻዬ
የእኔ ብቸኛ..የእኔ ብቸኛ
የአባቴ ምትክ ..የአባቴ ምትክ
የዓይን ማረፊያዬ….
/////
ከደቂቃዎች በኃላ ሬሳው እየተገፋ ተመላካቹን በእንባ በሚያራጭ እንግሩጉሮአዊ ዜማ እና አንጀት በሚበላ ሁኔታ በሚያለቅሱት እና ኩርምት ጭብጥ በሚሉት በወንድሙ ሰሎሞን እና በፍቅረኛው ሰላም መካከል አልፎ ወደሬሳው ክፍል ተወሰደ…..ሰሚራም እየተንቀጠቀጠች እና እየዘገነናት እራሷን ለማረጋጋት በትርምሱ መሀል ተሹለክልካ ከሁሉም ነገር በመሸሽ ቢሮዋ ገብታ ተሸጎጠች
እስከአሁን የሰራችው ስራ እና የፈጠረችው ተግባር ትልቅ ድንጋጤ ውስጥ ከቷት እየተንቀጠቀች ነው..የሚገርመውና ይበልጥ የሚጨንቀው ግን ከአሁን በኃላ የምትሰራው ስራ ነው…
በበቀልም ሆነ በጥላቻ ተነሳስቶ ሰውን ድፍት አድርጎ መግደል በጣም ቀላል ነው…ሳያስበው በሆነ ብረት ማጅራቱን መጠቅለል እና ዝርግፍ ብሎ ሲወድቅ ጭንቅላቱን በድልዱም ብረት መድገም ነው…አዎ እንደዛ ማድረግ ቀላል ነው… የሚከብደው ከገደሉት በኃላ ያለው ነገር ነው፡፡ሬሳውን ምን ላድርገው…?ግቢው ውስጥ ቆፍሬ ልቅበረው..….?ረሀብ ያንገላታው ውሻ ቆፍሮ አውጥቶ ቢያጋልጠኝስ…?በጆንያ አድርጌ ከከተማ አውጥቼ ራቅ ያለቦታ በመውሰድ ጫካ ውስጥ ልጣለው…?.መንገድ ላይ ፖሊስ ለፍተሻ ቢያስቆመኝስ……..?እንደዛ ሳደርግ ሰው ቢያየኝስ……..?ስቃይ ነው….በዛን ቅጽበት ከሟቹ በላይ ገዳዩ ያሳዝናል…በተለይ ገዳዩ እንደእሷ አማትር ገዳይ ሲሆን ......ሁኔታው እንደቅዣት ሆኖባት፤ በውስጧ ስትብሰለሰል ስልኳ ተንጫረረ….
ከፈጣሪ የተደወለባት ነው የመሰላት….በርግጋ ከተቀመጠችበት በመነሳት ተፈናጥራ ቆመችና የደዋዩን ማንነት ለደቂቆች አትኩራ ተመለከተች…. በፈራ ተባ ስሜት አነሳችው
‹‹አቤት››
‹‹የት ገባሽ…..?››
‹‹አለው ፈርቼ ቢሮዬ ቁጭ ብዬ ነው››
‹‹ምን ያስፈራሻል.…..?.››
‹‹እንዴ ድመት እኮ አይደለም ሰው ነው ያስገደላችሁኝ…..››
‹‹ማለቴ መግደልሽን ማን ያውቃል..…..?እንደውም ስትፈሪና ስትንቀጠቀጪ የስራ ባለደረቦችሽ እንዳይጠረጥሩሽ…በተለይ ዶክተሩ እንዴት ሞተ ……..?ይሞታል ብለን አልገመትንም ነበር ሲል ሰምቼዋለሁ››
‹‹እ!! እንደዛ አለ እንዴ…..? ››
‹‹አዎ ብሏል…ለማንኛውም አሁን ምን እናድርግ.››
‹‹ምን ለማድረግ አሰባችሁ?››
‹‹ሬሳውን አሁኑኑ ብትሰጡንና በጥዋቱ ቶሎ ብለን ብንቀብረው ጥሩ ነው፡፡››
‹‹ሬሳውንማ ላሰጣችሁ አልችልም …ጥዋት ነው መውሰድ የምትችሉት››
‹‹አይ አሁኑኑ መውሰድ አለብን… አሁን ሬሳ ሳጥን ገዝተው እንዲመጡ ሰዎች ልኬያለሁ…አንቺ ብቻ ደክተሩን አሳምነሽ እንዲፈርምልኝ አድርጊ…››
‹‹ዶክተሩ እኮ መሞቱን ብቻ ነው የሚያረጋግጥልህ….ሬሳውን በዚህ ምሽት እንድታወጣ የመፍቀድ ስልጣን ያላቸው ግን ሌሎች ናቸው››
‹‹ሌሎቹን ተያቸው ..ዶክተሩ ብቻ ካስፈረምሽልኝ ካንቺ ምንም አልፈልገም…..ወደቤትሸ ሄደሽ ተረጋግተሸ በድል መተኛት ትችያለሽ…የስራ ኮንትራታችንን እዛ ላይ ይጠናቀቃል….››
‹‹እዛ ላይማ አይጠናቀቅም … መቶ ሺ ብር ጨምርልሻለው ብለኸኝ ነበር››
‹‹ሀይለኛ ብር ወዳድ ልጅ ነሽ… አይዞሽ አረሳሁትም ግን እንደምታይኝ አሁን ሀዘን ላይ ነኝ ፡፡ ከሶስት ቀን በኃላ ያው እንደምንም መጽናናቴ ስለማይቀር አቀብልሻለሁ…››
‹‹ዋ እንዳትረሳ››
‹‹አረሳም አሁን ያልኩሽን ጨርሺና ደውይልኝ››
ስልኩ ተዘጋ……
✨ይቀጥላል✨
#ክፍል 40,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል✅
https://youtube.com/@Weygud18
#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇