ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
247K subscribers
291 photos
1 video
15 files
244 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሰላሳ

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

...አይሮፕላኑ ወደ ኋላ የማይመለስበት ቦታ ላይ ሊደርስ የቀረው ትንሽ ነው፡፡ ኤዲ አዕምሮው በጭንቀት እንደተወጠረ ከምሽቱ አራት ሰዓት ወደ ስራው ተመልሶ ገብቷል፡ በዚህ ሰዓት ፀሃይ ጠልቃ ጨለማ ነግሷል፡፡
የአየር ጠባዩም ተለውጧል፡፡ዝናቡ
የአይሮፕላኑን መስታወቶች
ይጠልዛቸዋል ኃይለኛው ነፋስ አይሮፕላኑን እንደወረቀት ስለሚወዘውዘው
ተሳፋሪዎቹን ጭንቀት ውስጥ ጥሏቸዋል፡

የአየር ጠባዩ ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ መጥፎ ቢሆንም ካፒቴኑ
የሚያበረው ባህሩ ጋ አስጠግቶ ነው፡፡ ከምዕራብ አቅጣጫ የሚመጣው ነፋስ
ዝቅተኛ የሆነበትን ከፍታ ለማግኘት ሲል ነፋሱን እያሳደደ ነው፡፡

የአየር ጠባዩ በትንበያው ከተገመተው በላይ እየተበላሸ በመምጣቱ
ሞተሮቹ ከተጠበቀው በላይ ነዳጅ አቃጥለዋል፡ ኤዲ ነዳጁ አነስተኛ መሆኑን በማወቁ ተጨንቋል፡፡ በነዳጅ ማጠራቀሚያው ውስጥ በቀረው ነዳጅ ምን ያህል ኪሎ ሜትር ሊሄድ እንደሚችል ለማስላት የስራ ቦታው ላይ ቁጭ አለ፡፡ የቀረው ነዳጅ ኒውፋውንድ ላንድ ካናዳ የማያደርስ ከሆነ አይሮፕላኑ ወደ ኋላ መመለስ የማይችልበት ቦታ ከመድረሱ በፊት ወደኋላ መመለስ አለበት።

ታዲያ ካሮል አን ምን ሊውጣት ነው?

ቶም ሉተር ጠንቃቃ በመሆኑ አይሮፕላኑ ሊዘገይ የሚችል መሆኑን ግምት ውስጥ አስገብቶ ከጓደኞቹ ጋር ያለውን ቀጠሮ ለማስረገጥ ወይም
ለማስለወጥ መንገድ ይፈልጋል፡፡

አይሮፕላኑ ወደ ኋላ የሚመለስ ከሆነ ካሮል አን በአፋኞቿ መዳፍ ስር ለሃያ አራት ሰዓት መቆየቷ ነው፡፡ ኤዲ ከስራ ውጭ በሆነበት ጊዜ ሁሉ አስሬ በአይሮፕላኑ መስኮት ሲመለከት አመሸ፡፡ እንቅልፍ እንደማይወስደው ስላወቀ ለመተኛት እንኳ አልሞከረም፡፡ ካሮል አን በዓይነ ህሊናው እየታየችው ጭንቅ ጥብብ ብሎታል ወይ ስታለቅስ ወይ እጅ እግሯ ታስሮ ወይ በድብደባ ቆስላ ወይ ፍርሃት ፍርሃት ብሏት ወይ ተስፋ ቆርጣ ትታየዋለች፡፡ ምንም ሊያደርግላት አለመቻሉን ሲያስበው በንዴት የአይሮፕላኑን ግድግዳ በጡጫ ይጠልዘዋል፡
አንድ ሁለት ጊዜ ደግሞ ለእሱ ተተኪ ለሆነው ሚኪ ፊን ስለአይሮፕላኑ የነዳጅ ፍጆታ ለመንገር በደመነፍስ በደረጃው እየወረደ ከራሱ ጋር እየታገለ ሳይነግረው ተመልሷል፡

ኤዲ ቶም ሉተርን በመብል ክፍሉ ውስጥ በነገር የነካካው አዕምሮው
በመረበሹ ነው፡፡ ቶም ሉተር ደግሞ ብዙም አይናገርም፡፡ እድሉ ሲጠም.ደግሞ ሁለቱ አንድ ጠረጴዛ ላይ ለመብል ተገናኙና አረፉት፡፡ ከራት በኋላ ኤዲ ምን ያህል ስርዓት የጎደለው ተግባር በተሳፋሪ ላይ ሲፈጽም እንደነበረ ጃክ ሲነግረው አመሸ፡፡ ኤዲና ቶም ሉተር የተጣሉበት ነገር እንዳለ ጃክ አውቋል፡፡ ጃክ ኤዲ ብዙም ሊነግረው እንዳልፈለገ ስለገባው ለአሁኑ ያለውን ተቀብሎታል፡፡ ኤዲ ከዚህ በኋላ መጠንቀቅ እንዳለበት አምኗል፡፡ ካፒቴን ቤከር የበረራ መሀንዲሱ የተሳፋሪዎችን ደህንነት የሚጎዳ ተግባር በግዴታ
እንዲፈጽም መታዘዙን ከጠረጠረ እንኳን አይሮፕላኑን ወደ ኋላ ከመመለስ አይቆጠብም፡፡ ይህም ኤዲ ሚስቱን ከእገታው ለማውጣት የሚያደርገውን መፍጨርጨር ያደናቅፍበታል፡፡ ስለዚህ  ካፒቴኑ  አንድም ነገር ማወቅ የለበትም።

በመርቪን ላቭሴይና በሎርድ ኦክሰንፎርድ መካከል የተነሳው
ጠብ  ትዕይንት ኤዲ በቶም ሉተር ላይ ያሳይ የነበረውን ሁኔታ
እንዲረሳ አድርጎታል፡፡ ኤዲ ሌላ የአይሮፕላኑ ክፍል ውስጥ ሆኖ በሃሳብ ተውጦ ስለነበር  አላየም፡፡  በኋላ ግን አስተናጋጆቹ የነበረውን ሁኔታ አጫወቱት።ሎርድ ጨካኝ ሰው መሆኑን በመረዳቱ ካፒቴኑ አደብ እንዲገዙ ማድረጉ ኤዲን አስደስቶታል፡ ኤዲ ታዳጊው ፔርሲ በዚህ እርጉም ሰው እጅ
ማደጉ አሳዝኖታል፡

ራት ከተበላ በኋላ ተመልሶ ጸጥታ መንገሱ አይቀርም፡፡ በእድሜ የገፉት ተሳፋሪዎች በየመኝታቸው ላይ ይሰፍራሉ፡፡ ብዙዎቹ በአይሮፕላኑ ውዝዋዜ
እንቅልፍን አጥተውት
ሲያንጎላጁ ያመሻሉ፡፡ ከዚያም አንድ በአንድ እያሉ ይተኛሉ፡፡ እንቅልፍ የማይጥላቸው ተሳፋሪዎች ደግሞ ወይ ካርታ ሲጫወቱ ወይም መጠጣቸውን ሲጨልጡ ያመሻሉ፡፡

ኤዲ የአይሮፕላኑን የነዳጅ ፍጆታ በቻርቱ ላይ ይከትባል፡ በግራፉ
የተመለከተው የአይሮፕላኑ
በቀኝ በኩል የነዳጅ ፍጆታ በእርሳስ
ከተመለከተው የእሱ ትንበያ በላይ ነው፡፡ ኤዲ የሃሰት የነዳጅ ፍጆታ ትንበያ ስላሰፈረ ይህ መሆኑ አይቀርም የአየር ጠባዩ መክፋት ደግሞ በትክክለኛው ፍጆታና በትንበያው ፍጆታ መካከል ያለውን ልዩነት እንዲጎላ አድርጎታል።

በቀሪው ነዳጅ አይሮፕላኑ ሊሄድ የሚችለውን ርቀት አስልቶ ሲጨርስ
ጭንቀቱ በረታ፡፡ የአይሮፕላኑም የነዳጅ መጠን አስተማማኝነት ደንብ እንደሚያዘው የቀረውን የነዳጅ መጠን በሶስት ሞተሮች ፍጆታ ሲያሰላው እስከ ኒውፋውንድ ላንድ እንደሚያደርሰው አወቀ።

ሌላ ጊዜ ቢሆን ይህን ሲያውቅ ለካፒቴኑ ወዲያውኑ መንገር አለበት፡ አሁን ግን አልነገረውም፡፡

የነዳጅ መጠኑ በአራት ሞተር ሲሰላ የነዳጅ እጥረቱ በጣም ስለሚያንስ
ምንም አያስጨንቅም፡፡ ከዚህም በላይ የአየር ጠባዩ ከተወሰኑ ሰዓቶች በኋላ ጸጥ ያለ ይሆን ይሆናል፡ የንፋሱ ግፊት ቀለል ያለ ከሆነ አይሮፕላኑ ከተተነበየው ያነሰ ነዳጅ ስለሚጠቀም ለቀረው ጉዞ ነዳጅ ሊተርፍ ይችላል የከፋ ነገር ከመጣ ደግሞ ርቀቱን ለማሳጠር ሲሉ የጊዜ አቅጣጫቸውን
ይለውጡና በሞገደኛው ንፋስ ውስጥ ይጓዛሉ፡፡ በዚህ አይነት ጉዞ ግን የሚሰቃዩት ተሳፋሪዎች ናቸው፡፡

ከኤዲ በስተግራ የተቀመጠው ራሰ በራው ቤን ቶምሰን በሞርስ ኮድ
የተቀበለውን የሬዲዮ መልእክት ወደ ጽሑፍ እየቀየረ ነው፡፡ ኤዲ ከፊታቸው ያለው የአየር ጠባይ የተሻለ እንዲሆን በመመኘት ከቤን ኋላ ሆኖ መልእክቱን ያነባል፡

የመጣው መልእክት ግን ማስደነቅ ብቻ ሳይሆን እንቆቅልሽ ሆኖበታል፡
መልእክቱ የተላከው ኤፍ.ቢ..አይ ኦሊስ ፊልድ ለሚባል ተሳፋሪ ሲሆን

‹ብቁጥጥር ስር ያለው እስረኛ ተባባሪ ሊሆኑ የሚችሉ ከተሳፋሪዎቹ መካhል ያሉ ስለሆነ በጥብቅ ክትትል አድርግ›› ይላል፡

ምን ማለት ነው? ከካሮል አን አፈና ጋር ግንኙነት አለው ይሆን ይህ
መልእክት?› ሲል አሰበ ኤዲ፡ ይህ ሊሆን እንደሚችል ሲያስበው ራሱን
አዞረው።

ቤን የኮድ ትርጉሙን ቀዶ
«ካፒቴን ይህን መልእክት ብታየው›› ብሎ ለአለቃው አቀበለው፡፡

ጃክ አሽፎርድ የሬዲዮ መገናኛ ባለሙያው አስቸኳይ መልእክት መኖሩን ሲናገር ሰምቶ ከሚያፈጥበት ቻርቱ ላይ ቀና አለ፡፡ ኤዲ ከቤን መልእክቱን ተቀብሎ ለጃክ አሳየውና ራቱን እየበላ ላለው ካፒቴን አሳየው።

ካፒቴኑ መልእክቱን አነበበና ‹‹እንዲህ አይነት ነገር ነው የማልወደው›› አለ፡፡ ‹‹ኦሊስ ፊልድ የኤፍ.ቢ..አይ አባል ሳይሆን አይቀርም::››

‹‹ተሳፋሪ ነው?›› ሲል ጠየቀ ኤዲ፡፡

‹‹አዎ፡፡ ሰውየው እንግዳ ባህሪ ነው ያለው፡ ድብርታም ነው፡፡ የተሳፋሪ
ሁኔታ የለውም: ፎየንስ ላይ ቆይታ ሲደረግ ከአይሮፕላኑ ላይ አልወረደም›› አለ፡፡

ኤዲ ሰውየውን ባያስተውለውም ናቪጌተሩ ጃክ ግን አይቶታል፡
‹‹ያልከውን ሰው አውቄዋለሁ›› አለ ጃክ አገጬን እያከከ፡፡ ‹‹ራሰ በራ
ነው፡፡ አብሮት ልጅ እግር ሰው ተቀምጧል፡ ሰዎቹ ሲታዩ ምናቸውም አይጥምም::››
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሰላሳ_አንድ

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ከመሐል አትላንቲክ ወደ ቦትውድ (ካናዳ)


ዳያና ላቭሴይ ባሏ ፎየንስ ላይ አይሮፕላኑን መሳፈሩ በእጅጉ አስቆጥቷታል፡ በመጀመሪያ ዱካዋን እግር በእግር ተከታትሎ በመምጣት መሳቂያ መሳለቂያ ስላደረጋት አፍረት ውስጥ ከቷታል፡ ባሏ እቤታችን እንሂድ ቢላትም ሀሳቧን መለወጥ አትፈልግም ከማርክ ጋር ወደ አሜሪካ ለመሄድ የወሰነች ብትሆንም መርቪን ግን የመጨረሻ ውሳኔዋ ነው ብሎ መቀበል አልቻለም፡፡ ይሄ ደግሞ በቁርጠኝነቷ ላይ ጥላ አጥልቶበታል፡፡እሱም ውሳኔዋን እንደገና እንድታጤነው ደጋግሞ ስላሳሰባት ውሳኔዋን
በተደጋጋሚ ገልጻለታለች፡፡ በመጨረሻ ግን የአየር ጉዞዋ የሰጣትን ደስታ
ነጥቋታል፡፡

በህይወት አንዴ ብቻ የሚገጥም ከፍቅረኛ ጋር የሚደረግ ጉዞ፡፡

ከሳውዝ ሃምፕተን ሲነሱ የነበረው የነጻነትና የደስታ ስሜት አሁን የለም: መርቪን ከመጣ ወዲህ ምቹው አይሮፕላን፣ ከተለያዩ ተሳፋሪዎች ጋር መቀላቀሉና እጅ የሚያስቆረጥመው ምግብ ደስታ እየሰጣት አይደለም፡መርቪን ባጋጣሚ ሲያልፍ ያየኛል ብላ ስለፈራች ከማርክ ጋር መላፋት፣መተሻሸትና መሳሳም አልቻለችም፡፡ መርቪን የት እንደተቀመጠ አታውቅም፡፡ካሁን አሁን ይመጣ ይሆን እያለች ትበረግጋለች። ማርክ ካሊፎርኒያ ስለሚጠብቃቸው ኑሮ በተስፋ ሲያወራና ሲቀልድ ቆይቶ ጣውንቱ ከሰማይ
እንደወደቀ ሁሉ ድንገት አይሮፕላኑ ውስጥ ጥልቅ ካለ ወዲህ ግን ቀልቡ
ግፍፍ ብሏል፡ አሁን የተነፈሰ ፊኛ መስሏል፡፡ ዳያና አጠገብ ቁጭ ብሎ
አንድም ቃል ሳያነብ የመጽሔቱን ገጾች ያገላብጣል፡፡ ስሜቱ መጎዳቱን ዳያና አይታለች፡፡ አንድ ወቅት ላይ ይዟት እንዲጠፋ ከቆረጠች በኋላ ሃሳቧን ለውጣ ነበር፡፡ አሁን ባሏ ስለመጣ ከእሱ ጋር እሄዳለሁ ብላ ሃሳቧን
የማትለውጥ መሆኗን እርግጠኛ መሆን አልቻለም፡፡
የአየሩ ሁኔታ እየከፋ መምጣቱ ደግሞ ሌላ ራስ ምታት ሆኖባታል

አይሮፕላኑ ልክ ኮረኮንች ላይ እንደሚሄድ መኪና ይንገጫገጫል፡፡ በየሰዉ
ፊት ላይ ፍርሃት ይነበባል፡፡ ተሳፋሪው ሁሉ የሚያወራው ይህንኑ ነው፡

ዳያና ባሏ የት እንደተቀመጠ ማወቅ ፈለገች፡፡ እግረ መንገዴን ባየው እየተዘዋወረች ብትቃኝም መርቪንን የበላው ጅብ አልጮህ አለ፡፡ በመጨረሻ የቀራት ክፍል የሙሽሮቹ ክፍል ብቻ ነው፡፡

የሴቶች መዋቢያ ክፍል ገባች። ክፍሉ ውስጥ ሁለት ወምበሮች ያሉ ሲሆን አንዱ ወንበር ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ ትኳኳላለች፡፡ ዳያና በሩን ልትዘጋ ስትል አይሮፕላኑ ዘጭ ሲል ሚዛኗን ስታ ልትወድቅ ምንም አልቀራትም፡፡ እንደምንም ተንገዳግዳ ሄዳ ባዶው ወምበር ላይ ዘፍ አለች።

‹‹ተረፍሽ?›› ስትል ጠየቀች ሴትየዋ፡፡

‹‹አዎ፣ አመሰግናለሁ›› አለች ዳያና ‹‹አይሮፕላን እንዲህ ሲሆን አልወድም››

‹‹እኔም አልወድም፡ ከዚህ በኋላ ጉዟችን የከፋ እንደሚሆን አንድ ሰው
ነግሮኛል፡ ዶፍ ዝናብ ይጠብቀናል›› አለች፡፡

የአይሮፕላኑ ውዝዋዜ ጋብ ሲል ዳያና ጸጉሯን ማበጠር ጀመረች።

‹‹ሚስስ ላቭሴይ ነሽ አይደለም?›› ስትል ጠየቀች

‹‹አዎ ዳያና በይኝ››
‹‹እኔ ናንሲ ሌኔሃን እባላለሁ:: ፎየንስ ላይ ነው የተሳፈርኩት”
ከሊቨርፑል ካንቺ. . . ከሚስተር ላቭሴይ ጋር ነው የመጣሁት››
‹‹ኦ!›› ዳያና ይህን ስትሰማ ፊቷ በእፍረት ቲማቲም መሰለ፡፡ ‹‹ጓደኛ እንዳገኘ አላወቅሁም ነበር›› አለች በምጸት፡፡

‹‹ይህን አይሮፕላን ለመሳፈር ወደ ሳውዝ ሃምፕተን ለመሄድ ፈልጌ
ሊቨርፑል ላይ መውጫ አጥቼ ስጨነቅ ባለቤትሽን አየር ማረፊያ ላይ
አገኘሁትና እንዲወስደኝ ለመንኩት››

‹‹እንኳን ቀናሽ›› አለች ዳያና፡፡ ‹‹የእሱ መምጣት እኔን እፍረት ውስጥ
ከቶኛል፡፡››

‹‹ማፈር የለብሽም፡፡ ሁለት ወንዶችን በፍቅር ማጥመድሽ ደስ የሚል
ነገር ነው፡፡ እኔ አንድ እንኳን ፍቅረኛ የለኝም፡፡››

ዳያና ናንሲን በመስታወት አየቻት፡፡ ሴትየዋ ቆንጆ ባትባልም የደስ ደስ አላት፡ ጸጉረ ጥቁር ስትሆን ከሰውነቷ ጋር የሚሄድ ልብስ ለብሳለች።
ስትታይ በራሷ የምትተማመን ትመስላለች፡ መርቪን ሊፍት ቢሰጥሽ
አያስገርምም፡ እሱ እንዳንቺ ያለች ሴት ነው የሚፈልገው አለች ዳያና በሆዷ፡፡
‹‹እንዴት ነው ያሳየሽ ባህሪ ጥሩ ነበር?›› ስትል ጠየቀቻት ናንሲን፡፡
‹‹ብዙም ጥሩ አልነበረም›› አለች በቅሬታ ፈገግታ፡
‹‹አዝናለሁ፡ ይህ ባህሪው ነው የሚያስጠቃው›› አለችና ሊፒስቲኳን ጨረገች

‹‹ሆኖም በችግሬ ጊዜ ስለደረሰልኝ ባለውለታዬ ነው›› አለችና ናንሲ
ተናፈጠች፡ ናንሲ ቀለበት ማሰሯን ዳያና አጤነች፡፡ ‹‹ትህትና ባይኖረውም
ጥሩ ሰው ይመስላል፡፡ ራትም ጋብዞኛል፡ ጨዋታ ያውቃል፡፡ የሴት ልጅን
ልብ የሚሰርቅ ቁመናና መልክ አለው›› አለች፡፡

ጥሩ ሰው ቢሆንም….... አለች ዳያና ‹‹ሰው ይንቃል፡፡ ትዕግስትም የሚባል ነገር ፈጽሞ አልፈጠረበትም፡፡››
ናንሲ ጥቁር ጥቅጥቅ ያለውን ጸጉሯን ታበጥራለች ሽበቷን ለመደበቅ ቀለም ትቀባ ይሆን?› አለች ዳያና በሆዷ።

አንቺን መልሶ በእጁ ለማስገባት ሲል የሚደርስበትን መከራ ለመቀበል ቆርጧል››

‹‹አይደለም ክብሩ ስለተነካ ነው›› አለች ዳያና ‹‹ሌላ ወንድ ስለወሰደኝ ነው ያንጨረጨረው፡፡ ተጋፊ ስለመጣበት ነው ተከትሎኝ የመጣው፡ ጥዬው
እህቴ ቤት ሄጄ ቢሆን ኖሮ እኔን ለመፈለግ እግሩን አያነሳም ነበር››

ናንሲ ሳቀችና ‹‹እንዳነጋገርሽ አንቺን ለማስመለስ ተስፋ ያለው
አይመስልም›› አለች፡፡

‹‹ምንም ተስፋ የለውም›› አለች ዳያና፡፡ ዳያና ድንገት ስሜቷ ስለተረበሸ ከናንሲ ጋር ከዚህ በላይ ማውራት አልፈለገችም፡፡ ሜክአፕና ማበጠሪያዋን ቦርሳዋ ውስጥ ከታታ ለናንሲ ያላት ጥላቻ እንዳይታወቅባት የውሽት ፈገግታ አሳየቻትና ‹‹ወደ ቦታዬ ልሂድ›› ብላ ተነሳች፡፡

‹‹መልካም ዕድል!››

ከሴቶች መዋቢያ ክፍል ስትወጣ ሉሉ ቤልንና ልዕልት ላቪኒያ የመዋቢያ ዕቃዎቻቸውን ያጨቁበትን ቦርሳዎቻቸውን አንጠልጥለው ገቡ፡፡
ወደ ቦታዋ ስትመለስ አስተናጋጁ ዴቭ መቀመጫቸውን ወደ ታጣፊ አልጋ ሲቀይር አየች፡፡ ዳያና አንድ ተራ ሶፋ እንዴት ወደ ተደራራቢ አልጋ ሊቀየር
እንደሚችል ገርሟታል። ዴቭ ከወምበሩ ስር አንሶላና ብርድ ልብስ አወጣና
አነጠፈ፡፡

ተደራራቢ አልጋዎቹ ምቹ ቢሆኑም ከሰው እይታ ውጭ ባለመሆናቸው
ዴቭ መጋረጃ አመጣና ጋረዳቸው፡ ከዚያም በአልጋዎቹ ጎን ትንሽ ታጣፊ
መሰላል አያያዘባቸው፡፡ ዴቭ ይህን የሰራው በሚያስደንቅ ቅልጥፍና ነው፡፡

ዴቭ ወደ ዳያናና ማርክ ዞሮ ፈገግታ ሳይለየው መኝታችሁ እንዲዘጋጅላችሁ ከፈለጋችሁ ንገሩኝና አዘጋጅላችኋለሁ›› አላቸው፡፡

‹‹ተደራራቢ አልጋዎቹ ውስጥ ሲተኙ ሰዎች አይታፈኑም?››
‹‹እያንዳንዱ አልጋ የራሱ አየር ማስገቢያ አለው›› ሲል መለሰ ‹ቀና ብለሽ ብታዪ ያንቺ አልጋ አየር ማስገቢያ አለው፡›› ዳያና ቀና ስትል መስቀያና መዝጊያና መክፈቻ ያለው በብረት ፍርግርግ የተሰራ አየር ማስገቢያ አየች:: "ከዚህ በተጨማሪ›› ሲል ቀጠለ ዴቭ ‹‹የራስሽ መስኮት፣ መብራት፣ የልብስ መስቀያና የመፀሐፍ ማስቀመጫ አለሽ።ከዚህ በተረፈ የምትፈልጊው ነገር
እንዲመጣልሽ ስትፈልጊረመ ይህን ቁልፍ ብትጫኚው ከተፍ እልልሻለሁ›› አላት።