ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
215K subscribers
284 photos
1 video
16 files
220 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
​​💔የባከነች_ነብስ💔
#የመጨረሻው ክፍል እነሆ
#ክፍል14⃣
🤦‍♀የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ🤦‍♀

🛎የመጨረሻው ክፍል🛎

...🖊 <<...ግንቦት 9 ቀን 2004 ዓ/ም ፍርድ ቤቱ በዋለዉ ችሎት ተከሳሽ ወ/ሪት ቤዛዊት አለሙ በፈፀመችዉ የከባድ ነብስ ማጥፋት ወንጀል ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ ክርክሩን ሰምቶ ወንጀለኛዋ የፈፀመችዉ ድርጊት ኢሰብአዊ በመሆኑ እንዲሁም ድርጊቱን የፈፀመችዉ በበቀል ተነሳስታ በመሆኑ በተጨማሪም በቀረበዉ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ወንጀለኝነቷ በመረጋገጡ በ 15 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኗል!>>

እንግዲህ ዓለም እንዲህ ናት ሚዛናዊ መሆን ይከብዳታል መንፈስና ሞራሌ ሲሰበር ማስረጃና ምስክር የጠየቁኝ ሁሉ ዛሬ እኔን በአደባባይ ለመወንጀልና ለእስራት ለመዳረግ ተሽቀዳድመዋል። አዎ እኔ አቤልን ገድዬዋለሁ የገዛ ሱቅ ዉስጥ በስለት ከ ሰባት ጊዜ በላይ ወግቼ ገድዬዋለሁ እዉነቱን መካድ አልችልም አልክድምም! የእኔና የእሱ ልዩነት አንድ ነዉ እሱ በክፋት ልቤን ወግቶ ክፉኛ አቁስሎኛል እኔ ደግሞ በስለት ወግቼ ከምድር አሰናብቼዋለሁ። በተፈረደብኝ ዉሳኔ ብቻ ሳይሆን በፈፀምኩት ወንጀል ከእየሩስ በስተቀር ሁሉም ዘመዶቼ ፊታቸዉን አዙረዉብኛል ለእኔ ግን ህይወት ፊቷን አዙራ ከጋተችኝ የመከራ ፅዋ የእነሱ ከእኔ መሸሽ ጋር ሲተያይ ዋጋ ቢስ ይሆንብኛል። ወደ ማረሚያ ቤት ከመግባቴ በፊት ካረፍኩበት የፓሊስ ጣቢያ ጊዜያዊ እስር ቤት እየሩስ ለመጨረሻ ጊዜ ልትጠይቀኝ መጣች። ገና ከፊት ለፊቷ ስቆም እንባዋን መቆጣጠር አቅቷት አምርራ አለቀሰች
<<እየሩሴ ለምን ታለቅሺያለሽ? ለምን? የንፁህ ሴቶችን ህይወት እያበላሹ በኩራት ደረታቸዉን ነፍተዉ ከሚራመዱ በርካታ ወንዶች መካከል እኔ መቀነስ የቻልኩት አንዱን ብቻ ነዉ! ፍርድና ዉሳኔ የፈጣሪ መሆኑን ባልክድም እሱ ላይ ባደረኩት ነገር ቅንጣት ታክል ፀፀት አይሰማኝም! በእኔ መንገድ ባይሆንም በደለኞችን የማጋለጥና ለንፁሀን የመቆም ሀላፊነት እንዳለብሽ ለደቂቃ እንኳን መዘንጋት የለብሽም!>>

እየሩስ አትሰማኝም! ወይም ደግሞ መስማት አትፈልግም! አልያም ደግሞ የምናገረዉ እያንዷንዷን ቃል ከልቧ እያተመችዉ ይሆናል! ብቻ እንቧዋን እያፈሰሰች ትኩር ብላ ከተመለከትችኝ በሗላ ተሰናብታኝ ሄደች!
ሁሉም ይሄዳል...የሚቆም ነገር አይኖርም...በመቆም ሳይሆን በመሄድ በተሞላች አዙሪታም ምድር ላይ መቆም ዋጋ የለዉም!
እኔም
አንቺም
አንተም
እናንተም
ሁላችንም ያለ መድረሻ እንሄዳለን የራቅን ይምስለን እንጂ እዉነታዉ አሁንም የጀመርንበት ቦታ መሆናችን ነዉ ካለን ላንጨምር ከተጨመረዉ ልናጎድል ለሰከንድ ፈገግታ የንፁሃንን ዘላለማዊ ደስታ ለምን እንደምናጠፋ አይገባኝም እንዲገባኝም አልፈልግም።

💦💦~~~ተፈፀመ~~~💦💦

🤦‍♀የባለታሪኳ መልዕክት

👉የህይወትን መራራ ፅዋ በትዕግስት ለተጎነጨዉ ከስኳር ልቆ ይጣፍጠዋል!

🙏ምስጋና
👉ታሪኩን በመከታተል አስተያየታችሁን ላደረሳችሁኝ በሙሉ!🙏

📮በታሪኩ ላይ ያላችሁን አስተያየት ከታች አስተያየት መስጫ የሚለውን በመንካት ያድርሱን፡፡

ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📮@Eyos18 አድርሱን

📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
📖📖📖📖
❤️​​​​ተወዳጁ
#የመጨረሻው ክፍል
#ክፍል21⃣

ኤልሳ ስትሮጥ ሄኖክ ሲከተላት መኪናዋን አቁማበት የነበረው ቦታ ደረሰች ወድያውም አስነስታ ልትሄድ ስትል ሄኖክ ደርሶ ኖሮ እያለከለከ ምን ሆነሻል ኤልሳ አትነግሪኝም ሲል በድጋሚ ጠየቃት
ኤልሳም እንባዋ በጉንጮቿ እየወረደ ሄኖኬ ጉድ ሆኛለው ልክ እንደናቴ አባቴንም በኔ ምክንያት ላጣ ነው አለች እሺ ክፈቺልኝ ልግባ ቅድሚያ አለ መደንገጡ እንዳይታወቅበት እየጣረ
ኤልሳም አይ ሄኒ ብቻዬን ልሂድ ምናልባት አብረን ሲያየን አባቴ ላይ እርምጃ ሊወስድ ይችላል አለችና በፍጥነት መንዳት ጀመረች ሄኖክ አላስቻለውም በኮንትራት ታክሲ ይከተላት ጀመር ከዛ ኤልሳ አባቷ ያለበት ቤት ደረሰች ግን በሚያሳዝን ሁኔታ አባቷን ሳታገኛቸው ቀረች ቤት ውስጥ ማንም አልነበረም ግን አንድ ነገር ተመለከተች ቤት ውስጥ ደም ተንጠባጥቧል ይሄኔ ኤልሳ እንደ እብድ አደረጋት መጮህና ማልቀስ የጠፋባት መሰላት... ወድያው ሄኖክ በሩን ከፍቶ ገባ እሮጣ ተለጠፈችበት ሁኔታዋ ግን ቅይርይር አለ ሰውነቷ ይንቀጠቀጣል ... አይዞሽ ውዴ ተረጋጊ አለ ሄኖክ እሱም ልክ እንደሷ ደሙን ሲያይ በጣም ደንግጧል ሄኖክ ገብቶ ጥቂት እንደቆዩ ወድያው ፖሊሶች ገቡ ጥቆማ ደርሶን ነበር አሉና ቤቱን መበርበር ጀመሩ ከዛም ወደ ጓሮ ዞሩ የኤልሳ አባት ተዘርረዋል...
ኤልሳና ሄኖክ ፊልም የሚተውኑ እስኪመስላቸው ነገሩ ከበዳቸው ከዛም ጓሮ ከገቡት አንዱ ፖሊስ ወደቤት በመግባት አለቃ አንድ ሰውዬ አግኝተናል ግን በህይወት አሉ ምናልባት ከተረፉ እንሞክር አምቡላንስ ይምጣ አለ እ አባቴ ነው እ ንገረኝ ፖሊስ አባቴ ነው እያለች ለማየት ስትጣደፍ ሁለቱን ተጠርጣሪ ወደ ጣብያ ውሰዷቸው ተባለ ... ምክንያቱ ምንም ሳይገባቸው ሄኖክና ኤልሳ ታሰሩ አባቷ መናገር ችለው ካልተናገሩ በርግጠኝነት እስኪጣራ እየተባለ አይፈቱም ኤልሳ የእስር ቤቱን ህይወት አልችል አለች እነዛ ያልተፈቱ እንቆቅልሾቿን ተፈተው እስክታይ ጓጉታ ታነባለች ልጇን ከዛ ሰውዬ ተቀብላ አባቷን እያስታመመች በሷ ምክንያት ያለፈ ስቃዩ ሳያንስ አሁንም የታሰረውን ፍቅረኛዋን ባሏ አድርጋ መካስ ትፈልጋለች በዚ መልኩ አንድ ወር ሊሞላ 6ቀን ቀረው አባቷ ነቅተው ልጄስ ብለው ጠየቁ የሚያስታምማቸው አንድም ዘመድ ባለመኖሩ ጎረቤታቸው አስካለ ከጎናቸው አትጠፋም ..ልጄስ አሏት ደግመው እሷም እምባዋን በነጠላዋ እየሸሸገች ልጅህ ታስራለች እስኪጣራ ብለው አስረዋታል አለች ተይ አስካለ ልጄ ስቃይ ላይ ሆና ዝም አልሽ አሉ የኤልሳ አባት በደከመ ድምፃቸው ወድያው ፖሊሶች ገብተው ... እግዜር ይማሮት አባት አሉ የኤልሳ አባትም አይናቸውን ቡዝዝ አርገው እያፈራረቁ ተመለከቷቸው ፖሊሶቹም ቃል መቀበል ጀመሩ በሰአቱ የኤልሳ ባል ሊገላቸው እንደነበርና .... ደውሎ ድረሽልኝ እንድላት ያረገኝ እሱ ነው አሉ ፖሊሶችም ወድያው ሄኖክንና ኤልሳን እንዲፈቱ ትእዛዝ ሰተው ሰውየውን መፈለግ ጀመሩ ... ከ24 ሰአታት ቡሃላ አገኙት ልጇን መልሶ ወደ እስር ቤት ተወሰደ ... አሁን ሄኖክ ተረጋግቶ ኤልሳን ሚስቱ አርጎ በተማረበት መስክ ስራ ጀምሯል ደስተኛ ቤተሰብ ሆነዋል ልጃቸውን በፍቅርና በስስት ማሳደግ ቀጥለዋል የኤሳ አባትም ደስተኛ ልጃቸው ቤት ህመማቸውን እያስታመሙ ነው።
በሰፈሩት ቁና እንዲሉ የኤልሳ የቀድሞ ባልም ፍርዱን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል.......

┈┈✦✿ ተፈፀመ💔 ✿✦┈┈

ይህ አሳዛኝ እና አስተማሪ የሆነውን ተወዳጁ❤️ የተሠኘው አጭር ልብ ወለድ ዛሬ በዚህ መልኩ ተፈፀመ እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለው ዳግም በሌላ ታሪክ እንገናኛለን መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ፡፡

ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
📖📖📖📖📖📖
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
💥ሞሮ💥
#የመጨረሻው ክፍል4⃣4⃣
#ተከታታይ ልቦለድ

ፀሃፊው ነኝ .... ከጥቂት ወራት በፊት በአንደኛው እለተሰንበት በእድሜ የሚበልጠኝ አንድ ጓደኛዬ ሲአምሲ አከባቢ ከሚገኘው ቤቱ እንደመጣ ጋበዘኝ እናንተ "ናኦድ" በሚለው ለፅሁፍ እንዲያመች በተቀየረው ስሙ ታውቁታላችው። እናም ግብዣውን ተቀብዬ ቤቱ ሄድኩ ወደቤቱ እየገባን እያለ አዲሱ ትዳር እንዴት ይዞሃል አልኩት በፈገግታ እሱም እየሳቀ አሪፍ ነው በልጄም በሚስቴም ደስተኛ ነኝ አለኝ አሪፍ ነው አልኩት። እንደለመደብኝ አዲስ ቦታ ስሄድ እንደማደርገው በአርክቴክት አይኔ ቤቱን ቃኘሁት ደስ ይላል ቀለል ያለ ኮተታኮተት ያልበዛበት የባለትዳር ቤት ይመስላል። ልክ ሳሎን ውስጥ እንደተቀመጥን ከመኝታ ቤት አንዲት ሴት ወጣች እንዴ... አቢጊ ብዬ አቀፍኳት ረጅም ግዜ ሆኖኝ ነበር ካገኘኃት ሞቅ ያለ ሰላምታ ሰጠኃት ናኦድን ሰላም ልትለው ስትል ከመኝታ ቤት የህፃን ልጅ ለቅሶ ሰማን ኤቤጊያ ውይ እፁዬ አለቀሰች ብላ እየሮጠች ወደመኝታቤት ተመለሰች ናኦድም ተከትሏት ሄደ። ትንሽ ከቆየ በኃላ ትንሿ በጣም እምታምረው ልጁን ይዟት ወጣ ብዙ ግዜ እኔ ህፃናት ብዙም አይመቹኝም ግን እፁብን እንዳየኃት ውድድድ አደረኳት እንዴት እንደምታምር ቀይ ድንቡሽቡሽ ልጅ ሉጫ ፀጉር ትልልቅ አይን ያላት ቆንጅዬ ልእልት ናት እፁብ። ከሶፋው ላይ ተነሳውና ወደናኦድ ተጠጋው ናዲ እምታምር ልጅ አለህ በጣም ነው ምታምረው አልኩና ግንባሯን በስሱ ሳምኳት አው ባክህ ቆንጅዬ ልእልት ናት ትንሽ እንቅልፏ ሲመጣ ለቅሶዋ መከራ ነው እንጂ አለኝ ህፃኗን እፁብ እሹሩሩ እያለ እንግዲ እኔ ስለህፃናት እማውቀው ነገር የለም አልኩት እየሳቀ ባክህ አንተም አግብተህ ስትወልድ ታየዋለህ አለኝ እኔም እየሳቅኩ ኡ.... ገና አልኩት። እፁብ ማልቀስ ስትጀምር እያባበላት ወደመኝታ ቤት ይዟት ሄደና ለአቢጊ ሰጥቷት ተመለሰ። እሺ እስራኤል እና ደህና ነህ ተጠፋፋን አይደል ያው ታውቀዋለህ ትዳር ስራ ምናምን ሲደራረብ አሁን ደግሞ እፁዬ መጥታለች ተጠፋፋን አለኝ አው ተጠፋፋን አልኩትና ከመቀመጫዬ ዳግም ተነሳውና ፊትለፊቴ ወዳለው ግርግዳ ሄድኩ የናዲ እና የሚስቱ የሰርግ ፎቶ በትልቁ በፍሬም ታሰቅሏል ባዶ ቦታዎቻቸው ላይ በወርቃማ እስክርቢቶ የወዳጅ ዘመዶቻቸው መልካም ምኞት አውቶግራፍ ተሞልቷል አይኔን አጥብቤ የተወሰኑትን ለማንበብ ሞከርኩ ደስ ይላሉ። ወደ ናኦድ እየዞርኩ ሳቅ ብዬ ለሰርጋቹ ግን ሳትጠሩኝ በጣም ታዝቢያቹሃለው አልኩት ናዲም እየሳቀ እኛማ ጠርተንህ ነበር አንተ አልመጣም አልክ እንጂ አለኝ። እና መቀሌ ነበርኳ ግቢ የእህቴን ሰርግ እራሱ አንድ ቀን ቆይቼ ነው የተመለስኩት ምናለ ለእረፍት እስከምንመለስ ብትጠብቁኝ እንኳን አንድ ብሬ ብጨርስ ነው አልኩት እየሳቅኩ ናዲም እየሳቀ አይ ረም ዘንድሮም ትኮምካለህ አ አለኝ እየሳቅኩ የቴሌቭዥኑ ስታንድ ጋር ሄጄ እዛ ላይ በፍሬም የተቀመጡትን ፎቶዎች እያነሳው ማየት ጀመርኩ ካሉት ውስጥ የምርቃታቸውን ፎቶ በእጄ አንስቼ አየሁት ናዲ መሃል ሆኖ ሰምሃል እና ኤቤጊያ በጎና በጎን ሆነው የተነሱት ፎቶ ነበር ወደናዲ እየዞርኩ ይሄ ፎቶዋቹ ደስ ይላል አልኩት። አውው... ባክህ ጥሩ ትውስታ ነው ግዜው ይሮጣል አይደል ከተመረቅን እንኳን አራት አመት ሆነን አይ ግዜዜዜ.... አለና ትንሽ በሃሳብ ሰመመን ሄደ። እኔ ፎቶዎቹን እያነሳው አይቼ ስጨርስ አስቀምጥና ሌላ አንስቼ ማየት ጀምራለው። ናዲ እንዳጎነበሰ ሲያስብ ከቆየ በኃላ ረምሃይ ብሎ ጠራኝ እእእ ናዲ አልኩት። እስኪ ና ቁጭ በል ስለ ግቢ አንድ ታሪክ ልንገርህ አንተ አስተዋይ እንደሆንክ አውቃለው ናሆሚም ነግራኛላች ግን ምናልባት እምትማርበት ነገር ይኖራል አለኝ እኔም ሄጄ አጠገቡ ተቀመጥኩ። ትንሽ አጎንብሶ ግንባሩን እያሸ ካሰላሰለ በኃላ ታውቃለህ ግቢ እያለው ብዙ ትዝታ ነበረኝ ብዙዎቹ መጥፎና አሳዛኝ ቢሆኑም በዛው ልክ ደግሞ ክፉውን ግዜ የሚያስረሱ ጥሩ ትዝታዎችና ምርጥ ጓደኞች ነበሩኝ። ግቢ ፍሬሽማን እና ሁለተኛ አመት ላይ በጣም ጎበዝ ተማሪ ቀለሜ ነበርኩ ብዙ ደሳስ እሚሉ ጓደኞች ነበሩኝ። ደስ የሚል ጊዜ እናሳልፍ ነበር በአስተማሪዎቼም ተወዳጅ ተማሪ ነበርኩ ግን ህይወት ልታስተምርህ ስትፈልግ ከፊትህ ፈተና ማስቀመጥ ትጀምራለች ልክ 2004 ሶስተኛ አመት እንደገባን አንዲት ሴት በፍቅር አንባረከከችኝ ሲለኝ በዚያው ቅፅበት ኤቤጊያ ከመኝታ ክፍሉ ቀስ ብላ እያተራመደች ወደኛ ጠጋ ብላ እፁ ተኝታለች ቀስ ብላችው ተጫወቱ እኔ ሰሙ ሳትመጣ ምሳ ልሰራራ ብላን በእግሮቿ ጣት ብቻ ቀስ ብላ እየተራመደች ከሳሎን ሄደች። ናዲ ወደኔ እያየ በእጁ አቢጊ ወደወጣችበት በር እየጠቆመ ያቺ በፍቅር ያንበረከከችኝ ሴት አቢጊ ነበረች አለኝ በአግራሞት ምን!? አልኩት አው አቢጊ በጣም ቆንጅዬ ቀበጥባጣ ልጅ ነበረች ያኔ አሁን እንደምታያየት የተረጋጋች አልነበረችም እና ስለሷ ሳስብ ስለሷ ሳልም ትምህርቴን እረሳው ያኔ ፍቅሯ ልቤን አውሮት በጣም እፈራት ነበር ገና ከርቀት ሳያት መንገዴን እቀይራለ ጓደኞቼ ሁኔታዬን እያዩ ይስቁብኝ ነበር ግዜያት እየተቆጠሩ ሲሄዱ እኔም ፍቅሯ በጣም እየባሰብኝ ሄደ....
ከውስጥ ኤቤጊያ ሽንኩርት ስትከትፍ የመክተፊያው ድምፅ ይሰማናል ተመስጬ እየሰማሁት ስለነበር ብዙም ልብ አላልኩትም ነበር ናዲ ብድግ አለና መኝታ ቤቱን ከፍቶ እፁ አለመነሳቷን ካረጋገጠ በኃላ ተመልሶ መጣና ፈገግ እያለ እና.... ራሴን መጣል ጀመርኩ እሷ እኔን አትመጥነኝም እል ነበር ፍቅሬን ድፍረት ኖሮኝ ብገልፅላት እንኳን ምሏሿ ተቀራኒ እንዳይሆን እልና እፈራለው እተወዋለው ስለሌላ ነገር ማሰብ ተሳነኝ ስልቹና ቸልተኛ ለምንም ነገር ግድ የማይሰጠኝ ሰው ሆንኩ ጓደኜቼ ለኔ ያላቸው ከበሬታ ቀስበቀስ እየቀነሰ ሄደ ይባስ ብለው ይስቁብኝና ይሳለቁብኝ ጀመር ታውቃላሃ "ሞሮ" ይሉኝ እንደነበር አለኝ አው አውቃለው ሰሙም ናሆሚም ነግረውኛል አልኩት። አው ሞሮ ማለት ምንም የማይገባው ደደብ ማለት ነበር የሚገርምህ ይህንን ስም ያወጡልኝ የገዛ ጓደኞቼ ናቸው የልብ ጓደኞቼ እምላቸው ነበሩ ሁሉም ከዱኝ ከአንድ በስተቀር ኪያር! ኪያር አሁንም ድረስ በጣም እምወደው እና እማከብረው የልብ ጓደኛዬና የስራ ባልደረባዬ ነው ከዛም በላይ ደግሞ የእህቴ ናሆሚ እጮኛም ነው።
ሶስተኛ አመት ሙሉ ስለኤቤጊያ ሳስብና ሳልም ኖርኩ ጓደኞቼ ሸሹኝ እኔም ከትምህርት ራቅኩ መማር አስጠላኝ ቀን ከቀን ተኝቼ እውላለው የጓደኞቼ ስድብና ኤቤጊያን መቼም እንደማላገኛት ሳስብ መጠጣት ጀመርኩ ሱስ ውስጥ ተዘፈቅኩ ዶርም ተኝቼ ካልሆነ በጠርሙስ ተደብቂያለው ወይ በሲጋራ ጭስ ራሴን ደብቂያለው ደህና የነበርኵት ልጅ በግዜ ሂደት መውጣት እማልችለው አዘቅት ውስጥ ተዘፈቅኩ ብዙ ግዜ ራሴን ላስተካክል ጣርኩ ግን አልሆነልኝም እንዲው እንደሆንኩ አራተኛ አመት ገባን የግቢው ቁጥር አንድ ጀዝባ እና ሞሮ ሆንኩ ለምንም ነገር ግድ አይሰጠኝም። አንድ ቀን ኤቤጊያን ከአንድ ራስታ ልጅ ጋር ስትሳሳም አየኃት በጣም ተናደድኩ በማግስቱ ልጁን ሺሻ ቤት አጊንቼ ተጣላን ጓደኞቹ ማታ ላይ ጠብቀው በጩቤ ወጉኝ ያኔ... ያኔ... ነበር ህይወቴን በሙሉ የምትቀይረዋን ሴት ያገኘሁት ሰምሃል! ኣለኝ ከሰሙ ጋር የተዋወቃቹት ያኔ ነው አልኩ በመገረም። አው ያኔ በሞትና በህይወት መካከል ሆኜ ያተረፈችኝ እሷ ነች ሆስፒታል ወስዳኝ ለመዳኔ ምክንያት ሆነች ከዛን ግዜ በኃላ ከሰምሃል ጋር
ሚኻዬል ጎርባቾቭ - ክፍል 4
@Eyosc1 on telegram
#የመጨረሻው ክፍል 4
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@Eyosc1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
📖📖📖📖📖📖
💍ሐሊማ🙋
#የመጨረሻው ክፍል🙌😍


...ቀድማ ነበር የደረሰችው ብዙም ሳትቆይ ሳሊም መጣ የቀዘቀዘ
ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ቀጥታ ወደ ጉዳያቸው ገቡ ሀሊማ
ይህንን አላማዋን ለማሳካት ያደረገችውን ነገር ነገረችው እንዴት
ብዪ ነው የምተወው እያለች ያደረገችውን ነገር ሁሉ ነገረችው....
ብዙ ነገር አድርገሽ ሊሆን ይችላል ግን ሁሉንም ያደረግሽው
ለክፋ ነገር ነው ደግሞ ሰሚራን ብትገድያት ምንም የምታገኝው
ነገር የለም እንደውም በተቃራኒው የህሊናሽ ወቀሳ ነው
የምታተርፊው መቼም ሰላም አታገኝም አላህ አንድን ነገር
ሲያደርግ ያለ ምክንያት አያደርግም ምን አልባት እናትሽ በሂወት
ብትኖር ኖሮ ዛሬ እዚህ መግባት አትቺይም ነበር ለምን ልትይኚ
ይሆናል አንቺ አሁን እንደዚ ትምህርትሽ ላይ ጠንክረሽ
የምትማሪው አንደኛው ምክንያት ሰሚራን ለመጉዳት ነው ግን
አንቺ ለክፋት አስበሽ ቢሆንም የተማርሽው ግን አንቺን ነው
የሚጠቅመው እናትሽ ብትኖር ግን እንደ አሁኑ ወጤታማ ላትሆኝ
ይችል ነበር
እያለ ብዙ ከመከራት በኃላ ውሳኔው የ አንቺ ነው
እሺ አስብበታለሁ ስለምክርህ እና አብረኃኝ ስለሆነክ
አመሰግናለሁ ብላው ሄደች ቀኑ ሀሙስ ነበር አርብ ቀን ነው
ሀሊማ ወደ ቤቷ የምትሄደው ቀኑን እንዲሁ ሁሉም ሲጨነቁ
ሲያስቡ አለፈ አርብ ጠዋት ሀሊማ ከድር ጋር ደውላ ሰላምታ
ከተለዋወጡ በኃላ
... ባባ ዛሬ ብቻዬን አይደለም የምመጣው ላሳውቅህ ብዪ ነው
ከድርም እሺ ብሎ ስልኩን ዘግቶ ሰሚራ ጋር ደውሎ ነገራት
ሀሊማ ለሳሊም ደውላለት አብሯት እንዲሄድ ለምናው እሺ አላት
ከጁምአ በኃላ እንገናኝ ብላ ስልኩን ዘጋችው ሀሊማ በጣም
ፈርታለች ጁምአ ሰግዳ ከሳሊም ጋር ተደዋውለው ወደ ሀሊማ
ቤት ሄዱ ሲደርሱ አንኳኩ ሰሚራ በሩን ከፍታ ወደ ውስጥ
እንዲገቡ ጋበዘቻቸው ሁለቱም ወደ ሳሎን ቤት ገቡ ሀሊማ እቤት
ስትደርስ ለ ከድር ደውላ እቤት እንዲመጣ እና ሰው
ልታስተዋውቀው እንደሆነ ነግራው ስልኩ ተዘጋ ብዙም ሳይቆይ
ከድር እቤት ደረሰ ምግብ ቀርቦ ሁሉም አብረው ተመገብ ሰሚራ
እና ሀሊማ እቃዎቹን አነሳስተው መጨዋወት ጀመሩ ትንሽ
አንደተጨዋወቱ ሀሊማ አንዴ በቅድሚያ እንግዳዬን
ለስተዋውቃቹ ሳሊም ይባላል ልክ እንደ ሴት ጓደኛዬ ነው እና
ለምን ይዤው እንደመጣሁ በኃላ አነግራችኃለሁ ዛሬ
የማውቀውን ልነግራቹ እና አፋ እንድንባባል ነው አለች ሰሚራ
እና ከድር ግራ ገብቷቸው ሀሊማ የምትለውን ነገረ ማዳመጥ
ጀመሩ ሀሊማ ያየችውን የሰማችውን ነገር አንድ በአንድ
ነገረቻቸው ሰሚራ የምትገባበት አጣች ከድርም በጣም ደንግጦ
ባለበት ደርቆ ቀረ እስከዛሬ አታውቀውም ብለው የሚያስቡትን
ነገር እያወቀች ዝም ማለቷ ከድርን አሸመቀቀው ሳሊም በተራው
መናገር ጀመረ ያለፈውን ረስታቹ ይቅር ተባብለቹ በሰላም ኑሩ
ብሎ ዝም አለ ሁሉም ዝም አሉ ሰሚራ ለሀሊማ አፉ በይኝ ይሄን
ሁሉ ነገር እያወቅሽ አብረሽኝ እንዴት ኖርሽ ከበደልም በላይ
በድዬሻለሁ አፉ በይኝ ከድርም አፉ በይኝ ብሎ በፀፀት ጠየቃት
ሀሊማ ሁለታችሁንም አፋ ብያቸዋለሁ ሁሉም ተቃቅፈው አለቀሱ
ሳሊምን ይዤው የመጣሁት እንድታመሰግኑልኝ ነው እንደዚህ
የመሆኑ ምክንያት እሱ ነው ብላ ተናገረች.......ቀኑ በ
ደስታ አሳለፋት ሊመሽ አካባቢ ሳሊም ወደ ቤቱ ሄደ በነጋታው
በዘይነባ ስም ሰደቃ አድርገው ለሚስኪኖች አከፋፈሉ........
ከ 15 ቀናት በኃላ ከድር እና ሰሚራ አነስ ባለ ዝግጅት ኒካ አሰሩ
ሳሊም እና ሀሊማም ከድር እና ሰሚራ ኒካ ባሰሩ በሳምንቱ አነሱ
ኒካ አሰሩ ሁለቱም ከተመረቁ በኃላ ተጋብተው አብረው መኖር
ጀመሩ ፡፡ እነሱ ሲጀምሩ እኔ እዚህ ላያ ጨረስኩ🙏፡፡

ይህንን ታሪክ ያነበባቹ በሙሉ ከዚህ እንደምትማሩ ተስፋ አደርጋለው፡፡

. . . ህይወት ይቀጥላል . . .


............ ተ ፈ ፀ መ..............

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
📖📖📖📖📖
‍ ​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​❤️ ፍቅር ሲፈርድ 📕

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል 1⃣5⃣



#እውነተኛ አሳዛኝና አስተማሪ ታሪክ


#የመጨረሻው ክፍል


በጩቤ ስትወጋ ተዘረረች ይሄኔ የነሳራ ግቢ ተከራዮች ይመለከቱ ስለነበር በጩኸት ሰፈሩን አደበላለቁት ሁሉም ከዛ የሳራ እንጀራ እናት ለማምለጥ ስትሞክር ባካባቢው የነበሩ ሰዎች ያዟት ወደጣብያም ተወሰደች ... ሰው በመግደል ሙከራ ተከሳ ወደ ማረፍያ ቤት ተላከች... ለምለምንም ወደሀኪም ቤት ከወሰዷት ቡሃላ ለልኡል አባት ደወሉለት የልኡል አባት ደግሞ ብዙነህ ጋር ደውሎ እሱ ከባህርዳር እስኪመለስ ለምለም ጋር እንዲቆይለት ጠየቀው ብዙነህ ኧረ ችግር የለውም ሲል የለምለምን ክፋትና በደል እረስቶት ነበር ...

ብዙነህ ለምለም የገባችበት ሆስፒታል ደርሶ ቀጥታ ወደ ድንገተኛ ክፍል አመራ በሩ ላይም ራሄል ልጇን አቅፋ ታለቅሳለች ብዙነህም አይቷት አለቃሽ በመታመሟ ነው እንዲ እምባሽ የሚዘምበው አላት ቡዜ እስቲ ዛሬ እንኳ ላሳዝንክ እኔኮ የልጅህ እናት ነኝ አለችው እሱም ትቷት ለምለም ጋር ሊገባ ሲል ዶክተሮቹ ብዙ ደም ስለፈሰሳት ባፋጣኝ ሌላ ሀኪም ቤት ሄዳ መታከም አለባት ብለው ሪፈር ፃፉላት ብዙነህም ለልኡል አባት ሁኔታውን አስረድቶ ወደ የካቲት ሆስፒታል ተወሰደችና አልጋ ያዘች ብዙነህና ራሄል ውጪ ቆመው ሳለ እሺ ለምን ነበር የምታለቅሽው አላት ራሄልም ልጇን በስስት እያየች ወ/ሮ ለምለም ልጄ የልጇ እንዳልሆነ አወቀች እናም አይንሽን እንዳላይሽ አለችኝ ማንም ምንም እንደሌለኝ እያወቀች ...ስትል ድሮስ እውነት ተደብቆ የሚቀር ይመስልሻል ራሄል አሁንም ልምከርሽ ከጥፋትሽ ተመለሽ ውሸት ይብቃ ተመልከች ሁሉም የስራውን...ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ የልኡል አባት ደወለና ስንት ቁጥር ናቹ አለ ብዙነህም ያሉበትን ነገረው...

ልክ ወደ ክፍሉ ሲሄዱ ራሄል ደንግጣ ቆመች ብዙነህም ድንጋጤዋ አስደንግጦት ምን እንዳየች ለማየት አይኗን ተከትሎ ዞረ ይሄኔ እሱም ተገረመ ሳራና ልኡል ከልኡል አባት ፊት ፊት ይሮጣሉ ብዙነህ በደስታ ሰከረ እሩጦ ሁለቱም ላይ ተጠመጠመ ምንድን ነው የማየው በፈጣሪ እውነት ነው ግን እያለ ሁለቱንም በየተራ ሳማቸው የመጡበትን ጉዳይ ለትንሽ ደቂቃ እረሱትና በብዙነህ ሁኔታ እንባቸው ፈሰሰ ከዛም የልኡል አባት ናልጄ በቃቹ እናትህን እንይ አለ ... ብዙነህም ውስጥ ዶክተሮቹ ስላሉ ሲወጡ እንገባለን አለ ሁሉም መንቆራጠጥ ጀመሩ ...

በመሀልም ሳራ ግንኮ አልገባኝም ወይዘሮ ለምለምን ማን ሊወጋት ይችላል አለች ሁሉም ቀጥ ብለው ወደሷ ተመለከቱ ልኡልና ሳራ በርግጥም አላወቁም ነበር ... አብረው የመጡት እማማ ሳራን እያረጋጉና በቀን በቀን ቤተክርስትያን እየሄደች እንድትፀልይ አድርገው ወደራሷ ሲመልሷት ሳሚ ደግሞ ልኡል የተኛበት ሆስፒታል ድረስ ሄዶ ያኔ ባለማወቅ ስለሚያፈቅራት ብቻ እንደዛ እንዳለና እሷ ግን ካንተ ውጪ ማንንም አታፈቅርም ባለማወቅ ለዚ ስለዳረኳቹ ይቅርታ በማለት ልኡል በድጋሚ ከሳራ እንዲገናኙ አድርጎ ልክ የልኡል አባት ልኡልን ይዘው እነሳራ ቤት ደርሰው ልኡልና ሳራ ሲተቃቀፉ ነበር ለምለም ተጎድታለች ተብሎ ለልኡል አባት የተደወለው...

ዶክተሩ ወቶ የለምለም ቤተሰቦች አለ ሁሉም አቤት አሉ ወደዶክተሩ እየተጠጉ ለምለም ከፍተኛ ደም ስለፈሰሳት ደም የሚለግስ ሰው ያስፈልጋል ከመሀላቹ ሲባል በቅድሚያ ባሏ ገባ ግን ባልየው መስጠት አይችልም ምክንያቱ ደግሞ የደም ታይፓቸው አንድ አይደለም ቀጥሎ ልኡል ገባ ልኡል ደግሞ ሙሉ ጤነኛ ባለመሆኑ እንደማይችል ነገሩት ብዙነህ እኔ እሰጣለው በቃ ብሎ ሲገባ የሱም እንደማይሄን ተነገራቸው ይሄኔ የልኡል አባት ዘመድ ጋር ለመደወል ስልካቸውን ሲያነሱ ሳራ እኔ አለው አለች ሁሉም ደነገጡ ያን ሁሉ በደል ያሳለፈች ሴት እንዴት ዛሬ ለበደለቻትና ህይወቷን ላበላሸች ሴት ደም እለግሳለው ትላለች እውነትም ሳራ እንቺን ያገኘሽ ልጄ ፈጣሪ ልቡን አይቶ ነው ተባረኪ አላት አጋጣሚ ደግሞ የሳራና የለምለም ደም ተመሳሳይ ነበርና ዶክተሮቹ ከሳራ ደም ወስደው ለለምለም ተኩላት ለምለም ስትነቃ ካጠገቧ የተኛችውን ሴት ሳራን ተመለከተች ለምን ከጎኗ እንደተኛች ለማወቅ ግዜ አልፈጀባትም ...

ለምለም መቃብሯን የቆፈረችላት ሴት ዛሬ ህይወቷን ስታድናት ከማየት በላይ ምን አለ ፀፀት ውስጧን አሰቃየው በተንጋለለችበት እምባዋ ቁልቁል ወደጆሮዋ ፈሰሰ... ለምለም ድና ስትወጣ በቅድሚያ ሳራንና ልጇን ድል ባለ ሰርግ ለመዳር መዘጋጀት ጀመረች ባሏንም ለልኡል አባቱ እንዳልሆንክ ይነገረው ስትል የልኡል አባት ግን በፍፁም አለ ልጄ የኔ እንደሆነ ይቀጥላል እስከዛሬ ያልተነገረውን ዛሬ መናገር የለብንም አለ ለምለምም በቃ አንተ እንዳልክ አለች ...

ለምለም ጠበቃ ቀጥራ የሳራን እናት በመግደል ወንጀል ከሰሰቻት ሳራም የአባቷን ሀብት ይገባሻል ሲባል ተፈረደላት ከብዙ ምርመራ ቡሃላም በለምለም ጥረት የሳራ እንጀራ እናት እድሜ ልክ እስራት ተፈረደባት ልኡልና ሳራም ድል ባለ ሰርግ እንዳዲስ ተጋቡ ...እማማም ባህር ዳርን አለቅም ብለው የነበረ ቢሆንም በሳራ ልፋት የአባቷን ቤት ሰታቸው መኖራቸውን ቀጠሉ ለምለምም ካሳ ይሁነኝ ስትል ጥሩ ቤትና መኪና ገዝታ ለሳራና ለልኡል ስጦታ ሰጠቻቸው ... የልኡል አባትም አሜሪካ ከመመለሳቸው በፊት ፍቅር ያሸንፋል ሲሉ ራሄልን አፈላልገው ከብዙነህ ጋር በማስታረቅ ለልጃቸውም ሲባል አብረው እንዲኖሩ አደረጉ ... ደስታ በየቤቱ ገባ ........

..................ተፈፀመ....................

ፍ ቅ ር ሲ ፈ ር ድ



#ይህ ነው ፍቅር ሲፈርድ ❤️😘

አብራችሁን በመሆን ሀሳብ አስተያየት እንዲሁም መስተካከል ያለባቸውን ነገሮች ለነገራችሁን ..
የተለያዩ አስተማሪ ታሪኮችን በመልቀቅ አብራችሁን ለሆናችሁ..
በእውነት በቻናላችን ስም🙏

የቀረ ሀሳብ ካላቹ 👉 @Eyos18

እ ና መ ሠ ግ ና ለ ን

❤️ ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
📖📖📖📖📖
🍁 መውደድ 😘

#የመጨረሻው ክፍል

#ክፍል 22🔥


...መሆን ስትፈልግ ብዙ ገፅታዎች ይኖሩሀል...ማስመሰልን ከመኖር በላይ እጅግ የበዙ ባህሪያቶችን ትላበሳለህ...ሰይጣን ስትሆን ደግሞ ከዛም በላይ......

...እስካሁን ምንም አይነት ቃል አላወጣችም....በዝም ተቀመጥታ ፀበሉ በአናቷ ቁልቁል እየወረደ ነው....አባ ወደ ሴቶቹ መጥመቂያ ክፍል ገብተው ከአጠገቧ ቆመው መስቀላቸውን ጭንቅላቷ ላይ አስቀመጡት....ቀስ በቀስ አፏ ሲላቀቅ ይታያል... መላ ሰውነቷን በመስቀሉ ሲዳስሱት አስደንጋጭ ጩኸቷን ለቀቀችው..... ፀበሉ ውስጥ የነበሩት ሰዎች ስላላሰቡት ነው ተደነጋገጡ....

..."ተው እባክህ" ምንም አይነት እንቅስቃሴ አታደርግም ግን መማፀን ጀመረች....
"አንተ ማነህ...እንዴት ገባህ...." አባ ብዙ ጥያቄዎችን አከታትለው ጠየቋት.... አልመለሰችም።.... በተደጋጋሚ በመስቀሉ እየዳሰሷት በደንብ ያጠምቋት ነበር.....
ከደቂቃዎች ቦኋላ ቀጥ ብለው ቆመች።... አባ አልጠየቋትም በራሷ መናገር ጀመረች.....

"እኛ እንወደው ነበር ...በጣም ነው የምንወደው እሱ ግን ያሸሸናል እንዴት ብለን ስንለው መልስ የለውም...በቃ ይኸው ለዚህ ህይወት ዳርገነዋል... በቃ ገብቶ የማይወጣበት ህይወት ውስጥ ጨምረነዋል አለቀ...የራሱ መዘዝ ነው...." በውስጧ ያለው መንፈስ መናገር ጀመረ....
"ስንት ናችሁ ?...ምንድነው ያደረጋችሁት?" አባ ልጅቷ ከፀበሉ አምልጣ ለመውጣት ስትታገል እየመለሷት ጠየቋት....
"ብዙ ነን ...ቤተሰብ ነን እኮ...ተባብረን ነው በውስጡ የምንኖረው... እሱ ግን አባታችን ከሌላ ስለወለደው እኛን አይወደንም... ጠላቶቹ እንመስለዋለን...በቃ አቃጠለን ተቃጠልን....እሱ ላይ ድግምቱንም..መተቱንም ስንሰራ አይሳካም... ዘውትር የማርያምን ስም እየጠራ ያከሽፍብናል ...ያኔ እንቃጠላለን...ሀሳባችን መና ባዶ ይሆናል.....ብዙ አመት ለፋን ለፋን...አልሆነም ሲፈልገው ክንፍ ያለው መልዓክ ይልክብን እና ሊያስጨርሰን ይሞክራል...በፀሎቶቹ መሀል የቅዱስ ሚካኤልን ስም እየጠራ እኛን ያወድቀናል....ታድያ ከዚ በላይ በደል አለ ...አለ ወይ?" ልጅቷ እራሷን አይደለችም በውስጧ የሚያወራው መንፈስ ተቆጣጥሯታል....እዛው ያሉ ሰዎች ያመሰግናሉ አንዳንዶችም ያለቅሳሉ......
"ታድያ እዚች ልጅ ውስጥ እንዴት ገባችሁ....ሰውየውስ ምናችሁ ነው?" አባ የእመቤታችንን ስም እየጠሩ ይጠይቃሉ ....

"ከዛማ በቃ በሱ አልሳካ ሲለን...300,000 (ሶስት መቶ ሺ ብር) ከፍለን ሌላ መተት በልጁ በኩል አሰራንበት...የልጁን ድክመት ተጠቀምንበታ!!!.. ቀን አሳቢ ሰው አድርገን ለሊት ሲዳራ የሚያድር ጅብ አድርገን አስተበተብንበት....ከአይኑ ብሌን በላይ የሚንከባከባትን ልጁን አስጥለን ወደ ሌላ ቦታ እራሱን ቀይሮ እንዲኖር ፈረድንበት.....በቃ ይህ ሲሳካልን ለአመታት በውስጡ ቆይተናል ደስ ብሎናልም....አሁን ግን በቃን !!!በቃን....የማናውቀው ሀይል እየተፈታተነን ነው....ፍፁም ብርሀን ያለው ምትሃታዊ ሀይል እያስቸገረን ነው....ዘውትር በነጭ ድምቅ ብሎ ይታየናል በቃን ተቃጥለናል እኮ በቃን በቃን!!!!!" ልጅቷ ያለ ቅጥ መጮኽ ጀመረች....
ፀበሉ ውስጥ ያሉት ሰዎች እያለቀሱ ፈጣሪን ያመሰግናሉ....ልጅቷ ለደቂቃዎች ከጮኸች ቦኋላ ወደራሷ ተመለሰች....ሰው ሁሉ እልልልል እያለ ፈጣሪን አመሰገነ....አሳዳጊዋ መሬቱ ላይ ተደፍታ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች..... ልጅቷ ብሩህ የሆነ ነገር ታያት ሁሉም የፀዳ ያህል...የአባን መስቀል እያለቀሰች ተሳለመች። በፀበሉ የበሰበሰውን ልብሷን ለማድረቅ ከአሳዳጊዋ ጋር ፀሀይ ወዳለበት ቦታ ሄደው ተቀመጡ......

"እትይ አሁን ግን ጋሽዬ የት እንደሆኑ ማወቅ አንችልም?" አሳዳጊዋ አይኗን በነጠላዋ እየጠረገች ጠየቀቻት...
"አላውቅም እናት ጥሎኝ ከሄደ እኮ ቆይቷል" እየተንቀጠቀጠች መለሰችላት....
"ተይ እትይ እንዲህ አትበይ ወደው አይደለም እሳቸውስ ....ምን ያድርጉት? ፍርጃ ነውኮ" የለፈለፈችውን በሙሉ እንባዋ እየፈሰሰ ነገረቻት....
ልጅቷ መለፍለፏ ቢታወቃትም ግን ምን እንደሆነ ስለማታውቅ ስትሰማ ከእስካሁኑ በበለጠ ሁኔታ ተንሰቀሰቀች.......
"አባዬ ይቅርታ" ድምጿ ተዘግቷል ወደ ሰማይ እያየች ፈጣሪን አመሰገነችው.....
"እናት ግን ሌላም ነገር እየጨነቀኝ ነው" አሳዳጊዋ ላይ አንገቷን ዘመም አድርጋ ጋደም አለች
"ምንድነው እሱ?" ደንገጥ ብላ ጠየቀቻት
"ናቲ...ናቲን አፍቅሬዋለሁ" ፈራ እያለች ነገረቻት...
"እሱ ያለው ይሆናል" ጭንቅላቷን በእናታዊ መውደድ ዳበሰቻት

...."ከጠበቅነው በላይ ነው። ቤቱ ውስጥ ለውስጥ ብዙ ቦታዎች አሉት እንዳጣራነው ከሆነም አብዛኛውን ጊዜ እዚህ ቤት ምሽት ምሽት ብቻ ነው የሚመጣው...ዛሬ ሀይል አጠናክረን እዛው ሌቱን የምናሳልፍ ይሆናል" ጠረጴዛውን ከበው ከተቀመጡት ፖሊሶች መሀል አንዱ ተናገረ.....
"በጣም ጥሩ ... ወርቄ የተባለችው ታካሚ ጉዳይ ግን በእርግጠኝነት የደረስኩበት ይመስለኛል.... ልጅቷ የሰው ጅብ ናት...በአይኔ ነው እግሯ ሲለወጥ ያየሁት...." ሴቷ ፖሊስ አይኖቿን ሌሎቹ ላይ እያንከራተተች ተናገረች....
"አይ የማይመስል ነገር አታውሪ ...የሰው ጅብ የሚባል ነገር አፈታሪክ ላይ የቀረ ነገር ነው....ድሮ ተረት ተረት ላይ በዛ ላይ ይችን የመሰለች ቆንጆ?? አይ አይሆንም እርግጠኝነትሽን አስተካክይ" ሌላኛው ፖሊስ እሷ ላይ እያፈጠጠ መለሰላት....
"ይቅርታ ከርዕሳችንም ሆነ ከደንባችን እያለፍክ ነው...ስለ ልጅቷ ውበት የሚመለከተን ነገር የለም ዋናው ጉዳያችን ተፈፀመባት ከተባለው ወንጀል ጋር እና ዶክተር ቅድምያ ጅብ ነው ያየሁት ብሎ ከሰጠን ቃል ጋር ነው። ተግባባን " ተኮሰታትራ መለሰች.....
"በእርግጥ ልክ ነሽ" ለራሱ በሚሰማ መልኩ አንገቱን አቀርቅሮ መለሰ....
ለደቂቃዎች ሲከራከሩ ቆይተው በአንድ ሀሳብ ተስማምተው ተለያዩ......

✧✥✤ ✧✥✤ ✧✥✤ ✧✥✤ ✧✥✤ ✧✥✤

....ሲመሽ ወርቄ ትዝ ትለዋለች...በእርግጥ ዘውትር ከሀሳቡ ጠፍታ አታውቅም.... መውደዱ እሷ ናትና ሊዘነጋት አይችልም.... ዛሬም ከቦታው ቢቆምም ሊያገኛት አልቻለም...ጅብም ብትሆን አፍቅሯታል....መውደድ ሲገዝም ምንነት አይታሰብም...በመውደድ ልክ ማፍቀር ሲኖር በመውደድ ልክ ጥላቻም ይገዝፋል...መውደድ አያመዛዝንም....ጅቧን ወርቄም አፍቅሯታል.....ብዙ ጠብቆ አላገኛትም....ከዚስ ቦኋላ? እራሱን ይጠይቃል...አላገኛትም እራሱ ይመልሳል.....

✧✥✤ ✧✥✤ ✧✥✤ ✧✥✤

....ፍፁም የሆነ ሰላም በውስጡ እያንሰራራ ነው... ከየት እንደመጣ ሳያውቀው ውስጡ በሀሴት እየተጥለቀለቀ ነው....ያውቀዋል አክሊሉ ይህ ስሜት ሊሰማው የሚችለው ጅብ ሲሆን ብቻ ነው...ዛሬ ግን ሰዓቱ ሳይደርስም ደስ ብሎታል ...ምን የተለወጠ ነገር እንዳለም ግራ እስኪገባው ድረስ ስሜቱ ተቀይሯል.....ሰዓቱን ተመለከተ.... ለምሽትነቱ ጥቂት ሰዓታት ቀርተውታል....አክሊሉ ዛሬም ሙከራውን አላቋረጠም። ሆዱን ሊበጣጥስ የሚችል ማላታይን በብልቃጥ ይዟል.... ዛሬን ባይተርፍ ምኞቱ ነው ....ይህ ህይወት መሮታል...በቅድሚያ ለሰዓታት ብሎ የተከራየውን የሆቴል ክፍል ውስጥ ሻወር መውሰድ ፈለገ... ሰዓቱ ደርሶ ከመለወጡ በፊት
💥💥ሐኑን💥💥

#የመጨረሻው ክፍል1⃣5⃣

#ፀሀፊ፦አሌክስ አብርሀም

ከራሱ ከናዳው መሃል ነበር መፍትሄውን ያገኘሁት።
አንዱ ሞኝ ናዳ መጣብህ ሲሉ "ተከናንቢያለሁ" አለ አሉ ካሉት ተረት! ለእኔ እንደዚህ “ሞኝ” እንደተባለ ሰው ብልህ ሆኖ ያገኘሁት ፍጥረት የለም፡፡ የሕይወት ግብግብ ዓላማው፣ ከሞት መዳን አይደለም። ሰው ፈጠነም ዘገየም እንድ ቀን የሞት ዕጣ የሚወድቅበት ፍጡር ነው፡፡ በዚህ የማይቀር ዕጣ ከናዳ ያድነኛል ብለን የምንለብሰው ከንብንብ፣ ማኅበረሰቡ የብረት መዝጊያ፣ ቅብርጥስ የሚለው ትዳር አይደለም፣ ትምህርት
እይደለም፣ ሥልጣን ቤተሰብ አይደለም፤ ሳያድንም ያድነኛል የሚል እምነት ተከናንቦ ሞትን እንደመጠበቅ ውብ ነገር የለም ፡፡ ያ እምነት ፍቅር ይባላል … ! ሐኑንን ሃብታም ቤተሰብ ከሕይወት ናዳ አልታደጋትም፡፡ እኔን ድል ባለ ሰርግ የተመሠረተው ትዳር ከሐሜት ናዳ አልታደገኝም ያንን ኢዮብ የሚባል ቦዘኔ፡ የዓመታት የድብድብ ታሪኩና ጡንቻው ከእኔ የቁጣ ናዳ አላዳነውም፡፡ ብቸኛው ታዳጊ፣ እንደክንብንብ ስስ የሆነው
በልባችን ያለው ፍቅር ብቻ ነው፡፡ እናም ወሰንኩ፡፡ ለየትኛውም የማኅበረሰብ እንቶፈንቶ የይሉኝታ ሕግ አልኖርም፤ማን ለኔ ኖረ? ቀሪ ዘመኔን ከናዳው ባያተርፈኝም እንኳን፣ የፍቅር ከንብንቤ ውስጥ ብቻ አሳልፋለሁ! ያ ክንብንብ ደግሞ የት እንዳለ ጠንቅቄ አውቃለሁ እንዴት እንደምለብሰውም ጭምር !!

ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት ሄድኩና አለቃዬን እንዲህ አልኩት "ቅያሬ እፈልጋለሁ፤ወደ ክፍለ ሐገር ወደ ባህር ዳር ፣ እባክህ ተባበረኝ..."

“ከአዲስ አበባ ወደባህር ዳር!"

“ማንም እንዲህ ዓይነት ዝውውር ጠይቆ አያውቅም፡፡ እዚያ ያሉት ይኼን ቢሰሙ እልል በቅምጤ ነው የሚሉት። በማንኛውም ሰዓት ይቀይሩሃል፡፡ ጠረጴዛዬን ያጣበበው ማመልከቻ ከከፍለ ሐገር ወደ አዲስ አበባ ቀይሩን የሚል ጥያቄ ነው፡፡ ከፈለግህ ብዙም ከባድ እይደለም ልንልክህ እንችላለን..."

ቀጥሎ አብሮኝ ወደ ተማረና የግል ቢሮ ወደከፈተ ጠበቃ ጓደኛዬ ጋ ሄድኩ፡፡ እናም "ፍቺ እፈልጋለሁ” አልኩት፡፡ …ሰርጌ ላይ ልቡ እስኪፈርስ የጨፈረ ነውና፣ ይሉኝታ
ይዞት የወጉን ምክር አደረሰ፡፡ ትንሽ ብትታገስ፣ ብትነጋገሩ፣ እንኳን ባልና ሚስት ምንትስ ይጋጫል …' እንደ ጠጠር የሚፈናጠሩ የምከር ናዳዎቹን እንደዝንብ ከፊቴ እሽ ብዬ የፍቺ ወረቀት አስጻፍኩ፡፡ ገና በቅጡ ሁለት ዓመት ያልሞላው በሽተኛ ትዳሬን፣ ሙሉ ዘመኔን እንደ ጋንግሪን ከመበከሉ በፊት፣ ቆርጨ ለመጣል ወሰንኩ፡፡ የፍቺ ማመልከቻዬን ይዤ ሄድኩት ወደ ሐኑን ነበር…ወደ ከንብንቤ፡፡ ፊት ለፊቷ ተቀመጥኩና ውብ ፊቷን… ንጹሕ ዓይኖቿን ትክ ብዬ አየኋቸው፡፡ አፍራ አቀረቀረች: “ሐኑን እይኝ ቀና ብለሽ እይኝ
አፈቅርሻለሁ! መጀመሪያ ቡና ልታደርሽልኝ ወደቤቴ ከመጣሽበት ቀን ጀምሮ፣ እስካሁን ልቤ ላይ ያለሽው አንቺ ብቻ ነሽ፡፡ ከሔራን ጋር ተኝቼ የማስበው አንቺን ነበር ሰርጌ ውብ ነበር፤ ብቸኛው ችግር ከጎኔ የነበረው ቪሎ ውስጥ አንቺ
አለመኖርሽ ብቻ ነበር፡፡ ሳገባ ከጎኔ ቬሎ የምትጎትተው ሴት ጥፋት፣ አንድ ብቻ ነበር፣አንቺን አለመሆኗ!"

ሔራንን ለመፍታት ወስኛለሁ፡፡ቀሪ ዘመኔን ሁሉ አንቺ ጋር መኖር ነው ፍላጎቴ፡፡ይኼን ከተማ እንለቃለን ባህር ዳር ወደሚባል ከተማ እንሄዳለን፡፡ እዚያ የዘንባባ ዛፎች አሉ፤ ባይኖሩም ግድ አይሰጠኝም፡፡ በዚያ ከዓመት እስከ ዓመት የማይነጥፍ ውሃ አለ፣ ባይኖርም ግድ አይሰጠኝም፡፡ በዚያ እንደ ናዳ ቁልቁል የሚወርድ ፏፏቴ አለ አብረን እንሄዳለን፣ አብረን እንኖራለን፡፡ ይኼ የማንንም ሠልጥኛለሁ ባይ የውሸት በራስ መተማመን፣ ከአፈር የቀላቀለ ውብ ፊትሽን በየቀኑ አያዋለሁ። ልክ እንደዚህ ዓይነት ውብ ፊት ያላቸው ልጆች እንወልዳለን፡፡ በዘንባባዎቹ ስር ድክ ድክ ይላሉ፣ በደፈረሰው ውሃ ይንቦራጨቃሉ… ስለወሰንኩ አትፍሪ፡፡ትዳር ብዬ ለገባሁበት ነገር መፍረስ፣ የአንቺ እጅ የለበትም። ካለበትም እንኳን ኖረበት፡፡ ካገባሁ በኋላ እንዳልነካሁሽ አንቺ ምስክር ነሽ፡፡ ለትዳሬም ታማኝ እንደነበርኩ፣ አንቺ ብቻ ምስክር ነሽ በእኔና አንቺ መኻል እውነት አለ።

ልታምኝኝ የምትችይ ሴት አንቺ ብቻ ነሽ ነፍሴ ከሚያምናት ልብ ሥር እንጅ ከሚያስገድዳት ክንድ ሥር መንበርከክ አታውቅበትም! የሌለሽበትን አንችን ለመከላከል ሲፍገመገሙ፣ የራሳቸውን ሚዛን መጠበቅ አቅቷቸው ለወደቁ ሁሉ አንዳችም ጸጸት እንዳይሰማሽ፤ አፈቅርሻለሁ! ሰው መስለውኝ ይሄን እውነት ሰውቸላቸው ነበር፤
አይገባቸውም!!

ሐኑን እንባዋ በጉንጫ ላይ እየወረደ ዝም ብላ ስታዳምጠኝ ቆየችና "ለመጨረሻ ጊዜ ስልክ ከዘጋሁብህ በኋላ ይኼን ሁሉ ጊዜ አንተን እያሰብኩ የታመምኩትን አላህ ነው የሚያውቀው፡፡አንተ ከወጣህ በኋላ ስንት ሌሊት በመስኮቴ ቆሜ፣ ባዶውን ወደ ተቀመጠዉ ቤትህ እንዳፈጠጥኩ አነጋሁ፡ እንደምወድህ ለማንም አልተናገርኩም፣ማንስ
ይሰማኛል? አባባ ሊሞት ሲያጣጥር ወደ ጆሮዎቹ ተጠግቼ እንደምወድህ ነገርኩት፡፡ ይስማኝ አይስማኝ እኔንጃ: አባባ አንድ ነገር ሲሆን፣ አንተን ፍለጋ የትም እንደምሄድ ነገርኩት፡፡አፉ በላኝ አልኩት ወንድሞቼ ባያባርሩኝም አተን ፍለጋ መምጣቴ አይቀርም ነበር፡፡ ልቤን እፈራው ነበር፣እንድ የስልክ ጥሪህ አባባን ጥየው እንድመጣ ሊያደርገኝ
ይችላል ብየ እፈራ ነበር ከድምፅህ ሸሸሁ! በዚህ ሁሉ አስቀያሚ ውጥንቅጥ ውስጥ እረጅና ተረጅ ሆነን የተቀመጥኩት እጅህን ከማየው በላይ፣ ዓይንህን በየቀኑ ለማየት ነው ትናፍቀኛለህ ፡አሁን እዚህ ተቀምጠህ እንካ ትናፍቀኛለህ…እወድሃለሁ"

አውቃለሁ ሁሉንም ነገር ቶሎ ጨርሼ እንሄዳለን፣ እንጋባለን”

“ኢንሻ አላህ!"

"ኢንሻ አላህ!"

በተጠቀለለ የፍቺ ማመልከቻዬ፣ ታፋዩን እየተመተምኩ ወደ መኪናዬ ስሄድ ዞር ብዬ ተመለከትኩ ሐኑን፡ የእኔ ውብ መልዓክ በሩን ተደግፋ ከኋላዬ ትመለከተኛለች፡፡ዓይኖቿ ውስጥ ስስት አለ፡፡ ይሄን ስስት ከዚህ በፊት በዘመኔ ያየሁት እናቴ ዓይኖች ውስጥ ብቻ ነበር፡፡ ፈገግ አልኩላት ፈገግ አለች! ፈገግታዋ ውስጥ እርካታ ከነ ሙሉ ክብሩ ነግሷል፡፡ በብልጣብልጥነት አልታገለችም፤ ያደረገችው ብቸኛ ነገር ማፍቀር ነበር፡፡ ማፍቀርና ዝም ማለት፤ፍቅርና ዝምታ መለኮታዊ ኃይሎች ናቸዉ ፈጣሪን
የምንፈራዉ ከተከታዮቹ ብዙ ጩኸት ይልቅ በጥልቅ ዝምታዉ ሳይሆን አይቀርም…እናም በዝምታ ግርማ ሞገስ ዉስጥ ባለ እዉነተኛ ፍቅር፡፡ዝምታን የሚያሸንፍ ጩኸት፣ ፍቅርንም የሚያንበረከክ ብልጣ ብልጥነት የለም፡፡ በዝምታ አፈቀረችኝ፣ እናም መላው
ዩኒቨርስ ዝምታ ከጎኗ ቆመ፡፡ አሁን የፈለገው ናዳ ይውረድ ተከናንቢያለሁ!! ተረታቸው ወደ ፊት ከሚያወርዱብኝ ናዳ ሥር ተከናንቤ ለምቆም እኔ'፣ የአሽሙር
ቀብድ ነው!!
.
.
.
💎💎🔥ተፈፀመ🔥💎💎

🙏ከኛጋ ስለነበራቹ ምስጋናችን ከልብ❤️
ነው በሌላ አዲስ ታሪክ እንገኛለን 🙏

🔔ግሩፑን ለማግኘት
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha

ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
‍ ​​🌹ሴና🩸

#የመጨረሻው ክፍል!

#ክፍል 3⃣7⃣

አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ ሴና🌺


. . . አይኔን ስገልጥ ነጭ ኮርኒስ ነው የታየኝ፡፡ አልጋ ላይ እንደተኛው ይሰማኛል፡፡ አንገቴን ወደ ጎን ዞር ሳደርግ አጠገቤ አንድ ነጭ ጋወን የለበሰ ሰው ቆሞ የአይዞሽ አሁን ደና ነሽ" አለኝ ግንባሬን በመዳፉ እየዳበሰ፡፡ የተኛውት የሀኪም ቤት ክፍል ውስጥ እንደሆነ ገባኝ፡፡ ወዲያው የክፍሉ በር ተከፍቶ እነ ሚጣ ተከታትለው ገቡ፡፡ "አሁን እንዴት ነሽ?" እያሉ ጥያቄ ያከታትሉብኝ ጀመር፡፡ "አሁን ደና ስለሆነች ይዛቹሀት መሄድ ትችላላቹ ፡፡ትንሽ ድንጋጤው እንጂ ሌላ ምንም ችግር የለባትም" አለ ባለ ነጭ ጋወኑ ሀኪም፡፡ እነ ሚጣ ደግፈው ከአልጋ ካወረዱኝ ብሀላ ጫማዬን አድርገውልኝ ከተኛውበት ክፍል ይዘውኝ ወጡ፡፡
ከክፍሉ ስወጣ ከግቢ ውጪ ያለ ሀኪም ቤት እንደነበርኩ ገባኝ፡፡ አይኔ ያነባል፡፡ እነ ሚጣ አይዞሽ ይሉኛል ፣ ጥያቄ ይጠይቁኛል ፣ማብራሪያ ይሰጡኛል ፣ሊያረጋጉኝ ይሞክራሉ፡፡ እኔ ግን ማልቀሴን አላቆምኩም፡፡ ከሀኪም ቤቱ በር ላይ ስደርስ ያየውት ግራ ገባኝ ፡፡ የወንድሜ መኪና ቆሞአል፡፡ እንዴት እንደሰማ ግራ ገባኝ፡፡ "ቆይ ውስጥ ነው ይመጣል"አለችኝ ሚጣ በቀኝ በኩል ደግፋኝ እንደቆመች፡፡ እንዴት መጣ? ማን ነገረው? ቆይ እኔ እንዴት እዚ መጣው?' ጠየኳት ሚጣን እንባዬ አሁንም እንደወረደ ነው፡፡ ድምፄ ጉንፋን እንደያዘው ሰው ተዘግቶአል፡፡ "ቆይ ሁሉንም እናውራለን፡፡ አሁን ተረጋጊ"አለችኝ ሚጣ ጉንጬ ላይ የወረደውን እንባዬን በሹራቧ ጫፍ እየጠረገች፡፡ በዚ መሀል ወንድሜ መጣ "አይዞሽ ምንም አልሆንሽም"ብሎ አቀፈኝ፡፡ ጥያቄ ሆነብኝ፡፡ ወዲያው የመኪናውን ሁዋላ በር ከከፈተልኝ ብሀላ ወደ ውስጥ ገባው፡፡ ሚጣ ተከትላኝ ገባች፡፡ ሌሎቹ ከተሰናበቱኝ ቡሀላ ሄዱ፡፡
ወንድሜ ወኪናውን አስነስቶ መሄድ ሲጀምር 'ቆይ ምንድነው ነገሩ ግራ አጋባቹኝ እኮ 'አልኩኝ በደከመ ድምፅ፡፡ ማንም መልስ አልሰጠኝም፡፡ ወንድሜ መኪናውን እየነዳ ከከተማ ወጣ ወዳለ ቦታ ከወሰደን ብሀላ መኪናውን ከአንድ ሜዳማ ስፍራ አቁሞ ሞተሩን ካጠፋ ብሀላ ከመኪናው ወረደ፡፡ሚጣም ተከትላው ወረደች፡፡ ግራ ገባኝ እኔም ተከትያቸው ወረድኩኝ፡፡ ወንድሜ መኪናውን ተደግፎ ቆመ፡፡ ገና ከመኪና ከመውረዴ ሚጣ ማውራትጀመረች፡፡ "የውልሽ ሴና ያኔ ለ እረፍት ወደ ቤት የሄድን ሰአት ነበር ፍሬ በድንገተኛ አደጋ ያረፈው፡፡ እና የዛን እለት ላንቺ ይሄንን ልነግርሽ አስቤ ነገር ግን እንደዚ አይነት ነገር በስልክ ብነግርሽ ያለሽበት ሁኔታ ደሞ ጥሩ ባይሆን ይሄንን ስትሰሚ የሆነ ነገር ቢፈጠር ወይም የሆነ ነገር በራስሽ ላይ ብታደርሺ ብዬ ስለፈራው ለወንድምሽ ደወልኩለት፡፡ የሱን ስልክ ከየት አገኘሽው ካልሽኝ እኛ ግቢ ምትማረው የባልደረባችን ልጅ ያልሽኝ ከሷ ነው የተቀበልኩት፡፡ የሷን ስልክ ደሞ ያገኘውት እነሱ ዶርም የምትኖር ልጅ ጉዋደኛ እሱን ጠይቄ በሱ በኩል አድርጌ አፈላልጌ ነው፡፡ ያ አማራጭ ባይኖረኝ የዛኔ ቀጥታ ሀዋሳ ቤታቹ መጣ ነበር፡፡ ይሄንን አድርጌ ለወንድምሽ ደውዬ ሁሉንም ነገር ነገርኩት፡፡ የዛን እለት ወንድምሽ ሰበብ ፈልጎ ስልክሽን ተቀበለሽ፡፡ ያንን ያደረግነው ደሞ ከሌላ ሰው እንዳትገናኚ እና ከሌላ ሰው እንዳትሰሚው አስበን ነው፡፡"
ሚጣ ይሄንን ስትነግረኝ ወንድሜን እየተመለከትኩት ማንባቴን ቀጠልኩ፡፡ ሚጣ ቀጠለች፡፡ " . . .ለ ዴቭ ስትደውይለት አጠገቤ ነበር፡፡ ፍሬን እንዳላየው እና ሀዋሳ እንሆነ እንዲነግርሽ የነገርኩት እኔ ነበርኩኝ፡፡ ሰኞ ለምዝገባ መጥተሽ ምዝገባ አርብ ነው ሀሙስ እንመጣለን ያልኩሽ ግዜ እኔ ግቢ ነበርኩኝ፡፡ ሌሎቹም የዶርም ልጆች መጥተው ከተመዘገብን ብሀላ ወንድምሽ ንቺን ግቢ እንዳደረሰሽ በሌላ በር ገብቶ አንቺ መምጣት እንደማትችይ ነግሮ ግቢ ውስጥ በሚያውቀው ሰው አማካይነት እንድትመዘገቢ አደረግን፡፡ ከዛ እኔና የዶርም ልጆች እናንተ ቤት ነበርን፡፡ ምክንያቱም ሀሙስ ነው ምንመጣው ያልንሽ ብቻሽን እንድትሆኚ ነበር፡፡ ብቻሽን እንድትሆኚ ካደረግን ብሀላ ወንድምሽ ኪሩቤልን ላከው፡፡ ኪሩቤል በአጋጣሚ ካፌ ውስጥ የተዋወቅሽው ተማሪ ሳይሆን የስነልቦና ባለሙያ የሆነ የወንድምሽ ጉዋደኛ ነው፡፡ የፍሬ ስልክ ሲሙ የወጣው በዴቭ ስም ነው፡፡ስለዚ ፍሬ ሲያርፍ ዴቭ ሲሙን አውጥቶ ስለነበር በዛ ስልክ ሚደወሉ ጥሪዎችን በሙሉ ለፍሬ የተደወሉ ይሆናሉ ስለሚል አያነሳውም፡፡
እኔና ወንድምሽ ይሄንን ስናደርግ ሀሳቡ የኪሩቤል ነበር፡፡ እኛ ያሰብነው ፍሬን ቀስ በቀስ እንድትረሺው ነበር፡፡ ለዛ ነው ኪሩቤል ቢዚ ያደረገሽ፡፡ ያው ባልጠበቅነው መንገድ እውነቱን አወቅሽ እነጂ" ፡፡ሚጣ ይሄንን ሁሉ ስታወራ እኔ እያነባው በግርምት አዳምጣት ነበር፡፡ ወንድሜ መኪናውን እንደተደገፈ ቆሞ ያዳምጣት ነበር፡፡ ወደወንድሜ እየተመለከትኩ ላወራ ስል "ሴና ከህፃንነችሽ ጀምሮ ሳደርግ የነበረው ነገር አንቺ እህቴን በጣም ሰለምወድሽ ነበር፡፡ ታላቅ እንደመሆኔ ደሞ አንቺን ከብዙ ነገር ጠብቄ ትልቅ ሰው ማድረግ ነበር እቅዴ ፡፡ እኔ ይህን ሳደርግ ደሙ ሙሉ ቤተሰባችን ስለሚቀበለኝ አንቺ ይሄንን ከጥላቻ ትቆጥሪያለሽ፡፡ በርግጥ እኔም አበዛውት ግን ላንቺው አስቤ የማደርገው ነገር ስለ. . . " አላስጨረስኩትም ወንድሜ ላይ ጥምጥም አልኩበት፡፡ ይሄንን ሁሉ ነገር ያደርግ የነበረው ለኔው ሲል መሆኑን ሳስብ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ፡፡ ወንድሜን ለቅቄ ሚጣን አቀፍኳት፡፡ ተቃቅፈን አለቀስን፡፡
ወደ ከተማ እየተመለስን በጭንቅላቴ ብዙ ሀሳቦች ተመላለሱ፡፡ ዠእውነት ለካ ቤተሰቦቼ ለኔ ፍቅር አላቸው፡፡ የተከተሉት መንገድ የጎዳኝ ቢመስለኝም ሁሉን ሚያደርጉት ለኔ ብለው ነው፡፡ የዶርሜ ልጆች እውነትም ለካ ከልባቸው ነው ጉዋደኝነታቸው፡፡ ለኔ ሰሜት ምን ያህል እንደሚጨነቁ አሰብኩኝ፡፡ እውነት እኛ ሰዎች ባሰቡልን ልክ እያሰብናቸው ነው?' ብዬ ራሴን ጠየኩት፡፡ ዶርም ስገባ ስለሁሉም ነገር ጉዋደኞቼን አመሰገንኳቸው፡፡ ከኪሩቤል ጋርም ጉወደኝነታችን ቀጠለ፡፡ ወንድሜና ጉዋደኞቼ ባደረጉት ነገር በጣም ብዙ ተማርኩኝ፡፡ ጉዋደኝነት ፣ቤተሰብ እውነተኛ ፍቅርን ከነሱ አገኘው፡፡ የፍሬ ህልፈት እጅጉን የከፋ ሀዘን ቢያደርስብኝም ቤተሰቦቼ እና ጉዋደኞቼ ከጎኔ በመሆናቸው ብርታት ሰጡኝ፡፡
ይሄ ታሪክ ከተፈጠረ አመት አለፈው፡፡ አሁን እኔ የሁለተኛ አመት ተማሪ ሆኛለው፡፡ ዶርም ስሄድ ቤቴ ቤት ስሄድ ዶርሜ ይናፍቀኝ ጀመር፡፡ በትምህርቴ ውጤታማ እየሆንኩኝ ነው፡፡እስካሁን የፍቀር ጉዋደኛ አልያዝኩም፡፡ ፍሬ ዛሬም በልቤ፥ አለ፡፡ ነገር ግን ቤተሰቦቼና ጉዋደኞቼ አብረውኝ ስላሉ ደስተኛ ነኝ፡፡ ለሁሉም ነገር ደሞ ፈጣሪን አመሰግናለው፡፡ አምላክ የፍቅርን ጉልበት በቤተሰቦቼና በጉዋደኞቼ በኩል አስተምሮኛል፡፡

ይህንን ታሪክ ያነበባቹ በሙሉ ከዚህ እንደምትማሩ ተስፋ አደርጋለው፡፡

. . . . ህይወት ይቀጥላል . . .

📍📍📍📍 ተ ፈ ፀ መ📍📍📍📍

🎙ግሩፑን ለማግኘት
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha

❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት
ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን