ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
242K subscribers
289 photos
1 video
16 files
237 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_አርባ_ሦስት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ዳያና ላቭሴይ እውነተኛ ፍቅር በአጭር ጊዜ እንደማይለቅ በሃዘን
አስታወሰች፡፡ መርቪን በፍቅሯ የተነደፈ ጊዜ የጠየቀችውን ነገር ሁሉ
በፍጥነት ለማድረግ ደስተኛ ነበር፡፡ አንድ ነገር ከፈለገች በመኪና በመሄድ ያመጣላት ነበር፡፡ ሲኒማ አምሮኛል ካለች ከስራውም ቀርቶም ቢሆን ይዟት ይገባ ነበር፡፡ ከባሰም ለጉብኝት ፓሪስ ይወስዳት ነበር፡ የፈለገችው ሻርፕ እስኪገኝ ድረስ በማንቼስተር ሱቆች እግሩ እስኪቀጥን እየዞረ ሲያስስ ቢውል አይደክመውም፡፡ ቴአትር ቤት ገብተው በመሃል ደበረኝ ካለችው ሳይጨርሱ ቢወጡ ቅር አይለውም፡፡ ታዲያ ይሄ ታዛዥነት ከተጋቡ በኋላ ቀስ በቀስእንደ ጉም በኖ ጠፋ፡፡ ከዚያ በኋላ የጠየቀችውን ባይነሳትም ያደርግ የነበረው
ግን በዳተኝነት ነበር፡፡ ግድ የለም ልታገስ ብሎ እንጂ እንደ በፊቱ በፍቅር
ማድረጉን እየተወ መጣ፡፡ በመጨረሻ እንደውም ትዕግስት እያጣ ሲመጣ
ሚስቱን ጭራሹን ‹‹ዞር በይ›› ማለት አመጣ፡፡
ታዲያ ማርክም እንዲህ ሊያደርገኝ ይችላል የሚል ፍርሃት አጫረባት፡

ማርክ እንግሊዝ አገር በቆየበት ጊዜ ባሪያዋ ሆኖ ነው የስነበተው
በጠፉ በሁለተኛው ቀን ተጣልተው መኝታ ለይተውነበር፡ ሆኖም እኩለ
ሌሊት ላይ እውጭ ያለው ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ አይሮፕላኑን እንዳልተገራ
ፈረስ ሲያሰግረው ዳያና በጣም ፈራችና ዓይኗን በጨው አጥባና ክብሯን ሽጣ ወደ ማርክ መኝታ ሄደች፡፡ እንደዚያም ሆኖ ውጤቱ አላማረም፡፡ በኋላ ወደ እኔ ይመጣል ብላ ብትጠብቅም እሱም ኩራት ልቡን ነፍቶት ሳይመጣ
በመቅረቱ በንዴት ኤሌክትሪክ ልትጨብጥ ምንም አልቀራትም:

ዛሬ ጧት ምንም አልተነጋገሩም ማለት ይቻላል፡፡ ጧት ከእንቅልፏ
የነቃችው አይሮፕላኑ ቦትውድ ሲያርፍ ሲሆን ከአልጋዋ ስትነሳ ማርክ
ወጥቶ መሄዱን አወቀች፡፡ ጧት ቁርስ ላይ መሳ ለመሳ ተቀምጠው በሃሳብ
ተውጠው ምግባቸውን ሲቆነጣጥሩ ነበር፡፡
ዳያናን መርቪን ከናንሲ ጋር የሙሽሮች ክፍልን ተጋርተው ማደራቸው
ለምን እንደዚህ እንዳናደዳት አልገባትም፡ ማርክ በዚህ ረገድ ቢያግዛት
በወደደች። በተቃራኒ አሁንም መርቪንን ትወጂዋለሽ እንዴ?ሲል
ጠይቋታል፡፡ ትዳሯንና ቤት ንብረቷን ትታ ከእሱ ጋር መኮብለሏን እያወቀ
ማርክ እንዲህ ማለቱ አናዷታል፡፡

ዙሪያዋን ስትመለከት በቀኝዋ የተቀመጡት ልዕልት ላቪኒያና ሉሉ ቤል
የቆጡን የባጡን ያወራሉ፡፡ ሁለቱም አይሮፕላኑ ሲወዛወዝ ስላደረ እንቅልፍ
ባይናቸው ሳይዞር ስለነጋባቸው ተዳክመዋል፡፡ በግራ በኩል የኤፍ.ቢ.አዩ ሰው ኦሊስ ፊልድና እስረኛው ፍራንኪ ጎርዲኖ በጸጥታ ምግባቸውን ይበላሉ።

የጎርዲኖ እግር በእግረ ሙቅ ከመቀመጫው ጋር ተጠፍሯል፡ሁሉም
በድካም የዛሉና ነጭናጫ ሆነዋል፡፡ እንዲህ ያለ አለቅጥ የረዘመ ሌሊት
ገጥሟቸው አያውቅም፡፡
አስተናጋጁ ዴቪ ቁርስ የተበላባቸውን ሰሃኖችና ቁሳቁሶች እየሰበሰበ
ነው፡፡ ልዕልት ላቪኒያ ‹‹እንቁላሉ አልበሰለም ሞርቶዴላው ደግሞ በጣም
ሙክክ ብሏል›› በማለት ስሞታ ያሰማሉ፡ ዴቪ ቡና ቢያመጣም ዳያና
አልጠጣችም::

ማርክን ሰረቅ አድርጋ አይታ ፈገግ ስትል እሱም በፈገግታ ተቀበላት
‹‹ከነጋ አንዴ እንኳን አላናገርከኝም›› አለችው፡፡
‹‹ምክንያቱም ከኔ ይልቅ ለመርቪን ልብሽ መጥፋቱን ስላወቅሁ ነው›
ወዲያው ጸጸት ገባት፡፡ መቅናቱ ትክክል ነው፡ ‹‹ይቅር በለኝ ማርክዬ›
አለች ‹‹ልቤ ያለው ካንተጋ ብቻ ነው እውነቴን ነው››
እጁን ሰዶ እጇን ያዝ አደረገና ‹‹እውነትሽን ነው?››
‹‹እውነቴን ነው፡፡ ትናንት ምን እንደነካኝ አላውቅም››

‹‹እሺ›› አለ ማርክ፡፡
ሁለቱም አፍቃሪዎቿ አፍጥጠውባታል፡፡ አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ
እንዳለባት አውቃለች፡ ከመርቪን ጋር ብቻዋን ብትነጋገር ማርክን
አስከፋዋለሁ ብላ ገምታለች፡፡ አሁን መርቪንን ትቼ ከማርክ ጋር ነው
ያለሁት ስለዚህ ማርክን ነው መደገፍ ያለብኝ ስትል አሰበች፡፡

ልቧ  ከበሮ  እየደለቀ ‹‹ማርክ ፊት የማታናግረኝ ከሆነ ልሰማው አልፈልግም›› አለችው፡:

መርቪን ደንገጥ አለና ‹‹እሺ›› አለ በብስጭት፡፡ ወዲያው ራሱን አረጋጋና ‹‹ከዚህ በፊት ያልሺኝን ተገንዝቤያለሁ፤ምን ያህል ቀዝቃዛ እንደነበርኩ አንቺም ምን ያህል ብቸኝነት ይሰማሽ እንደነበር…›› ንግግሩንቆም አደረገ፤ ዳያና ምንም መልስ አልሰጠችም፡፡ ይቅርታ ማለት ወይም መጸጸትን መግለጽ የመርቪን ባህሪ አይደለም፡፡ ምን ሊል ነው?› አለች ዳያና በሆዷ።

‹‹እስካሁን ላደረግሁት ሁሉ ይቅር በይኝ›› አለ መርቪን፡ ዳያና የመርቪን አባባል ቢገርማትም እውነቱን መናገሩን አውቃለች፡ ‹ይህ ሁሉ ለውጥ ከየት መጣ?›

መርቪን ቀጠለና ‹‹የተዋወቅን ሰሞን አንቺን ለማስደሰት ጥረት አደርግ
ነበር፡፡ እንዲከፋሽ አልፈልግም ነበር፡፡ አሁን ኑሮሽን ጨለማ ማድረጌ
ተሰምቶኛል፡ ደስታ ማግኘት መብትሽ ነው፡፡ የሰው ሁሉ ዓይን ማረፊያ እንደሆንሽ አውቃለሁ፡››

ዳያና ይህን ስትሰማ እምባዋ በዓይኗ ሞላ፡፡ የወንዶችን ዓይን መሳቧ
እውነት ነው፡፡

‹‹አንቺን ማሳዘኔ ሀጢያት ነው›› አለ መርቪን፡፡ ‹‹ከዚህ በኋላ አንቺን ለማስደሰት እጥራለሁ፡››

ከዚህ በኋላ ጥሩ እሆናለሁ› ማለቱ ፍርሃት ለቀቀባት፡ ወደ ቤቷ እንድትመለስ ይፈልጋል ማለት ነው፡፡ እሷ ግን እንዲጠይቃት እንኳን
አትፈልግም፡፡ ‹‹ወደ አንተ ተመልሼ አልመጣም›› አለች ዳያና፡

‹‹ከማርክ ጋር ደስተኛ ህይወት የምትኖሪ ይመስልሻል?››

ዳያና ራሷን በአዎንታ ነቀነቀች፡፡

‹‹ያስብልኛል ብለሽ ታምኛለሽ?››

‹‹አዎ ያስብልኛል››

ማርክ ጣልቃ ገባና ‹‹እኔን እንደ እቃ ቆጥራችሁ ስለኔ ትናገራላችሁ? አለ፡፡

ዳያና የማርክን እጅ ለቀም አድርጋ ያዘችና ‹‹እንዋደዳለን›› አለችው:
‹‹አይ!›› አለ መርቪን፡፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ፊቱ ላይ የለበጣ ፈገግታ
ተነበበ ‹‹ትዋደዳላችሁ›› አለ፡፡
መርቪን የተለሳለሰ መሰለ፡፡ ይሄ የእሱ ባህሪ አይደለም፡፡
ወይዘሮ ሌኔሃን ሄደህ ከሚስትህ ጋር ተነጋገር አለችህ እንዴ?›› አለች ዳያና ተጠራጥራ።
አላለችም፡፡ ሆኖም ልናገር እንደምችል ታውቃለች››
‹‹ታዲያ ፈጠን ብለህ ተናገረውና ይውጣልህ›› አለ ማርክ፡፡
መርቪን ማርክን ገላመጠውና ‹ጎረምሳው አንተን እዚህ ነገር ውስጥ
የሚያገባህ ነገር የለም፤ ዳያና እኮ አሁንም ባለቤቴ ናት›› አለ፡፡

ማርክ ፍቅረኛውን ለማገዝ ‹‹ተው እባክህ!  ከዚህ በኋላ ከእጅህ ወጥታለች፤ ደግሞ ጎረምሳው አትበለኝ ሽ
ሽሜ›› አለው መርቪንን፡፡

‹‹መርቪን እዚህ አምባጓሮ ማንሳት አትችልም የምትለው ካለህ
አውጣና ተናገረው፤ አለበለዚያ አንድ ዓይነት ኃይል ያለህ አታስመስል››
አለችው ዳያና፡፡
‹‹ደህና፧ ነገሩ እንዲህ ነው›› ትንፋሹን ዋጥ አደረገና ‹‹መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ፤ ወደ ቤትሽ እንድትመለሺ ስጠይቅሽ ‹ምን ሲደረግ ብለሻል፧ ይሄ ሰው እኔ ማድረግ የማልችለውን አድርጎ ከሆነና ከእሱ ጋር
መኖር ደስታ የሚሰጥሽ ከሆነ መልካም እድል ይግጠማችሁ፡፡ መልካሙን
እመኝላችኋለሁ ይሄው ነው›› አለ፡፡ ከዚያም ጸጥታ ነገሰ፡

ማርክ ሊናገር ሲል ዳያና አቋረጠችውና ‹‹አንተ የተረገምክ እምነተ ቢስ
የሆንክ ሰው!›› አለች ‹‹እንዴት ያለኸው ደፋር ነህ!›› አለችና ምራቋን ጢቅ
አደረገች፡፡

መርቪን አባባሏ ግራ አጋባውና ‹‹ምነው?›› አላት፡፡