ኢትዮ ቴክኖሎጂ ( Ethio technology )
6.9K subscribers
2.19K photos
73 videos
101 files
1.28K links
✔️በቻናላችን✔️
📲 የAndroid መተግበሪያ
💻 የPC SoftWare
📌 አዲስ ለሆኑ የቴክኖሎጂ ምርቶች ልዩ ዘገባ

👉ለአስተያየትና ሌሎች ፕሮግራሞችን ለማግኘት ይቀላቀላሉ
Download Telegram
ኮምፒውተር ላይ ልታውቋቸው የሚገቡ አቋራጭ የኪቦርድ መንገዶችን (#Shortcuts)

🛃Ctrl+C እና Ctrl+X
🔺Ctrl+C የመርጥነውን ጽሁፍ ወይንም #ፎልደር ፋይል ኮፒ ለማድረግ ይረዳናል!
🔺ወይም ድግግሞሽ ነው ቆርጬ (#Cut) ነው መውሰድ የምፈልገው ካልን ደሞ Ctrl+Xን መንካት ነው! #cut ካደረግንበት ቦታ ፋይሉን ወይም ጽሁፉን ያጠፋዋል!

⚠️አፕል ኮምፕዩተር ተጠቃሚዎች Ctrl በ #command (Cmd) በመተካት መጠቀም ይቻላል!

🛃Ctrl+V
🔺ይህ አቋራጭ የሚጠቅመን ከላይ #Copy ወይም #Cut ያደርግነውን በምፈልገው ቦታ ላይ ለማስቀመጥ ነው!
🔺የምንፈልገው ቦታ ላይ ሄደን Ctrl+V ስንነካ #Copy ያደረግነውን ፋይል #Paste ያደርገዋል!

⚠️ለአፕል ተጥቃሚዎች Cmd+Vን መጠቀም ይቻላል!

🛃Ctrl+F
🔺Ctrl+F በመንካት የመፈለጊያ ሳጥን (#Search) መክፈት እንችላለን!
🔺እንዲሁም የፈለግነዉን ጽሁፍ (Text) እና ፋይል ለማግኘት ይረዳናል!

⚠️ለአፕል ተጠቃዎች Cmd+F በመንካት መጠቀም ይቻላል!

🛃Alt+Tab
🔺Alt+Tab መጫን በተከፈቱ ፕሮግራሞች መሃል እንደፈለግን እንድቀያይር ይረዳናል!
▪️ለምሳሌ በBrowser ኢንተርኔት እየተጠቀምን ከነበረ እና ወደ ከፈትነው #Recent #ፋይል መሄድ ብንፈልግ Alt+Tab በመንካት መለወጥ እንችላለን!

⚠️ለአፕል ተጠቃሚዎች cmd+Tab መጠቀም ይችላሉ!

🛃Ctrl+Backspace , Ctrl+Left (Right arrow)

🔺BackSpace የጽሁፍ ፋይል ላይ አንድ ፊደልን ወይም ምልክትን ለማጥፋት ይጠቅምናል! ነገር ግን Ctrl+Backspace ሁሉንም ነገር አንድ ሳያስቀር ያጠፋልናል!
🔺Ctrl ተጭነን የግራ እና የቀኝ ቀስቶችን ስንነካ እንደ ከርሰር ተጥቅመን የምንፈልገዉን ተከታታይ ፋይል ወይም ጽሁፍ በጅምላ እንድንመርጥ ይረዳናል!

🛃Ctrl+S
🔺ዶክመንቶች እየፃፍን የሰራነውን ቶሎ #Save ለማድረግ ቢያስፈልገን የምንጠቀመው Ctrl+S ነው!

⚠️ለአፕል ተጠቃሚዎች Cmd+S መጠቀም ይችላሉ!

🛃Ctrl+Home እና Ctrl+End
🔺Ctrl+Home ከሆም ላውንች ወደ ዶክመንት (ፋይል) መመለሻ ነው
🔺Ctrl+End ደግሞ ከ Search ወደ ዶክመንታችን (ፋይላችን) ይወስደዋል!

🛃Ctrl+P
🔺Print ለማድረግ የምንፈልገው #ፋይል ካለ Ctrl+P ስንነካ የፕሪንትን መስኮት በመክፈት የፕሪንት አማራጮችን ያሳየናል!

⚠️ለአፕል ተጠቃሚዎች Cmd+P ን ተጠቀሙ!

🛃PageUp , SpaceBar , And PageDown

🔺ከስሙ መገመት እንደሚቻለው #PageUp እና #Pagedown ዶክመንታችን ላይ ወደ ቀጣይ ገጽ ወይም ወደ #ቀድሞ ገጽ ለመሄድ ይጠቅመናል!

🔺የኢንተርኔት #Browser በምንጠቀምበት ሰአት ደግሞ SpaceBar (Shift + Spacebar) በመጠቀም አንድ ገጽ ለመዝለል ያስችለናል!

የምንለቃቸው አዳዲስ መረጃዎች በቶሎ እንዲደርሳችሁ የቻናላችን #Notification #On ማድረጋቹን አረጋግጡ!

©️birhan tech

https://t.me/joinchat/VP0zpyXkgr_OmkCK
#በቫይረስ የተጠቃ ፍላሽ ዲስክ ሶፍትዌር ሳንጠቀም እንዴት ማፅዳት እንችላለን ?
በቫይረስ የተጠቃ ፍላሽ ዲስክ እንዴት ያለአንቲ ቫይረስ እንደምናጸዳውና ስንገዛው እንደነበረው አዲስ እንደምናደርገው እናያለን።
እባክዎ ከመጀመርዎ በፊት ፍላሹ ላይ ጠቃሚ ፍይል ካለዎት ወደ ሌላ ቦታ ኮፒ ያድርጉ። ምክንያቱም ፋይሉ ሙሉ በሙሉ ስለሚጠፋ!
በመጀመሪያ ኮምፒዩተራችን ላይ '#command_prompt' ወይም '#cmd' እንከፍታለን።
( '#cmd'ን ለመክፈት በመፈለጊያችን ላይ #cmd ብለን #search እናደርጋለን. #Cmd
ሲመጣልን right click አድርገን run as #administrator የሚለውን በመጫን cmdን
እንከፍታለን)
Cmd ከከፈትን በኋላ የሚከተሉትን ትእዛዞች በቅደም ተከተል እናስገባለን። እያንዳንዱን
ትእዛዝ ከጻፍን በኋላ ENTER ቁልፍን እንጫናለን
1. #DISKPART
2. #LIST DISK
(አሁን በኮምፒውተሩ ላይ ያሉትን ዲስኮች ይዘረዝርልናል. ለማጽዳት
የፈለግነውን ፍላሽ ቁጥር ከለየን በኋላ ወደ ሶስተኛው ትእዛዝ እንሄዳለን። ምሳሌ.disk 1)
3. SELECT DISK *
(በኮከቡ ፋንታ ሁለተኛው ትእዛዝ ላይ የለየነውን የፍላሽ ቁጥር እናስገባለን)
4. CLEAN
(በዚህ ጊዜ ፍላሹ ላይ ያለውን ማንኛውም ነገር ያጠፋዋል)
5. CREATE PARTITION PRIMARY
(ለፍላሹ ይዘት ይፈጥራል)
6. SELECT PARTITION 1
7. ACTIVE
(ይህ ፍላሹን ዝግጁ ያደርገዋል)
8. FORMAT FS=FAT32 Quick
(ይህ ፋላሹን በጥልቀት በመሰረዝ በውስጡ ያሉትን
ማንኛውም ቫይረስ ወይም ሌላ ችግር ያጠፋል። ሂደቱ የተወሰነ ጊዜ ስለሚወስድ
እስከሚጨርስ ወይም 100 % እስኪሞላ በትዕግስት እንጠብቀዋለን)
9. ASSIGN
(አዲስ ለፈጠርነው ፍላሽ የፊደል ስም ይሰጥልናል)
10. EXIT
(ፕሮሰሱን ይጨርስልናል)
አሁን አዲሱን ፋላሻችንን መንቀልም ሆነ መጠቀም እንችላለን። ይህንን መንገድ በመጠቀም
ማንኛውንም ቫይረሱ ያለበት ፍላሽ
ማስተካከል እንችላለን።