EthiopikaLink/ኢትዮጲካሊንክ
328 subscribers
89 photos
12 videos
49 links
EthiopikaLink is an infotainment formatted program produced and hosted by
💥Axum Pictures💥
@Ethiopikalink በfana 98.1fm.
Download Telegram
የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም
(የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን)
የደም ቀን (የካቲት 12)
×××××××××××××××
... አገር ተቃጠለ!
እሳተ ጎመራ ወረደ ከሰለ።
ጭስ አመድ አዋራ ሰማዩን ሸፈነው
ጥቁር ሰማይ ጥቁር!
ሸፈነውጨለማ ሞት በእናት ቅድስት አገር
በጀግናው ሕዝብ ላይ የጠላት ግፍ ቀንበር።
ፋሽስት አስተጋባ ፋስ ተሰነዘረ
ባካፋ መዶሻ ሕዝቡ ተወገረ።....
የሰው ጭንቅላት ኳስ …........
አባቶች ታረዱ
እናቶች ታረዱ
ቤት ንብረት ፈረሰ ከብቶቹ ተነዱ።
ዓለም መና ቀረ ................
* ገብረ ክርስቶስ ደስታ
(መንገድ ስጡኝ ሰፊ )
ክብር ለሰማዕታት!
የተከፈለልንን አንረሳም!
የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም
(የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን)
የደም ቀን (የካቲት 12)
@ethiopikalink
የዶክተር ያለህ!
ሃይ ኢትዮጲካሊንኮች
ፍቅረኛ አለኝ። ተጋብተን አብረን ለመኖር እያኮበኮብኩን ነው። ነገር ግን አንድ ስጋት
አለኝ። አንድ ቀን የፍቅረኛሞችን ቀን፣ የተገናኘንበትን ቀን፣ የተወለድኩበትን ቀን
አስታውሶ አንድ ነገር አድርጎ አያውቅም። እና ከልቡ የሚወደኝ አልመስል አለኝ። እስኪ
አንድ በለኝ። አመሰግናለሁ።
ሳምሪ ነኝ
በተለያዩ አዝናኝ መረጃዎች አብረናችሁ ለማምሸት ገብተናል። እስከ እኩለ ለሊት
በ90.7fm አድምጡን። እናመሰግናለን።
ፎቶ: ከእኛ ይልቅ እቃዎቻችን ያምራሉ አይደል?።

@ethiopikalink
እኔ፦ ዶክተር ሆዴን ጥሩ ስሜት አይሰማኝም
.
ዶክተር፦ ትላንት ማታ ምንድነው የተመገብከው
.
እኔ፦ በርገር ከበላሁ በኋላ ትንሽ ቆይቼ ፒዛ ጨመርኩበት ከዛ ወይን ጠጣሁ በቃ
.
ዶክተር፦ ይሄ እኮ ፌስቡክ አይደለም ትክክለኛውን ነገር ተናገር
.
.
.
.
.
.
.
.
.
እኔ፦ ሽሮ

@ethiopikalink
" በምኒልክ ግዜ የሐገሪቱ ክብር ከፍ አለ"
ኢትዮጵያ ከድል በኋላ ከዘመናዊነት ጋር ተዛመደች። ስልክ... ባቡር... ሆቴል...ፎቶ
ግራፍ... ወፍጮ ቤት...ፖስታ ቤት... ትምህርት ቤት...ሆስፒታል....እና ሌሎች
ዘመናዊነቶችን ተዋወቀች።
የዓድዋ ጦርነት በኢትዮጵያ ድል አድራጊነት ከተጠናቀቀ ኋላ የሀገሪቷ ክብር ከፍ ብሎ
ነበር።
በጥቁር ሀገራት ተደርጎ የማይታወቅ የቆንፅል ቢሮዎች ምኒልክን ለመወዳጀት
በኢትዮጵያ ምድር ተከፈቱ።
የምኒልክንና የጣይቱን ዝና የሰሙ ሁሉ የምኒልክን ቤተመንግስት ወታደርህ እንሁን
በሚል ጥያቄ አጨናነቁት። ዓለም አቀፍ ጋዜጦች ምስላቸውን ይዘው መታተም ጀመሩ።
አውሮፖውያን አዲስ ለተወለዱ ልጆቻቸው ምኒልክ የሚል ስያሜ አጎናፀፉ።
ሞተው ላስከበሩን የዘላለም ክብር ይሁን!!!
#የጥቁር_ሕዝብ_ድል #አድዋ #ኢትዮጵያ #VictoryOfAdwa #BlackExcellence
#Adwa #Ethiopia

@ETHIOPIKALINK
ጣይቱ ሆቴል የድዋን ድል እያከበረች ትገኛለች።
@ethiopikalink
መጣልኝ አድዋ ነፍስና ስጋዬን ሊለያያት... የድሉን ታሪክ ታይቶ እንደማያውቅ፣ ነፍስና
ስጋ ዘርቶበት መላ አካልን ውርር የሚያደርገውን የጂጂዬን ሙዚቃ እየሰማው ልቆዝም፣
በእህህታ “ዛሬስ የት ነን? ምንስ እናደርጋለን?” ብዬ ልብከነከን... በሙዚቃ እና ግጥም
ቀመር፣ ለአስደናቂ ታሪክ ድንቅ ሀውልት ተቀርጾ እንደሚቆም ጂጂ ቋሚ ምስክር ናት!
የእኔ እናት፥ ሴት ተኩል!
"የሰው ልጅ ክቡር
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቷል – ሰው ሊያድን፣
— ሰውን ሲያከብር
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፥ ሰው ሊኖር — ሰው ሞቶ፤”
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ካአጥንት፣
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር አድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር አድዋ፣ ትናገር አገሬ፤
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ፤
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኧው በቀን በቀን
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን።
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች፣
የጥቁር ድል አምባ፣ አድዋ
አፍሪካ፣ እምዬ ኢትዮጵያ
ተናገሪ… የድል ታሪክሽን አውሪ።
#የጥቁር_ሕዝብ_ድል #አድዋ #ኢትዮጵያ #VictoryOfAdwa #BlackExcellence
#Adwa #Ethiopia
Y
@ethiopikalink
🇪🇹❤️ እንኳን ለታላቁ የዓድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ።
የዓድዋ ድል መንፈስ ከሁላችን ጋር ይሁን!
#ዓድዋ122ኛዓመት🇪🇹❤️
የዶክተር ያለህ!
ሰላም ሰላም ኢትዮጲካሊንኮች!
ከአንድ የድሮ ጓደኛዬ ጋር ተገናኝተን ስናወራ ከሚስቱ ጋር 7 አመት አብረው ኖረው ልጅ መውለድ እምቢ ሲላቸው እንድተመረመሩና ችግሩ የእሷ እንደሆነ፤ ችግሩን ለመፍታት ትልቅ ህክምና ለማድረግ አስቦ አሁንም እሷ <ልጅን በገንዘብ አልገዛም> እንዳለችውና ልጅ ማግኘት እንደሚፈልግ አጫወተኝ።መደዋወል ስንቀጥል ቤት ውስጥ ሰላም እንዳጣ ይነግረኛል። እኔም አስበው ጀመር። እሱም አንድ ቀን በ”እወድሻለሁ ላግባሽና አብረን እንኑር” ብሎኝ አረፈው። ሚስቱን በሌላ መንገድ አውቃታለሁ። እና ምን ላድርግ?
አይኒ ከአዲስ አበባ
24/06/2010
የውስጥ አዋቂ ወሬዎቻችን ርዕሶች
የኤኮን የኢትዮጵያ ቆይታ ምን ይመስላል
- ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል
- በአፍሪካ ኅብረት ንግግር አድርጓል
- የቆይታውን ዝርዝር እንሰማለን

ሦስት ድርጅቶች ከአንድ ዝነኛ ፊልም ማስጠንቀቂያ ደረሳቸው
- ከአንድ ዝነኛ ፊልም ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው ሦስት ድርጅቶች እነማን ናቸው?
- ማስጠንቀቂያ የሰጠው ዝነኛ ፊልም የቱ ነው?

አንድ ባለስልጣን ወደ መንግስት ካዝና ገንዘብ ገቢ አደረጉ
- ወደ መንግስት ካዝና ገንዘብ ገቢ ያደረጉት ባለስልጣን ማን ናቸው?
- ባለስልጣኑ ይህን ያደረጉት ለምንድነው?

አንድ ታዋቂ አርቲስት በድንገተኛ አጋጣሚ አልጋ ላይ ወደቀ
- በድንገተኛ አጋጣሚ አልጋ ላይ የወደቀው ታዋቂ አርቲስት ማነው?
- ታዋቂው አርቲስት የደረሰበት ድንገተኛ አጋጣሚ ምንድነው?
አባዱላ ለሰሩት 2 የሒሳብ ስህተት ይቅርታ ጠየቁ በቃ አፉ በሉኝ ብለዋል ሙሉ

http://www.laroadvert.com/watch.php?vid=7da04dfe6
🙏ወንድሜ/እህቴ ሆይ እስኪ አንብበው...🙏
☞ ደሀ ብትሆን የመናጢ ልጅ ፤ ሀብታም ብትሆን ዶላር ያሳበጠው
ይሉሀል።
☞ ከሴት ጋር ብትሄድ ሴሰኛ ፤ ብቻህን ብትሆን ወፈፌ ይሉሀል ።
☞ ብትፈጥን ቀዥቃዣ ፥ ብትዘገይ ዘገምተኛ ።
☞ ብታወራ ለፍላፊ ፥ ዝምብትል ዝጋታም ።
☞ ብትራመድ አርፎ አይቀመጥም ፥ አርፈህ ብትቀመጥ ዝፍዝፍ
☞ ብትማር አወቅሁ ባይ ፥ ባትማር የአቡጊዳ ሽፍታ ።
☞ ብትወፍር ጠብደል ፥ ብትከሳ በልቶ ማይጠረቃ ።
☞ ብትይዝ ቋጣሪ ፥ ብትለቅ መንዛሪ ። በቃ ምን ልበላቹ ሰዎች ከማውራት አይቆጠቡም ነገር ግን አንተ ራስህ እንደገባህ እንጂ ሰዎች እንደተረዱህ አትኑር። ምክንያቱም ከአንተ በላይ ስላንተ የሚያውቅ የለምና።