EthiopikaLink/ኢትዮጲካሊንክ
322 subscribers
89 photos
12 videos
49 links
EthiopikaLink is an infotainment formatted program produced and hosted by
💥Axum Pictures💥
@Ethiopikalink በfana 98.1fm.
Download Telegram
#Ethiopia : 10 Most Powerful Passports in Africa 2017 List │በአፍሪካ ከፍተኛ አቅም
ያላቸው 10 የሀገራት ፓስፖርቶች
10) የዩጋንዳ ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 77/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 61
9) የኬፕቨርዴ ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 76/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 56
8) የዛምቢያ ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 74/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 61
7) የጋና ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 73/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 63
6)የጋምቢያ፣ማላዊና ስዋዚላንድ ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 72/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 69
5) የኬንያ ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 70/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 72
4) ናሚቢያ ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 68/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 61
3) ቦትስዋና ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 66/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 65
2) የደቡብ አፍሪካ ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 54/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 90
1) የሲሼልስ ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 31/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 116

@ethipikalink
@ethipikalink
ሽንቁር ልቦች የጉልሰረን አሟሟት እና የቀብር ስነስርዓት ቪዲዮውን ይህን ተጭነው
ይመልከቱ http://laroadvert.com/?p=324
ሰበር ዜና ሼክ ሁሴን አላሙዲን እድሜ ልክ ሊፈረድባቸው ነው http://
laroadvert.com/?p=985
ተወዳጇ ሀና ዮሀንስን በእርስዋ ምክንያት በተጣሉት ጉደኛሞች የደረሰባትን አስደንጋጭ ነገር
ይፋ አደረገች ይህን ተጭነው ያድምጡዋት>>> http://laroadvert.com/?p=1028
የሁለቱ ፍጥጫ መነሻው እና መጨረሻው ምን ሊሆን ይችላል የሚሚ ስብሀቱ አስገራሚ
ማብራሪያ እና ትችት ይህን ተጭነው ያድምጧት>>> http://laroadvert.com/?p=1024
ከኢትዮጲካሊንክ ውስጥ አዋቂ
-ዘመን ድራማ ከሰረ
-ብስራት ገመቹ 1.3 ሚሊዬን ተፈረደላት
-ጆሲ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው
-ወጣቱ መኪናውን ተዘረፈ
ዝርዝሩን ይህን ተጭነው ያድምጡ>>>http://laroadvert.com/?p=1026
#የዶክተር_ያለህ!
አረ ባካችሁ ሴቶችን የሚያስደስታቸው ነገር ምንድ ነው?
እንደኔ ተንከባካቢ ሰው የለም። የሚፈልጉትን ነገር ሁሉ አደርግላቸዋለሁ። እንደሚፈልጉት
እሆንላቸዋለሁ። ነገር ግን የማፈቅራቸው ሴቶች ሁሉ ይከዱኛል። በቅርቡ ላገባት የነበረች
ሴት ሳትነግረኝ ጥላኝ ውጭ ሄደች። አግብቼ መውለድ፤ መረጋጋትና ቤተሰቦቼን ማስደሰት
ብፈልግም ሊሳካልኝ አልቻለም። ምን ላድርግ? ያልገባኝ ነገር አለ?
ኤስ ከአዲስ አበባ
#አናቶሊ_ታደሰ - አቶ ኢትዮጲካሊንክ
የአቶ ኢትዮጲካንክ አሸናፊ አናቶሊ ታደሰ ሆኗል፡፡ እንኳን ደስ አለህ እንለዋለን፡፡ አናቶሊን
ጨምሮ ለፍፃሜ የደረሱት ምንተስኖት ታዬ እና ዊሊያም ሰለሞንም ጥሩ ብቃት ያሳዩነበሩ፡፡ ወደፊት ስኬታማ የሬዲዮ ሰዎች እንደሚሆኑ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

@ethiopikalink
አስቸጋሪ ባህሪ ያላቸው 10 ሰዎች ...
፩ (1). የታንክ ባህሪ ያላቸው :-
• ያገኙትን እየጨፈለቁ የሚሄዱ ናቸው።
• እጅግ በጣም ጨካኝ ናቸው።
• ሲበዛ ይቆጣሉ።
• ሲናገሩ ጥብቅ አድርገው የሚናገሩ ናቸው።
• በጣም በጋለ ስሜት ያወራሉ።
• ከመጠን በላይ ግምት ያበዛሉ።
• ጉልበተኞች ናቸው።
፪(2). ኢላማ አላሚ ባህሪ ያላቸው :-
• ድብቅ ብለው ከምንናገረው ነገር ውስጥ ስህተት ላይ ያፈጣሉ።
• እራሳቸውን ይደብቃሉ።
• ማንነታቸውን በሰው ፊት አይገልጡም።
• ብዙ ጊዜ ስብሰባ ላይ መሃል ወይ መጨረሻ መቀመጥ ይወዳሉ።
• ብልጣ ብልጥ ባህሪ ያበዛሉ።
• በደካማ ጎናችን ይመጡብናል።
• ስህተታችንን እኛ ከሄድን በዋላ ከሰው ጋር ያወራሉ።
• ሃሜት በጣም ይወዳሉ።
• ስብሰባዎች ላይ ንግግሩ ላይ ስህተት ይፈልጉና እነሱ በሚናገሩ ሰአት ያን ሰው
ያጣጥሉታል።
• ሚስጥር በማባከን ማኛ ናቸው።
፫ (3). የቦንብ ባህሪ ያላቸው ሰዎች:-
• አብዝተው የሚጮሁ እና ቁጡ ሰዎች ናቸው።
• ለመደነቅና ትክክል ለመምሰል ጥረት ያደርጋሉ።
• በመጀመሪያ በጣም ዝምተኛና ጥሩ ይመስላሉ።
• በማንጠብቀው ቦታና ጊዜ ከመጠን በላይ በጣም ጮክ ብለው በመናገር ትክክል
ለመምሰል ይሞክራሉ።
• በመጮህ ውስጥ ራሳቸውን የሚደብቁ።
• ጮክ ብለው በመናገር መሰ'ማት ይፈልጋሉ።
፬ (4). ሁሉንም አውቃለሁ የሚሉ:-
• ሁሉንም እናውቃለን ይላሉ ውስጣቸው ግን እንደማያውቁ ያውቃል ግን አላውቅም
ማለት ይደብራቸዋል።
• የፈለከውን ጠይቀኝ እመልሳለሁ ይላሉ።
• አውቃለሁ ስለሚሉ ሰው እንዲያርማቸው አይፈልጉም።
• ካረሟቸው ይናደዳሉ ... ትንሽ የሆኑ ይመስላቸዋል።
• በፍፁም ሰው አያዳምጡም።
• ዝም ብለው ያወራሉ (የማያውቀው ነገር የለም ይባልላቸዋል)
፭ (5). ሁሉንም እንደሚያውቁ የሚያስቡ:-
• እነዚህ 4ኛ ላይ ካሉት ይከፋሉ።
• ሳያውቁ እንደሚያውቁ ያስባሉ።
• የሚያወሩልህን ነገር እንደማታውቅ ከነገርካቸው የማይሆን መረጃ እየጨመሩ ግራ
ያጋቡሃል።
• እጅግ በጣም መደነቅ እና ትኩረትን ይፈልጋሉ።
• አያውቁም መባልን ስለሚፈሩ ስለሁሉም ነገር ያወራሉ።
፮ (6). እሺ የሚሉ :-
• እነዚህ ትልቅ ትኩረታቸው ሰው ነው።
• በጣም ዝርክርክ ናቸው ... ብዙ ነገር ውስጥ ራሳቸውን ይከታሉ።
• ሁሉንም ሰው እሺ ማለት ያዘወትራሉ።
• በአንድ ነገር በቶሎ ይስማማሉ ግን በቶሎ አይፈፅሙም።
• ብዙ ነገር ስለሚሰበስቡ ግራ ይጋባሉ።
• እከሌን እንዳላስቀይመው እሺ አልኩት ይላሉ።
፯ (7). ምናልባት የሚሉ:-
• በጣም የመወሰን ችግር አለባቸው ... መወሰን አይችሉም።
• ሁሌም ነገ ውስጥ ነው የሚኖሩት።
• ለችግራቸው በራሱ ጊዜ መፍትሔ ይመጣል ብለው ያስባሉ።
• ስራን ለነገ ማስቀመጥ የሚወዱ ናቸው።
• ስትቀጥራቸው (ለምሳሌ ነገ 4 ሰአት እንገናኝ ብትላቸው እስኪ ሶስት ሰአት ላይ
ደውልልኝ) የሚሉህ አይነት "የምናልባት" ሰዎች ናቸው።
• ስራ አብረሃቸው ብትሰራ ቶሎ ስለማይወስኑ ስራው ይጎተታል።
፰ (8). ምንም ነገር የማይሉ ሰዎች:-
• አይቃወሙም።
• በምንም ጉዳይ አይሳተፉም።
• በቃልም ሆነ በሁኔታ ምን እያሰቡ እንዳለ አይታወቅም።
• ዝምታ ያበዛሉ።
• አንድ ነገር ነግረሃቸው ምን እንዳሰቡ ማወቅ አይቻልም።
• በጣም ግራ ያጋባሉ።
፱ (9). አይሆንም ብቻ የሚሉ:-
• ሁሉም ነገር ትክክል እንዲሆን ይፈልጋሉ።
• አንድ ትልቅ ሃሳብን አስረድተሃቸው በአንድ ትንሽ ቃል "አይሆንህም" ይሉሃል።
• ለችግርህ መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ ችግርህን መንቀፍ ይቀናቸዋል።
• ሃሳብህን ያጣጥሉና (አውቄ ሳይሆን እውንነታውን ነው የምነግርህ) ይላሉ።
• ሰውን በጣም ያጥላላሉ ... የበታች ያደርጋሉ።
• ሌሎችን ተስፋ ቢስ ያደርጋሉ።
• አሪፍ የቢዝነስ ሃሳብ ብትነግራቸው ሃሳብን ለማጣጣል ስህተት ይፈልጋሉ።
፲ (10). የሚያማርሩ እና የሚነጫነጩ:-
• ትክክል ባልሆነ አለም እንደሚኖሩ ያስባሉ።
• ለማንኛውም አለም የተዳከመ ስሜት አላቸው።
• አለም እና ሰው ሁሉ ስህተት እንደሆነ ያስባሉ።
• ሰው ሁሉ እንደነሱ እንዲያማርር ይፈልጋሉ።
• እነዚህ ሰዎች "አይ እቺ አለም እና አይ ጊዜ" ማለት ያዘወትራሉ።
••••••••••••
ምንጭ :- ድንቅ ተፈጥሮ መፅሐፍ.
•••••••••••••
••• ራሳችንን እንፈልገው ... የቱ ጋር ነን !

@ethiopikalink
@ethiopikalink
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቀለ ገርባ እና ወዳጆቻቸው (ጉርሜሳ አያኖ፣ አዲሱ ቡላላ፣ ደጀኔ
ጣፋ፣ ጌቱ ግርማ፣ ተስፋዬ ሊበን እና በየነ ሩዳ) ተፈቱ

@ethiopikalink
ከአዋጆቹ መካከል የእግር ኳስ ጨዋታዎች የሁከት መነሻዎች በመሆናቸው ማንኛውም
የኢትዮጵያ የሊግ ጨዋታዎች በዝግ ስታዲዮም እንዲካሄዱ እንደሚደረግ አንድ አንድ
እየወጡ ያሉ መረጃዎች ጠቁመዋል።
@ethiopikalink
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና ንግስት ይርጋ ጨምሮ የ119
ተጠርጣሪዎች ክስ ተቋረጠ
@ethiopikalink
ሥልጣንን በፈቃድ መልቀቅ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ
በኢትዮጵያ የተመዘገበ ታሪክ ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው የለቀቁ የመጀመሪያው መሪ
ዐፄ ካሌብ ናቸው፡፡ ሥልጣናቸውን ለልጃቸው ለዐፄ ገብረ መስቀል አስረክበው አባ
ጰንጠሌዎን ገዳም በመግባት ቀሪ ዘመናቸውን በምናኔ ነው ያሳለፉት፡፡ ከእርሳቸውም
በኋላ በቅርቡ ታሪካችን አፄ ሱስንዮስና አድያም ሰገድ ኢያሱ በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን
ለቅቀዋል፡፡ ዐፄ ሱስንዮስ ሕዝብ ባደረሰባቸው ግፊት የተነሣ ሰኔ 5 ቀን 1624 ዓ.ም.
ሥልጣናቸውን ለቅቀው ለዐፄ ፋሲል አስረክበዋል፡፡ አድያም ሰገድ ኢያሱ ደግሞ ሰኔ 21
ቀን 1698 ዓ.ም. በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ለቅቀው መንነው ገዳም ገብተዋል፡፡

👉#በኢትዮጵያ ታሪክ ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው (ወይም የሥልጣን መልቀቂያ በማስገባት) የለቀቁ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጸሐፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ናቸው፡፡

@ethiopikalink
#የዶክተር_ያለህ!
28 ዓመቴ ነው። 5 አመት የቆየ ብዙ መስዋትነት የከፈልኩበት የፍቅር ህይወት አለኝ።
ከፍቅር ጓደኛዬ ጋር በተደጋጋሚ እንጋጫለን። የተለያዩ ምክንያቶችን እያነሳች ግጭት
ይፈጠራል። በእኔ በኩል ችግሩን ለመፍታት ጥረት ሳደርግ ይብስባታል፤ ተስፋ ቆርጨ
ዝም ስል ተመልሳ ትመጣና ይቅርታ ተባብለን ግንኙነቱ ይቀጥላል። ስንጣላ ተስፋ
አስቆራጭ ነገሮችን ትናገራለች፤ ስቀር ራሷ ትመጣለች። በዚህ አይነት ሁኔታ 5ቱን ዓመት
በመጣላትና በመታረቅ አሳለፍን። የሚገርመው በቅርቡ ለመጋባት እቅደናል። ሆኖም
አሁንም ይሄ ነገራችን አልቀረም። እንዳልተዋት እወዳታለሁ፤ በዚያ ላይ ብዙ መስዋዕትነት
የከፈልኩበት ፍቅር ነው። እባካችሁ መንታ መንገድ ላይ ቆሜያለሁ መፍትሄ ስጡኝ።
ስሜ ይቅር
@ethiopikalink
እስከ አንድ ሰዓት ድረስ በዛሚ 90.7 ኤፍኤም፣ በሞባይል አፕሊኬሽን
(EthiopikaLink) ወይም በድረገፃችን EthiopikaLink.net እንድታደምጡን
እንጋብዛለን፡፡ መልካም ቆይታ!
@ethiopikalink