EthiopikaLink/ኢትዮጲካሊንክ
322 subscribers
89 photos
12 videos
49 links
EthiopikaLink is an infotainment formatted program produced and hosted by
💥Axum Pictures💥
@Ethiopikalink በfana 98.1fm.
Download Telegram
#Ethiopia : 15 Things Poor People Do That The Rich Don’t │ደሀ ሰዎች ሁል ጊዜ
የሚያደርጓቸው 15 ነገሮች (ባለሀብቶች የማያደርጓቸው)
ደሀ ሰዎች፡-
1) ብዙ ሰአት ቴሌቪዥን ይመለከታሉ፣
2) አዘውትረው ፈጣን ምግቦችን ይመገባሉ(በኛ ሀገር ላይሰራ ይችላል)፣
3) የቅናሽ ልብሾችንና እቃዎችን ይሸምታሉ፣
4) በማለዳ ከመኝታቸው አይነሱም፣
5) ስፖርትን አዘውትረው ይከታተላሉ(ልክ እንደቲቪው)፣
6) የሰውነታቸውን ንፅህና ሻወር በተጋጋሚ በመውሰድ አይጠብቁም፣
7) የድህነታቸው ምክንያት ሌሎች ሰዎች እንደሆኑ በማሰብ ሌሎችን ይወቅሳሉ፣
8) ገንዘብ አይቆጥቡም፣
9) የተበደሩትን ብድር ቁምነገር ላይ አያውሉም፣
10) ገና በወጣትነት ጊዜያቸው ብዙ ልጆችን ይወልዳሉ፣
11) ከመታመማቸው በፊት ጤናቸውን ህክምና ቦታ በመሄድ ክትትል አያደርጉም፣
12) ገንዘብ ከማግኘታቸው በፊት ገንዘብ ያጠፋሉ(በብድር ወይ ዱቤ )፣
13) አኗኗራቸው ወይም ውሏቸው ደሀ ከሆኑ ሌሎች ሰዎች ጋር ነው፣
14) የተሰጣቸውን እምቅ ችሎታ ለመጠቀም አይፈልጉም ወይም አይጠቀሙም፣
15) ስኬታማ እንዲሆኑ በሌሎች ሰዎች የግድ መረዳት አልብኝ ብለው ያምናሉ፡፡
መረጃዉን ለመመልከት ሊንኩን ወይም ምስሉን ይጫኑ፡፡
አዳዲስ መረጃ እንዲደርስዎ Like ያድረጉ፣ አስተያየት ይስጡ፣ ለጓደኛዎ ያጋሩ፡፡

@ethipikalink
@ethipikalink
#Ethiopia : 10 Most Powerful Passports in Africa 2017 List │በአፍሪካ ከፍተኛ አቅም
ያላቸው 10 የሀገራት ፓስፖርቶች
10) የዩጋንዳ ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 77/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 61
9) የኬፕቨርዴ ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 76/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 56
8) የዛምቢያ ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 74/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 61
7) የጋና ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 73/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 63
6)የጋምቢያ፣ማላዊና ስዋዚላንድ ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 72/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 69
5) የኬንያ ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 70/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 72
4) ናሚቢያ ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 68/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 61
3) ቦትስዋና ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 66/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 65
2) የደቡብ አፍሪካ ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 54/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 90
1) የሲሼልስ ፓስፖርት
የአለም ኢንዴክስ ደረጃ፡ 31/120
ያለቪዛ የሚጓዙበት ሀገር ብዛት፡ 116

@ethipikalink
@ethipikalink
" በምኒልክ ግዜ የሐገሪቱ ክብር ከፍ አለ"
ኢትዮጵያ ከድል በኋላ ከዘመናዊነት ጋር ተዛመደች። ስልክ... ባቡር... ሆቴል...ፎቶ
ግራፍ... ወፍጮ ቤት...ፖስታ ቤት... ትምህርት ቤት...ሆስፒታል....እና ሌሎች
ዘመናዊነቶችን ተዋወቀች።
የዓድዋ ጦርነት በኢትዮጵያ ድል አድራጊነት ከተጠናቀቀ ኋላ የሀገሪቷ ክብር ከፍ ብሎ
ነበር።
በጥቁር ሀገራት ተደርጎ የማይታወቅ የቆንፅል ቢሮዎች ምኒልክን ለመወዳጀት
በኢትዮጵያ ምድር ተከፈቱ።
የምኒልክንና የጣይቱን ዝና የሰሙ ሁሉ የምኒልክን ቤተመንግስት ወታደርህ እንሁን
በሚል ጥያቄ አጨናነቁት። ዓለም አቀፍ ጋዜጦች ምስላቸውን ይዘው መታተም ጀመሩ።
አውሮፖውያን አዲስ ለተወለዱ ልጆቻቸው ምኒልክ የሚል ስያሜ አጎናፀፉ።
ሞተው ላስከበሩን የዘላለም ክብር ይሁን!!!
#የጥቁር_ሕዝብ_ድል #አድዋ #ኢትዮጵያ #VictoryOfAdwa #BlackExcellence
#Adwa #Ethiopia

@ETHIOPIKALINK
መጣልኝ አድዋ ነፍስና ስጋዬን ሊለያያት... የድሉን ታሪክ ታይቶ እንደማያውቅ፣ ነፍስና
ስጋ ዘርቶበት መላ አካልን ውርር የሚያደርገውን የጂጂዬን ሙዚቃ እየሰማው ልቆዝም፣
በእህህታ “ዛሬስ የት ነን? ምንስ እናደርጋለን?” ብዬ ልብከነከን... በሙዚቃ እና ግጥም
ቀመር፣ ለአስደናቂ ታሪክ ድንቅ ሀውልት ተቀርጾ እንደሚቆም ጂጂ ቋሚ ምስክር ናት!
የእኔ እናት፥ ሴት ተኩል!
"የሰው ልጅ ክቡር
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቷል – ሰው ሊያድን፣
— ሰውን ሲያከብር
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፥ ሰው ሊኖር — ሰው ሞቶ፤”
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ካአጥንት፣
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር አድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር አድዋ፣ ትናገር አገሬ፤
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ፤
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኧው በቀን በቀን
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን።
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች፣
የጥቁር ድል አምባ፣ አድዋ
አፍሪካ፣ እምዬ ኢትዮጵያ
ተናገሪ… የድል ታሪክሽን አውሪ።
#የጥቁር_ሕዝብ_ድል #አድዋ #ኢትዮጵያ #VictoryOfAdwa #BlackExcellence
#Adwa #Ethiopia
Y
@ethiopikalink