EthiopikaLink/ኢትዮጲካሊንክ
340 subscribers
88 photos
12 videos
48 links
EthiopikaLink is an infotainment formatted program produced and hosted by
💥Axum Pictures💥
@Ethiopikalink በfana 98.1fm.
Download Telegram
የዶክተር ያለህ!
ጤና ይስጥልኝ ኢትዮጲካሊንክ... በጣም የምወዳት ሚስት አለችኝ። ረዥም ጊዜ በፍቅር ከቆየን በኋላ
ከሁለት ዓመት በፊት ተጋብተን አብረን እየኖርን ነው። ከእሷ በፊት ከሌላ ሴት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት
ኖሮኝ አያውቅም። ሚስቴ ይሄ ነገር እረፍት ይነሳታል መሰለኝ ሁል ጊዜ አጀንዳ ታደርገዋለች።
"አላምንህም" ትለኛለች። አለመታመኔና ጉዳዩ የዘወትር አጀንዳ መሆኑ አበሳጭቶኝ በእልህ ከሌላ ሴት ጋር
ግንኙነት አደረግኩ። ሚስቴ እንደለመደችው ጉዳዩን ስታነሳብኝ ብልጭ ይልብኝና ልነግራት ብዬ ከአፌ
እመልሰዋለሁ። ብነግራት ሰላም ትሰጠኝ ይሆን? አንድ በሉኝ።
ቢኬ ከአዲስ አበባ
@ethiopikalink
#አልበርት_አንስታይን በዩኒቨርሲቲዎችና በየምርምር ተቋም እየዞረ ስለ ታወቂው አንፃራዊነት ቲዎሪ ሌክቸር ሲሰጥ
ሁሌም አብሮት የሚሄድ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጠው የታክሲ ሹፌር ( cab driver ) ነበረው። ሹፌሩ አነስታይን ሌክቸር ሲሰጥ በተደጋጋሚ ሰዎች በተመስጦ ሲያዳምጡ በማየቱ እሱም በትኩረት እና በተመስጦ እየተከታተለ ከሞላ ጎደል ፅንሰ ሐሳቡ በሚገባ ገብቶታል። አንድ ምሽት የተለመደውን ሌክቸር እንዲሰጥ አንስታይንን ይዞት እየሄደ ሳለ ባጋጣሚ አነስታይን
ይታመማል ሹፌሩም "እንመለስና ወደ ሆስፒታል ልውሰድህ" ቢለው አንስታይንም" በፍፁም አይሆንም ባይሆን ሌክቸሩን
ከሰጠሁ በኋላ ወደ ህክምና እሄዳለሁ" ብሎ እምቢ አለው። በዚህ ግዜ ሹፌሩም "ይህን ያህል ጊዜ አብረን ስንውል የምታስተምረውን ሌክቸሮች ከመከታተሌ ብዛት ሀሳቡ በሚገባ ስለገባኝ አንተን ተክቼ መስጠት ስለምችል አንተ አረፍ በልና እኔ ሌክቸሩን ልስጣቸው " ይለዋል።
አንስታይንም በዛ ምሽት ሌክቸሩን በሚሰጥበት ቦታ በስም እንጂ ማንም በአካል እንደማያውቀው በማወቁ በሹፌሩ ሐሳብ ተስማማና ወደ ክፍሉ ገብቶ ጥጉን ይዞ ተቀመጠ። ሹፌሩም ራሱን አነስታይን ነኝ ብሎ በማስተዋወቅ ወደ ሌክቸሩ ገባ ጥሩም አድርጎ አስተምሮ ጨረሰ ተሰብሳቢውና
የሳይንስ ተማሪዎቹ መርካታቸውን በጭብጨባ ገለጹ እሱም አመስግኖ ተሰናብቶ ሊወጣ ሲል አንድ ኘሮፌሰር ቀረብ ብሎ ፈታኝ የሆነ ነገር ግን ሆን ብሎ ለማሳጣት የፊዚክስ ጥያቄ ጠየቀው። ሹፌሩም ምንም ሣይደናገጥ ጥቂት አሰብ አደረገና " ይሄ እኮ በጣም ቀላል ጥያቄ ነው በእርግጠኝነት ሹፌሬን ብትጠይቀው በአጥጋቢ መልኩ አብራርቶ ይመልስልሀል "
በማለት በኩራት ለኘሮፌሰሩ መለሰለት ። ኘሮፌሰሩም ጥግ ላይ ተኮራምቶ የተቀመጠውን ሹፌር በንቀትና ፌዝ በተቀላቀለበት መልኩ ቢጠይቀው ሹፌሩም ( አነስታይን) ከበቂ በላይ ሰፋ ባለ መልኩ አብራርቶ መለሰለት።ኘሮፌሰሩም በጣም በመደናገጥና በመሸማቀቅ ጭንቅላቱን ደፍቶ በአግራሞት ምንም ነገር ሳይናገር ወጥቶ ሄደ።
እናም በማናለብኝነት ራስን አግዝፎና ሰቅሎ በማስቀመጥ ሌላውን ደግሞ አሳንሶ መመልከት ያልታሰበ ውርደት ውስጥ ሊከትህ ስለሚችል ወዳጄ ሆይ ሰውን አትናቅ ማንንም ቢሆን !!
👉ምንጭ ከብዕር ጠብታ @ethiopikalink
የዶክተር ያለህ!
ጤና ይስጥልኝ ኢትዮጲካሊንክ። የ40 ዓመት ሴት ነኝ። ታዳጊ እያለሁ በቤተሰብ ተገድጄ
ከገባሁበት ትዳር የ24 ዓመት ወንድ ልጅ አለኝ።የልጄን አባት ከፈታሁት በሗላ ሙሉ
ሃላፊነት ወስጄ ልጄን ለወግ ለመአረግ አድርሼዋለሁ። ችግሩ ታዲያ ልጄ ሌላ ባል
እንዳገባ አይፈልግም። የሚቀርቡኝን ወንዶች ሁሉ አቃቂር እየፈለገ ያባርርብኛል።
እባካችሁ ምን ላድርግ?
ስሜ አይጠቀስ
@ethiopikalink
#ኢትዮጲካሊንክ
በ90.7fm ላይ እስከ እኩለ ለሊት ድረስ አብረናችሁ እናመሻለን። መልካም ምሽት።
(በነገራችን ላይ የዮናስ ሃጎስ የስዕል ችሎታ እንዴት አያችሁት?)

@ethiopikalink
በሀገር ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000239345488
ሲሆን በውጭ ሀገራት ለምትኖሩ https://www.gofundme.com/help-save-fikadu-tmariam039s-life ነው ከዚህ ውጪ የሚከፈቱ አካውንቶች ከእውቅና ውጪ መሆናቸውን ጊዜያዊ ኮሚቴው አስታውቋል::
እባክዎ ሼር በማድረግ ለብዙዎች እንዲደርስ ያድርጉ:: @ethiopikalink
15/07/2010
የውስጥ አዋቂ ወሬዎቻችን ርዕሶች
ተወዳጁን አርቲስት ፈቃዱ ተክለማርያምን ለማዳን ርብርቡ ቀጥሏል
- በዘመቻው ዙሪያ ምን አዳዲስ ነገሮችን አሉ?
- ውስጥ አዋቂያችን የዘመቻውን የእስካሁን ሂደት ይነግረናል

ታዋቂው አርቲስት ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ የሚያስገቡትን ሥራዎች ለቀቀ
- ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ የሚያስገቡትን ሥራዎች የለቀቀው አርቲስት ማነው?
- አርቲስቱ ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ የሚገባው እንዴት ነው?

አወዛጋቢው የፈጠራ ሰው ለሌላ አስገራሚ ነገር እየተዘጋጀሁ ነው አለ
- ለሌላ አስገራሚ ነገር እየተዘጋጀ የሚገኘው የፈጠራ ሰው ማነው?
- ግለሰቡ አወዛጋቢ የሆነው እንዴት ነው?

ዝነኛው ጀግና ኢትዮጵያዊ ኪሳራ ደረሰበት
- ኪሳራ የደረሰበት ጀግና ኢትዮጵያዊ ማነው?
- ጀግናው ኢትዮጵያዊ የደረሰበት ኪሳራ ምንድነው? @ethiopikalink
#ሰበር_ዜና
የኢህአዴግ ምክር ቤት ዶ/ር አብይ አህመድን የግንባሩ ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ
ምክር ቤቱ ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ሲያካሂደው በቆየው ስብሰባ የድርጅቱ የታሀድሶ
ሂደት በየደረጃው የደረሰበትን ደረጃ በጥልቀት መገምገሙን አስታውቋል፡፡
በተለይ በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴና በአራቱ ብሄራዊ ድርጅቶች የግምገማ ሪፖርት ላይ
በሰፊው ተወያይቷል፡፡
የግንባሩ ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ያቀረቡትን የመልቀቂያ ጥያቄ
ተቀብሏል፡፡
ይህን ተከትሎ ምክር ቤቱ ባካሄደው ምርጫ ዶ/ር አብይ አህመድን የድርጅቱ
ሊቀመንበር በማድረግ መርጧል፡፡ @ethiopikalink
🇪🇹 #ዶ/ር አብይ አህመድ ማናቸው?
ዶ /ር አብይ በ1968 ኦሮሞ ሙስሊም ከሆኑት አባታቸው እንዲሁም አማራ ክርስቲያን
ከሆኑት እናታቸው ተወለዱ

-ዶ/ር አብይ የፕሮቴስታንት ክርስትና ሀይማኖት ተከታይ ናቸው
-ዶ/ር አብይ አማርኛ፣ ኦሮምኛና ትግርኛ ቋንቋ ይናገራሉ።
የትምህርት ዝግጅታቸው
-በ1993 ከማይክሮ ሊንክ ኮሌጅ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አገኙ
-በ1997 በ Cryptography, Machine Dynamics Cipher-ED ከደቡብ አፍሪካው
ዩኒቨርስቲ ማስተርሳቸውን ያገኙ ሲሆን

-በ2003 በእንግሊዝ ለንደን ከሚገኘው Greenwich University ሁለተኛ
ማስተርሳቸውን በTransformation Leadership and Change አግኝተዋል

-በ2005 በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ከአሜሪካው Ashland University ዩኒቪርስቲ
በርቀት ሶስተኛ ማስተርሳቸውን አግኝተዋል

-በ2009 በሰላም እና ጸጥታ ጥናት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዶክትሬት ድግሪያቸውን
ወስደዋል

-ዶ/ር አብይ በ15 አመታቸው በ1983 ኢህአዲግን ተቀላቅለው ወታደር በመሆን እስከ
ሌተናል ኮሌነርነት ድረስ የደረሱ ሲሆን ከሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ በኋላ በሩዋንዳ
የሰላም ማስከበር ስራ ላይ ተሳትፈዋል እንዲሁም ከ1999-2001 በተደረገው የኢትዮ
ኤርትራ ጦርነት ላይ የኤርትራ ጦር ያለባቸውን ቦታዎች የሚጠቁም የintelligence
ቡድን መሪ ነበር

-ዶ/ር አብይ ከ12 በላይ ተቋማት የቦርድ አባል እና የቦርድ መሪ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን
ከነዚህም መካከል
-ከ2000-2002 የETV ቦርድ አባል ነበሩ
-ከ2001-2002 የኢትዮጲያ ኮሚኒኬሽን እና ቴክኖሎጂ መስሪያቤት ቦርድ አባል ነበሩ
-ከ2000 - 2002 የኢትዮጲያ የኤሌክትሮኒክ መታወቂያ ሲስተም ማቋቋሚያ ተቋም መሪ
-በ2007 የኢትዮጲያ ፈጣን መንገዶች ቦርድ መሪ ሆነው የአዳማ የክፍያ ፈጣን መንገድን
መርተዋል
-ከ2007- 2008 የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሆነው አገልግለዋል
-ከ2008 ጀምረው የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት እና የኦሮሚያ ክልል የከተሞች
እና ቤቶች ልማት ሀላፊ ሆነው አገልግለዋል፤
ከዚህ ሁሉ ሀላፊነቶች በተጨማሪ በአንድ ወቅት በጅማ ተከስቶ የነበረውን የሀይማኖት
ግጭት ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ሰላም እንዲወርድ በሰሩት ስራ የአለም አቀፍ
የሰላም አምባሳደርነትን ሽልማት አግኝተዋል
በቀጣይ ደግሞ የኢትዮጲያ ጠቅላይ ሚኒስቴር እና የመከላከያ ጠቅላይ አዛዥ ይሆናሉ @ethiopikalink
{መታየት ያለበት }
የ ዶ/ር አብይ አህመድ የኩረጃ ገመና ሲጋለጥ በማሰርጃ የተደገፈ ቪዲዮ ይመልከቱ፤
አንዳንዶች ይሄ መኮረጅ ሳይሆን ያነበቡትን ምን ያህል ቃል በቃል እንደሚያስታውሱና
በተገቢው ሰዓት ያነበቡትን እንደወረደ ለሌሎች ማካፈል እንደሚችሉ ነው የሚያሳየው
ብለዋል
http://www.hiber123.com/mobile/watch.php?vid=ff355c3d3

@ethiopikalink
የዶክተር ያለህ!
ሰላም የኢትዮጲካሊንክ ሃኪሞች። ዓላማ ያለኝ፤ በራሴ እውቀትና ችሎታ ዓላማዬን
ማሳካት፤ ለሃገሬና ለህዝቤ የቻልኩትን አስተዋፅኦ ማበርከት እፈልጋለሁ። ነገር ግን ፈተና
በዛብኝ። ፈተናው የስራ... የህይወት ፈተና እንዳይመስላችሁ። ትልቅ ፈተና የሆነብኝ
የወንዶች ባህሪ ነው። ቁንጅናዬ የስራና የአስተሳሰብ ብቃቴን እየሸፈነብኝ ተቸግሬያለሁ።
ወንዶች ሃሳቤን ከመስማትና ስራዬን ከማየት ይልቅ አካላዊ ውበቴን ማድነቅና
መጎምጀት ይቀናቸዋል። ብዙ ወንዶች ቢሮ ሳይሆን ሬስቶራንትና ሆቴል ይቀጥሩኛል።
በዚህ ችግር ብዙ ስራ ለመቀየር ተገድጃለሁ። አሁን ግን አልቻልኩም የምወዳትን ሃገሬን
ለቅቄ ለመሄድ እየተገደድኩ ነው። እባካችሁ ሃሳቤን የሚያስቀይር ነገር ካላችሁ ንገሩኝ።
አመሰግናለሁ።
ቤላ

@ethiopikalink
22/07/2010
የውስጥ አዋቂ ወሬዎቻችን ርዕሶች
ለተወዳጁ አርቲስት ፈቃዱ ተክለማርያም ህክምና የሚደረገው ገቢ ማሰባሰብ ቀጥሏል
- የአንድ ድራማ ተዋንያን 100 ሺህ ብር ለግሰዋል
- የኢንተርኔት ዘመቻው ስኬታማ ሆኗል
- የርብርቡ አጠቃላይ ሂደት ምን ይመስላል?

ወጣቷ በቤተሰቧ ላይ አስገራሚ ድርጊት ፈፀመች
- ወጣቷ በቤተሰቧ ላይ የፈፀመችው አስገራሚ ድርጊት ምንድነው?
- ሊደመጥ የሚገባው ወሬ ነው

አንድ ኢትዮጵያዊ ትልቅ ዓለም አቀፍ ክብር አገኘ
- ትልቅ ዓለም አቀፍ ክብር ያገኘው ኢትዮጵያዊ ማነው?
- ኢትዮጵያዊው ያገኘው ዓለም አቀፍ ክብር ምንድነው?

ቀጣዩ የሃገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር ሰኞ ቃለ መሃላ ይፈፅማሉ
- የዶ/ር አብይ አህመድ የሰኞ ውሎ ምን ይሆናል?
- የትዳር ህይወታቸው ምን ይመስላል?
- ቀጣይዋ ቀዳማዊት እመቤት ማን ናቸው?
@ethipikalink
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለፓርላማ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ...
”ትላንት፣ አባቶቻችን በመተማ፣ በአድዋ፣ በማይጨውና በኦጋዴን አጥንታቸውን ከስክሰው
የከበረ ደማቸውን አፍስሰው በክብርና በአንድነት ያቆይዋት አገር አለችን። እኛ እድለኞች
ነን። ውብ አገር-አኩሪ ታሪክ አለን።
@ethiopikalink
የበረራ እንግዳችን አንጋፋው ገጣሚ፣ ደራሲ፣ የቴአትር አዘጋጅና ሃያሲ ጋሽ አያልነህ ሙላቱ ናቸው፡፡ በህይወታቸው ዙሪያ ጥሩ በረራ ይኖረናል፡፡ አያምልጣችሁ፡፡
@ethiopikalink
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ ፡፡
@ethiopikalink