EthiopikaLink/ኢትዮጲካሊንክ
322 subscribers
89 photos
12 videos
49 links
EthiopikaLink is an infotainment formatted program produced and hosted by
💥Axum Pictures💥
@Ethiopikalink በfana 98.1fm.
Download Telegram
#አልበርት_አንስታይን በዩኒቨርሲቲዎችና በየምርምር ተቋም እየዞረ ስለ ታወቂው አንፃራዊነት ቲዎሪ ሌክቸር ሲሰጥ
ሁሌም አብሮት የሚሄድ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጠው የታክሲ ሹፌር ( cab driver ) ነበረው። ሹፌሩ አነስታይን ሌክቸር ሲሰጥ በተደጋጋሚ ሰዎች በተመስጦ ሲያዳምጡ በማየቱ እሱም በትኩረት እና በተመስጦ እየተከታተለ ከሞላ ጎደል ፅንሰ ሐሳቡ በሚገባ ገብቶታል። አንድ ምሽት የተለመደውን ሌክቸር እንዲሰጥ አንስታይንን ይዞት እየሄደ ሳለ ባጋጣሚ አነስታይን
ይታመማል ሹፌሩም "እንመለስና ወደ ሆስፒታል ልውሰድህ" ቢለው አንስታይንም" በፍፁም አይሆንም ባይሆን ሌክቸሩን
ከሰጠሁ በኋላ ወደ ህክምና እሄዳለሁ" ብሎ እምቢ አለው። በዚህ ግዜ ሹፌሩም "ይህን ያህል ጊዜ አብረን ስንውል የምታስተምረውን ሌክቸሮች ከመከታተሌ ብዛት ሀሳቡ በሚገባ ስለገባኝ አንተን ተክቼ መስጠት ስለምችል አንተ አረፍ በልና እኔ ሌክቸሩን ልስጣቸው " ይለዋል።
አንስታይንም በዛ ምሽት ሌክቸሩን በሚሰጥበት ቦታ በስም እንጂ ማንም በአካል እንደማያውቀው በማወቁ በሹፌሩ ሐሳብ ተስማማና ወደ ክፍሉ ገብቶ ጥጉን ይዞ ተቀመጠ። ሹፌሩም ራሱን አነስታይን ነኝ ብሎ በማስተዋወቅ ወደ ሌክቸሩ ገባ ጥሩም አድርጎ አስተምሮ ጨረሰ ተሰብሳቢውና
የሳይንስ ተማሪዎቹ መርካታቸውን በጭብጨባ ገለጹ እሱም አመስግኖ ተሰናብቶ ሊወጣ ሲል አንድ ኘሮፌሰር ቀረብ ብሎ ፈታኝ የሆነ ነገር ግን ሆን ብሎ ለማሳጣት የፊዚክስ ጥያቄ ጠየቀው። ሹፌሩም ምንም ሣይደናገጥ ጥቂት አሰብ አደረገና " ይሄ እኮ በጣም ቀላል ጥያቄ ነው በእርግጠኝነት ሹፌሬን ብትጠይቀው በአጥጋቢ መልኩ አብራርቶ ይመልስልሀል "
በማለት በኩራት ለኘሮፌሰሩ መለሰለት ። ኘሮፌሰሩም ጥግ ላይ ተኮራምቶ የተቀመጠውን ሹፌር በንቀትና ፌዝ በተቀላቀለበት መልኩ ቢጠይቀው ሹፌሩም ( አነስታይን) ከበቂ በላይ ሰፋ ባለ መልኩ አብራርቶ መለሰለት።ኘሮፌሰሩም በጣም በመደናገጥና በመሸማቀቅ ጭንቅላቱን ደፍቶ በአግራሞት ምንም ነገር ሳይናገር ወጥቶ ሄደ።
እናም በማናለብኝነት ራስን አግዝፎና ሰቅሎ በማስቀመጥ ሌላውን ደግሞ አሳንሶ መመልከት ያልታሰበ ውርደት ውስጥ ሊከትህ ስለሚችል ወዳጄ ሆይ ሰውን አትናቅ ማንንም ቢሆን !!
👉ምንጭ ከብዕር ጠብታ @ethiopikalink