Ethio Fm 107.8
19.4K subscribers
5.77K photos
16 videos
4 files
2.26K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
ናይጂሪያ ሞተር ብስክሌትን ለደህንነት ስትል ልታግድ ነው፡፡

ናይጂሪያ ይህንን አይነት ውሳኔ ለመወሰን የተገደደችው በሞተር ብስክሌት እየተጓዙ ጥቃት የሚፈጽሙ እስላማዊ ታጣቂዎች በመበራከታቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡
ይህ ወሳኔ የተሰማው ከቀናት በፊት በሞተር ብስክሌት የሚጓዙ ታጣቂዎች በሰሜን ምዕራብ የናይጄሪያ ግዛት ካትሲና ውስጥ፣ በተለያዩ ስፍራዎች ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች አምስት ፖሊሶችን ጨምሮ 17 ንጹሀን ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ነው፡፡

በዚሁ በያዝነው ሳምንት ረቡዕ ዕለት 300 የሚሆኑ በሞተር ብስክሌት የመጡ ታጣቂዎች ካንካራ በሚባል ቦታ ላይ የሚገኝን ፖሊስ ጣቢያ ኢላማ አድርገው ጥቃት ፈጽመዋል።
እንደ ቢቢሲ አፍሪቃ ዘገባ ከሆነ እነዚሁ ታጣቂዎች በፖሊስ ጣቢያው አቅራቢያ በሚገኝ አንድ መንደር ውስጥ በመግባት ሦስት ሰዎችን ገድለዋል፤ከብቶችን ጨምሮ ሌሎች ንብረቶችንም ዘርፈዋል።

በተመሳሳይ ሌላ ጥቃት ደግሞ ታጣቂዎች ፋሳካሪ በሚባለው አካባቢ በሚገኙ በርካታ መንደሮች ውስጥ በፈጸሙት ጥቃት ዘጠኝ ሰዎችን ገድለዋል፡፡

ካትሲና ግዛት በናይጄሪያ በታጣቂዎች ከፍተኛ ጥቃት ከሚፈጸምባቸው ቦታዎች አንዷ ስትሆን የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሙሐመዱ ቡሃሪ ትውልድ ስፍራ ናት።

በያይኔአበባ ሻምበል
ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም
የሲራላካ ወታራዊ ሀይል የተቃውሞ ካምፖችን ወሯል ..የተቃውሞ መሪዎችንም ማሰራቸው ተሰምቷል፡፡

ተቃዋሚዎች አርብ ማለዳ ላይ ወታደሮች የዋና ከተማዋ ኮሎምቦ አከባቢዎችን ከተቁጣጠሩ በኃላ፣ በአንዳንዱች ላይ 'በአሰቃቂ ሁኔታ ጥቃት ደርሶባቸዋል' ብለዋል።
በስሪላንካ የሚገኘው ጦር በተቃዋሚዎች ላይ ጭካኔ በተሞላበት ሆኔታ ድብደባን ከፈጸመ በኋላ በዋና ከተማው የሚገኘውን የፕሬዚዳንቱን ሴክሬታሪያት ተቆጣጥሯል።
በጎታጎጋማ የተቃውሞ ቦታ ላይ በወታደሮቹ በርካታ ድንኳኖች ወድመዋል፣ከ100 በላይ የተቃውሞ ሰልፈኞች ታስረዋል፤ በርካቱችም ተከበዋል ብሏል፤ የአልጀዚራ ዘገባ፡፡
የሲሪላንካው አዲሱ ፕሬዝዳንት ራኒል ዊክርሜሲንግህ በመላው አገሪቱ የሚጸና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸው ብዙዎችን ያስቆጣ ነበር።

ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ተላልፈውታል። በወቅቱ ዊክርሜሲንግህ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተላለፉትን “ፋሺስቶች” ሲሉ ጠርተዋቸዋል።

ፕሬዝደንቱ ጨምረውም ወታደራዊ ኃይሉ የሀገሪቱን ሰላም እና ጸጥታ እንዲያስጠብቅ መመሪያ ማሳለፋቸውን ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ የተጠናከረ የቁጥጥር ስራ እየተሰራ ስለመሆኑ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም
በኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 800 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ድርቤ ወልተጂ ወደ ፍፃሜ አልፋለች።
ፀሐይ ባንክ በዛሬዉ እለት በይፋ ስራ ጀምሯል፡፡

ባንኩ በ30 ቅርንጫፎቹ ዛሬ ወደ ስራ መግባቱን ነዉ ያስታወቀዉ፡፡

ባንኩ በ2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር የተፈረመና በ734 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ተቋቁሟል፡፡
“ለሁሉ” በሚል መሪ ቃል ዛሬ ሐምሌ 16 ቀን 2014 በይፋ ሥራ የጀመረዉ ባንኩ፣ ዝቅተኛ የአክሲዮን ግዢውን ከብር 100 ሺህ በመጀመር፣ በ373 ባለአክሲዮኖች መመስረቱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

“ለሁሉም የሆነ ባንክ” እንዲሆን የአገልጋይነትን ዕሴትን ተላብሶ ስራ ጀምሯል የተባለው ባንኩ፣ ዛሬ 30 ቅርንጫፎች የባንክ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ተገልጿል፡፡
በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ፣30 ባንክ እና 40 የማይክኦሮ በአጠቃላይ ከ80 በላይ የፋይናንስ ተቋማት እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡
የባንኮች ተልእኮ የህዝብን የቁጠባ ባህል ለማዳበር እና የብድር አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ መሆኑን ጠቁመዉ፣ በአሁኑ ወቅት ለባንኮች በገበያ ደረጃ የሚያሳስብ ነገር እንደሌለም አመልክተዋል፡፡

ዘግይተው ገበያውን የተቀላቀሉ ባንኮች በቀላሉ ስኬታማ መሆን የሚችሉበት የቴክኖሎጂ ዘመን ላይ እንገኛለን ያሉት ዋና ገዥዉ፣
ገበያው ለውጭ ባንኮች የሚከፈት መሆኑ አይቀሬ በመሆኑ ለሚገጥማቸዉ ዉድድር ራሳቸዉን አዘጋጅተዉ እንዲጠብቁም አሳስበዋል፡፡
ጸሃይ ባንክ በይፋ ስራ መጀመሩን ምክንያት በማድረግ ለ4 ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ማለትም፤
ለጌርጌሴኖን 300ሺህ ብር፣ለኒያ ፋውንዴሽን 300ሺህ ብር፣ለኩላሊት ህመምተኞች በጎአድራጎት ድርጅት 500ሺህ ብር እንዲሁም ለኢትዮጲያ የልብ ህሙማን ማእከል 500ሺህ ብር የስጦታ ገንዘብ አበርክቷል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር
ሐምሌ 16 ቀን 2014 ዓ.ም
የአላሰካ አየር መንገድ በረራ በአብራሪዎቹ ጸብ ምንክኒያት መዝግየቱ ተገለጸ።

ከዋሽንግተን ተነስቶ ወደ ሳንፍራንሲስኮ ሊበር የነበረዉ የአላስካ አዉሮፕላን ቦይንግ 737 በአብራሪቹ ፀብ ምክንያት ወደ ተርሚናሉ እንዲመለስና ተጨማሪ ሰአት እንዲዘይ መገደዱን አየር መንገዱ አስታውቋል ፡፡

ጸቡ ሲፈጠር ተሳፋሪዎች በአዉሮፕላኑ ውስጥ ሆነው ጉዟቸውን ሲጠባበቁ ነበር።

7፡05 የበረራ ሰአቱን ይጨርሳል የተባለዉ አዉሮፕላን ከታቀደለት ሰአት ዉጪ ሁለት ሰአት በመዘግየት 9፡34 በረራዉን አጠናቋል ነው የተባለው።

ካፒቴኑና የመጀመሪያ መኮንኑ ለምን በረራዉ ዉስጥ ጸብ እንደተፈጠሩ ግልጽ ምክንያት አልተነገረም።

አየር መንገዱ ግን ድርጊቱን የሙያ አለመግባባት በማለት ጉዳዩን ቀለል ለማድረግ መሞከሩን ሀፊንግተን ፖስት ዘግቧል።

በቤዛዊት አራጌ
ሐምሌ 16 ቀን 2014 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
ዌብሳይት https://ethiofm107.com/
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
በኬንያ የድምጽ መሰብሰብ ሂደቱን ለማጨበርበር ሙከራ ያደረጉ ሶስት ባለሞያዎች በቁጥጥር ስራ ዋሉ፡፡

በኬኒያ ሊደረግ ከታሰበው ሃገራዊ ምርጫ ቀደም ብሎ በሚሰበሰበው ድምጽ ላይ የማጭበርበር ሙከራ ያደረጉ ሶስት ተጥርጣሪዎች በሃገሪቱ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተነግሯል፡፡

የምርጫ ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው፣ ተጠርጣሪዎቹ “ስማርት ማቲ” የተባለ የምርጫ ቴክኖሎጂ ድርጅት ሰራተኞች ናቸው፡፡
ኮሚሽኑ አክሎም በፈረንጆቹ ነሃሴ 9 ከሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ ቀደም ብሎ የተሰበሰበው ድምጽ በርካታ ትችቶች እየተሰነዘሩበት ይገኛል፡፡

ከዚህም የተነሳ ተጠርጣሪዎቹ ጥፋተኛ ሆነው የሚገኙ ከሆነ ከፍተኛ ቅጣት እንደሚጥብቃቸው ዘገባው አመላክቷል፡፡
በሌላ በኩል የተጠርጣሪዎቹ ለእስር መዳረግ በምርጫው ላይ ከፍተኛ የሆነ ውጥረትን ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋቶች እየተሰሙ መሆኑ ተግልጿል።

በዚህ ድርጊት ላይ ተሳታፊ ናቸው ከተባሉ ሰዎች መካከል እንዱ የውጪ ሃገር ዜጋ ሲሆን፤ስለተቀሩት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ግን የተባለ ነገር እንደሌለ የአልጀዚራ ዘገባ አመላክቷል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን
ሐምሌ 16 ቀን 2014 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
ዌብሳይት https://ethiofm107.com/
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
በሴቶች በ5ሺህ ሜትር ጉደፍ ፀጋይ የወርቅ ዳዊት ስዩም የነሃስ ሜዳሊያ አሸንፈዋል!

ለተሰንበት ግደይ 5ኛ ሆና አጠናቃለች::
Audio
የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን 18-11-14
የተሰረዘው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ይወጣል ተባለ፡፡

ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በይፋ ዕጣ ከወጣበት በኋል የማጭበርበር ከባድ የሙስና ወንጀል ተፈጽሞበታል ተብሎ፣ ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ የተደረገው የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ እንደሚወጣ ተገልጧል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙኃን እንዳስታወቁት፣ ትክክለኛ ቀኑን እርግጠኛ ሆኖ መናገር ባይቻልም፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ይወጣል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ በቅርብ ለማውጣት ሌላ ሶፍትዌር እንደሚጠቀሙና፣ ጥራቱ መረጋገጥ እንዳለበት ጠቁመው፣ ትንሽ መታገስ አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል።

ቤቱን የሚጠባበቀው ሕዝብ ለጥራት ቅድሚያ እንዲሰጥና አስተዳደሩም በጥራት ለመሥራት የሚችለውን ሁሉ ጥረትና ጥንቃቄ እንደሚያደርግ ጠይቀዋል።

ከንቲባዋ ወ/ሮ አዳነች በድርጊቱ የተጠረጠሩ 16 የሚደርሱ የአስተዳደሩ ሠራተኞችም በሕግ ቁጥጥር ሥር መሆናቸውንና ሌላም የሚመለከተው ሰው ካለም ሕግ የማስከበር ዕርምጃው ይቀጥላል፤›› ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊን
ሐምሌ 18 ቀን 2014 ዓ.ም
ኬንያ ወደ ሶማሊያ በድጋሚ ጫት መላክ ጀምራለች፡፡

የኬንያዉ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የሶማሊያዉ አቻቸዉ ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በጋራ ምክክር ካካሄዱ በኋላ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለዉ ድንበር ክፍት እንዲሆን ተስማምተዋል፡፡

በዚህም የንግድ ዝዉዉሩ እንዲፋጠን ባደረጉት ስምምነት መሰረት ኬንያ በድጋሚ ወደ ሶማሊያ የጫት ምርት መላክ ጀምራለች፡፡

የኬንያዉ ግብርና ሚኒስቴር በትናንትናዉ ዕለት ጫት የጫነ የጭነት አዉሮፕላን ወደ ሞቃዲሾ መብረሩን ገልጸዋል፡፡

ሶማሊያ በፈረንጆቹ 2020 ከኬንያ ጋር በተፈጠረ የባህር ድንበር ዉዝግብ ምክንያት ከኬንያ ምንም አይነት የጫት ምርት ወደ ሀገሯ እንዳይገባ ዕገዳ ጥላ ነበር ፡፡

ከሶማሊያዉ ፕሬዝዳንት ድጋሚ ወደ ስልጣን መምጣት በኋላ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለዉ ግንኙነት እየተሻሻለ የመጣ ሲሆን፣ የሀገራቱ ነባራዊ ሁኔታም ሰላማዊ እና የረገበ እንደሆነ ሲጂቲኤን አፍሪካ ነዉ የዘገበዉ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

በእስከዳር ግርማ
ሐምሌ 18 ቀን 2014 ዓ.ም
የቱኒዚያን ህገ-መንግስት ለማሻሻል ዜጎች ህዝበ ዉሳኔ መስጠት ጀምረዋል::

በቱኒዚያዉ ፕሬዝደንት ካይስ ሰኢድ የቀረበዉን አዲስ ህገ መንግስት መቀበል አለመቀበል ላይ ድምጽ መስጠት መጀመሩን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ሃገሪቱን ወደ አምባገነናዊ አገዛዝ ሊወስዳት ይችላል ያሉትን ሂደት፤ ህጋዊ ለማድረግ በሚደረገዉ ጥረት ላይ ብዙዎች አድማ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የፕሬዝዳንታዊ ስርአትን ለመፍጠር ምን ጊዜም አዲስ ህገ መንግስት ማስተዋወቅ የ ካይስ ፕሮጀክት አካል እንደነሆነ ነዉ የተነገረዉ፡፡

የህግ አዉጭዉ ምርጫ ምንም ይሁን ምን ፕሬዝደንቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የመመረጥ ከፍተኛ እድል እንዳላቸዉም አየተነገረ ነዉ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

በቤዛዊት አራጌ
ሐምሌ 18 ቀን 2014 ዓ.ም
ያለኝ የደም ክምችት ለአምስት ቀናት ብቻ የሚሆን ነዉ---የኢትዮጵያ ደምና ቲሹ ባንክ አገልግሎት፡፡

በአሁኑ ሰዓት በቀን ከ250 ዩኒት አስከ 300 ዩኒት ደም እየተሰበሰበ መሆኑን የኢትዮጲያ ደም እና ቲሹበ ባንክ ተናግሯል፡፡

ጊዜው የክረምት ወቅት እንደመሆኑ የደም መለገስ ተግባሩ በከፍተኛ ሁኔታ መቀዛቀዙን ነግሮናል፡፡

የዛሬ አመት በህግ ማስከበር ዘመቻው የነበረው አይነት መነቃቃት ዓለመኖሩ የኢትዮጵያ ደም እና ቲሹ ባንክ ም/ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሃብታሙ ታዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓትም በቀን ከ250 ዩኒት ደም እስከ 300 ዩኒት ደም እየተሰበሰበ ቢሆንም ወደ ክልል ከተሞችና ለመንግስት ሆስፒታሎች በዛው ልክ እየወጣ በመሆኑ ያለው ክምችት አገልግሎት ላይ ቢውል ከ5 በላይ አያገለግልም ነው ያሉት፡፡

የተከሰተዉ እጥረት እንደየ የደም አይነቱ የሚለያይ ቢሆንም ፕላትሌት የተሰኘው የደም አይነት የደም አይነት “O” እና የደም አይነት ‘’- O’’ መሆኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ቀደም ሲል ከነበረው የፆም ወቅት እና የበአል ወቅት በመሆኑ የደም ልገሳ ልምዱ መቀነሱን ከብሄራዊ ደም ባንክ የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

አሁን የደም እጥረቱ ያለመሻሻሉን ብሎም ክምችቱ ከ5 ቀን በላይ እንደማያገለግል ሰምተናል፡፡

በደም ባንክ የደም እጥረት ሲያጋጥም በየ ሆስፒታሎች ደግሞ የደም ፍላጎት ስለሚጨምርም በዚህ ፍጥነት አገልግሎት ማግኘት ያለባቸው ታካሚዎች መደራረብን ያመጣል ተብሏል።

ለዚህም ሲባል የደም ልገሳውን ህብረተሰቡ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡ ብሔራዊ የደም ባንክም በተለያዩ ቦታዎች ዘመቻዎችን በማድረግ ድንኳኖችንም በመትከል በጎ ፈቃደኞች ደም እንዲለግሱ የማድረግ ስራ እየሰራ መሆኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
ሐምሌ 18 ቀን 2014 ዓ.ም
በትግራይ ክልል በተለያዩ ዞኖች በግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው የውሃ አውታሮች ተጠግነው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ፡፡

በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ እና ማዕከላዊ ዞኖች በግጭት ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የውሃ አውታሮች ጥገና ተደርጎላቸው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

በግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የውሃ አውታሮች ወደ ነበሩበት ለመመለስ÷ የውሃ ፓምፖች፣ ጄኔሬተሮች እና የውሃ ማጣሪያ ኬሚካሎችን በመለገስ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ መደረጉን የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ መረጃ ያመላክታል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 18 ቀን 2014 ዓ.ም
የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችንን ይከታተሉ፦


በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ12:30-2:30)


-ከቤት ሳንወጣና ስፖርታዊ ጉዳዮችን ትሰማላችሁ

- በመንገዳችን ላይ፦በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች የዘመሙ የኤሌክትሪክ ሀይል ተሸካሚ እንጨቶች በተለይም በህጻናት እና አረጋዊያን ህይወት ላይ አደጋ ደቅነዋል፤ ለምን? ከጥንቅሩ ትሰሙታላችሁ።

- ለጤናችን፦ በታሸጉ ምግቦች ውስጥ የሚገኘው ትራንስ ፋቲ አሲድ ብዙዎችን ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች እየዳረገ ይገኛል።

መፍትሄው ምን ይሆን? የባለሙያ ምክረ ሀሳብ ይዘንበታል።

- በፍተሻ ሰዓታችን፦ ሩሲያና አሜሪካ ኢትዮጵያን የግላቸው ለማድረግ በዛሬው ዕለት ይፋዊ ዘመቻ ይጀምራሉ።

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ።
የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛም በተመሳሳይ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።

ሁለቱ አገራት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያን ለምን መረጡ?

በዚህ ጉዳይ የህግና የፖለቲካ ባለሙያዎችን አስተያየት እንዲሁም የኤምባሲዎችን ምላሽ አካተናል፤ ጉዳዩን ፈትሸነዋል።


-በኢትዮ ገበያችን ፦
በከፍተኛ የዋጋ ንረትና በውጭ ምንዛሬ እጥረት እየተጨነቀች ለምትገኘው ሀገራችን ኢትዮጵያ መተንፈሻ መፍትሄው ይህ ነው ሲል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ጥናቱን ይፋ አድርጓል፤ ትሰሙታላችሁ።

-በዓለም ጉዳይ፦ በቱኒዝያ ህዝቡና መሪዋ የተለያየ ጉዞ ጀምረዋል።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ካይስ ሰኢድ ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ ህገ መንግስቱ ይሻሻል እያሉ ነው፤
ብዙሀኑ ቱኒዚያዊያን ግን ይህን አይፈልጉም።

ህዝብና መንግስት በዚህ ልዩነት ውስጥ ሆነው ህገ መንግስቱን ለማሻሻል ድምጽ መስጠት ተጀምሯል፤ በትንታኔ አዘጋጅተንላችኋል።


-በኮሮና ቫይረስ የተጠቁት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ማገገማቸው ተነግሯል።

- በሳውዲ ዓረቢያ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ተጠቂዎች ተገኝተዋል።

- እንዲሁም ሌሎች አዳድስ የሀገር ውስጥና ዓለምዓቀፋዊ ጉዳዮችንም አሰናድተንላችኋል

እንድታደምጡ ተጋብዛችኋል።

ለአስተያየትዎ '6321' አጭር የጽሁፍ መልዕክት

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
# ኢትዮጵያና ሩሲያ

በዛሬዉ እለት የሩስያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ።
ላቭሮቭ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ለማድረግ ነው ዛሬ አዲስ አበባ የሚገቡት።

በአዲስ አበባ ቆይታቸው ፦

- በኢትዮጵያ እና ሩስያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ፤
- ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ እና ሩስያ መካከል የተፈረሙ ስምምነቶች ላይ ይመክራሉ፤
- ከአፍሪካ ህብረት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ላቭሮቭ በፈረንጆቹ 2018 ላይ ኢትዮጵያን ጎብኝተው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም