Ethio Fm 107.8
20.6K subscribers
7.93K photos
16 videos
4 files
2.31K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
10 ሽህ ብር ጉቦ ስትቀበል እጅ ከፍንጅ ተያዘች፡፡

የመሬት አስተዳደር የንብረት ግምት ባለሙያ የሆነች አንዲት ግለሰብ 10 ሺ ብር ጉቦ ስትቀበል እጅ ከፍንጅ መያዟን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

የጉለሌ ክ/ከተማ የመሬት አስተዳደር የንብረት ግምት ባለሙያ የሆነችው ግለሰብ አንድን ባለ ጉዳይ ጉዳይህን እኔ እጨርስልሀለሁ በማለት 10ሺ ብር ጉቦ ስትቀበል ሀምሌ 6 ቀን 2014 ዓ/ም እጅ ከፍንጅ ተይዛ አስፈላጊው ምርመራ ተጣርቶ ክስ እንደተመሰረተባት የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የግል ተበዳይ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከድንበር ጋር የተያያዘ ጉዳዩን ለማስጨረስ በሄደበት አጋጣሚ ግለሰቧ 30 ሺህ ብር ጉቦ የጠየቀችው ሲሆን 10ሺ ብር ቅድሚያ እንደሰጣት እና ቀሪውን 20 ሺህ ብር ደግሞ ጉዳዩ ሲያልቅ ለመወሰድ መጠየቋን የግል ተበዳይ ለክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ አሳዉቋል፡፡
በመሆኑም ሐምሌ 8 ቀን 2014 ዓ/ም ጉቦውን ስትቀበል በፖሊስ እጅ ከፍንጅ ተይዛ አስፈላጊው ምርመራ ተጣርቶ ክስ እንደተመሰረተባት የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡
ማህበረሰቡ መሰል ወንጀል ፈፃሚዎችን ለህግ አካል አጋልጦ የመስጠት ልምዱ ይበል የሚያሰኝ ተግባር መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ተናግሯል፡፤
ወደፊትም ህዝብን እና መንግስትን የሰጣቸውን እምነት በማጉደል በማህበረሰቡ ላይ በደል የሚፈጽሙ አካላትን ወደ ህግ ለማቅረብ የሚደረገው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብሏል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም
የኢራኑ ናሽናል እና የሩሲያዉ ጋዝ ፕሮም ታሪካዊ ነዉ ያሉትን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የኢራን ናሽናል ነዳጅ ኩባንያ እና የሩሲያዉ ነዳጅ አምራች ጋዝ ፕሮም ወደ 40 ቢሊዮን የሚጠጋ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸዉን የኢራን የነዳጅ ሚኒስቴር ዜና ወኪል ሻና ዘግቧል፡፡
የኢራን ባለስልጣናት እንደገለጹት 20 ሚሊዮኑ ለኪሽ እና ለሰሜናዊ ፓርስ የጋዝ ማምረቻ የሚከፋፈል ሲሆን፤በቀን የ100 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ተጨማሪ ጋዝ እንዲያመርቱም ይረዳል ነዉ የተባለዉ፡፡

የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከኢራኑ አቻቸዉ ጋር ለመምከር ወደ ቴህራን ባቀኑበት ወቅት የሁለቱም ኩባንያ ሃላፊዎች በኦንላይን ባደረጉት ዝግጅት ነዉ ስምምነቱ የተፈረመዉ፡፡
ጋዝ ፕሮም የኢራን ናሽናል ነዳጅ ኩባንያን የኪሽ እና ሰሜናዊ ፓርስ የጋዝ ማምረቻ ቦታዎችን በማልማት ረገድ እንደሚደግፋት እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ ስድስት የጋዝ ማምረቻ ቦታዎችን በማልማትም ትብብር እንደሚያደርግ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ጋዝ ፕሮም ከዚህ በተጨማሪም የተፈጥሮ ጋዝ አምራች ፕሮጀክትን እና የጋዝ ማስተላለፊያ ቱቦዎችን በመገንባት ኢራንን እንደሚረዳ ተገልጿል፡፡

ኢራን ከሩሲያ በመቀጠል በዓለም ሁለተኛዋ ከፍተኛ የጋዝ ክምችት ያላት ሀገር ብትሆንም፣ የአሜሪካ ማዕቀብ ከቴክኖሎጂ ጋር ግንኙነት እንዳይኖራት ያቀባት በመሆኑ ወደ ዉጭ የሚላከዉ የጋዝ ዕድገት አዝጋሚ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
የሩሲያ-ዩክሬንን መዉረር በዓለም ነዳጅ እና የነዳጅ ገበያዉ ላይ ባሳደረዉ ተጽዕኖ ምክንያት የፑቲን የቴህራን ጉብኝት በከፍተኛ ሁኔታ የዓለምን ትኩረት የሳበ እንደሆነ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም
በትላንትናው እለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ ስምንት ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደረሰባቸዉ፡፡

ከአዲሱ ገበያ ወደ ፒያሳ በማቅናት ላይ የነበረ አይሱዙ የጭነት መኪና መንገድ በመሳቱ ምክንያት ነው አደጋው የደረሰው፡፡
በአደጋው ምክንያትም ስምንት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አቤት ጠቅላላ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

እንደዚሁም በአካባቢው የነበሩ አምስት መኪኖችም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
አደጋ ያደረሰው የጭነት መኪናው መንገድ ስቶ ስለነበረ በሁለት የንግድ ሱቆች ላይም የንብረት ጉዳት ማድረሱ ነው የተነገረው፡፡
ዜናዉ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ያለዉ መረጃ ይህ ነዉ፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም
ቻይና አሜሪካ በህዋ ላይ የምታደርገዉን ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንድታቆም አሳሰበች::

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን ዋሽንግተን በህዋ ላይ የምታደርገዉን ወታደራዊ እንቅሰቃሴ እንድታቆም አሳስበዋል፡፡
አሜሪካ በህዋ ላይ ትጥቅ በመታጠቅ ላይ ነች ያሉት ቃል አቀባዩ፣ከድርጊቷ በመቆጠብ የህዋ ደህንነትን ማስጠበቅ አለባት ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አሜሪካ በህዋ ላይ የበላይነትን የማስፈን ስትራቴጅንና እንደ ዳይሬክት ኢነርጅ፤የተቆጣጣሪ ኮሙኒኬሽን ሲስተም በመዘርጋት ላይ እንደምትገኝም ተነግሯል፡፡
አገሪቱ አደገኛ የውጭ ጠፈር መሳሪያዎችን በከፍተኛ ሁኔታ በማዘጋጀትና በማሰማራት ላይ ትገኛለች ስትልም ቻይና ከሳለች፡፡
በተጨማሪም ዋሽንግተን በአለም አቀፍ ስትራቴጂካዊ መረጋጋት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል በተባለዉ ጠፈር ላይ ስለላ ስለመጀመሯም ቤጂንግ ማስታወቋን ሲ ጂ ቲኤን ዘግቧል፡፡

በቤዛዊት አራጌ
ሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም
በ3 ሺህ የሴቶች መሰናክል ኢትዮጵያ የብርና ነሐስ ሜዳልያ አገኘች።


በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ንጋት ላይ በተካሄደ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል የፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያ የብርና የነሐስ ሜዳሊያዎች አገኘች።

አትሌት ወርቅውሃ ጌታቸው የብር እና መቅደስ አበበ የነሐስ ሜዳሊያዎችን አስገኝተዋል።

የወርቅ ሜዳሊያውን የካዛኪስታን አትሌት አግኝታለች።

ኢትዮጵያ ሶስት የወርቅ፣ አራት የብር እና አንድ የነሃስ ሜዳሊያዎችን በመያዝ ከአሜሪካ ቀጥላ በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጣለች።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም
Audio
የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን 14-11-14
በሀገራችን ከ40 በመቶ በላይ የሞት ምጣኔ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚከሰት ነዉ ተባለ፡፡

በሀገራችን ካለው የሞት ምጣኔ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስደው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚከሰት ሞት መሆኑ ተገልጿል።

ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር፣ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እያደረሱ ያሉት ጉዳት በሚል ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

የማህበሩ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ ጌትነት እንደተናገሩት፣ በሀገራችን ከሚከሰት ሞት ውስጥ 40 በመቶው የሚከሰተው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ነው።

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በሀገራችን ስር እየሰደዱ እንደሚገኙ ያነሱት ምክትል ዳይሬክተሩ ለዚህ ጉዳይ መባባስ ብዙ ምክንያቶች እንዳሉ ያነሳሉ።

አሁናዊው በሀገራችን ያለው የአመጋገብ ስርዓት አንዱ መሆኑን ያነሱት አቶ አክሊሉ፣ በይበልጥ በወጣቱ ዘንድ የተለመደው በፋብሪካ የተቀነባበሩ የታሸጉ ምግቦችን መመገብ ሲሆን፣ ይህም ተላላፊ ላልሆኑ የበሽታ አይነቶች ተጋላጭነታቸው እንደሚጨምር እንደሚያደርግ አንስተዋል።

ሌላው እና ዋናው ምክንያት ነው ተብሎ የሚነሳው ደግሞ ትምባሆ ማጨስ ፣አልኮል መጠቀም እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ ናቸው።

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ተብለው የሚጠቀሱት የልብ ህመም ፣ካንሰር ፣የመተንፈሻ አካላት ህመም ፣የደም ግፊት እንዲሁም የስኳር ህመም ናቸው ።
በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው የሞት ምጣኔ 71 በመቶው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ሲከሰት ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአመት በአለም 41 ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸውን ያጣሉ ተብሏል።

በእስከዳር ግርማ

ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም
ሰርጌ ላቭሮቭ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኝው የሩስያ ኤምባሲ እንዳስታወቀዉ የሩስያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ፡፡

ኢምባሲው በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሐምሌ 19-20 ድረስ በአዲስ አበባ ቆይታ የሚያደርጉ ሲሆን የጉብኝታቸው ዋና ዓላማ እየተጠናከረ የመጣው የራሽያ -አፍሪካ ግንኙነት መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ያላቸውን ጉብኝት እንዳገባደዱ በራሽያ- አፍሪካ ጉባኤ ዝግጅት ዙሪያ ለጋዜጠኞች እና ለዲፕሎማቲክ አባላት ሐምሌ 20/2014 ዓ.ም በኢምባሲው ግቢ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ጨምሮ ገልጿል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም
የዩክሬኗ ቀዳማዊት እመቤት አሜሪካን ተማጽነዋል፡፡

የዩክሬን ቀዳማዊት እመቤት ኦሌና ዜኔኒስካ የአሜሪካ ኮንገረስን አጥብቀው መማጸናቸው ተነግሯል፡፡

ኦሌና ኮንግረሱን የተማጸኑት ከፍተኛ የጦር መሳርያዎችን ለሀገራቸው እንዲሰጥ ነው ተብሏል፡፡
ከሩስያ ጋር እያደረግነው ያለነው ጦርነት ለኛ ብቻ አይደለም፣ እኛን ለመሳሰሉ ሀገራት ጭምር ነው ሲሉም ተናግረዋል ኦሌና፡፡

አሜሪካ ጦርነቱ ከተጀመረበት ቀን አንስቶ እጅግ ዘመናዊ የተባሉ የጦር መሳርያዎችን ወደ ዩክሬን መላኳን የተናገሩት ቀዳማዊት እመቤቷ፣ አሁንም ተጨማሪ መሳርያ ያስፍልገናል ብለዋል፡፡
ከሩስያ ጋር በቀላሉ መዋጋት የሚቻል አይደለም፣ በመሆኑም በፍጥነት እርዳታችሁ ያስፈልገናለ ሲሉ ጥሪያቸውን አቀርበዋል፡፡

ኦላና ይህንን የተናገሩት በዋሽንግተን ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ላይ ነው፡፡
ቀዳማዊት እመቤቷ በተደጋጋሚ የጦር መሳርያ የጦር መሳርያ ሲሉ ጥሪያቸውን ለኮንግረሱ አሰምተዋል፡፡
የዩክሬን ቀዳማዊት እመቤት ከዚህ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ስለጦርነቱ ተጠይቀዉ በዚህ ምድር ላይ ባሌን ከኔ የሚነጥቀኝ ማንም የለም ጦርነትም ቢሆን ሲሉ ተናግረው ነበር፡፡
አሁን ጦርነቱ እቤታቸው የደረሰ የመሰላቸው ቀዳማዊት እመቤቷ የድረሱልን ጥሪያቸውን እያሰሙ እንደሚገኙ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም
ፀሐይ ባንክ ሐምሌ 16 ቀን 2014 በይፋ ሥራ ጀምራለሁ ብሏል፡፡

ባንኩ በ2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር የተፈረመና በ734 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ተቋቁሟል፡፡

“ለሁሉ” በሚል መሪ ቃል የፊታችን ሐምሌ 16 ቀን 2014 በይፋ ሥራ እንደሚጀምር ያስታወቀው ባንኩ፣ ዝቅተኛ የአክሲዮን ግዢውን ከብር 100 ሺህ በመጀመር፣ በ373 ባለአክሲዮኖች መመስረቱን አስታውቋል፡፡

የመስራች ጉባኤውን የካቲት 11 ቀን 2013 በማካሄድ የባንክ ኢንዱስትሪውን መቀላቀሉን የባንኩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ያሬድ መስፍን አስታዉሰዋል፡፡

ዓላማችን የባንክ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን በፋይናንስ ዘርፉ በቂ ትኩረት ያላገኙትን የስራ ፈጠራን እና የስራ ፈጣሪዎችን፤ የጥቃቅንና አነስተኛ፣ የግብርናውን ዘርፍ እንዲሁም የአምራች ኢንዱስትሪውን ተደራሽ ለመሆን አልመናል ብለዋል፡፡
“ለሁሉም የሆነ ባንክ” እንዲሆን የአገልጋይነትን ዕሴትን ተላብሶ ሃምሌ 16 ስራ ይጀምራል የተባለው ባንኩ፣ በእለቱ 30 ቅርንጫፎች የባንክ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ተገልጿል፡፡

በቅርቡም ባንኩ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ከ50 በላይ የማሳደግ እቅድ ያለው መሆኑን የገለፀ ሲሆን፣ በአንድ አመት ውስጥም በመላው የሃገራች አካባቢዎች 100 የሚሆኑ ቅርጫፎችን ወደ ስራ ለማስገባት ማቀዱን ባንኩ ይፋ አድርጓል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር
ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም
የኩላሊት ታማሚዎች ለሚደረግላቸዉ የኩላሊት እጥበት በወር እስከ 42 ሽህ ይጠየቃሉ ተባለ፡፡

የኩላሊት ሕመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ፤በዓሁኑ ወቅት ለኩላሊት እጥበት የሚሰጠዉ ትኩረት እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም በቂ ግን አይደለም ብለዋል፡፡
ህሙማኑ አሁንም ችግር ውስጥ መሆናቸውን አቶ ሰለሞን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በድርጅቱ ዉስጥ የክልል እና ገጠር ከተሞችን ሳይጨምር በአዲስ አበባ ብቻ፣ ኩላሊት እጥበት የሚያከናውኑ ከ3 ሽህ 500 በላይ ታማሚዎች ይገኛሉ ነዉ ያሉት፡፡
እነዚህ ታማሚዎችም በግል ሆስፒታሎች ለአንድ ጊዜ እጥበት በትንሹ ከ1 ሽህ 950 እስከ 3 ሽህ 500 ብር በሳምንት ለሶስት ጊዜ እንደሚያወጡ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ይህም በወር በትንሹ ከ23 ሺህ 400 እስከ 42 ሺህ ብር የሚጠጋ ወጭ ለኩላሊት ለዕጥበት እንደሚያወጡ ተናግረዋል፡፡
ሁሉም ነገር ዋጋዉ በጨመረበት በዚህ ወቅት እነዚህ ህሙማን የሚደርስባቸዉን የፋይናንስ ጫና ለማቃለል ሁሉም የቻለዉን ትብብርና ድጋፍ ቢያደርግ መልካም መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ

ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም
ትኩረት

የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኤሌክትሪክ አቅርቦት፡-

የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አርብ ሃምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ስራ ያከናውናል፡፡

በዚህም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ በሲቪል ሰርቪስ ፊት ለፊት፣ በሲ ኤሚ ሲ ልዩ ቤቶች፣ በተባበሩት፣ በሲ ኤ ሚ ሲ ሚካኤል እና አካባቢዎች፤

እንዲሁም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ በአያት 49 ማዞርያ፣ በአየር መንገድ ቤቶች፣ በአያት 2፣ 3፣ 4 ኮንደሚኒየም፣ በቦሌ አራብሳ እና አካባቢዎቻቸው ኤሌክትሪክ ይቋረጣል፡፡

በመሆኑም በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞቹ ይህንን ተገንዝበዉ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳስቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም
የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኮቪድ 19 መያዛቸዉ ተነገረ፡፡

ነጩ ቤተመንግስት በዛሬዉ እለት እንዳስታወቀዉ፣ባይደን በኮቪድ 19 መያዛቸዉ የተረጋገጠዉ በዛሬዉ እለት ነዉ፡፡

ፕሬዝዳንቱ የኮቪድ 19 ክትባትን በተሟላ መልኩ መዉሰዳቸዉና ማጠናከሪያ/ቡስተር/ ወስደዉ እንደነበርም ተነግሯል፡፡

የ79 ዓመቱ ባይደን በአሁኑ ወቅት ደረቅ ሳል፣ድካምና ሌሎች የህመም ስሜቶች እንደሚታዩባቸዉም ሲ ኤን ቢሲ ዘግቧል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም
Audio
የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን 15-11-14
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ታጣቂዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የፈጸሙት ጭፍጨፋ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ አምነስቲ ጠየቀ፡፡

ድርጅቱ በጥቃቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተገደሉ ከዓይን ምስክሮችና በሕይወት ከተረፉ ሰዎች ሰምቻለሁ ብሏል፡፡
የጥቃቱ ፈጻሚዎች የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መሆናቸውን ከጥቃት የተረፉ ሰዎች ነግረውኛል ሲልም አምነስቲ አክሏል።

ጥቃቱ እንደተጀመረ የአካባቢው አስተዳደር መረጃው ቢደርሰውም፣ መንገዱ ተዘግቷል በማለት ጸጥታ ኃይል ሳይልክ እንደቀረ አምነስቲ ከምንጮቹ ማረጋገጡን መጥቀሱን ዋዜማ ሬድዮ ዘግባለች፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም