Ethio telecom
329K subscribers
7.01K photos
123 videos
122 files
2.35K links
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Download Telegram
STAY SAFE! #Huawei_4G_Modem is on SALE! Buy now and stay connected! Follow our Instagram page https://www.instagram.com/ethiotelecom/
Stay Safe!
Looking for a super-fast internet connectivity? #Huawei_E5785 _92C_4G_WiFi_Modem is here to meet your demands! NOW AVAILABLE FOR SALE @ OUR SHOPS!
Follow our Instagram page https://www.instagram.com/ethiotelecom/
የኔትወርክ ኮኔክሽን ያልደረሳቸውን መድረስ! በአዲስና ዘመናዊ የገጠር ሞባይል ኮኔክቲቪቲ አገልግሎት የገጠር ቀበሌዎችን ወደ ዲጂታሉ አለም መቀላቀል!

ኢትዮ ቴሌኮም፣ በMWC Barcelona 2024 ኹነት 500 የገጠር የሞባይል ጣቢያዎችን በሃገራችን ራቅ ባሉ የገጠር መንደሮች ለመገንባት ከሁዋዌ ጋር የማዕቀፍ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

በፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ እ.ኤ.አ በ2024፣ 100 የገጠር የሞባይል ኔትወርክ ጣቢያዎችን በመገንባት አገልግሎት ለማዳረስ የታቀደ ሲሆን በዚህም የኔትዎርክ ሽፋን ውስንነት ወይም ምንም ሽፋን ለሌላቸው አካባቢዎች ቅድሚያ ይሰጣል።

ዝርዝሩን ይመልከቱ 👆

#Ethiopian #CommunicationAuthority #Huawei #ZTE #Ericsson #GSMA #AU #ITU #WORLDBANK #OECD #G6countries #SmartAfrica #HOPR #HOF
ኩባንያችን ዜጎች እንዲሁም ተቋማት ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎች የሚመለከቱበትና በተግባር የሚሞክሩበት የኤክስፒሪየንስ ማዕከል በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በይፋ አስመረቀ፡፡

የኤክስፒሪየንስ ማዕከሉ ዜጎች ምርትና አገልግሎቶችን የሚመለከቱበት፣ አዳዲስ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን የሚሞክሩበት፣ ለፈጠራ የሚነሳሱበት፣ የዘመናችንን ግኝቶችን የሚመረምሩበት እና አዳዲስ አሰራርን የሚፈትሹበት ነው፡፡

ማዕከሉ ለሀገራችን ልማትና ኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ ሚና ያላቸው በተለያዩ ዘርፍ ያሉ ኢንዱስትሪዎች፣ ቢዝነሶች፣ መንግሥታዊ የሆኑና ያልሆኑ ተቋማት አሰራራቸውን በቴክኖሎጂ መደገፍ እንዲሁም ምርታማነታቸውን ማሳደግ የሚችሉበትን ዘመናዊ አሰራር እውን በማድረግ ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መፋጠን አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥር ነው፡፡



ለተጨማሪ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://bit.ly/4c7KgUU

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #DigitalEconomy #Huawei #ZTE #Ericsson #GSMA #AU #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #SmartAfrica
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮ ቴሌኮም ኤክስፒሪየንስ ማዕከል በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም

Ethio telecom Experience center
#AdwaMuseum

Experience the Digital Space! Inspire your Imagination! & Explore the Future!

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #DigitalEconomy #EthiopianCommunicationAuthority #Huawei #ZTE #Ericsson #GSMA #AU #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #SmartAfrica #HOPR #HOF
የቴክኖሎጂ አጋራችን ሁዋዌ ቴክኖሎጂስ የአፍሪካ ክፍለ አህጉር ኃላፊዎች ልኡካን ቡድን በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚገኘውን የኩባንያችንን የኤክስፒሪየንስ ማዕከል ጎበኘ፡፡

ልዑካን ቡድኑ በማዕከሉ የሀገራችንን የቴሌኮም ታሪካዊ ጉዞ አሁን እስከደረሰበት የእድገት ደረጃ የሚያመላክቱ ቴክኖሎጂዎችን የጎበኙ ሲሆን፣ የስማርት ግብርና፣ ትምህርት፣ ማዕድን ልማትን እና ቱሪዝም የመሳሰሉት የስማርት ሶሉሽኖች ለሀገራችን ዲጂታል ኢኮኖሚ ይዞት የሚመጣው ትሩፋት ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በኤክስፒሪየንስ ማዕከሉ በቀረቡት የዲጂታል ሶሉሽኖች እና በአመራሩ ብቃት መደነቃቸውን የገለጹ ሲሆን ኩባንያችን ለዲጂታል ኢትዮጵያ እውን መሆን እየተጫወተ ያለው ሚና ለሌሎች አፍሪካ ሀገራት አርአያ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

#DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #Huawei #GSMA #ITU #Ethiotelecom #telebirr
ኩባንያችን አዲስና አካታች የዲጂታል ስነምህዳር ለመገንባት በሚያደርገው ጥረት ምርትና አገልግሎታቸውን በአጭር ጊዜ Time To Market (TTM) ተደራሽ ለማድረግ የሚፈልጉ አጋር ድርጅቶች ከቴሌብር ሱፐርአፕ ጋር ሲስተሞቻቸውን በፍጥነት ለማስተሳሰር (to integrate) የሲስተም ሙከራ የሚያከናውኑበት የዴቨሎፐርስ ፖርታል አዘጋጅቶ በይፋ አስጀመረ፡፡

የዴቨሎፐርስ ፖርታሉ በዋነኛነት የአጋር ድርጅቶች ሲስተም ወደ ዋናው ቴሌብር ሲስተም ከመተሳሰሩ በፊት በተለየ የሙከራ ቦታ ላይ (sandbox environment) የኢንተግሬሽን ሙከራ ለማከናወን ያስችላል፡፡ አገልግሎቱ ከሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት፣ የሲስተም መፈተሻ እና የትግበራ ቦታ በተጨማሪ ለዴቨሎፐሮች ዶክመንቴሽኖች፣ መመሪያዎች፣ የቪዲዮ ቱቶሪያሎች፣ የኮድ ናሙናዎች፣ የኤፒአይ ማጣቀሻዎች እና ሌሎች አጋዥ መርጃ መሳሪያዎች ያካተተ ነው፡፡

ፖርታሉ ዴቨሎፐሮች ከኩባንያችን ሲስተሞች ጋር በፍጥነት እንዲላመዱ እና ክህሎት በመጋራት ደረጃቸውን የጠበቁ በርካታ ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎች እንዲያፈልቁ ከማስቻሉ በተጨማሪ የኦንላይን ማህበረሰብ በመፍጠር የስነምህዳሩን ተደራሽነት ይጨምራል ብለን እናምናለን፡፡

የዴቨሎፐርስ ፖርታሉን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን https://developer.ethiotelecom.et ይጠቀሙ!

#telebirrEngage #telebirr #Ethiotelecom #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #Huawei #GSMA #ITU
ኩባንያችን ከሁዋዌ ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር በኢትዮቴል ኢኖቬሽን ፕሮግራም የጀማሪ ፈጠራ ባለሙያዎችን (Startup) ክህሎት ለማሳደግ የሚያስችል የአንድ ሳምንት ስልጠና ሰጠ፡፡

የስልጠና ፕሮግራሙ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለሙያዎችን ቢዝነስ ክህሎት ለማሳደግ ከማስቻሉ ባሻገር በክላውድ እና ቴሌብር ዲጂታል ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ሲሆን በዘርፉ ልምድ ያላቸው የስራ ፈጣሪዎች (Entrepreneur) ልምዳቸውን ያጋሩበት ነበር፡፡

በመርሃ ግብሩ ማጠናቀቂያ ሰልጣኞች በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በሚገኘው የኩባንያችን ኤክስፒሪያንስ ሴንተር እና የዳታ ማዕከላችን ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ኩባንያችን በቀጣይ የማህበረሰባችንን የዕለት ከዕለት ህይወት የሚያቀልሉ የፈጠራ ሃሳቦችን ለማበረታታት በማለም ሽልማት የሚያስገኝ የሥራ ፈጣሪዎች ሃሳብ (Pitch presentation) ውድድር የሚያከናውን ይሆናል፡፡

#Ethiotelecom #telebirr #Huawei #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia