Ethio telecom
364K subscribers
6.77K photos
121 videos
120 files
2.24K links
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Download Telegram
ኢትዮ ቴሌኮም እና ሲንቄ ባንክ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ለማስፋት ያለመ ስትራቴጂያዊ ምክክር አደረጉ!

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እና የሲንቄ ባንክ ፕሬዚዳንት ነዋይ መገርሳ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የሚያቀርቡትን አካታችነትን እና ተደራሽነትን የሚያረጋግጡ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ለማስፋት ያለመ ስትራቴጂያዊ ውይይት አደረጉ፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ኢትዮ ቴሌኮም ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በአጋርነት ዜጎች የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ተጠቃሚ በማድረግ አካታች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ቀጣይነት ላለው ሀገራዊ እድገት የበኩሉን ሚና በመጫወት ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አክለውም ከሲንቄ ባንክ ጋር በአጋርነት በማህበረሰባችን ህይወት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጡ አዳዲስ የፋይናንስ አገልግሎቶችን በማቅረብ ሁሉን አቀፍ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያፋጥኑ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል፡፡

የሲንቄ ባንክ ፕሬዚደንት ነዋይ በበኩላቸው ባንካቸው በአጭር ጊዜ ሁሉን አቀፍ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በማድረግ ፈጣን ለውጥ በማስመዝገብ ላይ መሆኑን በመግለጽ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር አጋርነት ማጠናከር የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት በፍጥነት ለማረጋገጥ አስቻይ መደላድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አክለውም ኢትዮ ቴሌኮም ከቅርብ አመታት ወዲህ በተለይም በዲጂታል ፋይናንስ ስነ-ምህዳሩ ላይ እያደረገ ያለው ፈጣን ለውጥ በማድነቅ ለዚህም አመራሩ ለባንካቸው መልካም አርአያና መበረታቻ እንደሆነ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #SmartAfrica #GSMA #ITU #Ethiotelecom #Siinqee #telebirr
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሚያዝያን ለኒያ ፋውንዴሽን ጆይ ኦቲዝም ማዕከል!!

በዚህ ወር በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች ብዛት ልክ 30 ብር እንዲሁም በሚጋሩ Share ልክ 10 ብር ለኒያ ፋውንዴሽን ጆይ ኦቲዝም ማዕከል እንለግሳለን!

🤝 እርስዎም ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ፤ ፖስቶቻችንን ያጋሩ፤ ለወገን ድጋፍ ይተባበሩ!

ቴሌግራም | ፌስቡክ | ኢንስታግራም | ሊንክዲን | ዩትዩብ | ቲክቶክ

በተጨማሪም በቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ለበጎ አድራጎት በሚለው አማራጭ የፈቀዱትን የገንዘብ መጠን በመለገስ ለወገንዎ ተስፋ ይሁኑ!

🙏 ዘላቂ የጋራ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለወገን ብሩህ ተስፋ!


#MatchingFundForSustainableFuture
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!

ኢትዮ ቴሌኮም ከ47 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች የአክሲዮን ድርሻ ባለቤት ለማድረግ የሚያስችለውን ወሳኝ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ሲገልጽ በታላቅ ደስታ ነው!!

መንግስት ያደረገውን የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ ኢትዮ ቴሌኮምን ወደ አክሲዮን ማኀበርነት ለመቀየር የተቋሙን 10 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ሽያጭ ከጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለ121 ቀናት በዲጂታል መንገድ ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በዛሬው ዕለት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎችን በስፋት በመሳተፍ በተከናወነው የመደበኛ አክሲዮን ሽያጭ ከ47,377 ዜጎች ከ10.7 ሚሊዮን የአክሲዮን ድርሻ በዲጂታል መንገድ በማከናወን ብር 3.2 ቢሊየን የሚጠጋ ሀብት በማሰባሰብ ዜጎች በካፒታል ገበያ የሚሳተፉበትን መደላድል መፍጠር ተችሏል፡፡

የተሸጡ አክሲዮኖች ድልድል በካፒታል ገበያ ባለስልጣን የማጽደቅ ሂደት ከተከናወነ በኋላ ውጤቱን የምናሳውቅ ሲሆን፣ ቀሪ አክስዮኖችን በተመለከተ አክሲዮን የገዙ ባለድርሻዎችን መብት ባስጠበቀ መልኩ በቀጣይ በዝርዝር የሽያጭ ሂደቱን የምንገልጽ ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/42u5SrT
🎁 የአካል ጉዳተኞች የሞባይል ጥቅል!!

ከመደበኛ ጥቅል እስከ 35% በሚደርስ ታላቅ ቅናሽ የቀረቡትን ልዩ ጥቅሎች በ *999# ወይም 999 በመደወል ያገኟቸዋል፡፡

👉 በቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ሲገዙ ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር!

⚠️ መግዛት የሚችሉት ከአካል ጉዳተኞች ማኅበር በተላከልንን ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ብቻ ሲሆኑ መግዛት ያልቻሉ ደንበኞች አቅራቢያቸው በሚገኝ የማኅበሩ ቅርንጫፍ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡

ማንኛውም ሰው ጥቅሎቹን ለተመዘገበ የማኅበሩ አባል መግዛትና በስጦታ መላክ ይችላል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡ https://bit.ly/3GECypV


#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
🎬 🎁ሉበት ሆነው ምርጥ ሀገርኛ ፊልሞችን በ #ቴሌቲቪ እየተመለከ እስከ 100 ሺህ ብር ይሸለሙ!!

ፊልሞቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ በመግዛት በየሳምንቱ እስከ 100ሺህ ብር፣ ስማርት ስልክ እንዲሁም ሌሎች ሽልማቶችን ያግኙ!

🔗 ቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ላይ ወይም በመተግበሪያ teletv.et/download ያገኙታል፡፡

🗓 እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

ለበለጠ መረጃ ወደ 9801 ይደውሉ!


#teletv
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
📸👍 ልዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ጥቅል!!

ዘና እያሉ ቁምነገር የሚገበዩባቸውን የማኅበራዊ ሚዲያ ጥቅሎች በ*999#፣ በማይ ኢትዮቴል፣ በአርዲ ቻትቦት እንዲሁም በቴሌብር ሱፐርአፕ በልዩ ቅናሽ ይግዙ።

❇️ በዕለታዊ
❇️ ሳምንታዊ እና
❇️ ወርኃዊ አማራጮች!

🔗 ቴሌብር ሱፐርአፕን https://bit.ly/telebirr_SuperApp ይጫኑ!


ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
ኢትዮ ቴሌኮም ከሲንቄ ባንክ ጋር በአጋርነት 15 ቢሊየን የብር መጠን ያለው የቴሌብር የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎቶችን እና የዲቫይስ ፋይናንሲግ አገልግሎቶች ማስጀመሩን በይፋ ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው!

በዚህ የአጋርነት ትብብር ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች/ነጋዴዎችና ወኪሎች አነስተኛ ንግድ/ቢዝነስ እንዲጀምሩ ወይም እንዲያስፋፉ በዋስትና እና ያለዋስትና እስከ ብር 1.2 ሚሊየን የሚደርስ ብድር እንዲያገኙ የሚያስችል ስምምት የተደረገ ሲሆን፣ ይህም በዓመት እስከ ብር 10 ቢሊየን ለደንበኞች ለማቅረብ ያስችላል፡፡

በተጨማሪም የደመወዝ ብድር አገልግሎቱ ወርሃዊ ደመወዛቸው በቴሌብር እና በሲንቄ ባንክ ለሚከፈላቸው የግል እና የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች፣ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ድረስ ብድር እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ ይህም በዓመት እስከ 1.3 ቢሊየን ብር የሚደርስ የብድር አቅርቦት ስምምነትን ያካተተ ነው፡፡

ሁለቱ ተቋማት በአጋርነት የስማርት ስልክ ስርጸትን ለማሳደግ ያለመ የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ያስጀመሩ ሲሆን፣ ይህም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ስማርት ስልኮችን እና ሲም ካርዶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እና በረጅም ጊዜ ክፍያ እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ በዚህም በአጋርነት በዓመት እስከ 2 ሚሊዮን ዲቫይሶችን ለማቅረብ ከሲንቄ ባንክ ጋር የ4 ቢሊዮን ብር የገንዘብ አቅርቦት ስምምነት ተደርጓል።

ይህም የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ በቀጥታ ከመደገፉም ባሻገር የዲጂታል ክፍተትን ለማጥበብ በተለይ ቀደም ሲል አገልግሎት በበቂ ሁኔታ ያላገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመደገፍ ለሀገራችን ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡


ለተጨማሪ መረጃ፡ https://bit.ly/4cZKlLd