#ትኩረት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ወደ ኢትዮጵያ እስከ 200 ኪሎ ሜትር ዘልቀው በመግባት የአንድ ወረዳ ከተማ ስም እስከመቀየር እንደደረሱ በፓርላማ ተገልጿል፣ የአንደኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ደግሞ አብዛኛውን ህዝብ ፈጅተው ወደ 50 እና 60 ሰዎች ብቻ ናቸው የቀሩት ተብሏል።
መቼም ለጋምቤላ እና ለደቡብ ምዕራብ ክልሎች በደንብ የሚጮህላቸው አክቲቪስት እና ሚድያ ባይኖራቸውም መረጃውን እናጋራላቸው። ከወራት በፊትም ይህ መረጃ ወጥቶ እኔም አጋርቼው እንደነበር አስታውሳለሁ፣ አንዳንድ ባለስልጣናት ግን በወቅቱ "ውሸት ነው" ብለው ሲያጣጥሉት ነበር።
ሪፖርተር በዚህ ዙርያ ያወጣው መረጃ ይህን ይመስላል:
https://www.ethiopianreporter.com/116093/
@EliasMeseret

#ትኩረት ተሰምቶ እንጂ ታይቶ የማይታወቅ ድርቅ፣ ረሀብ እና ቸነፈር በበርካታ ስፍራዎች ተከስቷል። ጉዳዩ በሚመለከታቸው ችላ ቢባልም (ለዜና ሽፋን እንኳን ባይበቃም) ክስተቱ የሚልዮኖች እንስሳቶችን እና በአንዳንድ ስፍራዎች ደግሞ የሰው ህይወት እስቀመቅጠፍ እየደረሰ እንደሆነ ታውቋል።
ይህ አሳዛኝ ክስተት እንደ ቦረና ባሉ ለአምስት ተከታታይ አመታት ዝናብ ባላገኙ አካባቢዎች የከፋ ሆኗል። የቦረና ዞን አስተዳደር 800,000 ገደማ ነዋሪዎች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ገልፀዋል።
የእርዳታ ድርጅቶች 22.6 ሚልዮን ዜጎቻችን የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው፣ 11.8 ሚልዮኑ ከፍ ያለ ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ እንዲሁም በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ቢያንስ ለመጪዎቹ አስር ወራት በዚህ ሁኔታ እንደሚቀጥሉ እና ከፍ ያለ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል እያሳሰቡ ይገኛሉ።
"ከ110 ሚልዮን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት ስለተገኘ ወደ ውጭ ኤክስፖርት ሊደረግ ነው" የሚለው ሀሳብ ይህን ሲሰማ ምን ይሰማው ይሆን?
ለማንኛውም፣ ሁላችንም የተቻለንን ርብርብ ለማድረግ እንዘጋጅ፣ በቅርቡ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ እንጀምራለን።
📸 File ©️ Elias Meseret

#ትኩረት መገናኛ ከቦሌ ወደ ዲያስፖራ አደባባይ የሚያሸጋግረው መንገድ ላይ ያለው ድልድይ ዋና ተሸካሚው በመሰነጣጠቁ እና ቦታውን በመሳቱ ያልታሰበ አደጋ ከማስከተሉ በፊት ጥገናና እና ወቅታዊ ክትትል ሊደረግለት ይገባል እንላለን።
Via Driving in Addis
@EliasMeseret
Via Driving in Addis
@EliasMeseret
#ትኩረት በኮንሶ ዞን በሚገኙ በርካታ ስፍራዎች የኮሌራ ወረርሽኝ እንደተከሰተ እና ህዝቡ አፋጣኝ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ከስፍራው የሚደርሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በዚህ አደገኛ እና ገዳይ በሽታ በርካቶች እንደተያዙ እና የሚያዙት ሰዎች ቁጥርም ከእለት ወደ እለት በፍጥነት እየጨመረ እንደመጣ የሰገን ወረዳ ፅ/ቤት አረጋግጧል።
ፅ/ቤቱ ወረርሽኙ በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑንና የህክምና ድጋፍ እያነሰ መሆኑን ገልጾ የሁሉም አካላት ከፍተኛ አስቸኳይ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ጠይቋል፣ ድጋፉ በአስቸኳይ ካልደረሰ በወረርሽኙ የተያዙ ወገኖች ለጉዳት እንደሚዳረጉ በአጽንኦት ተገልጿል።
ሁሉም የሚመለከታቸው የመንግሥት፣ ሰብዓዊና የልማት አጋር ድርጅቶች ወረርሽኙ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ አስቸኳይና ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ የኮንሶ ልማት ማህበርም ጥሪውን አቅርቧል።

#ትኩረት ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር በሚወስደው መንገድ ላይ "አሊዶሮ" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ቁጥራቸው ቢያንስ 30 የሚሆኑ በአብዛኛው ሹፌሮች እና ተጓዦች ዛሬ ጠዋት በ "ታጣቂዎች" ታግተው እንደተወሰዱ የአይን እማኞች ያደረሱኝ መረጃ ይጠቁማል።
እገታው በመሀል መንገድ ላይ በርካታ ደቂቃዎችን ፈጅቶ ሲፈፀም የደረሰ አንድም የፀጥታ ሀይል እንዳልነበር፣ "መንግስት ኦነግ ሸኔ የሚላቸው" ናቸው ብለው ምንጮች ያደረሱኝ ታጣቂዎች ሲፈልጉ ወደሰማይ ደጋግመው ሲተኩሱ እና ዘና ብለው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ገልፀዋል።
አዲስ ማለዳ እንደዘገበው በተመሳሳይ እሁድ ሰኔ 4/2015 ዕለት ከሌሊቱ አምስት ሰዓት አካባቢ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ባቱ (ዝዋይ) ከተማ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከዚሁ ሀይል ጋር ባደረጉት ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ የአራት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡
ከሟቾቹ መካከል አንዲት ሴትን ጨምሮ ሦስቱ የመንግሥት የጸጥታ አካላት መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፤ አንዱ ደግሞ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን አባል ነው ተብሏል። የተገደለው የታጣቂ ቡድን አባል እግሩን ተመትቶ መሸሽ ባለመቻሉ፤ የታጣቂ ቡድኑ አባላት መረጃ እንዳያወጣ በማለት ገድለውት እንደሸሹ ተጠቁሟል።
ለተከታታይ ሁለት ሰዓታት በላይ ሲደረግ ነበር የተባለው የተኩስ ልውውጥ ዓላማው እስረኛ ለማስፈታት እንደሆነ ተገልጿል።
የታጣቂ ቡድኑ አባላት አሉ ወደተባለበት ኦኢቱ አካባቢ የመንግሥት የጸጥታ አካላት በተደጋጋሚ ቢያቀኑም "በሕይወት ተርፈው የሚመለሱት ጥቂቶች ናቸው" ሲሉ ነዋሪቹ ተደምጠዋል ብሎ ሚድያው ዘግቧል።
በሌላ በኩል፣ በቅርብ ቀናት በሱሉልታ ከተማ እና አካባቢው በርካታ እገታዎች እየተፈፀሙ፣ የታገቱት ሰዎችን ለመልቀቅ ደግሞ እስከ ሚልዮኖች እየተጠየቀ እንደሆነ ታውቋል።

#ትኩረት በስልጤ ዞን ቅባት ከተማ በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መኖርያ ቤቶች ላይ ዘረፋ እና ጥቃት እየተፈፀመ እንደሆነ በስፍራው ያሉ ዜጎች አሳውቀውኛል።
ሰኞ እለት ቤተክርስቲያን ላይ ጭምር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራ ተደርጎ በፀጥታ አካላት ትብብር መክሸፉ ቢታወቅም አሁን ድረስ ጥቃቱን ፈርተው በየቤተክርስቲያኑ ተጠልለው የሚገኙ በርካታ ዜጎች እንዳሉ ታውቋል።
ይህን ተከትሎ ከስልጤ ዞን ቅባት ከተማ የተወጣጡ የእስልምና እምነት ተከታይ የሀገር ሽማግሌዎች ከታቦተ ማርያም ጋር ተሰደው የሚገኙ ሰዎችን ቡታጅራ ድረስ በመሄድ አጽናንተዋል።
እንዲህ አይነት ድርጊቶችን ክርስቲያን ሙስሊም ሳንል ሁላችንም ልናወግዝ ይገባል።
Photo: social media

#ትኩረት ተከማችተው የሚገኙት አደገኛ ኬሚካሎች ጉዳይ ከምን ደረሰ?
የዛሬ ሶስት አመት ገደማ በቤይሩት ከተማ ውስጥ ተከማችቶ በነበረ ኬሚካል አማካኝነት እጅግ ከፍተኛ ፍንዳታ ተከስቶ እንደነበር ይታወሳል።
ይህ ከሆነ በሗላ ኢትዮ ኤፍኤም ሬድዮ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርን በመጥቀስ በአዲስ አበባ 250 ኪ/ሜ ዙርያ ያሉ ስፍራዎችን ሊያወድም የሚችል የኬሚካል ክምችት አለ ብሎ አንድ ዜና ሰርቶ ነበር።
ይሁንና መረጃው በስፋት ተሰራጭቶ እና ብዙ ትኩረት አግኝቶ ስለነበር የኤጀንሲው ስራ አስኪያጅ ወደ ሚድያ ብቅ ብለው እርሳቸው ያሉት 250 ሜትር እንጂ 250 ኪ/ሜር እንዳልሆነ ገልፀው ነበር (250 ሜትር በራሱ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትል ልብ እንበል)፣ "ብዬ ከነበረም የአፍ ወለምታ ነው" ብለዋል።
በወቅቱ በሚድያ የተነገረው ሌላው ጉዳይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን በኬሚካሎች ክምችት ዙርያ ጥናት እየተሰራ እንደነበር እና ውጤቱም ሚያዝያ 2014 ላይ ይፋ ይሆናል ተብሎ ነበር።
ይህ ጥናት ምን ላይ ደረሰ? ኬሚካሎቹስ ተወግደው ይሆን? ብዬ ለኤጀንሲው ስራ አስኪያጅ ተደጋጋሚ ጥያቄ ባቀርብም መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ሪፖርተር ጋዜጣ አምና እንደዘገበው በመንግሥትና በተለያዩ ኩባንያዎች አማካይነት ወደ አገር ውስጥ ገብተው፣ ለበርካታ ዓመታት ጥቅም ላይ ሳይውሉ ተከማችተው የሚገኙ ኬሚካሎችን ለማስወገድ ተጀምሮ የነበረው ሥራ የተፈለገው ገንዘብ ባለመገኘቱ መስተጓጎሉ ገልፆ ነበር።
የኤጀንሲው ሀላፊ "በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ኬሚካሎችን ለማስወገድ ከለጋሽ አካላት ይገኛል ተብሎ የታሰበው ገንዘብ ከአገሮቹ ጋር በነበረው ሁኔታ እንደተጠበቀው ባለመሄዱ ኬሚካሎችን የማስወገድ ሥራው በታሰበለት ጊዜ እየሄደ አይደለም" ብለው ለጋዜጣው ነግረዋል።
ታድያ እነዚህ በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የሆነ አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ የተባለውና የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው ኬሚካሎች ክምችት ምን ላይ እንዳለ አደጋ ሳይከሰት በፊት መንግስት የማስወገድ እርምጃ ሊወስድም፣ ለህዝብ ተከታታይ መረጃ ሊያቀርብም ይገባል።
ይህ ህዝብን alarm ለማረግ ሳይሆን አደጋ ከመከሰቱ በፊት አስፈላጊ ከሆነ የውጭ ባለሙያዎችን እርዳታ በመጠየቅ የማስወገድ ስራ እንዲሰራ ለማሳሰብ ነው። ሴኔጋል ይህ የክምችት ስጋት ኖሮባት ችግሩን የተወጣችው በዚህ መልኩ ነበር።
በዚህ ዙርያ ምላሽ ካለ ይዤ እመለሳለሁ።
Photo: File

#ትኩረት ከሰሞኑ በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መሀል የተፈረመውን የወደብ ኪራይ ስምምነት ተከትሎ አንዳንድ የሶማልያ ዜጎች በሀገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የተለያዩ ዛቻዎችን እያደረሱ ይገኛሉ።
ለምሳሌ 'አብዲካሪን ኤደን' የተባለ 'The Party of Hope' ድርጅት መሪ ኢትዮጵያዊያን ወደሀገራቸው ይሸኛሉ በማለት የቪድዮ መልእክት አስተላልፎ የሬሳ ሳጥን ምስል አስቀምጧል። በሌላ በኩል በምስሉ ላይ እንደሚታየው 'ፋሊስ ሀሺ' የተባለ ግለሰብ ከ500,000 በላይ ዶክመንት የሌላቸው ኦሮሞዎች በሶማልያ ይገኛሉ፣ አሁን ግን ከሀገሪቱ ሊወጡ ይገባል የሚል መልዕክት አስፍሯል።
ይህ ለምሳሌ ያቀረብኩት ነው እንጂ ሶማልያ ውስጥ ከሰሞኑ በሬድዮ፣ ቴሌቭዥን እና ሶሻል ሚድያ ተመሳሳይ መልእክቶች በስፋት እየተሰራጩ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ታድያ በዚህ ዙርያ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሊሰራ ይገባል፣ እኛም እንዲህ አይነት መልእክቶችን ስንመለከት ቢያንስ ሪፖርት በማድረግ መልእክቶቹ በስፋት እንዳይሰራጩ ማድረግ እንችላለን (ይህን ከላይ የጠቀስኩትን የአብዲካሪን ቪድዮ ሪፖርት እናድርግ፣ ሊንኩ ይህ ነው: https://fb.watch/ptsmoyph3a/?mibextid=Nif5oz)
በተለይ በሶሻል ሚድያ የሚደረጉ ቅስቀሳዎች ሊያደርሷቸው የሚችሉ ጉዳቶች በጣም አሳሳቢዎች ናቸው፣ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት እንኳን በፌስቡክ እና ዩትዩብ "በለው፣ ፍለጠው፣ ቁረጠው...ወዘተ" በሚል አካሄድ በርካታ ንፁሀን አልቀዋል።
መንግስትም የተፈራው 'አይደርስም' ሳይሆን 'ሊደርስ ይችላል' በሚል እሳቤ ዜጎችን ለመጠበቅ እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከሶማልያ ለማውጣት እቅድ ሊኖረው ይገባል።

#ትኩረት ሌላ አለም ላይ እንዲህ አይነት የከፋ አደጋ ሲያጋጥም የመንግስት የአደጋ መከላከል አካላት፣ አስፈላጊ ከሆነም የጦር ሰራዊት አባላት በምድር እና በአየር ተረባርበው ህይወት ለማትረፍ ይጥራሉ፣ የሰው ህይወት የረከሰበት እኛ ሀገር የአደጋው መረጃ በአብዛኞቹ የመንግስት ሚድያዎች ለህዝብ አልደረሰም (ስፖኪዮ የሰረቀ ልጅ ተያዘ የዛሬ ዋና ዜናቸው ነበር)።
የዛሬ 14 አመት ቺሊ ውስጥ የማዕድን ማውጫ የተደረመሰባቸው 33 ሰራተኞች ከ69 ቀናት ትግል በኋላ ህይወታቸው የተረፈበት አጋጣሚን አስቤ ይህን የእኛን ስሰማ አዘንኩ። መረጃው ከታች ይገኛል ⬇️
በደቡብ ወሎ ውስጥ በማዕድን ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ በቁጥር እስከ 30 የሚሆኑ ዜጎች ባለፈው ሀሙስ ዋሻ ተደርምሶባቸው ያሉበት ሁኔታ አልታወቀም።
በደላንታ ወረዳ ውስጥ በህጋዊ መንገድ ኦፓል በማውጣት ላይ የነበሩ እነዚህ ሰዎችን ለማውጣት የሚደረገው ጥረት በአካባቢው ማህበረሰብ እስከዛሬ ቢቀጥልም ውጤት አለመገኘቱ ታውቋል።
ትናንት እሁድ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አያሌው በሪሁን ባለፉት ቀናት ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች በነፍስ አድን ሥራው ላይ እገዛ ለማድረግ ወደ ሥፍራው ቢያቀኑም ወደ ዋሻው ለማምራት የሚያስችለው መንገድ ጠባብ እና በአንድ ጊዜ ከአስር ሰዎች በላይ ማስገባት ባለመቻሉ ጥረታቸው አዝጋሚ መሆኑን ተናግረዋል።
ስምንቱ የማኅበሩ አባላት በናዳው ተይዘው እንደሚገኙ የገለጸው ወርቅ ዋሻ የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር ሊቀመንበር ተስፋዬ አጋዥ በበኩሉ እስካሁን በተደረገው ጥረት 150 ሜትር ርዝማኔ ወዳለው ዋሻ ዘልቆ ለመግባት መቆፈር የተቻለው 33 ሜትር ገደማ ብቻ መሆኑን ለሚድያው ተናግረዋል።
ይህ አደጋ ከተከሰተ በኋላ በመንግሥት በኩል የተቀበሩትን ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅም ሆነ ከዋሻው ለማውጣት የተደረገላቸው ድጋፍ እንደሌለም ገልጿል።

#ትኩረት ከወደ ደቡብ ኦሞ የሚሰማው የዜጎች ስቃይ እና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ልብ ይሰብራል። ከአንድ ቤተሰብ በርካታ ሰው በወባ እየሞተ ነው፣ ሰሞኑን በተከሰተ የውሀ ሙላት ደግሞ መድረሻ ያጣው ብዙ ነው... ኦሞራቴ ከተማን ሙሉ በሙሉ ሊውጥ የሚችል የውሀ ስጋት ተደቅኗል
ሙሉ መረጃው ከመሠረት ሚድያ ⤵️
"እኛ የሚጮህልን ሚድያም ሆነ አክቲቪስት የለንም፣ ብዙ ህዝብ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ነው ያለው። ከብቶቼም አልቀዋል፣ ንብረቴም ወድሟል፣ የእኔ መኖር ምን ዋጋ አለው የሚለው ብዙ ነው"- የደቡብ ኦሞ ነዋሪዎች ለመሠረት ሚድያ
ሊንክ: https://www.facebook.com/61562533862014/posts/pfbid02cNNr2ytX9HaeSiASdNgGJo2QFJvnNzbPYQm3QvgVPZD7vHK6sHg8Wfqo54J5z9mql/