ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
133K subscribers
6.05K photos
113 videos
6 files
986 links
Journalist-at-large
Download Telegram
ጠ/ሚሩ ቪየትናም ናቸው!

ቪየትናም ደግሞ በቅርብ አመታት የአለማችን ግዙፍ የማምረቻ (manufacturing) ማዕከላት መገኛ ሆናለች። ሀገሪቱ ከአይፎን እስከ ሳምሰንግ ስልኮች፣ ከአዲዳስ እስከ ናይኪ ልብስ እና ጫማዎች እንዲሁም ግዙፍ የመኪና እና መርከብ አምራች ኩባንያዎች የስበት ማዕከል ሆናለች።

የዛሬ አመት ገደማ ጠ/ሚር አብይ ሲንጋፖርን ሲጎበኙ ያዩት የከተማ ልማት ለኮሪደር ልማት ላይ መነቃቃትን ፈጥሮ ነበር ተብሎ ተዘግቦ ነበር።

አሁንም የቪየትናም ጉብኝታቸው እጅጉን እየተዳከመ ላለው እና ከፍ ያለ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ላለው የሀገራችን የአምራች ኢንደስትሪ ዘርፍ መነቃቃትን ይፈጥር ዘንድ ምኞቴ ነው።

ፎቶ: የቪየትናም የማምረቻ ኢንደስትሪዎች በከፊል

@EliasMeseret
"የኬንያ ዜጎች እንኳን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጭምር ተጓጉዘው ሀገራቸው ገብተዋል"- በሚያንማር የሚገኙ ዜጎች በስልክ ከነገሩኝ

በሚያንማር የሚገኙ ዜጎች ጉዳይ አሳሳቢም፣ አስገራሚም እየሆነ ነው። ከ740 በላይ ዜጎቻችን ተይዘውበት ከነበረው አደገኛ ካምፕ በአንድ ታጣቂ ቡድን ነፃ ሆነው አሁን ላይ በግዜያዊ መጠለያ ውስጥ ቢገኙም ተረክቧቸው ወደ ሀገራቸው የሚመልሳቸው አካል አጥተው እንዳሉ በርካቶች በአጭር ፅሁፍ መልዕክት እና በስልክ ነግረውኛል።

አንዳንዶቹ በተስፋ መቁረጥ ራስን የማጥፋት ሙከራ አርገዋል፣ ኮማ ውስጥ ያሉ አሉ፣ የአካል ጉዳትም የደረሰባቸው አሉ። ውጭ ጉዳይ አንድ ሰሞን ጉዳዩን ይዞት እንደነበር ሰምተን ነበር፣ አሁን ላይ ምንም ነገር የለም፣ ሲጠየቁ "ፕሮሰስ ላይ ነው" የሚል ምላሽ ይሰጣሉ።

ዜጎቻችንን ከካምፑ ነፃ ያወጡት ታጣቂዎች እንኳን "መንግስታችሁ በፍጥነት ካልወሰዳችሁ ወደነበራችሁበት ካምፕ ከመመለስ ውጭ ምርጫ የለንም" እያሏቸው ነው።

ኬንያን ጨምሮ ሌሎች 25 ሀገራት ዜጎቻቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በመጠቀም አጓገዘው አውጥተዋል። ጉዳዩን በቶክዮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ይዞት ነበር ተብሎ ነበር፣ አሁን ደህሞ ህንድ ያለው ኤምባሲ እየተከታተለው ነው ከሚል ውጭ ምላሽ የለም።

የሚገርመው 400 የሚሆኑት የመመለሻ ትኬት አላቸው፣ ሊረዷቸው የሚችሉ NGO ድርጅቶችም አሉ፣ ነገር ግን መንግስት የመመለስ (repatriation) ሂደቱን ካልጀመረ ምንም ማድረግ አይቻልም።

ልጆቹ አንዴ ተታለው ተወስደዋል፣ መንግስት ግን ሊደርስላቸው አይገባም? ሀገር ማለት ህዝብ ማለት አልነበር?

በአፋጣኝ ትኩረት ካልተሰጠው አሳዛኝ ውጤት ይታየኛል።

@EliasMeseret
#FactCheck የመንግስት ሚድያዎች "የቀድሞው ፕሬዝደንት መንግስቱ ኀይለ ማርያም አውሮፕላን" የሚል መረጃ ደጋግመው ሲጠቀሙ ታይተዋል፣ ይህ ደግሞ አሳሳች ነው።

ኮ/ል መንግስቱ ሲጠቀሙ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን እንጂ የራሳቸው አውሮፕላን አልነበራቸው። ይኼ ነገር ምናልባት ከሰሞኑ ቅንጡ እና የ VIP አገልግሎት የሚሰጥ አውሮፕላን ሀገር ቤት አገልግሎት ሊጀምር ስለሆነ እና ጠ/ሚሩ ይጠቀሙበታል ስለተባለ እሱን ዜና ማደንዘዣ እንዳይሆን ብዬ አሰብኩ።

ሙሉ ዘገባው ኢትዮጵያ ቼክ ገፃ ላይ: https://t.me/ethiopiacheck/2548

@EliasMeseret
#FakeNewsAlert ይህ መረጃ ነጭ ውሸት ነው!

ቀላሉ ማስረጃ እና ማንም በሰከንዶች ጉግል አድርጎ የሚረዳው ሀቅ አለ፣ እሱም እሷ በለጠፈችው ፎቶ ላይ የሚታየው እና ታድሶ መብረር ቻለ ተብሎ በመንግስት ሚድያዎች ጭምር ስሙ ተጠቅሶ የነበረው DHC Buffalo የተባለ የካናዳ ስሪት አውሮፕላን ሲሆን እሷ የምታወራው ስለ ሶቪየት ህብረት አውሮፕላን ነው። ማስረጃው: https://www.baesystems.com/en/heritage/de-havilland-canada-dhc-5-buffalo

ምናልባት ለማለት የፈለገችው በአንድ ወቅት ሶቪየቶች ለኮ/ል መንግስቱ ሰጥተውት ስለነበረው "መሸሻ" የሚል ቅፅል ስም ስለነበረው Tupolev ስሪት አውሮፕላን ሊሆን ይችላል፣ እሱ ግን ሌላ አውሮፕላን ነው።

ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል እና፣ ስለዚህ "መሸሻ" ስለተባለ የሶቪየት አውሮፕላን በቅርቡ የሰማሁትን ላካፍላችሁ።

ሶቪየቶች ይህን አውሮፕላን ለኮ/ል መንግስቱ ከሰጡ በኋላ ፕሬዝደንቱ አልተጠቀሙበትም ነበር። ሙሉ ነጭ የተቀባው እና ጭራው ላይ የኢትዮጵያ ባንዲራ ያለው "መሸሻ" ለበርካታ አመታት በቢሾፍቱ አየር ሀይል ግቢ ቆሞ ነዋሪዎች ያዩት ነበር።

ከዛም ኢህአዴግ ከገባ በኋላ እና ሜቴክ ከተቋቋመ በኋላ ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ይህን የሶቪየት አውሮፕላን ለጠ/ሚር መለስ ዜናዊ የ VIP አውሮፕላን እንዲሆን እቀይረዋለሁ በማለት ቆራርጠው፣ ቀጥለው፣ ነቃቅለው፣ ሰካክተው ጨረሱ።

ከዛ ለበረራ ብቁነት ምዝገባ ሲቪል አቪዬሽንን ሲጠይቁ ተቆጣጣሪዎቹ "ይሄ ለበረራ ብቁ አይደለም" ብለው ፍቃድ እንደተከለክሉ እና ከዛ በኋላም ቆሞ እንደቀረ ሰምቻለሁ።

* ከላይ ያለውን መረጃ የፃፍሽው ትክክለኛው የኮ/ል መንግስቱን ትዝታዎችን የፃፍሽው ገነት አየለ ከሆንሽ መንግስቱ የነገሩሽን ደግመሽ አጣሪው

@EliasMeseret
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል ይሁንላችሁ፣ ይሁንልን።

@EliasMeseret
መምህራንን በእንዲህ አይነት መልኩ ማሰቃየት አላማው ምንድነው?

ስላስተማሩ ብቻ ከዚህ በፊትም ህይወታቸውን ያጡ መምህራን በአማራ ክልል አሉ፣ አሁንም በዚህ መልኩ እና ከዚህ በባሰ ሁኔታ የሚሰቃዩ አሉ። ትክክል አይደለም ብሎ መግለፅ ጉዳዩን ማሳነስ ይሆናል፣ ከግፍም በላይ ነው።

በክልሉ በየቀኑ የሚቀጠፉትን ዜጎች፣ በድሮን የሚጨፈጨፉትን ወጣቶች እና ወጥተው የሚቀሩ የሀገር ተረካቢዎችን በተመለከተ ድምፅ ስንሆን እንደቆየነው ሁሉ እንዲህ አይነት ድርጊት ስናይም የማውገዝ ስብዕና እና የሞራል ልዕልና ሊኖረን ይገባል። 

@EliasMeseret
#GoodNews ቦይንግ የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ መክፈቱ መልካም ዜና ነው

የዚህ ክስተት ዋናው መንስኤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተከታታይ ስኬት እና ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ከምስረታው ጀምሮ የነበረው ታሪካዊ ትስስር ነው።

አሁንም ይህ ትብብር በሌሎች ሀገራት እንደሚታየው ወደ አውሮፕላን ቁሶች ማምረት እና በሀገር ውስጥ ያለውን የ Maintenance, Repair እና Overhau (MRO) አገልግሎቶችን ወደማሳደግ እና ማዘመን እንዲያድግ ምኞታችን ነው።

#FlyEthiopian #Boeing

@EliasMeseret
የዲሲፕሊን ግድፈት አለበት የተባለን ግለሰብ ገጠር ገብቶ እንዲሰራ ማዘዝ ምን ማለት ነው? ገጠር ያለው ህዝብስ ዲሲፕሊን ባለው የጤና ባለሙያ መስተናገድ የለበትም?

ይህ የሚያሳየን ወጣት ዶክተሩ ጥፋት ኖሮበት ሳይሆን የሰሞኑን የጤና ባለሙያዎችን ድምፅ ስላሰማ ለመቅጣት ነው፣ ይህ ደግሞ አደገኛ አዝማሚያ ነው።

የጤና ባለሙያዎች በሰላማዊ ሁኔታ መብታቸውን እየጠየቁ ነው፣ በተለያዩ ቦታዎች ግን የማሸማቀቅ ስራ እየተሰራ እንዳለ የሚደርሱኝ መረጃዎች ያሳያለ።

This will backfire!

ዜናውን መሠረት ሚድያ ላይ ለማንበብ:
https://t.me/meseretmedia/923

@EliasMeseret
በኢትዮጵያ የአንድ የጠቅላላ ሀኪም ወርሀዊ ደሞዝ= 11 ሺህ ብር

የመንግስት አክቲቪስቶች ወርሀዊ ድጎማ= 240,000 ሺህ ብር

#Justice

@EliasMeseret
#በነገራችንላይ በግሌም ሆነ #መሠረትሚድያ ላይ የሚቀርቡ መረጃዎች ለመንግስት አካላት ከፍተኛ ግብአት ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ

በማደርገው ክትትል እንደማየው በአንዳንድ አካላት የሚፈፀሙ አስተዳደራዊ በደሎች፣ ዝርፊያዎች እና የሙስና ስራዎች በአብዛኛው እርምጃ ይወሰድባቸዋል፣ ይህንን ማስተካከያቸውን ራሳቸው ተቋማቱ ጭምር መልሰው ያሳውቁኛል።

ትችት ማለት ተቃውሞ የሚመስለው በዝቶ እንጂ ከስድብ፣ መዘላለፍ እና መጠላለፍ የዘለለ በመረጃ የተደገፈ ዘገባ መንግስትን ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። ይህንን ደግሞ የፌስቡክ ገፁን አከራይቶ የሚጮኸው አክቲቪስት እንጂ ብዙዎቹ አመራሮች ይረዱታል ብዬ አስባለሁ።

መልካም ምሽት!

@EliasMeseret
አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ላሉ ዜጎቹ ⤵️
"ለግል ደህንነታችሁ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳትረሱ... እንደ ሰልፍ ያሉ ህዝብ ከሚሰበሰቡባቸው ስፍራዎች ራቁ"

የፌደራል ፖሊስ በኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገፁ ፖስቱ ስር የሰጠው አስተያየት ⤵️
"ደርሶኛል"

🤔🤔

@EliasMeseret
የፍትህ ስርዐታችን እዚህ ደርሷል!

በእኔ እድሜ ኢትዮጵያ ውስጥ የፍትህ የበላይነት ተረጋግጦ እና ሁሉም ከህግ በታች ሆኖ አላየሁም፣ በዚህ ደረጃ ግን ወርዶ አየዋለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም።

ያሳዝናል!

ዜናውን ያንብቡ: https://t.me/meseretmedia/934

@EliasMeseret
በሚያንማር ያሉ ዜጎችን ካሉበት ቦታ ለማውጣት ለሚያስፈልገው የባስ ትራንስፖርት ወጪ መንግስት ክፍያ ለመፈፀም ስላልቻለ ቤተሰቦቻቸው እስከ 20 ሺህ ዶላር እንዳዋጡ ሰማሁ።

"እንደዛም ተከፍሎ የመንግስት ልኡክ ቡድን ስለሚያስፈልግ እየጠበቅናቸው ነው፣ ግን ለእሱም እየተግደረደሩ ነው" ያሉኝ እዛው ያሉ ዜጎቻችን ናቸው።

ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች እንኳን ሰዎቻቸውን በአውሮፕላን አጓገዘው ከጨረሱ ሰነባብተዋል፣ የእኛዎቹ ለባስ ክፍያ ለመክፈል እና አቀባበል ለማድረግ የሉም።

በዚህ መልኩ ወደ ሀገራቸው ሲገቡ "መንግስት ባደረገው የተቀናጀ እና የተሳለጠ እንቅስቃሴ ለሀገራቸው በቁ" ተብሎ መዘገቡ አይቀርም።

@EliasMeseret
ከጥቂት አመታት በፊት በኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ዜጎች የሚከፈላቸው አነስተኛ ክፍያን፣ የሚደርስባቸው ወከባን እና የሚያጋጥማቸውን የአካል ጉዳት በተመለከተ ለ Associated Press ዜና በመስራቴ በወቅቱ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር የነበሩት አምባ. ፍፁም አረጋ እና የኮሚኒኬሽን ሀላፊ የነበሩት ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በፃፉት ደብዳቤ የነበረኝ የሚድያ Accreditation እንዲነጠቅ ደብዳቤ ፅፈው ነበር፣ ግን አልተሳካላቸውም።

ውጤቱን ግን አሁን እያየነው ነው።

@EliasMeseret
ከየመንገዱ እና ሰፈሩ እየታፈሱ ወደ ወታደራዊ ካምፕ የሚላኩት ህፃናት በከፊል ይህን ይመስላሉ፣ የመንግስት ሚድያዎች እና የክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮዎች ደግሞ ካለምንም ሀፍረት ፎቷቸውን እንዲህ እየለቀቁ ይገኛሉ።

አብዛኞቹ በ14-16 እድሜ ያሉ እንደሆኑ መገመት ይቻላል፣ ይህ ደግሞ የሀገሪቱንም ሆነ አለም አቀፍ የህፃናት ደህንነት ስምምነቶችን የጣሰ ነው።

ተዋጊ ካነሰ ህፃናትን ከመማገድ ጦርነቱን ለማስቆም ጥረት ማረግ አይሻልም?

@EliasMeseret
ለቁጥር የሚታክቱ እንዲህ አይነት መልዕክቶች በየቀኑ ይደርሱኛል፣ ከዛሬዎቹ አንዱ ይህ ነው ⤵️

"ዛሬ/24/8/17 እዚህ አዲስ አበባ ትንሽዬ ካፌ እሠራለሁ፣ ከዛ መንገድ ላይ የሚኖሩ ልጆች ተመላሽ ይኖረው ይሆናል ብለው የተቀመጠውን ቆሻሻ ይዘው ወጥተው ፈትሸው ያገኙትን ለቃቅመው የማይጠቅመውን ጥለው ይሄዳሉ።

ባጋጣሚ ደንቦች አይተው ከየት አመጣህ ሲባል የኔን ካፌ ይጠቁማል፣ እነሱም መጥተው ወረዳ ወሰዱኝ ሄድሁ፣ ምን ተፈጥሮ ነው ስላቸው 'ጭራሽ ታናግረናለህ' አመናጨቁኝ ነው ምላችሁ።

አስቡት እንግዲህ ቆሻሻው ከየት እንደወጣ አላውቅም ልጁ ነገረን የሚሉኝ። እነሱ ልከውት ቢሆንስ በምን አውቄ? ጥጋባቸውን፣ የበቀል፣ የምን ታመጠላህና እንደሰው ያለመቁጠር እብሪታቸውን ካያችሁ አቅም እንደሌለህ ባወቅህ ጊዜ ምስኪኑ የቀጨኔ ሊስትሮ ትናንት ራሱን ያጠፋው ምርጫ ይሆናል።

መጨረሻውንም አላወቅሁ ለግዜው መታወቂያየን ይዘው ለቀውኛል። ሀምሳ ሺህ ብር እንቀጣሀለን ነው ሚሉኝ። እኔ ደግሞ ስራ አጥ ሆኜ ሀያ ሺህ ብር ከሰው ተቀብዬ ላለመራብ የምውተረተርባት ሥራ እንጂ ማርያምን እስካሁን ትርፍ የለኝም። ያው ቢያስሩኝ ነው ያ የለመድሁትን እራብ መጋፈጤ እንጂ!"

#ሰውተኮር ምንድን ነበር?

@EliasMeseret
#መልካምዜና የሀይማኖት አባቶች ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ መደረጉ መልካም አካሄድ ነው።

ክልከላዎችን፣ ወከባዎችን፣ እስሮችን እና እንግልቶችን ለማስቆም የሚወሰዱ እርምጃዎች ለሀገር ጠቃሚ በመሆናቸው ሁሉም ሊደግፋቸው እና ሊያበረታታ ይገባል።

@EliasMeseret