Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
8.69K subscribers
117 photos
1 video
18 files
179 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

የነጃሺ መስጂድና እስላማዊ ማዕከል የኪነ ሕንጻ ንድፍ ማሻሻያ እንዲደረግበት ፕሬዚደንቱ አሳሰቡ

የካቲት 21፣ 2016 (አዲስ አበባ) - የነጃሺ መስጂድና ማዕከል ንድፍ እስላማዊና ታሪካዊ እሴታችንን ባካተተ መልኩ ማሻሻያ እንዲደረግበት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት አሳሰቡ።

የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ይህን ያሳሰቡት፣ የነጃሺ መስጅድና እስላማዊ ማዕከል ግንባታ ዐብይ ኮሚቴና የኪነ-ሕንጻ ንድፍ ውድድሩ ዳኞች በዛሬው ዕለት ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንትና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ስለ ዳኝነቱ ሂደትና ስለ አሸናፊው የኪነ ሕንጻ ንድፍ ማብራሪያ በሰጡበት ጊዜ ነው።

የኪነ ሕንጻ ንድፍ ውድድሩ የዳኞች ቡድን ዘጠኝ ባለሙያዎችን ያካተተ እንደነበረና፣ ሂደቱም ምሥጢራዊና ፍትኃዊ አካሄድን የተከተለ እንደነበር በዚሁ ጊዜ ተነግሯል።

የዳኝነት ቡድኑ አባላት፣ በውድድሩ ተመርጠው ደረጃ ያገኙትን የኪነ ሕንጻ ንድፎች 'በ3-D አኒሜሽን' ለዕይታ በማቅረብ ከማሳየታቸውም በላይ፣ የማወዳደሪያ መስፈርቶችን በተመለከተ ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ገለጻውን ካደመጡ በኋላ በሰጡት አስተያየት፣ የሚገነባው ታሪካዊ መስጂድ የኢትዮጵያ ሙስሊም በአፍሪካ ደረጃ የሚታወቅበት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ፕሬዚደንቱ አክለውም፣ በእስልምና ታሪክ ከፍ በሚያደርገን ንጉሥ ስም የምንገነባው የነጃሺ መስጂድና ማዕከል ያለ ሚናራ የሚታሰብ አይሆንም በማለት አሳስበዋል።

ሸይኽ ሐጂ በተጨማሪም፣ በውድድሩ ከፍ ያለ ነጥብ ያገኘው የኪነ ሕንጻ ንድፍ እስላማዊና ታሪካዊ ማንነታችንን ባካተተ መልኩ ማሻሻያ ሊደረግበት ይገባል ብለዋል።

መስጂድ በቅርጽ ደረጃ ከሚታወቅበት መገለጫ አንዱ ሚናራ በመኾኑ፣ ይህ ታሪካዊ መስጂድ ወጪን በቆጠበ መልኩ አራት ሚናራ ቢታከልበት አይበዛበትም ሲሉ ተናግረዋል።

አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ዕድል የተሰጣቸው የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አመራር አባላትም ንድፉ በባለሙያ ዐይን ደረጃውን የጠበቀ ሊኾን ቢችልም፣ የእስልምናንና የሙስሊሞችን እሴት የሚገልፅ የመስጂድ ባህሪ የለውም ብለዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን እና የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ ንድፉ የእስልምና እሴትን ያካተተ አይደለም በማለት ንድፉ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ለነጃሺ መስጂድና እስላማዊ ማዕከል ግንባታ የተመሠረተው ዐብይ ኮሚቴና የኪነ-ሕንጻው የሙያ ዳኞች ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራር የቀረበውን አስተያየትና ቅሬታ ተቀብለው፣ በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት ማሻሻያ እንደሚያደርጉ የጋራ ግንዛቤ መወሰዱን ተናግረዋል።

**
ሻዕባን 19፣ 1445
*****
የኢ.እ.ጉ.ጠ.ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc1
ኢስላሚክ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሜኒሶታ ያስተማራቸውን ተማሪዎች በሸራተን አዲስ ሆቴል ያስመርቃል።

የካቲት 22/16( አዲስ አበባ)ኢስላሚክ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሜኒሶታ 50 በሁለተኛ ዲግሪና 16 በዲፕሎማ ያስተማራቸውን ተማሪዎች በሸራተን አዲስ ሆቴል ከደቂቃዎች በኋላ የማሰመረቅ መርሐ ግብሩን ያካሂዳል።

በዛሬዉ የዩኒቨ ርስቲዉ የምርቃት መርሐግብር ተመራቂዎች ዉስጥ ሁለት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚዎች እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል።

እንደ አውሮፖ አቆጣጠር በ2016 ማስተማር የጀመረው መቀመጫዉን በአሜሪካ ያደረገው ኢስላሚክ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሜኒሶታ የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱን በኢትዮጵያ ከከፈተ በኋላ የዛሬው ምርቃት የመጀመሪያው ነው።

****

ሻዕባን 20፣ 1445 ዓ.ሒ

ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.co
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

​የሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አዳዲስ አመራሮችን ሰየመ።

የካቲት 28፣ 2016 (አዲስ አበባ) - የሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ፣ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት ባልቻሉት አመራሮች ምትክ፣ አዳዲስ አመራሮችን መረጠ።

መጋቢት 30፣ 2015 በተካሄደ ጠቅላላ ጉባዔ ተመርጦ የነበረው የሥራ አስፈጻሚ የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት መወጣት ካለመቻሉም በላይ፣ የተጣለበትን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው በጭቅጭቅ በመጠመዱ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ችግሩን ለመፍታት ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።

ይሁንና፣ ሁኔታው ሊሻሻል ባለመቻሉ፣ ጉዳዩ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ከመድረሱ በፊት ጠቅላይ ምክር ቤቱ በሕገ መጅሊሱ አንቀፅ 23፣ ንኡስ አንቀፅ 7 በተደነገገዉ መሠረት፣ የእርምት እርምጃ ለመዉሰድ ተገድዷል።

ለችግሩ መፍትኄ ለመስጠት የመጅሊሱ ከፍተኛ አመራር በተገኘበት በዛሬው ዕለት፣ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ፣ የሥራ አስፈፃሚ ሹም ሽር አድርጓል። በዚህም መሠረት፣

1. ሸኽ አብዱሽኩር አብዱልቃድር ሽብሩ - ፕሬዚደንት
2. ሸኽ ናስር ሸኽ ዑስማን አማን - ምክትል ፕሬዚደንት
3. ሐጅ ኑሪ ናስር አማራ - ዋና ፀሐፊ
4. ሐጅ ዑመር ሑሴን አደም - አባል
5. ሸኽ ሙኽታር ሙስጠፋ ማህሙድ - አባል
6. አቶ መሐመድ አብዱልቃድር ሬቦ - አባል
7. ሸኽ ጀማል አብዱሽኩር - አባል
8. ሸኽ ከድር ጀማል - አባል
9. ሸኽ ዓሊ አደም - አባል
10. ሸህ ሱለይማን ዑስማን - አባል
11. ኢንጂነር ሚፍታህ መሐመድ አባል በመሆን ተመርጠዋል።

****
ሻዕባን 26፣ 1445 ዓ.ሒ
****
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.co
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
በጠቅላይ ምክር ቤቱ ባለቤትነት የዕርቀ ሠላም ኮንፈረስ የመጀመሪያ ዙር ወይይት ተጀመረ

የካቲት፣ 29/2016(አዲስ አበባ)
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ባለቤትነት በሱማሌና በአፋር ክልሎች መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት የተዘጋጀ የዕርቀ ሠላም ኮንፈረስ የመጀመሪያ ዙር ወይይት በሸራተን አዲስ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በእዚህ የዕርቀ ሠላም ኮንፈረስ ከሁለቱም ወንድም ሕዝቦች የተወከሉ ኡጋዞች፣ ዑለሞች ፣የሀገር ሽማግሌዎች ፣ሱልጣኖችና ተዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል።
***
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/ei
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የረመዳን መልክት አስተላለፉ።

የካቲት 29፣ 2016 (አዲስ አበባ) -
ታላቁ የረመዳን ወር የእዝነት፣ የመተሳሰብ፣ የምህረት ወር በመኾኑ ደካሞችን፣ ችግረኞችን፣ ተፈናቃዮችን እንዲሁም ወላጅ አልባ ሕጻናትን በመርዳትና ማዕዳችንን በማካፈል በመተሳሰብና አላህን በመለመን ልናሳልፈው ይገባል ሲሉ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ተናገሩ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ዛሬ በሸራተን አዲስ በሰጡት የረመዳን ዋዜማ መግለጫ፣ የምንቀበለው የረመዳን ወር የእዝነት፣ የምህረትና ከእሳት ነጃ የምንወጣበት፣ አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው የዒባዳ ወር ይሁንልን ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

ፕሬዚደንቱ በዚሁ መግለጫቸው ለመላው ሙስሊም ማኀበረሰብ እንኳን ለ1445 ዓ.ሂ /2016 የረመዷን ወር በሰላም አደረሳችሁ በማለት የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዚደንቱ መንፈሳዊ ልዕልና የሚኖረው ሰላም ሲኖር በመኾኑ፣ ለሀገራችን ሰላም እና ለሕዝባችን ደኅንነት ዱዐ ልናደርግ ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

በመግለጫው ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን እና የሐጅ ዘርፍ ኃላፊው ሸይኽ አብዱልአዚዝ ሸይኽ አብዱልወሊ ተገኝተዋል።

****
ሻዕባን 27፣ 1445 ዓ.ሒ
****

የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/ei
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ለአካል ጉዳተኞች ትኩረትና ድጋፍ እንዲሰጥ ጥሪ ቀረበ።

የካቲት 30፣ 2016 (አዲስ አበባ) - ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ታላቁን የረመዳን ወር ሲቀበል፣ ለአካል ጉዳተኛ ሙስሊም ወገኖቹ ትኩረት ሊሰጥ፣ ሊያግዝና ሊደግፋቸው እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ጥሪ አቀረቡ።

ዋና ፀሐፊው ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ ይህን ጥሪ ያቀረቡት "የመስሊም አካል ጉዳተኞች ጉዳይ ምን እና የማን?" በሚል መሪ ቃል ከ'ኸይራት የአካል ጉዳተኞች እስላማዊ ማኀበር' ጋር በመተባበር በተዘጋጀ መድረክ ላይ ነው።

በአካል ጉዳተኛ ሙስሊሞች ፍላጎቶች ላይ ባተኮረው በዚህ መድረክ ላይ፣ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ አካል ጉዳተኝነት ማለት አለመቻል ማለት አለመኾኑን ጠቅሰው፣ በአካለ ጸጋ ወንጀል ሰብስቦ ከመጠየቅ እንደሚያድን አብራርተዋል።

ሸይኽ ሐሚድ አክለውም፣ መላው ሙስሊም ማኅበረሰብ ለአካል ጉዳተኞች አስፈላጊውን ድጋፍና ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሀሩን መጅሊስ ለማንኛውም መስሊም አገልግሎት የመስጠት ኃላፊነት አንዳለበት ጠቅሰው፣ "በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ ያለው ክፍተት ሰፊ በመኾኑ፣ መጅሊሱ ይህን መሰል ማኅበራትን ያበረታታል፣ ያግዛልም" ብለዋል።

በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ የትምህርትና ማኀበራዊ አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር አብደላ ኸድር በበኩላቸው፣ "ከማኅበሩ ጋር በትምህርት ዙሪያ አቅም በፈቀደ መጠን አካል ጉዳተኞች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ትስስር እንፈጥራለን" ብለዋል።

ዑስታዝ ባህሩ ዑመር በእስልምና ታሪክ ውስጥ አካል ጉዳተኛ ሆነው ትልልቅ ገድል የፈፀሙ የነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ.) ባልደረባዎች፣ የእስልምና ባለውለታዎች፣ ሙጃሂድና ሸሂድ የኾኑ ትልልቅ ሰብዕናዎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ደርስ አቅርበዋል።

የኸይራት የአካል ጉዳተኞች እስላማዊ ማኀበር ፕሬዚደንት አቶ ሡልጣን ኢሰሙ፣ አካል ጉዳተኞች በሚፈልጓቸው አገልግሎቶች እና ድጋፎች ላይ ያተኮረ ጽሑፍ አቅርበዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የኾኑት እጩ ዶክተር በፈንታው ዓለሙ ቴክኖሎጂ ለአካል ጉዳተኞች አስቻይ መኾኑ ስላለው ጠቀሜታ ማብራሪያ የሰጡ ሲኾን፣ ከመድረኩ በተነሱ ሐሳቦች ዙርያ ተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የባቡል ኸይር ተቋም ዋና ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሀናን ሙሐመድ፣ "ኸይራት የአካል ጉዳተኞች እስላማዊ ማኀበር ዓላማውን ለማሳካት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ማገዝ የሥራችን አካል ስለኾነ፣ ምንጊዜም ከጎናችሁ ነን" ብለዋል።

"ስለ እኔ" የተባለው የበጎ አድራጎት ማኅበር የ6ኛ ዙር ሠልጣኞች በበኩላቸው፣ ለኸይራት የአካል ጉዳተኞች ማኀበር ግምቱ ከ45 ሺህ ብር በላይ የኾነ ተሽከርካሪ ወንበር እና የብሬል ቁርአን ድጋፍ አድርገዋል።

የኸይራት የአካል ጉዳተኞች እስላማዊ ማኀበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ሁሉም በየዘርፉ ላደረገው አስተዋጽዖ አመሥግነው፣ "የአካል ጉዳተኞች ማኀበር የማቋቋም ፋይዳው ሙስሊም አካል ጉዳተኞች የዲን ትምህርት እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ መፍጠር በመኾኑ ደጋፋችሁ አይለየን" ብለዋል።

***
ሻዕባን 28፣ 1445 ዓ.ሒ
***
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/ei
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

በታላቁ የረመዳን ወር ምዕመናን የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት እንዲያሳልፉ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት አሳሰቡ።

መጋቢት 4፣ 2016 (አዲስ አበባ) - ታላቁ የረመዷን ወር ከመቼውም በላይ የአብሮነትና የመተሳሰብ ወር በመሆኑ፣ ምዕመናኑ የተቸገሩ ወንድምና እህቶችን በመደገፍ እንዳያሳልፉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ አሳሰቡ።

ታላቁ የረመዳን ወር ቀኑን በፆም፣ ምሽቱን በኢባዳ የምናሳልፍበት ታላቅ ወር በመኾኑ፣ መስሊሙ ማኅበረሰብ ወሩን በተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

ረመዷን የአብሮነት ወር በመኾኑ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ይህን የኢፍጣር መርኃ ግብር ማዘጋጀቱን ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል።

የፕሬዚደንቱ ልዩ አማካሪ ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ ታላቁ የረመዷን ወር የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና የአብሮነት ወር በመኾኑ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የተቸገሩ ወገኖቻችንን በመርዳት እንዲያሳልፍ ጠይቀዋል።

በመርኃ ግብሩ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈፃሚዎች፣ የዓሊሞች ጉባዔ የሥራ ኃላፊዎች፣ የኢፌዲሪ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የክልል መጅሊስ ሥራ አፈፃሚዎች፣ ዱዓቶችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ታድመዋል።

****
ረመዷን 4፣ 1445 ዓ.ሒ
****
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር |https://x.com/eiasc1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ማሳሰቢያ

• የሐጅ ምዝገባ ክፍያዎን በተጠቀሱት ባንኮች ብቻ ይፈጽሙ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለ1445 ዓ.ሒ (የ2016 ዓ.ል) የሐጅ ጉዞ፣ "የዘመነ መስተንግዶ ለአል-ረህማን እንግዶች" በሚል መሪ ቃል፣ በ27 የምዝገባ ጣቢያዎች ከጥር 25፣ 2016 ዓ.ል ጀምሮ ምዝገባ እያካሄደ መኾኑ ይታወቃል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ በዚህ ዓመት የሐጅ መስተንግዶ ክፍያ እንዲሰበስቡ ለባንኮች ባወጣው የማወዳደሪያ መስፈርት መሠረት ከ12 ባንኮች ጋር ስምምነት በማድረግ በመሥራት ላይ ይገኛል።

በዚህም መሠረት፣ የሐጅ መስተንግዶ ክፍያ እንዲሰበስቡ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር ስምምነት ያደረጉት ባንኮች የሚከተሉት ናቸው:-

1. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
2. አዋሽ ባንክ
3. የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ
4. ዘምዘም ባንክ
5. ወጋገን ባንክ
6. ኦሮሚያ ባንክ
7. ዳሸን ባንክ
8. ሒጅራ ባንክ
9. አቢሲኒያ ባንክ
10. ራሚስ ባንክ
11. ሲንቄ ባንክ
12. ቡና ባንክ።

ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 12 ከተጠቀሱት ባንኮች ውጪ፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅ መስተንግዶ ክፍያን እንዲሰበስብ ውል የሰጠው ባንክ የለም። በመኾኑም ሕብረተሰቡ ይህን አውቆ ፣ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግና የሐጅ መስተንግዶ ክፍያውን በተጠቀሱት ባንኮች ብቻ እንዲፈጽም ጠቅላይ ምክር ቤቱ ያሳስባል።

መጋቢት 6፣ 2016 ዓ.ል
(ረመዷን 5፣ 1445 ዓ.ሒ)
**
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

እስላማዊ ወንድማማችነትን በማጠናከር ልዩነቶችን ማጥበብ እንደሚገባ ፕሬዚደንቱ አሳሰቡ።

መጋቢት 9፣ 2016 (አዲስ አበባ) - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የዓለም ሙስሊሞች ሊግ ባዘጋጀው ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ ንግግር አደረጉ።

ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም በንግግራቸው እስልምና አንድነትን ጠብቀን ተባብረን በሰላም እንድንኖር ማስተማሩን ቅዱስ ቁርኣንና የነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ሐዲስን በማጣቀስ ተናግረዋል።

ልዩነቶች ተፈጥሯዊ መሆናቸውን የጠቀሱት ፕሬዚደንቱ፣ ልዩነቶች ሲከሰቱ ወደ ቁርኣን እና ሐዲስ በመዉሰድ መፍታት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመካ እየተካሄደ የሚገኘው ዓለም አቀፍ
ጉባዔ "በእስልምና መዝሐቦች መካከል ድልድይ መገንባት" በሚል መሪ ቃል በሙስሊሙ የእርስ በርስ አንድነት፣ ሰላምና መተባበር ላይ ያተኮረ እንደኾነ ለማወቅ ተችሏል።

ሸይኽ ሐጂ የዓለም ሙስሊሞች ቂብላ በሆነችው በቅድስቲቱ መካ ከተማ፣ በታላቁ የረመዷን ወር በዚህ የዓሊሞች ጉባዔ ላይ ንግግር የማድረግ ዕድል በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትና በራሳቸው ስም ገልፀዋል።

የእስልምና አስተምህሮዎች ያላቸውን ልዩነት በውይይት ማጥበብን ዓላማ ባደረገው በዚህ ዓለም አቀፍ ጉባዔ "መዝሐቦች በእስልምና እንዴት ይደጋገፋሉ?" እና "መዝሐቦች በዩኒቨርሲቲዎችና በትምህርት ተቋማት ተባብረው እስልምናን እንዴት ይገነባሉ?" በሚሉ መነሻ ሐሳቦች ዙርያ ጽሑፎች ቀርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በመካ እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሼይኽ አብዱልከሪም ሼይኽ በድረዲንን ጨምሮ፣ ከመላው ዓለም የመጡ ሙፍቲዎችና ዓሊሞች ተሳታፊ እንደሆኑ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ቃል አቀባይ ከላከው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

**
(ረመዷን 8፣ 1445 ዓ.ሒ)
**
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮችና ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተዉጣጡ አባቶች ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር ዐብይ አህመድ ጋር ተወያዪ።

መጋቢት 10፥2016 ( አዲስ አበባ)የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮችና ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ አባቶች ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር ዐብይ አህመድ ጋር ዛሬ ከሰዐት በኋላ ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ።

የጠቅላይ ምክርቤቱ አመራሮችና ከክልል የተዉጣጡ አባቶች በጧቱ ክፍለ ጊዜ በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውሮ ጉብኝት አድርጓል።

ረመዷን 9፣ 1445 ዓ.ሒ)
**
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አመራሮችና ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ አባቶችን አስፈጠሩ።

መጋቢት 10፣ 2016 (አዲስ አበባ ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የ1445ዓ.ሒ(2016 ዓ.ል) የታላቁን የረመዷን ፆምን ምክንያት በማድረግ ዛሬ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች እና ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ አባቶችን አስፈጠሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች እና ከተለያዩ ክልሎች ከተወጣጡ አባቶች ጋር ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡

ረመዷን 9፣ 1445 ዓ.ሒ)
**
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
የአማራ እስልምና ጉዳዮች ከተለያዩ የሐገራችን አካባቢዎች ተፈናቅለው በክልሉ ለተጠለሉ ወገኖች የዕርዳታ ጥሪ አቀረበ።

መጋቢት 12፣ 2016 (አዲስአበባ) የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት "ፆማችንን ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን" በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ የሐገራችን አካባቢዎች ተፈናቅለው በክልሉ በጊዚያዊ መጠለያ ጣቢያና በ ተለያዩ ቦታዎች ለተጠለሉ ወገኖቻችን የእርዳታ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብርን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በተሰጠው በዚህ መግለጫ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕረዚዳንት ሼይኽ ሙሐመድ አንዋር እንደተናገሩት ፤ ነብያችን ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ሁሌም ቸር ሲሆኑ በታላቁ የረመዷን ወቅት የሚያደርጉት ቸርነት ግን ከሌላው የተለየ እንደ ነበሩ ነብያዊ ሐዲስን አስታዉሰዋል።

በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ የሐገራችን አካባቢዎች ተፈናቅለው በክልሉ በጊዚያዊ መጠለያ ጣቢያዎችና በተለያዩ ቦታዎች ለተጠለሉ ወገኖቻችንን ለመርዳት መላው ደጉ ሕዝባችን እጁን ሊዘረጋ እንደሚገባ ጥሪያቸው አስተላልፈዋል።

የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አደረጃጀት የልማት ዘርፍ ኅላፊ ሐጂ አመዴ ይማም የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ከመቼውም በተለየ የሁላችንም ድጋፍና ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ወቅት በመሆኑ በሐገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር የሚገኙ ወ ገኖቻችን የዕርዳታ እጁን ሊዘረጋ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የክልሉ እስልምና ዋና ፀሐፊ ሼይኽ አብዱራህማን ሱልጣን የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት "ፆማችንን ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን " በሚል መሪ ቃል የዕርዳታ ማሰባሰቢያ መርሐግብር በገንዘብ፣ በደረቅ ምግብ እና በአልባሳት ሕብረተሰቡ መርዳት እንዲችል አማራጮችን ማቅረቡን ተናግረዋል።

ለዕርዳታ አሰባሰቡ በክልሉ እስልምና ጉዳዮች አማካኝነት ስድስት ባንኮች መከፈታቸውን ገልፀዋል።
እነርሱም 1. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000 6219 77777
2. አማራ ባንክ 8800000992254
3.ሒጅራ ባንክ100 529 7390 001
4. ዳሸን ባንክ 790 207 0047 911
5. ዘምዘም ባንክ 0038848 410301
6. ፀሐይ ባንክ 1004462781 መሆናቸውን ፀሐፊው ገልፀዋል።

ለደረቅ ምግብና አልባሳት ድጋፍ ማሰባሰቢያ ተውፊቅ (ፍል ውሐ)፣ ኢማሙ አህመድ ( ቤተል አለም ባንክ) እና የታላቁ የንጉስ ነጃሺ መሳጂድ ቅጥር ጊቢ ውስጥ የመቀበያ ቦታዎች መዘጋጀታቸውን ሼይኽ አብዱራህማን ሱልጣን ተናግረዋል።

ረመዷን 11፣ 1445 ዓ.ሒ)
**
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
ማሳሰቢያ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የሐጅ ምዝገባ ማጠናቀቂያ ቀነ ገደብ ይፋ አደረገ።

በ2016/1445 ሂጅሪያ ሐጅ ለማድረግ ላሰባችሁ ኢትዮጲያዉያን የሙስሊም ማህበረስብ በሙሉ፤ እንድሚታወቀዉ የዘንድሮዉ ሐጅ አሰራር ከዚህ ቀደም ከነበረዉ በማዘመን የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ "የዘመነ አገልግሎት ለአር-ረሕማን እንግዶች" በሚል መሪ ቃል ምዝገባዉን በፊት ከተለመደዉ አሰራርና ጊዜ ቀደም ብሎ ከጥር 25/2016 ጀምሮ በይፋ አዉጆ ሲያከናዉን ቆይቷል።

በዚሁ መሰረት ላለፉት ተከታታይ 2 ወራት ገደማ ምዝገባው በጥሩ ሁኔታ ሲካሄድ የነበረ ሲሆን፥ የተሰጠንን ኮታ ለመሙላት የቀረዉ ከ1400 ሰዎች ኮታ በታች የሆነ ከመሆኑ ጋርና የምዝገባ ሂደቱም ተቋጭቶ ወደሚቀጥለው ሂደት መተላለፍ አስፈላጊ በመሆኑ የምዝገባዉ የመጨረሻ ቀን ረመዳን 25 (መጋቢት 26) እና የክፊያ ማጠናቀቂያ የመጨረሻ ቀን ደግሞ ረመዳን 29 (መጋቢት 30) እንዲሆን ተወስኗል፡፡

በመሆኑም ሐጅ ለማድረግ ኒያ ኖሯችሁ የምዝገባውን ሂደት ላላጠናቀቃችሁ በሙሉ በቀሩት የምዝገባ ቀናት ዉስጥ በአቅራብያችሁ በሚገኙት የምዝገባ ጣቢያዎች በመቅረብ እንድትመዘገቡና ክፊያችሁንም እንድታጠናቅቁ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ጥሪ እያስተላለፈ፣ በተጨማሪም ኮታዉ ከተባለዉ ቀን በፊት የሚሞላ ከሆነ የተቀመጠዉን ቀነ ገደብ ሳይደርስ ምዝገባውን እንደሚያጠናቅቅ መልዕቱን ያስተላልፋል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት

መጋቢት 18/2016 ዓ.ል
ረመዳን 17/1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

"አላህ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምን እንዲያመጣልን ተማፀኑ" ሲሉ ፕሬዚደንቱ ጾመኞችን አሳሰቡ።

መጋቢት 18፣ 2016 (አዲስ አበባ) - "በሰው ሠራሽ አደጋዎች በችግር ውስጥ ለወደቁ ወገኖቻችን ዱዓ አድርጉ፣ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምን እንዲያመጣልን አላህን ተማፀኑ" ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ለሀገሪቱ ሙስሊሞች ጥሪ አቀረቡ።

ፕሬዚደንቱ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ይህን ጥሪ ያደረጉት፣ አራተኛው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርኃ ግብር ዛሬ በአዲስ አበባ በአደባባይ በድምቀት በተከናወነበት ጊዜ ነው።

"በነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ.) "'ጾመኛ ከሚደሰትባቸው ሁለት ቅጽበቶች አንዱ' ተብሎ የተወሳውን ኢፍጣር እንዲህ በአንድ ስፍራ ተሰባስበን በጋራ ለማፍጠር መብቃታችን የሚያስደስት በመኾኑ፣ ሁላችሁንም እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም።

አክለውም፣ "እንዲህ ተሰባስበን በጎዳና ላዬ ስናፈጥር የምንደሰተውን ያህል፣ በተለያዩ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በጎዳና ላይ ዝናብና ፀሐይ እየተፈራረቀባቸው የሚገኙ ወገኖቻችንን ስናስብ ከፍተኛ ሐዘን ይሰማናል" ብለዋል።

በተጨማሪም ሸይኽ ሐጂ፣ "ጾመኞች በሚያፈጥሩበት ጊዜ የሚያደርጉት ዱዓ አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው በመኾኑ፣ ሁላችሁም በዚህ ቅጽበት በጦርነት ሳቢያ በችግር ውስጥ ለሚገኙት ወገኖቻችን ዱዓ እንድታደርጉና ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምን እንዲያመጣልን አላህን እንድትማፀኑ" ሲሉ ምዕመናኑን ጠይቀዋል።

"ሁላችንም በዱንያ ያየነውን ደስታ፣ አላህ በጀነትም የምናይ ያድርገን" ሲሉ ዱዓ አድርገዋል።

በመርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸይኽ ሡልጣን አማን ኤባ በበኩላቸው፣ ለታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስኬት አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን አመስግነዋል።

"በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት የተከናወነው የጎዳና ኢፍጣር ባማረ ሁኔታ እንዲጠናቀቅና አዳቡን በጠበቀ መንገድ እንዲከናወን ሕዝበ ሙስሊሙና የአዲስ አበበ ከተማ መስተዳድር ያበረከቱት አስተዋጽዖ ጉልህ በመኾኑ፣ ምስጋና ይገባቸዋል" ብለዋል ሸይኽ ሡልጣን አማን።

በዝግጅቱ ላይ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች በተውጣጡ ሐፊዞች መካከል በተካሄደ የቁርኣን ሂፍዝ ውድድር አንደኛ የወጣው ሐፊዝ የሐጅ ጉዞ ሽልማት እንደተመቻቸለት የተነገረ ሲኾን፣ ሁለተኛ የወጣው ተወዳዳሪ የ250 ሺህ ብር፣ ሦስተኛ የወጣው ተወዳዳሪ ደግሞ የ100 ሺህ ብር ተሸላሚ መሆናቸው ተነግሯል።

በመርኃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ የፕሬዚደንቱ አማካሪ እና የመርኃ ግብሩ የበላይ አሥተባባሪ ኡስታዝ አቡበክር አሕመድ፣ ከተለያዩ ሀገራት የተወከሉ ሙፍቲዎች፣ ምሁራን እና ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል።

**
ረመዳን 17፣ 1445 ዓ.ሒ)
**
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የበላይ መሪዎች፣ አል ኢምራን የቁርኣን ሂፍዝና እስላማዊ ማዕከልን ጎበኙ።

መጋቢት 19፣ 2016 (አዲስ አበባ) - በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራ የመጅሊሱ የበላይ አመራሮች ሲኤምሲ የሚገኘውን የአል ኢምራን የቁርኣን ሂፍዝ እና እስላማዊ ማዕከል ጎበኙ።

የመጅሊሱ የበላይ መሪዎች ከስፍራው ሲደርሱ፣ የማዕከሉ የበላይ ጠባቂና አሚሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በአቀባበሉ ላይ፣ የአል ኢምራን የቁርኣን ሂፍዝ እና እስላማዊ ማዕከል የበላይ ጠባቂና አሚሮች ዑስታዝ ሙሐመድ ጀማል ጎናፍር፣ ዑስታዝ አቡበክር አብደላ፣ ሐጂ ዩኑስ ፈቂህ፣ ዑስታዝ ሰዒድ ዓሊ በያን፣ ዑስታዝ አብደልፈታህ፣ ሸይኽ ሸሪፍ፣ ዑስታዝ ሙሐመድ አብዱሰላም፣ ዑስታዝ አዲል አሕመድ ሸሪፍ እና ዑስታዝ ሙሐመድ ዚያድ ተገኝተዋል።

የማዕከሉ ዳይሬክተር ዑስታዝ አስለም ዩሱፍ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ አመራሮች የማዕከሉን የጉብኝት ግብዣ አክብረው በስፍራው በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ምሥጋና አቅርበዋል።

በተጨማሪም የማዕከሉ ዳይሬክተር ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት እና ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት፣ እንዲሁም የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ስለ ማዕከሉ መንፈሣዊ አገልግሎት ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በዚሁ ጊዜ፣ በማዕከሉ የበላይ ጠባቂና አሚሮች ስለተደረገላቸው አቀባበል አመሥግነው፣ የዲን ተቋማት ከመንፈሣዊ አገልግሎታቸው በተጓዳኝ፣ የጋራ ተቋማቸውን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ለማጠናከር በጋራ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም አክለውም፣ እስላማዊ ተቋማት ከዲን ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ችግሮች በምክክር እየፈቱ፣ ወንድማማችነትን በማስቀጠል ላይ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ይህ ማዕከል በርካታ ወንድሞችና እህቶቻችን፣ ወጣቶቻችንና ልጆቻችን ያለባቸውን የዲን ዕውቀት ክፍተት የሚሞላና፣ መንፈሣዊነትን የሚያጎለብት መኾኑን የጠቀሱት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም፣ አክለውም፣ "ጠቅላይ ምክር ቤታችን ይህን ማዕከል እንደ አንድ አጋዥ ተቋም ትልቅ እውቅና ይሰጠዋል" ብለዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን በበኩላቸው፣ "በመግባባት ላይ የተመሠረተ ሕብረትና አንድነት ላይ የቆመ ዲን የጠንካራ አለት ያህል በመኾኑ፣ ከሁሉም በላይ ወንድማማችነትን ማስቀደም ይገባል፤ በትብብራችን ብዙ እንጓዛለን" ብለዋል።

የፕሬዚደንቱ ልዩ አማካሪ ዑስታዝ አቡበክር አሕመድ በበኩላቸው፣ አል ኢምራን የቁርኣን ሂፍዝ እና እስላማዊ ማዕከል የብዙ አባቶችና አዒማዎች አሻራ ያረፈበት መሆኑን ጠቅሰው፣ ማንኛውም ችግር በሹራ እየተፈታ፣ በማዕከሉ አሚሮች በሚታቀዱ በማናቸውም ተግባራት ላይ የአቅማቸውን ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በጉብኝቱ መጨረሻ፣ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እና ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን ለጎብኚዎች በተዘጋጀው የክብር መዝገብ ላይ የእስላማዊ ተቋማትን መልካም ግንኙነት እና ትስስር በማጠናከር ዙሪያ ሐሳቦቻቸውን አስፍረዋል።

**
ረመዳን 18፣ 1445 ዓ.ሒ
**
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በአድዋ ሙዝየም ረመዳን እና ዐቢይ ፆምን በማስመልከት ልዩ "የፍቅር እና የአብሮነት ማዕድ" አስተናገዱ።

መጋቢት 19፣ 2016 (አዲስ አበባ) - የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬዉ ዕለት ረመዳንና ዐቢይ ጾምን ምክንያት በማድረግ ልዩ የጋራ ማዕድ መርኃ ግብር አካሄዱ።

በኢፍጣር ሰዓት በተካሄደው በዚህ ልዩ የጋራ ማዕድ መርኃ ግብር ላይ የፌደራሉ ጠቅላይ ምክር ቤትና የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የበላይ አመራሮች፣ የኢ.ኦ.ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እና የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያን አባቶች፣ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የተሰናዳውን ይህን ልዩ መርኃ ግብር አስመልክተው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸዉ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ክንዋኔውን፣ "የፍቅር እና የአብሮነት ማዕድ" ሲሉ ገልፀውታል።

“በብዝኃነት ተዉባ፣ ሁሉም ተዋዶ በአብሮነት የሚኖርባት አዲስ አበባ ዛሬ ምሽት የረመዳንና የዐቢይ ጾምን ምክንያት በማድረግ ክርስቲያን እና ሙስሊም የእምነት አባቶች፣ ወንድምና እህቶች፣ እንዲሁም የሁሉም እምነት ተከታዮች የተሳተፉበት የፍቅርና የአብሮነት መዓድ በመቋደስ፣ እንኳን አደረሳችሁ በመባባል የጋራ ጸሎት አድርገናል” ብለዋል ከንቲባ አዳነች።

**
ረመዳን 18፣ 1445 ዓ.ሒ
**
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ                           
የአፋርና የሶማሊ ክልሎች በጠቅላይ ምክር ቤቱ አደራዳሪነት ደም መፋሰስን ለማቆም፣ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ።

ሚያዚያ 11፣ 2016 (አዲስ አበባ) -
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ አደራዳሪነት ሲካሄድ በቆየው የአፋርና የሶማሊ ክልሎች የእርቀ ሰላም ውይይት ሁለቱ ክልሎች ተኩስ ለማቆም ከስምምነት ደረሱ።

ይህ የተነገረው በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተነሳሽነት በአል-ነሀሪ ሆቴል በአፋር እና በኢሳ በኩል ያሉ ታላላቅ ኡጋዞች እና መሪዎች የተሳተፉበት የአንድ ቀን ከግማሽ ሰፊ ውይይት ዛሬ በተጠናቀቀበት ጊዜ ነው።

የሶማሊና የአፋር ክልል ወንድማማች ሕዝቦች በመካከላቸው በተፈጠረው ያለመግባባት ሳቢያ የነበረውን አላስፈላጊ ደም መፋሰስ ለማቆምና ችግሩን በንግግር ለመፍታት እንደ መጀመሪያ እርምጃ፣ ሁለቱም ወገኖች ቃታ ከመሳብ ለመታቀብ ተስማምተዋል።

የሶማሊ ክልል ተደራዳሪ ኡጋዝ ሙስጦፋ ሙሐመድ እና የአፋር አቻቸው ሐጂ አበቶ ሙካ ሙሐመድ በሃይማኖት ተቋማችን አማካይነት ይህን መሰል እርቀ ሰላም መጀመሩ የሚያበረታታ መሆኑን ተናግረው፣ ጉዳዩ ረጅም  ዕድሜ ያለው ቢሆንም፣ የተጀመረው የሰላም ሂደት ትልቅ ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም በዚሁ ጊዜ፣ ይህን የሰላም ጥረት ስኬት መነሻ በማድረግ፣ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚካሄዱ ግጭቶችን በንግግርና በድርድር የመፍታት ጥረት እንዲጀመር የሰላም ጥሪ አቅርበዋል።

በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በመካሄድ ላይ ያሉ የወገን ለወገን የእርስ በርስ ግጭቶች እና አላስፈላጊ ደም መፋሰሶችን ለማቆም የንግግር፣ የውይይት እና የድርድር በሮች ሊከፈቱ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም፣ "የግጭት መንስኤዎችን መርምረን፣ የሐሳብ ልዩነቶችን እና ችግሮችን በውይይት በመፍታት በሰላም ጥላ ስር ተሰባስበን ሀገራችንን እናልማ" ብለዋል።

የሃይማኖት ተቋም መሪነት ትልቅ ሥራ በመኾኑ፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ይህን ተነሳሽነት መውሰዱ በጣም ያበረታታል ብለዋል የሁለቱ ወገን ተደራዳሪዎች።

አያይዘውም በሁለቱ ወንድማማች ማኅበረሰቦች መካከል አላስፈላጊ ደም መፋሰስን ለማቆምና አንድነታቸውን ለማጠናከር በሁለቱም በኩል በየክልላቸው በርካታ ሥራዎችን መሥራት እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የሶማሊና የአፋር ወንድሞቻችን
ቀደም ሲል ለተፈፀሙ ስህተቶች ለአላህ ብለው አውፍ በመባባል፣ወደፊት የወገኖቻችን የእርስ በርስ ደም መፋሰስን በማቆም፣ዘላቂ የተኩስ አቁም ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸው ይህን ቀን ታሪካዊ ያደርገዋል ብለዋል።

የሁለቱ ክልሎች የማኅበረሰብ መሪዎች የስምምነቱን ሂደት አሳክተው በቀጣዩ ሳምንት በጠቅላይ ምክር ቤቱ ሰብሳቢነት እንደሚገናኙ ለማወቅ ተችሏል።

ለአንድ ቀን ተኩል በተካሄደው የእርቀ ሰላም ውይይት ላይ የሁለቱም ሕዝቦች ከፍተኛ የጎሳ መሪዎች፣ ኡጋዞች፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚደንትና የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ አብዱልአዚዝ ሸይኽ አብዱልዋሊ፣ እንዲሁም የፕሬዚደንቱ ልዩ አማካሪ ኡስታዝ አቡበክር አሕመድ የተገኙ ሲኾን፣ ከመንግሥት በኩል የሰላም ሚኒስቴር  በታዛቢነት ተገኝተዋል።

****
ሸዋል 10፣ 1445 ዓ.ሂ
****
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከነገ ጀምሮ ለተወሰኑ ቀናት የሐጅ ምዝገባ ያካሂዳል።

ሚያዝያ 11፣ 2016 (አዲስ አበባ) - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ፣ ተቋርጦ የነበረውን የሐጅ ጉዞ ምዝገባ ከነገ ሚያዝያ 12፣ 2016 ጀምሮ ለተወሰኑ ቀናት እያካሄደ እንደሚቀጥል አስታወቀ።

የምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ፣ ለሐጅ ነይተው ሳለ በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን ላልተመዘገቡ ዜጎች ተጨማሪ ዕድል ለመስጠት፣ አቁሞ የነበረውን የሐጅ ጉዞ ምዝገባ፣ ከቅዳሜ ሚያዝያ 12 ጀምሮ ለተወሰኑ ቀናት ማራዘሙን አስታውቋል።

አዲስ ተመዝጋቢ ሑጃጆች ለምዝገባ ሲመጡ የታደሰ ፓስፖርት፣ መታወቂያ እና ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዘው እንዲመጡ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ አሳስቧል።

ፓስፖርት የሌላቸውና እድሜያቸው ከ50 ዓመት በታች የሆኑ ተመዝጋቢዎች፣ የልደት ሰርተፊኬት ማቅረብ እንደሚኖርባቸው ያሳሰበው ዘርፉ፣ ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የኾናቸው አዲስ ተመዝጋቢዎች መታወቂያ እና ጉርድ ፎቶ ግራፍ ብቻ ይዘው መቅረብ አለባቸው ብሏል።

ምዝገባው የተራዘመው ለጥቂት ጊዜያት እና አነስተኛ ቁጥር ላላቸው ተመዝጋቢዎች ዕድል ለመስጠት እንደኾነ የጠቀሰው የሐጅና ዑምራ ዘርፍ፣ ዘንድሮ ሐጅ ለማድረግ ነይተው እስካሁን ያልተመዘገቡ ምዕመናን በዚህ ዕድል እንዲጠቀሙ አሳስቧል።

*****
ሸዋል 10፣ 1445 ዓ.ሂ.
*****​
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ሚያዝያ 12፣ 1966 ዓ.ል. በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደውን ታላቁ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ 50ኛ ዓመት ለመዘከር፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን በንባብ ያሰሙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የሕዝብ ግንኙነት ተጠሪ የሆኑት ሸይኽ ሑሴን ሐሰን ሲኾኑ፣ የመግለጫው ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ቀርቧል።
* * *

ሚያዝያ 12፣ 1966 በአዲስ አበባ የተካሄደውን ታላቁ የሙስሊሞች ሰላማዊ ሰልፍ 50ኛ ዓመት ለመዘከር፣ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡

በሀገራችን የቅርብ ዘመን ታሪክ 50 ዓመታት ወደኋላ ስንሄድ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮት የፈነዳበትን የካቲት 1966 እናገኛለን፡፡ ይህ ወቅት፣ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካም ኾነ በማኅበራዊ መስኮች ሀገራችን ውስጥ የነበሩ የተለያዩ ችግሮችን የሕዝቡ ጫንቃ ሊቋቋም እማይችልበት ደረጃ ላይ የደረሰበት ጊዜ ነበር፡፡ የዘውድ አገዛዝ ሥርዓቱ ቢያንስ ከ1950ዎቹ መጨረሻ አንስቶ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይስተጋባ ለነበረው የ“መሬት ለአራሹ!” ጥያቄ እንኳ፣ ተገቢ ምላሽ ለመስጠት አልቻለም ነበር፡፡ እናም ሕዝቡ ከጫፍ እስከ ጫፍ፣ ፊውዳላዊው የዘውድ አገዛዝ ሥርዓት በቃኝ ብሎ በአመጽ ተነሳ፡፡ ሕዝባዊ አብዮት ተቀጣጠለ፡፡

ከየካቲት ወር 1966 ጀምሮ በነበሩት የአብዮቱ ጊዜያት ከተካሄዱ ሕዝባዊ ንቅናቄዎች እጅግ ጎልቶ በታሪክ የሚጠቀሰው ሚያዝያ 12፣ 1966 የተካሄደው የሙስሊሞች ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ነው፡፡ የዛሬ 50 ዓመት በዛሬዋ ዕለት የተካሄደው ይህ ሰልፍ፣ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የቅርብ ዘመናት ታሪክ ውስጥ ልዩ ስፍራ ያለው ሕዝባዊ ክንዋኔ ነው፡፡ ይህ ሕዝባዊ ክንዋኔ፣ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በረጅሙ የንጉሣዊ አገዛዝ ዘመን ሲፈፀሙባቸው የነበሩ የተለያዩ መድልዎዎች እንዲያከትሙ፣ የዜግነት መብቶቻቸው እንዲከበሩ፣ የሃይማኖት እኩልነት እንዲሰፍን በይፋ ለመጠየቅ፣ በሀገሪቱ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ደማቅና ታሪካዊ ሰልፍ ያካሄዱበት ዕለት ነው፡፡

“ንጉሥ አይከሰስ፣ ሰማይ አይታረስ” ይባልባት በነበረችው የዚያን ጊዜዋ ኢትዮጵያ፣ አያሌ የሀገሪቱ ማኅበረሰቦች፣ ዘውዳዊው የአገዛዝ ሥርዓት ያደርስባቸው የነበረው በደል የፈጠረባቸውን ምሬትና ብሶት አምቀው፣ ለዘመናት ከበደል፣ ከጭቆና እና ከመድልዎ ጋር ኖረዋል፡፡ በዚያ ዘመን ሥርዓታዊ፣ ተቋማዊ እና ስልታዊ በኾነ መልኩ ይካሄድ የነበረው ጭቆናና መድልዎ ተጎጂ ኾነው ከኖሩት የሀገሪቱ ሕዝቦች ውስጥ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዋነኛ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ከአንድ ሺህ ዓመታት በላይ በሀገሪቱ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዕድገት ላይ የራሳቸውን አሻራ ያሳረፉት የሀገራችን ሙስሊሞች፣ በሃይማኖታቸው ሳቢያ የተለያዩ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና የዜግነት መብቶቻቸውን ተነፍገው ይኖሩ ነበር፡፡

በተለይ ከ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመጀመሪያው ሩብ መጨረሻ ጀምሮ፣ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ሀገራችን ብለው በሚኖሩባት ሀገራቸው በማንነታቸው ተገፍተው፣ የዜግነት ክብር ተነፍገው፣ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየታዩ ይኖሩ ነበር፡፡ የታሪክ ምሁራን ሰሎሞናዊ በማለት የሚጠሩት ሥርወ መንግሥት ዘመን፣ ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በገዛ ሀገራቸው እንደ ባይተዋር ይታዩ የነበረበት የጨለማ ዘመን ነበር፡፡

ቀደምት ሙስሊም አባቶቻችን ከ1920ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ባሉት ረጅም ዓመታት፣ እንደ አንድ የሃይማኖት ማኅበረሰብ ተሰባስቦ ለመደራጀት፣ ሃይማኖታዊ ጉዳዮቻቸውን በተመለከተ ኃላፊነት ወስዶ የሚሠራ የጋራ ተቋም ለመመሥረት እልህ አስጨራሽ ትግሎችን አካሂደዋል፡፡ በገዛ ሀገራቸው እንደ ባዕድ እና ከዚያም አልፎ እንደ ጠላት እየታዩ፣ ከባድ የስነ ልቦና ጫናዎችን ተቋቁመው አሳልፈዋል፡፡ በተለይ ከ1966 ጥቂት ቀደም ብሎ፣ በ1964 አንዋር መስጂድን ማዕከል አድርጎ በተመሠረተው የሙስሊም ወጣቶች ክበብ አሥተባባሪነት፣ በአዲስ አበባ ሙስሊሙ ስለ ሃይማኖቱ እና ስለ ዜግነት መብቶቹ እንዲያውቅ ለማድረግ የተደረገው መጠነ ሰፊ ንቅናቄ፣ በአብዮቱ ፍንዳታ ማግሥት፣ አጠቃላይ የሕዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች በይፋ ለመንግሥት እንዲቀርቡ መንገድ የጠረገ ነበር፡፡

በሚያዝያ 1 ቀን 1966 በአዲስ አበባ ነዋሪ የኾኑ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተወካዮች ለወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው መኮንን በቁጥር 13 ጥያቄዎችን አቀረቡ፡፡ እነዚህም ጥያቄዎች የሚከተሉት ነበሩ፡

1ኛ. “መንግሥት ለእስልምና ሃይማኖት ድጋፍ የሚሰጥ መኾኑን በሕገ መንግሥት እንዲያሰፍርና፣ በተግባርም እንዲያውል፡፡”
[ይህ ጥያቄ ዛሬ ላይ ኾነው ሲሰሙት ግር ሊል ይችላል፡፡ ነገር ግን፣ በዚያ ዘመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሲሦ መንግሥትነት የሀገሪቱ ሀብት ባለ ድርሻ የነበረች ሲኾን፣ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ግን ከሀገሪቱ ሀብት ምንም ድርሻ ያልነበራቸው ከመኾኑ የመነጨ ጥያቄ ነበር፡፡]

2ኛ. "ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሃይማኖት አሥተዳደር ማኅበር፣ ወይም ተቋም እንድንመሠርት በመንግሥት ይፈቀድልን፡፡››
[ይህ ጥያቄ፣ ንጉሣዊው አገዛዝ ከወደቀና በደርግ ከተተካ ከሁለት ዓመታት በኋላ በ1968 ነው ምላሽ ያገኘው፡፡]

3. ‹‹የሸሪኣ ፍርድ ቤቶች ያለ ምንም ተጽዕኖ ነፃ ኾነው እንዲቋቋሙና ከመንግሥት በጀት እንዲመደብላቸው፣ ይህም በሚሻሻለው ሕገ መንግሥት እንዲካተት፣ የሚል ነበር፡፡
[ይህ ጥያቄ የአቶ እንዳልካቸው መኮንን ካቢኔ አዲስ ሕገ መንግሥት የሚያረቅቅ ኮሚሽን አቋቁመው የነበረ መኾኑን ታሳቢ በማድረግ የቀረበ ነበር፡፡]

4. "የሙስሊም ሃይማኖታዊ በዓላት መንግሥታዊ እውቅና አግኝተው በብሔራዊ ደረጃ ይከበሩ" የሚል ነበር፡፡
[ይህ ጥያቄ ምላሽ ያገኘው፣ ንጉሣዊው አገዛዝ ተወግዶ፣ ደርግ ሥልጣን ላይ ከወጣ በኋላ፣ በታሕሣሥ ወር 1967 ለመጀመሪያ ጊዜ ዒድ አል አድኃ አረፋ ብሔራዊ በዓል ኾኖ እንደሚውል በበዓሉ ዋዜማ ታሕሣሥ 14 ቀን 1967 በይፋ ከተነገረ በኋላ ነው፡፡ ኋላ በዓላትን የሚመለከት አዋጅ ሲወጣ፣ ሁለቱ ዒዶች እና የነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ልደት (መውሊድ) ብሔራዊ በዓላት ኾነው ታወጁ፡፡]

5. "የሙስሊም ወጣት ወንዶች እና የሙስሊም ወጣት ሴቶች ማኅበራት በአዋጅ እውቅና ተሰጥቷቸው ይቋቋሙ፤"
[ይህም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የዘመናት ጥያቄ አካል ኾኖ ነው የቀረበው፡፡ ንጉሣዊው አገዛዝ በአጠቃላይ ሙስሊሞችንና በሙስሊሞች የሚቋቋሙ ማኅበራትን ሁልጊዜም በጥርጣሬ ይመለከት ስለነበር፣ ወጣት ወንዶችና ወጣት ሴቶች ምንም ዓይነት ማኅበር የማቋቋም የዜግነት መብት አልነበራቸውም፡፡]

6. "ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የመሬት ባለቤት የመኾን መብታቸው ይከበር።"

7. ‹‹'አገር የጋራ ነው፣ ሃይማኖት የግል ነው› የሚለው አባባል በተግባር ይተርጎም›› የሚል ነበር፡፡
[በዘመኑ ይህ አባባል አልፎ አልፎ በንጉሡም ጭምር ይባል የነበረ ቢኾንም፣ በተግባር ግን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የርስት መሬት ባለቤት እንዳይኾኑ መከልከላቸው፣ ሀገር የጋራ ነው የሚለው አባባል የይስሙላ እንደነበር የሚያረጋግጥ ነበር፡፡]