ጥቅምት 8፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 15፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
"ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሚሰጠን ድጋፍና የሚያደርገው ክትትል አቅም ሆኖናል" - ሼይኽ ሙሐመድ ኸሊል
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
"የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እየሰጠን ያለው ድጋፍና የሚያደርገው ወቅታዊ ክትትል አቅም ሆኖናል" ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሼይኽ ሙሐመድ ኸሊል ተናገሩ።
ፕሬዘደንቱ ይህን የተናገሩት ትላንት ሐሙስ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ (ተቅዪም) ወራቤ ከተማ በሚገኘው የምክር ቤቱ ጽ/ቤት በተካሄደበት መድረክ ላይ ነው።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ በ2016 ዓ.ል የበጀት ዓመት ለክልሉ የእስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤት የተለያዩ የአቅም ግንባታ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን የተናገሩት ፕሬዚደንቱ፣ በቀጣይም መሰል ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።
ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማው በ2016 ዓ.ል በምክር ቤቱ በተከናወኑ ሥራዎች ላይ ትኩረት ማድረጉን የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ተጠሪ ሼይኽ ሑሴን ሐሰን ተናግረዋል።
በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል፣ በታዩ ክፍተቶች ላይ የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ በያዝነው 2017 ዓ.ል የበጀት ዓመት የክልሉ እስልምና ምክር ቤት ካለፈው ዓመት የተሻለ ውጤት ያስመዘግባል ብለው እንደሚጠብቁ ሸይኽ ሑሴን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ነሐሴ 18፣ 2016 ዓ.ል ባደረገው 2ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባዔ በወሰነው ውሳኔ መሠረት፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤቶች የ2016 ዓ.ል ክንውናቸውን እንዲገመግሙ ባመላከተው አቅጣጫ መሠረት የተጀመረው ዓመታዊ ግምገማ ዉጤታማ መሆኑ ተነግሯል።
ትላንት በወራቤ ከተማ የተጀመረው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ነገ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ በቦታው የሚገኘው ቃል አቀባያችን መረጃ ያመለክታል።
•••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
ጥቅምት 8፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 15፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስማት የተሳናቸው ወገኖች ቁርኣን የሚቀሩባቸው ተቋማት እንዲስፋፉ ተጠየቀ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
መስማት የተሳናቸው ወገኖች ቁርኣን የሚቀሩባቸው ተቋማት ሊስፋፉ እንደሚገባ በኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች ማኅበር ፕሬዚደንት አቶ ኑርሰፋ ኸሊል ተናገሩ።
ፕሬዚደንቱ ይህን የተናገሩት ማኅበሩ ዛሬ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የስብሰባ አዳራሽ፣ "እኛም በቋንቋችን ቁርኣን መቅራት እንችላለን" በሚል መሪ ሐሳብ ለአባላቱ ባካሄደው የዳዕዋ መርኃግብር ላይ ነው።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ሳቢያ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን የሚደግፍ የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት መከፈቱን የጠቅላይ ምክር ቤቱ የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ኦፊሰር ሲስተር ኢንትሳር አየለ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለ'በኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች ማኅበር' የሕጋዊነት ፈቃድ እና ቢሮ ሰጥቶ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ሲ/ር ኢንትሳር ተናግረዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የሳዑዲ አረቢያ ዜግነት ያላቸው ሼይኽ ኢህሳም ሙሐመድ አል-አንሷሪ ኢትዮጵያ ውስጥ መስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች በማኅበር ተደራጅተው ዲናቸውን እንዲያውቁ የሚሠራ ድርጅት በመኖሩ ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሕጋዊ እውቅና የተሰጠው ''በኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች ማኅበር'' በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋ ሳቢያ መስማት የተሳናቸው ወንድምና አህቶችን በምልክት ቋንቋ የቅዱስ ቁርኣንና የዲን ትምህርት ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው አወሊያ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ በአዲስ አበባ አሥራ አምስት መስጂዶችና በአራት ክልሎች ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
ዛሬ በተካሄደው የዳዕዋ መርኃግብር ላይ በተለያዩ ጊዜያት በምልክት ቋንቋ የዲን ትምህርት በመስጠትና በማስተርጎም ማኅበሩን ላገለገሉ በጎ ፈቃደኞች የምሥጋና የምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲኾን፣ የተለያዩ አስተማሪ ፕሮግራሞች በማኅበሩ አባላት ለታዳሚው ቀርበዋል።

ጥቅምት 9፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 16፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በሀዲያ ዞን በሙስሊሞችና በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች መካከል የተፈጠረ ግጭትና አለመግባባት በእርቀ ሰላም ተፈታ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ወራቤ |
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በሀዲያ ዞን፣ አንሌሞ ወረዳ በ2015 ዓ·ል ከገና በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ በጭንጎ ቀበሌ ነዋሪ ሙስሊሞች እና በበንደሊቾ ቀበሌ ነዋሪ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች መካከል ተፈጥሮ የነበረው ግጭትና አለመግባባት በእርቀ ሰላም መፈታቱ ተሰምቷል።
ግጭትና አለመግባባቱ በእርቀ ሰላም መፈታቱን ለማብሰር የሰላም ኮንፈረንስ መርኃግብር ተካሂዷል።
እርቁ የተካሄደው የሁለቱም ሃይማኖት የበላይ መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ባደረጉት ያልተቋረጡ ጥረቶች እና ተከታታይ ውይይቶች መኾኑ ተነግሯል።
በእርቀ ሰላም ኮንፈረንሱ ላይ ለመገኘት ከኢትዮጵያ አስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሰላም ክልልና የዲያስፖራ ጉዳይ ዋና ተጠሪ ሐጂ ሙስጠፋ ናስር፣ የሕዝብ ግንኙነት ተጠሪ ሼይኽ ሑሴን ሐሰን፣ የወጣቶችና የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ ሼይኽ አብዱል ሐሚድ አህመድ ወደ ስፍራው መጓዛቸውን ለማወቅ ተችሏል።
በኮንፈረንሱ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዚደንት ሐጂ ሙሐመድ ኸሊል፣ የክልሉ መጅሊስ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልወሃብ ሸይኽ በድረዲን ሱሩር ፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ሸይኽ ዑመር ሙስጠፋ፣ ዋና ፀሐፊው ኡስታዝ ሳዲቅ ወጌቦ፣ የሰላምና እርቅ ተጠሪው ሸይኽ ሙዘይን ሰዒድ፣ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠሪው ሸይኽ አባስ ያሲን፣ የክልሉ የመንግሥትና የፀጥታ አካላት፣ የሀዲያ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ማትዮስ አኒዮ፣ የዞኑ የመንግሥትና የፀጥታ አካላት፣ የአንሌሞ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አማኑዔል እና የወረዳው የመንግስትና የፀጥታ አካላት ተገኝተዋል።
በመጨረሻም ለእርቀ ሰላሙ አስተዋፅዖ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች የዕውቅናና የሰርተፊኬት ሽልማት ተበርክቶ፣ ኮንፈረንሱ በሁለቱም ሃይማኖቶች መሪዎች ዱዓ እና ፀሎት ተጠናቋል።

ጥቅምት 11፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 18፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው እስላማዊ ዩኒቨርሲቲ በጠቅላይ ምክርቤቱ ፕሬዚደንት ተመርቆ ተከፈተ።

ባሌ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኾነውን የባሌ ሮቤ እስላማዊ ዩኒቨርሲቲ መርቀው ከፈቱ።
በምረቃ ስነ ሥርዓቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን እና ከፍተኛ ዓሊሞች ተገኝተዋል።
የባሌ ሮቤ እስላማዊ ዩኒቨርሲቲ መሥራችና ዋና አስተባባሪ ዶክተር ጀይላን ገለታ በምረቃ ስነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የዩኒቨርሲቲው መከፈት በአካባቢው ማኅበረሰብ የእስልምና እውቀት ላይ ትልቅ አሴት ይጨምራል ብለዋል።
የዩንቨርሲቲው መሥራች ለባሌ እስላማዊ ዩኒቨርሲቲ መከፈት ከአካባቢው ማኅበረሰብና ከበጎ አድራጊዎች ትብብር ባሻገር መንግሥትም ትልቅ ድጋፍ በማደረጉ ምስጋና አቅርበዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት በዩኒቨርሲቲው ምረቃ ላይ ሲናገሩ፣ ባሌ ሮቤ በኢትዮጵያ የእስልምና ትምህርት ላይ ትልቅ አሻራ ያሳረፈ የዓሊሞች መፍለቅያና ትልቅ ታሪክ ያለው አካባቢ መኾኑን ጠቅሰው፣ ይህን መሰል ዩኒቨርሲቲ መከፈቱ ለእስላማዊው ትምህርት ጥራት ትልቅ የብርሃን ጎዳና እንደሚሆን ተናግረዋል።
በአሁኑ ጊዜ 80 በመቶ ግንባታው የተጠናቀቀው ይህ ዩንቨርሲቲ ከሃይማኖታዊ ትምህርት ባሻገር በተለያዩ የአካዳሚ ዘርፎች ትምህርት የሚሰጥበትና ማኅበረሰቡን የሚያገለግል በመኾኑ፣ ሙስሊሙም ሆነ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች ዩኒቨርሲቲውን እንደ ሃብታቸው እንዲንከባከቡት ፕሬዚደንቱ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የባሌ ሮቤ እስላማዊ ዩኒቨርሲቲ መከፈት ማኀበራዊ ችግርን በእውቀት ለመፍታት፣ ለመንፈሳዊ ሕይወት ልዕልና፣ እንዲሁም ለትምህርት ጥራት አስተዋጽዖ እንደሚያበረክት ክቡር ሸይኽ ሐጂ ተናግረዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት በዚሁ ጊዜ በዩኒቨርሲቲው ምሥረታ ሂደት ላይ የተሳተፉትን የአካባቢው ማኅበረሰብ አባላት፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናትን፣ እንዲሁም ዓሊሞችን አመሥግነዋል።
መንግሥት የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ከሚያደርገው ጥረት አኳያ የዩኒቨርሲቲው መከፈት ለሀገር ትልቅ ዕድል መኾኑ የተጠቀሰ ሲኾን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሚቻለው ሁሉ ከዩኒቨርሲቲው ጎን ለመቆም ቃል ገብቷል።
በባሌ ሮቤ እስላማዊ ዩኒቨርሲቲን የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ መርቀው በከፈቱበት ስነ ሥርዓት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ የመንግሥት ተወካዮች፣ የዑለማ ጉባዔ ተወካዮች እና ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል።

ጥቅምት 12፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 19፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ የክልልና የከተማ እስልምና ምክር ቤቶችን የሦራ አፈፃፀም ግምገማ በማድረግ ላይ ይገኛል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፣ የሱማሌ :የሐረ ር : የድሬደዋ እና የአፋር ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤቶች የ2016 ዓ.ል የሥራ አፈፃፀም ግምገማ (ተቅዪም) መጠናቀቁን የግምገማ ቡድኑ አባል ሼይኽ ኢድሪስ ዓሊ ሁሴን (ደጋን)ተናገሩ።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ነሐሴ 18/2016 ዓ.ል በአዲስ አበባ ባደረገው 2ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባዔ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች እስልምና ምክር ቤቶች የ2016 ዓ.ል የስራ ዕቅድ አፈፃፀም ክንውናቸውን እንዲገመግም አቅጣጫ መሠረት ያደረገው የክልልና የከተማ እስልምና ጉዳዮች የሦራ አፈፃፀም ግምገማ በሶስት ቡድን ተከፍሎ እየተሰራ መሆኑን ሼይኽ ኢድሪስ ተናግረዋል።
የእስልምና ምክር ቤቶቹ ያስመዘገቡት ውጤት እንደ ክልሎቹ ነባራዊ ሁኔታ እንደሚለያይ ሼይኽ ኢንድሪስ ተናግረዋል።
ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማው (ተቅዪም) በ2016 ዓ.ል በምክር ቤቱ በተከናወኑ ሥራዎች አፈፃፀም ላይ ትኩረት ማድረጉን የተናገሩት ሼይኽ ኢድሪስ ፤ በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን ይበልጥ በማሰቀጠል የታዩ ክፍተቶችን በመለየትና የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ በያዝነው 2017 ዓ.ል እስልምና ምክር ቤቶቹ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አቅም ይፈጥርላቸዋል ብለዋል።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ የተጀመረው የክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች የ2016 ዓ.ል በጀት ዓመት ስራ አፈፃፀም ግምገማ (ተቅዪም) ግምገማ ባልተደረገባቸው ክልሎች እንደቀጠለ ሼይኽ ኢድሪስ ተናግረዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ ክፍሎች የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች የ2017 ዓ.ል. የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።
በምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተካሄደውን የግምገማ መድረክ የከፈቱት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን፣ የመድረኩ ዓላማ በምክር ቤቱ የሚገኙ የሥራ ክፍሎች በ2017 ዓ.ል የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በሥራ አፈጻጸም ረገድ ያሳዩዋቸውን መልካም ውጤቶች ማስቀጠል እና ክፍተቶችን ማረም ነው ብለዋል።
በዚሁ የግምገማ መድረክ ላይ በምክር ቤቱ ውስጥ የሚገኙ ሀያ የሥራ ክፍሎች የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲኾን፣ ከቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎችና ለተሰጡ አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ዓመታዊ የሥራ ግምገማ ተጀመረ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ (ተቅዪም) ቦንጋ ከተማ በሚገኘው የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት እየተካሄደ ነው።
ዛሬ የተጀመረውና በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ ሑሴን ሐሰን የተመራው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በ2016 ዓ.ል በምክር ቤቱ በተከናወኑ ሥራዎች ላይ ትኩረት አድርጓል።
ግምገማው በ2016 ዓ.ል በከፍተኛ ምክር ቤቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስቀጠል የታዩ ውሱንነቶችን በመለየትና የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ በ2017 ዓ.ል. ለክልሉ እስልምና ምክር ቤት አቅም መፍጠር መሆኑን ሸይኽ ሑሴን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ነሐሴ 18፣ 2016 ዓ.ል በአዲስ አበባ ባደረገው የ2ኛ ዓመት፣ 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደር የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤቶች የ2016 ዓ.ል የሥራ አፈጻጸማቸውን እንዲገመግሙ አቅጣጫ ማመላከቱ ይታወሳል።
ዛሬ በቦንጋ ከተማ በክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተጀመረው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በነገው ዕለትም እንደሚቀጥል ከቦታው የሚገኘው ቃል አቀባያችን የላከው መረጃ ያመለክታል።

ጥቅምት 16፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓ. 23፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የኢሰመኮ ልዑካንን ተቀብለው አነጋገሩ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሸይኽ ሙሐመድዘይን ዘኽረዲን በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የሴቶች፣ ሕጻናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር የኾኑት ወ/ሮ ርግበ ገብረኃዋሪያን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
በዚሁ ጊዜ ኮሚሽነሯ በኢሰመኮ ሕጋዊ ቁመናና ተልዕኮ ዙርያ ሰፋ ያለ ገለጻ ካደረጉ በኋላ፣ ኢሰመኮ ግርዛት በሴቶች እና በሕጻናት ላይ የሚያደርሰውን የከፋ ጉዳት በማስቀረት ዓላማ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ የሙስሊም ሊቃውንት ጉባዔ ጋር ተቀራርቦ ለመሥራት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።
የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው ሸይኽ ሙሐመድዘይን ዘኽረዲን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በግርዛት ሳቢያ በሴቶችና በሕጻናት ላይ ለሚደርሱ የከፉ የጤና ችግሮች መፍትኄ በመሻት ከዑለማ ምክር ቤቱ ጋር በጋራ ለመሥራት ያሳየውን መነሳሳት በማድነቅ ምሥጋና አቅርበዋል።
ኃላፊው አያይዘውም በእስልምና አስተምህሮ፣ አላህ በሰዎች ላይ ጉዳት የሚያደርስ ምንም ዓይነት ትዕዛዝ ያዝዛል ተብሎ እንደማይታመን፣ ሰዎችም ራሳቸውን ከሚጎዱ ድርጊቶች እንዲታቀቡ የታዘዙ መኾናቸውን ተናግረዋል።
ሸይኽ ሙሐመድዘይን ሴቶች በእስልምና አስተምህሮ ከፍተኛ ቦታ እንዳላቸው፣ ነገር ግን በዚህ ዙሪያ በርካታ የተዛቡ መረጃዎች እንደሚነዙና የተሳሳቱ አካሄዶችም መኖራቸውን አውስተው፣ በእስልምና የእናትን ሐቅ በአግባቡ መወጣት ጀነት እስከማስገባት የሚደርስ ከፍ ያለ ደረጃ እንዳለውና በአጠቃላይም እስልምና ለሴት ልጅ ትልቅ ክብር እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
ሴቶችና ሕጻናት በግርዛት ሳቢያ ለአካላዊም ኾነ ለስነ ልቦናዊ ጉዳት እንዲጋለጡ ማድረግ የእስልምና አስተምህሮ እንዳልኾነ የጠቀሱት ሸይኽ ሙሐመድዘይን፣ ሰዎች የሃይማኖቱን ሕግጋት (ትዕዛዛት) በውል ባለመረዳትና የግል ስሜታቸውን በመከተል ስህተት የሚፈጽሙባቸው፣ በሂደትም ስህተት እንደ ባህል ስር እየሰደደ የሚሄድባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ተናግረዋል።
በእስልምና ስም ብዙ ሃይማኖቱን መሠረት ያላደረጉ ድርጊቶች ሲፈፀሙና በዚህም ሳቢያ በሴቶችም ኾነ በሕጻናት ላይ ጉዳትና ችግሮች ሲፈጠሩ ስለሚታይ፣ ይህን ለመቅረፍ የጋራ ሥራ እንሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ኢሰመኮ የሴቶች ግርዛትን አስመልክቶ ያለውን ሃይማኖታዊ እሳቤ፣ በጤና ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ደግሞ በህክምና ባለሙያ ሙያዊ አስተያየት ላይ በመመስረት፣ በልማዳዊ ድርጊቶች ሳቢያ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለማስወገድ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ጋር አብሮ ለመሥራት ፈቃደኛ እንደኾነ ኮሚሽነሯ ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሴቶችና የወጣቶች ዳይሬክተሯ ዑስታዛ ፋጡማ ሐሰን፣ በኢሰመኮ አፋር፣ የሰመራ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ መሐመድ አሕመድ፣ በኢሰመኮ የሰብኣዊ መብቶች ምርምርና ክትትል ዳሬክተር፣ እንዲሁም ከፍተኛ የሰብኣዊ መብቶች ባለሙያዋ ፈዲላ ሸሂባ ተገኝተዋል።
ኢሰመኮ በሰብኣዊ መብቶች መከበር ዙሪያ የሚሠራና ተጠሪነቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኾነ መንግሥታዊ ተቋም ነው።

ጥቅምት 18፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ዓ. 25፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራም ቱፋ የሥራ ጉብኝት አድረጉ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራም ቱፋ የተመራ ልዑካን በአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በመገኘት የሥራ እንቅስቃሴ ጉብኝት አደረጉ።
የአዲስ አበባ መጅሊስ የከፍተኛ ምክር ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሪያድ ጀማል የየክፍሎቹን የሥራ ሁኔታና የሠራተኞቹን ማንነት በጠቅላይ ምክር ቤቱ ለተመራው ልዑካን ቡድኑ አብራርተዋል።
አመራሮቹም የከፍተኛ ምክር ቤቱን የስራ ክፍሎች ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በየክፍሎቹ የተመለከቱት የሥራ እንቅስቃሴ በጣም አስደሳችና አበረታች መሆኑን የልዑካን ቡድኑ መሪና የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ተናግረዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የልዑክ ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቱ ቆይታው እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትን በመመልከት ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ይሆናል
በጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራም ቱፋ በተመራው የልዑካን ቡድኑ ውስጥ የተካተቱት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፤ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ የተገኙ ሲሆን የአዲስ አበባከፍተኛ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ፣ የአዲስ አበባ መጅሊስ ምክትል ፕሬዝደንቱ ፈትሁዲን ሐጂ ዘይኑ ሙቅና፣ ዋና ፀሐፊው ሸይኽ ሁሴን በሽር እና የስራ አስፈጻሚ አባላት ተገኝተዋል።
ጉብኝቱ በተለያዩ የሐገሪቱ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሱ የሥራ ጉብኝት በማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት አካል መሆኑ ታውቋል።
#የዜናው ምንጭ:-#የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት ነው።

ጥቅምት 19፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 26፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ የማስፋፊያ ግንባታ ጨረታ ተከፈተ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የልማት ክንፍ ለኾነው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ የቢሮ ማስፋፊያ ግንባታ በወጣው ጨረታ መሠረት የቀረቡ የመጫረቻ ሰነዶች በይፋ ተከፈቱ።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ከመስከረም 28፣ 2017 ዓ.ል ጀምሮ በተቋሙ የፌስቡክ ገጽ፣ በኤጀንሲውና በተለያዩ መስጂዶች የጨረታ ማስታወቂያውን ለሕዝብ ይፋ አድርጎ እንደነበረ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አብዱልሐዲ ሙሐመድ አስታውሰዋል።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ (ኢሙልኤ) እየሰጠ ያለውን አገልግሎት ለማስፋት በማሰብ በወጣው የቢሮ ማስፋፊያ ግንባታ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ አሥራ ሁለት የግንባታ ድርጅቶች የጨረታ ሰነድ መግዛታቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።
ዝግ የሥራ ቀናትን ጨምሮ ለአሥራ ዘጠኝ ቀናት በአየር ላይ የዋለውና ዛሬ 8:00 ሰዓት ላይ የተዘጋው ጨረታ፣ 8:30 ላይ ተጫራቾችና ታዛቢዎች በተገኙበት በይፋ ተከፍቷል።
በዚሁ ጊዜ በጨረታ ሂደቱ ላይ ቅሬታ ያለው ተጫራች ካለ ቅሬታውን እንዲገልጽ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊው ዕድል የሰጡ ሲኾን፣ ተጫራቾች ምንም ቅሬታ እንደሌላቸው ተናግረዋል።
በጠቅላይ ምክር ቤቱ የመሰብሰብያ አዳራሽ የጨረታ ሰነዶች በይፋ ከተከፈቱ በኋላ፣ ሁለት ድርጅቶች የጨረታውን መስፈርት ባለማሟላታቸው በአጫራች ኮሚቴው ከጨረታው መሰረዛቸው ተነግሯል።
በጠቅላይ ምክር ቤቱ የፕሮጀክት ጽ/ቤት የወጣውና ዛሬ በተወዳዳሪዎች ፊት የተከፈተው የጨረታ ሰነድ፣ በተጫራቾች የቀረቡ የመጫረቻ ሰነዶች የፋይናንስና የቴክኒክ ምክረሐሳብ በጨረታ ኮሚቴ ተጣርቶ ከቀናት በኋላ አሸናፊው ድርጅት ይፋ እንደሚደረግ አቶ አብዱልሐዲ ሙሐመድ ተናግረዋል።
••••••••••••••••••

ጥቅምት 20፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 26፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በሐጅ ወቅት በጀዳ አውሮፕላን ማረፊያ #ሻንጣ_ለጠፋባችሁ የ1445 ዓ.ሒ (2016 ዓ.ል) ሐጃጆች።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በ1445 ዓ.ሒ (2016 ዓ.ል) የዘመነ መስተንግዶ ለአል ረሕማን እንግዶች በሚል መሪ ሐሳብ ሐጃጆችን ማስተናገዱ ይታወሳል።
የሐጅ ሥርዓታችሁን አጠናቅቃችሁ ሻንጣችሁን ከመካ ወደ ሀገር ቤት ለመላክ ከመካ የሽኝት አስተባባሪ የሻንጣ ታግ ወስዳችሁ፣ ነገር ግን ሻንጣችሁ በጀዳ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የጠፋባችሁ ሐጃጆች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጀዳ አውሮፕላን ማረፊያ የተገኙ የኢትዮጵያውያን ሐጃጆች ሻንጣዎችን ወደ አገር ቤት አምጥቶ ለጠቅላይ ምክር ቤታችን ያስረከበ በመሆኑ፣ ሻንጣ የጠፋባችሁ ሐጃጆች የፓስፖርታችሁን ቅጂ (ኮፒ) እና የሻንጣችሁን ታግ ቅጂ ከዚህ በታች በተቀመጠው ስልክ ቁጥር 0911 82 19 15 (በቴሌግራም) እንድትልኩ እንጠይቃለን።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ጉዞ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት።

ጥቅምት 21፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 28፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ሊገነባ ለታቀደ ው ሕንጻ የዲዛይን እና የኮንትራት አማካሪ ጨረታ በይፋ ተከፈተ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊያስገነባ ላቀደው ባለ 2 መሠረትና ባለ 13 ወለል የአፓርትመንት ሕንጻ የዲዛይን እና የኮንትራት አማካሪ ጨረታ በይፋ ከፈተ።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልሃዲ ሙሐመድ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገነባው B+2፣ G+13 የአፓርትመንት ሕንጻ የዲዛይን እና የአማካሪ ጨረታ በተመረጡ ድርጅቶች መካከል ብቻ የተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ስምንት (8) ድርጅቶች የተመረጡ ሲኾን፣ ከመንግሥት ድርጅቶች ሦስት (3)፣ ከግል አምስት (5) መሆናቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።
በጨረታ መክፈቻ ስነ ሥርዓቱ ላይ ከስምንቱ (8) ድርጅቶች አራቱ (4) የተገኙ ሲኾን፣ ጨረታው ታዛቢዎች በተገኙበት ተከፍቷል።
ድርጅቶቹ በፕሮጀክት አማካሪዎች የተጠቆሙና በፕሮጀክት አፈጻጸም ጥሩ ስም ያላቸው መሆናቸውንም ኃላፊው ተናግረዋል።

ጥቅምት 22፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 29፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በአዲስ አበባ ዓለምአቀፍ የሃይማኖት ጉባዔ ሊካሄድ ነዉ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የሰላም ሚኒስቴር ከሙሐመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ዓለምአቀፍ የሃይማኖት ጉባዔ ሊያካሂድ መሆኑን ተናገረ።
ጥቅምት 25 እና 26፣ 2017 ዓ.ል (ሰኞና ማክሰኞ) በአዲስ አበባ ኃይሌ ግራንድ ሪዞርት የሚካሄደውን ይህን ዓለምአቀፍ ጉባዔ አስመልክቶ ሚኒስቴሩ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ደዔታ ዶክተር ኸይረዲን ተዘራ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ሲናገሩ ኢትዮጵያ ቀደምት የሰዎች መገኛ ብቻ ሳትሆን፣ እስልምናና ክርስትና ለዘመናት በሰላምና በሃገር ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉባት ታሪካዊ ሀገር መሆኗን አውስተዋል።
በዓይነቱ የመጀመሪያ የኾነው ይህ ዓለምአቀፍ ጉባዔ ሃይማኖቶች ለሀገራችን ሰላምና አብሮነት ያደረጉትን ጉልህ አስተዋፅዖ ይበልጥ ለማጠናከር የሚያግዝ መሆኑን ሚኒስትር ደዔታው ተናግረዋል።
ለዚህም ዓላማ መሳካት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ጋር ተቀራርቦ እየሠራ እንደሚቀጥል ሚኒስትር ደዔታው ተናግረዋል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ዓለምአቀፍ ጉባዔ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባል ቤተ እምነት አባቶች፣ አውሮጳና ኤዥያን ጨምሮ ከአሥራ ሦስት ሀገራት የሚመጡ የሃይማኖት ሊቃውንት፣ አሥራ አምስት ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ሦስት መቶ ሰዎች በጉባዔው ላይ እንደሚሳተፉ ተነግሯል።
በጉባዔው ላይ በምሑራን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች እንደሚቀርቡ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ተናግሯል።
••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13

ጥቅምት 23፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል አወል፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስትራቴጂያዊ እቅድ ንድፈ ሐሳብ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚዎች ቀርቦ ፀደቀ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስትራቴጂያዊ እቅድ ንድፈ ሐሳብ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እና ለሥራ አስፈጻሚዎች ቀርቦ ማሻሻያዎችን በማከል ወደ ሥራ እንዲገባ ፀድቋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ስትራቴጂያዊ እቅድ ምክር ቤቱ በ50 ዓመት ታሪኩ ያላሳካው የሕገ-መጅሊሱ አካል በመኾኑ ሁሉን አካታች የለውጥ ብርሃን ሆኖ በታሪክ ትልቅ መሠረት የሚጥል ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ባለንበት የሃለፊነት ጊዜ የአላህ ባሪያዎች የሚገለገሉበት እንደ ዘመናቸውና ተጨባጩ እያሳደጉ የሚሰሩበት ትልቅ ታሪክ ነው ብለዋል።
ፕሬዚደንቱ አያይዘውም የሥራ አስኪያጅ ጽሕፈት ቤት ኃላፊነት ወስዶ ከቦርዱ ጋር ተቀናጅቶ የስትራቴጂያዊ እቅዱን ንድፈ ሐሳብ ለፍሬ በማብቃቱ ምሥጋና አቅርበዋል።
የምክር ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅና የስራትራቴጃዊ እቅድ ዝግጅት ዐብይ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢው አቶ አብዱልዓዚዝ አሎ የስትራቴጂያዊ እቅድ ንድፈ ሐሳቡን ለማበልፀግ ላለፈው አንድ ዓመት የተከናወኑትን የፕሮሲጀርና የዝግጅት ሂደቶችን ያብራሩ ሲኾን፣ እቅዱ በስድስት ወር ተጠናቅቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የስራትራቴጂያዊ እቅድ ዐብይ ኮሚቴ አባላት ላለፈው አንድ ዓመት ያህል ያለምንም ክፋያ ላደረጉት የጊዜና የሙያ አስተዋጽዖ ክቡር ፕሬዚደንቱ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ምሥጋና አቅርበዋል።
የስራትራቴጂያዊ እቅድ ዝግጅት ዐብይ ኮሚቴው ያወጣውን መስፈርት ያሟሉ የመስኩ ባለሙያና በእስላማዊ ትምህርት በቂ ዝግጅት ያላቸው አማካሪው አቶ ሺሃቡዲን ሼኽ ኑራ በተቋሙ ስራትራቴጂያዊ እቅድ ንድፈ ሐሳብ ዙሪያ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።
ባለሙያው የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ ስትራቴጂያዊ እቅድ ለተቋማዊ ለውጥና ለሁለንተናዊ እድገት ያለውን ፋይዳ፣ አቃፊነት እና ዘላቂነት ያለው እድገት ለማምጣት ለመሪዎች ትልቅ መሣሪያ እንደሆነም በንድፈ ሐሳብ አሳይተዋል።
የእቅዱ ንድፈ ሐሳብ ዝግጅት ዐብይ ኮሚቴ አባላት ስትራቴጃዊ እቅድ በመሪዎች ንቁነትና ተግባራዊነት የሚታገዝ በመሆኑ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚዎች እስከታች በመውረድ የለውጥ መሣሪያ እንዲያደርጉት አደራ ብለዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚዎችም በቀረበው የስትራቴጂያዊ እቅዱ ንድፈ ሐሳብ ላይ ግብዓት ሰጥተው፣ ማብራሪያ የሚስፈልገውን ጠይቀው ምላሽ ተሰጥቷቸዋል።
እቅዱ የተበታተነ ሥራችን መርኅ እና ስትራቴጂን የተከተለ እንዲሆን እገዛ የሚያደርግ፣ ሁለን የሚያስተናግድ፣ ከአካባቢያዊና ከተጨባጩ ሁኔታ ጋር እየተገናዘበ ሊሻሻልና ሊጎለብት የሚችል በመኾኑ በኃላፊነት ለመሥራት የሚያነሳሳ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
በዚህ ስትራቴጂያዊ እቅድ ንድፈ ሐሳብ ማብራሪያ መድረክ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ ምክትል ፕሬዚደንትና የሐጅ እና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ሸይኽ አብዱልዓዚዝ አብዱልወሊ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ፣ እንዲሁም ባለሙያዎችና የቦርድ አባላት ተገኝተዋል።

ጥቅምት 25፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል አወል 2፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ዓለምአቀፉ የሃይማኖት ጉባዔ በአዲሰ አበባ ተጀመረ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የሰላም ሚኒስቴር ከሙሐመድ ቢን ዛይድ ፎር ሂዩማኒቲ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ጉባዔ አዲስ አበባ በሚገኘው ኃይሌ ግራንድ ሪዞርት ተጀመረ።
የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለሁለት ቀናት የሚቆየውን ይህን ዓለምአቀፍ ጉባዔ ሲከፍቱ ባደረጉት ኢትዮጵያ ለአያሌ ዘመናት የኖረ የሃይማኖቶች የመከባበርና የመቻቻል ታሪክ ያላት አገር መሆኗን ተናግረዋል።
በዓለማችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህን የአብሮነት ባህል የሚንዱ ትርክቶች በማኅበራዊ ትስስር ገፆች እየተነዙ ለክቡሩ የሰዎች ሰላም እጦት ምክንያት መኾናቸውን ተናግረዋል።
ፕሬዚደንቱ የሃይማኖት አባቶች አሁን ዓለም ያለችበትን ዉስብስብ ሁኔታ በመቀየር በሰላምና በጋራ አብሮ መኖር ላይ የምንናፍቃትን ዓለም እንድንጨብጥ አባታዊ ትምህርታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም በበኩላቸው ሃይማኖቶች የአገር አንድነትና የጥንካሬ ምንጭ መኾናቸውን ተናግረዋል።
የሃይማኖት ተቋማት በአገር ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ኃላፊነት በመጠቀም የሰዎች በሰላም አብሮ የመኖር እሴት እንዲጠናከር መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
አገራችን ኢትዮጵያ በሃይማኖት ብዝኃነት የተገነባች መሆኗን የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ሰላምና መቻቻል የሰፈነባት አገር እንድትሆን መስሪያ ቤታቸው ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ጋር ተቀራርቦ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ፀሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ በዕምነት መጻሕፍት የተወሳች አገር ነች ካሉ በኋላ፣ ዓለማችን የሰላም እጦት ላይ በመሆኗ የሃይማኖት አባቶችን ልብ የሰበረ ክስተት መሆኑን ተናግረዋል።
የሃይማኖት አባቶች ለሰው ልጆች ሁለንተናዊ ሰላም በቀጣይ ተጠናክረው እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
የተባበሩት አረብ ኤሚሬት መሐመድ ቢን ዛይድ ፎር ሂዩማኒቲ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ዶ/ር ኸሊፋ ሙባረክ ዳኽሪ በአገራቸው እና በኢትዮጵያ መካከል የሰላም እሴትን በማጠናከር ማኅበራዊ ሰላምን ለማጎልበትና ወንድማማችነትን ለማጠናከር ያለመ አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ መከፈቱን ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሕዝቦች መካከል የመነጋገር ባሕልን የሚያጎለብቱ ሥራዎች መሥራት እንደሚሻ ተናግረዋል።
በጉባዔው ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባል ቤተ እምነት አባቶች፣ አሜሪካ፣ አውሮጳ እና ኤዥያን ጨምሮ ከአሥራ ሦስት ሀገራት የመጡ የሃይማኖት ሊቃውንት፣ አሥራ አምስት ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ሦስት መቶ ሰዎች በጉባዔው ላይ ተሳታፊ ሆነዋል።
ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ጉባዔ ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች በምሁራን እንደሚቀርቡ ለማወቅ ተችሏል።

ጥቅምት 25፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡውላ 2፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት በዓለም አቀፍ የሃይማኖት ጉባዔ ላይ ጽሑፍ አቀረቡ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ በአዲስ አበባ ዛሬ በተከፈተው ዓለም ዓቀፍ የሃይማኖት ጉባዔ ላይ ጽሑፍ አቀረቡ።
ክቡር ፕሬዚደንቱ ያቀረቡት ጽሑፍ "የመከባበርና የመቻቻል ባህልን ለማዳበር የሃይማኖት ተቋማት የሚያደርጉት አስተዋጽዖ" የሚል ርዕስ ያለው ሲኾን፣ ሸይኽ ሐጂ ከ1440 ዓመታት በፊት እስልምና ወደ ኢትዮጵያ በገባበት ጊዜ በሐበሻው ንጉሥ አስሐመተል ነጃሺ እና ወደ ሐበሻ በስደት የመጡት የነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ.) ባልደረቦች መሪ በነበረው ታላቁ ሶሃባ ጃዕፈር ቢን አቡ ጧሊብ መካከል እምነትን አስመልክቶ የተካሄደውን ውይይትና መተማመን የመቻቻል አብነት እንደኾነ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ነብያችን ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) "ከእናቴ ቀጥላ ሁለተኛ እናቴ (ሞግዚቴ)" ያሏት የዑሙ አይመን አገር መሆኗን የጠቀሱት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም፣ ታላቁ ነብይ (ሶ.ዐ.ወ) ቀደምት ተከታዮቻቸው በመካ የቁረይሽ ባላባቶች ግፍ እና መከራ በደረሰባቸው ጊዜ፣ "ወደ ሐበሻ ሂዱ፤ እርሷ እርሱ ዘንድ አንድም ሰው የማይበደልበት እውነተኛ መሪ ያለባት የፍትኅ አገር ናት" ማለታቸው በጽሑፋቸው ጠቅሰዋል።
ሼይኽ ሐጂ አክለውም አገራችን ኢትዮጵያ የነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ሙአዚን የቢላል ኢብኑ ረባህ አገር እንደኾነችና የታላቁ ነቢይ (ሶ.ዐ.ወ) ቀደምት ባልደረቦች ቀብር የሚገኝባት ታላቅ አገር መሆኗን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ልዩነትን የማስተናገድ ከአስሐመተል ነጃሺ የተወረሰ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት አገር መሆኗን የጠቀሱት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም፣ ዓለም ይህንን ልምድ ከኢትዮጵያ ሊወስድ ይገባዋል ብለዋል።
ዛሬ በተጀመረው ዓለምአቀፍ የሃይማኖት ጉባዔ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባል ቤተ እምነት አባቶች፣ አሜሪካ፣ አውሮጳ እና ኤዥያን ጨምሮ ከአሥራ ሦስት ሀገራት የመጡ የሃይማኖት ሊቃውንት፣ አሥራ አምስት ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ከሦስት መቶ በላይ ሰዎች በጉባዔው ላይ ተሳታፊ ሆነዋል።
ለሁለት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ በምሁራን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች መቅረባቸው እንደሚቀጥል ተነግሯል።

ጥቅምት 25፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 2፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ እና ዳብሊ ፋውንዴሽን አብሮ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ ዳብሊ (DABLIE) ከተባለ ሀገር በቀል ድርጅት ጋር የወጣቶችን አቅም በመገንባት፣ የሙስሊም ሴቶችን ሁለንተናዊ ዕድገት ከፍ የሚያደርጉ የተቀናጁ ፕሮግራሞች በትብብር በማዘጋጀትና በመተግበር ዙሪያ አብሮ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
የመግባቢያ ሰነዱን የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱልዓዚዝ አሎ እና የዳብሊ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢማድ አብዱልመጂድ ፈርመዋል።
በዚሁ ጊዜ የዳብሊ ፋውንዴሽን ባልደረባ ድርጅቱ ስለሚያካሂዳቸው እንቅስቃሴዎች በስላይድ የተደገፈ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ፋውንዴሽኑ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ ጋር የሚሠራበት ማዕቀፍ እና የጋራ ዓላማ በመግባቢያ ሰነዱ ውስጥ መካተቱ ተነግሯል።
የሙስሊም ወጣቶችን ክህሎት ማጎልበት እና በማኅበረሰብ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሙያ ሥልጠና መስጠት የመግባቢያ ሰነዱ አካል መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱልዓዚዝ አሎ ጠቅላይ ምክር ቤቱ መስሊሙን እና በአጠቃላይም ሀገርን በሚጠቅም ጉዳይ ላይ አቅምና ብቃት ካላቸው ድርጅቶችና ተቋማት ጋር ለመሥራት በሩ ክፍት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በመግባቢያ ሰነዱ ፊርማ ስነ ሥርዓት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሴቶችና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ ዑስታዛ ፋጡማ ሐሰን፣ የመጅሊሱ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የትምህርትና ማኅበራዊ ዘርፍ ተጠሪ ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ፣ እንዲሁም የዳብሊ ፋውንዴሽን አመራር አባላት ተገኝተዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••

ጥቅምት 27፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡውላ 5፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የዑለማ ጉባዔ ጽ/ቤት ለክልል የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤቶች ሥጦታ አበረከተ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስር ያለው የዑለማ ጉባዔ ጽ/ቤት ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በመተባበር የክልል ዑለማ ጉባኤ ጽሕፈት ቤቶችን ለማጠናከር የኮምፒዩተር፣ የፎቶኮፒ ማሸን እና የፕሪንተር ሥጦታዎች አበረከተ፡፡
ለክልል የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤቶች ሥጦታ በተበረከተበት ስነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት
እና የዑለማ ጉባዔ ሰብሳቢው የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እንደተናገሩት፣ "ሥጦታው ለክልል የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤቶች ምቹ የሥራ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ ነው" ብለዋል።
"የኢትዮጵያ ዓሊሞች ከመቀበል አልፈው እንዲህ እንደዛሬው መስጠት መቻላቻው ትልቅ ለውጥ በመሆኑ፣ አልሃምዱሊላህ ለዚህ ያደረሰን አላህ (ሱ.ወ.) ምሥጋና ይገባዋል" ብለዋል፡፡
ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም አያይዝውም "የቀድሞ ዓሊሞች እኛን ጨምሮ በሉህ (አነስተኛ መክተፊያ የሚያህል ዝርግ ጣውላ) እየተጻፈና እየታጠበ ስንማር (ስንቀራ) የነበረበት ጊዜ ሩቅ አይደለም" ሲሉ አስታውሰዋል፡፡
"ዓሊሞቻችን ዛሬ ዓለም የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ደረጃ የሚወክል እና የዳዕዋ ሥራቸውን የሚያቀልል ዘመናዊ መገልገያ ለመጠቀም መድረሳቸው ትልቅ የለውጥ ሂደት ነው" ብለዋል፡፡ ቀኑንም "የሥጦታ ቀን" በማለት ደስታቸውን አካፍለዋል።
የኢትዮጵያ ዓሊሞች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለ12 ክልሎች እና ለሁለት የከተማ አስተዳደር የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤቶች ያበረከተው ሥጦታ ዋና ዓላማው ለዳዕዋ ሥራ ምቹሁኔታን መፍጠር በመኾኑ፣ የየክልሉ የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤቶች ይህን አማና ተቀብላችሁ በዳዕዋ ሥራ አንድትበረቱ ሲሉ አደራ ሰጥተዋል።
በጠቅላይ ምክር ቤቱ አዳራሽ በተካሄደው የሥጦታ ርክክብ ስነ-ሥርዓት መረኃግብር ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ የዓሊሞች ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢና የፈትዋ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢው ዶክተር ጄይላን ኸድር፣ ምክትል ፕሬዚደንትና የሐጅ እና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊው ሸይኽ አብዱልዓዚዝ አብዱልወሊ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጅ ከማል ሐሩን፣ የኦሮሚያ መጅሊስ ፕሬዚደንት እና የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና የዑለማ ጉባዔ ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።
••••••••

ጥቅምት 27፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 4፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጋምቤላ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዓመታዊ የሥራ ግምገማ አደረገ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የጋምቤላ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ (ተቅዪም) ጋምቤላ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት አካሄደ።
ትላንት የተጀመረው የጋምቤላ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በ2016 ዓ.ል በምክር ቤቱ በተከናወኑ ሥራዎች ላይ ትኩረት ማድረጉን የግምገማ መድረኩን የመሩት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ ሑሴን ሐሰን ተናግረዋል።
ዛሬ የተጠናቀቀው የጋምቤላ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዓመታዊ ግምገማ በ2016 ዓ.ል በምክር ቤቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስቀጠል፣ በታዩ ውሱንነቶች ላይ የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድ ሸይኽ ሑሴን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ነሐሴ 18፣ 2016 ዓ.ል በአዲስ አበባ ባደረገው የ2ኛ ዓመት፣ 4ኛ መደበኛ ጉባዔ፣ የክልልና የከተማ አሥተዳደር የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤቶች የ2016 ዓ.ል የሥራ አፈጻጸማቸውን እንዲገመግሙ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።
የጋምቤላ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አፈጻጸም ገምጋሚ ቡድን በዛሬ ውሎው በከፍተኛ ምክር ቤቱ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውሮ መጎብኘቱን ከሸይኽ ሑሴን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።