بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
የዘንድሮ የሐጅ ጉዞ ምዝገባ የካቲት 27፣ 2016 ያበቃል።
• ለሐጅ የነየቱ ምዕመናን በቀሩት ቀናት እንዲመዘገቡ ጠቅላይ ምክር ቤቱ አሳሰበ።
የካቲት 7፣ 2016 (አዲስ አበባ) - የ1445ኛው የሐጅ ጉዞ ምዝገባ የካቲት 27፣ 2016 ዓ.ል. (ሻዕባን 25፣ 1445 ዓ.ሒ) የሚጠናቀቅ በመሆኑ፣ ዘንድሮ ሐጅ ለማድረግ የነየቱ (ያቀዱ) ምዕመናን፣ በቀሩት ጥቂት ቀናት እንዲመዘገቡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳሰበ።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ ዘንድሮ የሐጅ ጉዞ ኒያ ያላቸው ምዕመናን የምዝገባ ቀኑ ከመጠናቀቁ በፊት እንዲመዘገቡ የመስጂድ ኢማሞች፣ የአሊሞችና የዱዓቶች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በየመሳጂዱ ሙስሊሙን ማሕበረሰብ እንዲቀሰቅሱ አሳስበዋል።
የዘንድሮ የሐጅ ምዝገባ ጥር 25፣ 2016 (ረጀብ 22፣ 1445ዓ.ሒ) ጠቅላይ ምክር ቤቱ በተለያዩ ክልሎች በከፈታቸው 27 የሐጅ ምዝገባ ጣቢያዎች መጀመሩን ሐጂ ከማል አስታውሰዋል።
የዘንድሮ የሐጅ ጉዞ ምዝገባ ከሌሎች ዓመታት ቀድሞ መጀመሩን የጠቀሱት ሥራ አስኪያጁ፣ የዚህም ዋነኛ ምክንያት የሳዑዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስቴር፣ የአላህ እንግዶች ምዝገባ የካቲት 27፣ 2016ዓ.ል (ሻዕባን 25፣ 1445ዓ.ሒ) እንዲጠናቀቅ ቀነ ገደብ በማስቀመጡ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅ ምዝገባ ሥርዓቱን ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ፣ አምና የነበሩትን 15 የምዝገባ ጣቢያዎች ወደ 27 ማሳደጉን ተናግረዋል።
ወደ ምዝገባ ጣቢያ የሚሄዱ የአሏህ እንግዶች የመኖሪያ አካባቢያቸውን የሚገልፅ የቀበሌ መታወቂያ፣ የአገልግሎት ጊዜው ከአሥራ አንድ ወራት ያላነሰ ፓስፖርት፣ አንድ ጉርድ ፎቶ፣ እንዲሁም የኮቪድና የቢጫ ወባ ክትባት ካርድ ይዘዉ መቅረብ እንዳለባቸው ተናግረዋል።
**
ሻዕባን 5፣1445 ዓ.ሒ
**
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/e

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
የነጃሺ እስላማዊ ማዕከል የኪነ-ሕንፃ ንድፍ ውድድር አሸናፊዎች ተሸለሙ፡፡
የካቲት 7፣ 2016 (አዲስ አበባ) – ATM ዲዛይነር ኃላፊነቱ የተ/የግ/ማ በታላቁ ንጉሥ ለተሰየመው ነጃሺ እስላማዊ ማዕከል ግንባታ የተካሄደውን የኪነ ሕንፃ ቅድመ ንድፍ ውድድር በማሸነፍ የአንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነ።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ አፍሪካ ሕብረት አቅራቢያ ለሚያስገነባው የነጃሺ እስላማዊ ማዕከል የኪነ ሕንፃ ንድፍ ውድድር ባቀረበው ጥሪ መሠረት፣ ሥራቸውን ካቀረቡ አሥር ተወዳዳሪዎች መካከል፣ ኤቲኤም ዲዛይነር አሸናፊ መኾኑ የተነገረው ዛሬ በስቴይ ኢዚ ሆቴል በተካሄደ ስነ ሥርዓት ላይ ነው።
በውድድሩ አሸናፊ የኾነው ኤቲኤም ዲዛይነር የ1.2 ሚሊዮን ብር ሽልማቱን ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ከክብር ዶክተር ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እጅ ተቀብሏል።
ፕሬዚደንቱ በዚሁ ጊዜ ባደረጉት ንግግር፣ ‹‹በኮሚቴ ሥራ ታሪክ ሲሠራ ያየሁት፣ ይህን እውን ለማድረግ ገንዘቡን እና ጊዜውን በሰዋው በዚህ ኮሚቴ ነው›› በማለት የኮሚቴውን አባላት በሙሉ ካመሠገኑ በኋላ፣ ‹‹አላህ ይህን ትልቅ ሥራ ጨርሰን ለመመረቅ ያብቃን›› ብለዋል።
‹‹የነጃሺ ታሪክ የዓለም ሙስሊሞች ታሪክ ነው›› ያሉት ፕሬዚደንቱ፣ አክለውም፣ ‹‹ከዓለም ሙስሊሞች ጋር ተባብረን መልካም ስሙን እና ታሪኩን ከፍ አናደርገዋለን›› ብለዋል።
ለግንባታው በተሰጠው ቦታ ላይ ያልተጠናቀቁ የወሰን ጉዳዮችን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከከተማው ከንቲባ ክብርት አዳነች አበቤ ጋር በመነጋገር ቀሪ ሂደቶችን እንደሚጨርሱ ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል፡፡
በኪነ-ሕንፃ ቅድመ ንድፍ ውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከ60 ያላነሱ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ መውሰዳቸው የተነገረ ሲኾን፣ ከእነዚህ ውስጥ ለውድድሩ ሥራቸውን ያቀረቡት 18 ድርጅቶች እንደኾኑ የኪነ-ህንፃ ንድፍ ውድድሩ የዳኞች ሰብሳቢ አቶ መሐመድ አህመድ ጠሃ ተናግረዋል፡፡
ሥራቸውን ለውድድር ካቀረቡት 18 ድርጅቶች ውስጥ አሸናፊዎችን ለመምረጥ 125 የሥራ መለኪያ መስፈርቶች ተዘጋጅተው ከማንኛውም ተጽዕኖ በፀዳ እና ጥንቃቄ በተመላበት አሠራር የመጨረሻዎቹ አሥሩ መለየታቸውን አቶ መሐመድ ተናግረዋል፡፡
በመሠረታዊነት የኪነ-ህንፃው ንድፍ ውድድሩ የአምልኮ ቦታን፣ የማኅበረሰብ አገልግሎት መስጫ እና የቢዝነስ ማዕከልን ያካተተ ኾኖ፣ ለሙያዊ ፈጠራ ምህዳሩን ክፍት ያደረገ እንደነበር ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡
ከዘጠኝ ባለሙያዎች የተዋቀረው የዳኝነት ኮሚቴ ሥራውን ሙያዊ ስነ ምግባርን በጠበቀና ምሥጢራዊነትን በጠበቀ መልኩ እንደፈፀመ ሰብሳቢው አቶ መሐመድ ተናግረዋል።
በዳኝነት መስፈርቱ መሠረት ከ5ኛ እስከ 10ኛ ለወጡት ተወዳዳሪዎች የ100 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት አማካሪና የነጃሺ እስላማዊ ማዕከል ግንባታ ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ የሚገነባው የነጃሺ እስላማዊ ማዕከል የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ የሆነችውን አዲስ አበባ ከተማን የሚመጥን፣ የታላቁን ንጉሥ ስም ከፍ የሚያደርግና ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ ዘመን ተሻጋሪ አሻራ እንደሚኾን ተናግረዋል፡፡
‹‹ይህ የሁሉም አሻራ ብርሃን በመሆኑ በዚህ ውድድር የሳተፋችሁ ድርጅቶች ሁላችሁም አሸናፊ ናችሁ›› ብለዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን በውድድሩ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ለወጡት ድርጅቶች እንደ ቅደም ተከተላቸው የ600 ሺህ እና የ400 ሺህ ብር ሽልማት አበርክተዋል።
የነጃሺ እስላማዊ ማዕከል ግንባታ ዐብይ ኮሜቴ አባል የኾኑት ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ በውድድሩ አራተኛ ለወጣው ድርጅት የ200,000 ሽልማት አበርክተዋል።
ሥራቸውን ለውድድር ያቀረቡት 18 ድርጅቶች እና ባለሙያዎቻቸውም የእውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
በዚህ ታሪካዊ የነጃሺ እስላማዊ ማዕከል የኪነ-ህንፃ ቅድመ ንድፍ ውድድር ውጤት ይፋ ማድረጊያ ስነ ሥርዓት ላይ የኢ/እ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ከፍተኛ አመራሮች፣ የአ/አ/እ/ጉ/ከ/ም/ቤት ፕሬዚደንት ሸይኽ ሡልጣን አማን ኤባ እና ዋና ጸሐፊው ሸይኽ ሑሴን፣ የኦሮምያ/እ/ጉ/ከ/ም/ቤት ፕሬዚደንት ፣የነጃሺ እስላማዊ ማዕከል ግንባታ ዐብይ ኮሚቴ አባላት፣ የቢላሉል ሐበሺ የበላይ ጠባቂ ዑስታዝ ሙሐመድ ጀማል ጎናፍር፣ ዱዓቶች፣ ተወዳዳሪ ድርጅት ተወካዮች፣ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ወጣቱ ትውልድ በሀገሪቱ የሰላምና የልማት ሥራዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ ሊኾን ይገባል ተባለ
የካቲት 9፣ 2016 (አዲስ አበባ) - ወጣቱ ትውልድ በሀገሪቱ የሰላምና የልማት ሥራዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ መሆን እንዳለበት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳሰበ።
"እስላማዊ የአመራር ክህሎትን በማጎልበት ሥራ ፈጣሪ ትዉልድን ማፍራት" በሚል መሪ ቃል የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ የሁለት ቀናት ሥልጠና ተጀምሯል።
በሥልጠናው መክፈቻ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሀሩን ባደረጉት ንግግር መጅሊሱ በአዋጅ እንደ አዲስ ከተቋቋመ ወዲህ ከተሠሩ የለውጥ ሥራዎች አንዱ የሴቶችና የወጣቶች ዘርፍ ማቋቋሙ መኾኑን ተናግረዋል።
በምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተጀመረዉ በዚህ ሥልጠና ላይ ከሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች የሴቶችና የወጣቶች ዘርፍ ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን የወጣቱ ቁጥር ከሀገሪቱ ሕዝብ ሰባ በመቶ እንደሚሸፍን ጠቅሰው ወጣቱ በሀገሪቱ ዉስጥ በሚደረጉ የሰላምና የልማት ሥራዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ መሆን አለበት ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት አምራች ኃይል የሆነው ወጣቱ ትውልድ ውጤታማ እንዳይሆን የተለያዩ ሱሶች እየጎተቱት በመሆኑ ይህን በመቅረፍ ለሀገሩና ለዲኑ ውጤታማ ሥራ እንዲሠራ ማድረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት መሆኑን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሴቶችና ወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፌደራል መጅሊስ እስከ መስጂድ የሴቶችና የወጣቶች ዴስክ አደረጃጀት ዘርግቶ በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ ዑስታዛ ፋጡማ ኢብራሂም በእስልምና ወጣቶችን የማበረታታትና የማብቃት ሃይማኖታዊ ኃላፊነትን ቅዱስ ቁርኣን እና የነቢዩ ሙሐመድን (ሶ.ዐ.ወ) ሐዲስ በማጣቀስ አቅርበዋል።
እስልምና ለሴቶች ከፍተኛ ቦታ የሰጠ መሆኑን የጠቀሱት ዑስታዛ ፋጡማ፣ የሴቶችን አቅም በማሳደግ ማኅበረሱን ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።
በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሴቶችና የወጣቶች ዘርፍ በተዘጋጀዉ የሁለት ቀናት ሥልጠና ላይ የሥራ አመራር ክህሎትና በአንተርፕረነርሺፕ ላይ ያተኮረ ሥልጠና የሴቶችና ወጣቶች አማካሪ ቦርድ አባላት በሆኑ ምሁራን እንደሚሰጥ ታውቋል።
**
ሻዕባን 7፣ 1445ዓ.ሒ

ፕሬዚደንቱ የአብደላህ ኢብኑ ኡሚ መኽቱም ማኅበርን የዐይነ ስውራን ሕጻናት አዳሪ ትምህርት ቤት ጎበኙ
የካቲት 9፣ 2016 (አዲስ አበባ) - "አላህ ሲሳያችሁን ያሰፋላችሁ (ሀብታም) አማኞች፣ ማንም ሳያያችሁ መጥታችሁ፣ አብደላህ ኢብኑ ኡሚ መኽቱም የዐይነ ስውራን ሕጻናት አዳሪ ትምህርት ቤትን እንድትረዱ" ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ጥሪ አደረጉ።
የክብር ዶ/ር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ይህን ጥሪ ያደረጉት በሸገር ከተማ፣ ቡራዩ ክፍለ ከተማ የሚገኘውንና በአብደላህ ኢብኑ ኡሚ መኽቱም የበጎ አድራጎት ማኅበር የሚንቀሳቀሰውን ማየት የተሳናቸው ሕጻናት ትምህርት ቤት በጎበኙበት ጊዜ ነው።
ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ "እስካሁን ይህን ተቋም በቅርበት ሳናውቀው ቆይተናል፤ ከዚህ በኋላ ግን ፕሮጀክት ተቀርፆ የምክር ቤታችን የልማት ክንፍ ከኾነው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ ጋር በትብብር የምትሠሩበትን ሁኔታ እናመቻቻለን" ብለዋል።
"እነዚህ ሕጻናት እስልምናን ከቃል ባሻገር በብሬል እያነበቡ ተምረው የዓለም ብርሃን እንዲኾኑ፣ አቅም ያለው ወገን ሁሉ እገዛ ሊያደርግላቸው ይገባል" ሸይኽ ሐጂ አሳስበዋል።
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር፣ አቶ ኢብራሂም ሰዒድ ይህ ተቋም ሕፃናት ዐይነ ስውራን ትምህርት እንዲያገኙና መንፈሳዊ አቅማቸው እንዲጎለብት በማድረግ ረገድ በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ውስጥ ያለውን ክፍተት ለመዘጋት መልካም ጅማሮ መሆኑን ተናግረዋል።
የትምህርት ቤቱ ግቢ እና የተማሪዎቹ ማደሪያ በተቻለ መጠን ማየት ለተሳናቸው ሕጻናት አመቺ እንዲሆን ተደርጎ እንደተዘጋጀ በጉብኝቱ ወቅት ለማወቅ ተችሏል።
በአብደላህ ኢብኑ ኡሚ መኽቱም የዓይነ ሥውራን ትምህርት ቤት በተካሄደው በዚህ ጉብኝት ላይ፣ ከምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ጋር የሕዝብ እንደራሴ የተከበሩ ዑስታዝ ካሚል ሸምሱ፣ ዑስታዝ አሕመዲን ጀበልና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
"ማየት የተሳናቸው ወገኖችን መርዳት ራሱን የቻለ ዳዕዋ ነው" ያሉት ሸይኽ ሐጂ፣ "ጠቅላይ ምክር ቤታችንም ከጎናችሁ ይቆማል፤ ውድ ባለሃብቶችም ወደዚህ ተቋም መጥታችሁ አንድ ነገር አበርክቱ፤ እነዚህን ሕጻናትን የሁላችንንም እገዛ ይፈልጋሉ" ብለዋል።
የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ከድር ማሕሙድ በዚሁ ጊዜ ሲናገሩ፣ የማኅበሩን የበጎ አድራጎት ሥራ ለማስፋት ለመንግሥት የ6 ሺህ ካሬ ሜትር የቦታ ጥያቄ ማቅረባቸውን ጠቅሰው፣ ለተፈጻሚነቱ መጅሊስ ከጎናቸው እንዲቆም ጠይቀዋል።
አብደላህ ኢብኑ ኡሚ መኽቱም ማየት የተሳናቸው ሕጻናት አዳሪ ትምህርት ቤት፣ በአሁኑ ጊዜ 20 ማየት የተሳናቸው ሕጻናትን ተቀብሎ በማኅበረሰብ ድጋፍ እያስተማረ ይገኛል።
ማኅበሩ የተመሠረተበትን 10ኛ ዓመት በቅርቡ (የካቲት 22) በግራንድ ኤሊያና ሆቴል እንደሚያከብርም ለማወቅ ተችሏል።
******
ሻዕባን 7፣ 1445 ዓ.ሒ

ረቂቅ የሥራ መመሪያው በውይይት ዳብሮ ሲፀድቅ መጅሊሱን የተማከለ ሥራ ለመሥራት ያስችለዋል ተባለ።
የካቲት 11፣ 2016 (አዲስ አበባ) - በአዲስ መልክ የተዋቀረው የጠቅላይ ምክር ቤቱ የትምህርት እና የማኀበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ለውይይት ያቀረበው ረቂቅ የሥራ መመሪያ የሙስሊሙን መብትና ሃይማኖታዊ እሴት የሚያስጠብቅ ሊሆን ይገባል ተባለ።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳሬክተር ዶክተር አብደላ ኸድር የውይይቱን አስፈላጊነት ሲገልፁ አንድነትን ባስጠበቀ መልኩ የተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት ዳሬክቶሬቱ ረቂቅ ሰነዱን አዘጋጅቷል ብለዋል።
ረቂቅ ሰነዱ ከውይይት በተገኙ ግብዓቶች ዳብሮ ሲፀድቅ ሁሉን ተጠቃሚ የሚያደርግና መጅሊሱን የተማከለ ሥራ ለመሥራት የሚያስችለው እንደሚሆን አብራርተዋል።
በትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ረቂቅ የሥራ መመሪያ ላይ ገለጻ ያደረጉት የማኅበራዊ አገልግሎት ኃላፊው ዶ/ር ቶፊቅ በራራ ረቂቅ የሥራ መመሪያው ጠቅላይ ምክር ቤቱ ተልዕኮውን እንዲያሳካ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል።
የዳይሬክቶሬቱ የትምህርትና ሥልጠና ኃላፊ አቶ መሐመድ ይመር በበኩላቸው በረቂቅ የሥራ መመሪያው ላይ በሰጡት ማብራሪያ፣ የሕዝበ ሙስሊሙን የትምህርት ሽፋን ለማሳደግና ዘመኑን ሊመጥን የሚችል ተወዳዳሪ ሙስሊም ተማሪዎችን ለማፍራት ትጋት ያለው ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
በቀረበው ረቂቅ የሥራ መመሪያ ላይ ጠንከር ያለ ክርክር እና ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።
ረቂቅ የሥራ መመሪያውን በማዘጋጀት ሂደት ላይ ከትምህርትና ማኀበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር ለሦስት ወር ጥናት ሲያደርጉ የነበሩ ምሁራን በረቂቁ ላይ ባለድርሻ አካላት ያደረጉት የነቃ ተሳትፎና የሰጡት አስተያየት ያስደሰታቸው መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ባዘጋጀው ረቂቅ የሥራ መመሪያ ውስጥ የትምህርትና ሥልጠና ኃላፊነት ከፍ ያለ መኾኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ ዶክተር አብደላ ኸደር፣ ዳይሬክቶሬቱ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን የአካል ጉዳተኞች ሁኔታ ያማከለ፣ እስላማዊ እሴቶችን ያከበረና መማር ማስተማሩ ጤናማ እንዲሆን የሚሠራ መሆኑን በአጽንዖት ተናግረዋል።
ረቂቅ የሥራ መመሪያው ዳብሮ ከፀደቀ በኋላ ክልሎች እንደየአካባቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ በማድረግ የመጅሊስን ሥራ ለማሳለጥ የጋራ ትስስር መፍጠር ጠቀሜታው ከፍ ያለ መሆኑም ከመድረኩ ተነግሯል።
**
ሻዕባን 9፣ 1445 ዓ.ሒ

ዓሊሞችና ዱዓቶች እስላማዊ እሴቶችን የሚያጎለብቱ ትምህርቶችን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበ።
የካቲት 10፣ 2016 (አዲስ አበባ) - ዓሊሞችና ዱዓቶች እስላማዊ እሴቶችን የሚያጎለብቱ ትምህርቶችን ከመቼውም በበለጠ መልኩ እንዲሰጡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አሳሰቡ።
ዋና ሥራ አስኪያጁ ሐጂ ከማል ሐሩን ይህን ያሳሰቡት ለክልልና ለከተማ አሥተዳደር እስልምና ጉዳዮች የሴቶችና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊዎች ለሁለት ቀናት የተሰጠው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ማጠናቀቂያ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
የመረጃ ዝውውሩ ፈጣን በሆነበት በዚህ ዘመን ሴቶችና ወጣቶችን ከዓላማቸው ሊያዘናጉ፣ ከእስላማዊ እሴታቸውም ሊያፋቱ የሚችሉ ማኅበራዊ ሚዲያዎች መበራከታቸውን ዋና ሥራ አስኪያጁ አውስተዋል።
የሴቶችና የወጣቶችን ስብዕና በእስላማዊ እሴቶች በመገንባት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ እንደሚገባም ዋና ሥራ አስኪያጁ አሳስበዋል።
በሥልጠናው መክፈቻ ላይ ዋና ሥራ አስኪያጁ "በአሁኑ ወቅት አምራች ኃይል የሆነው ወጣቱ ትውልድ ውጤታማ እንዳይሆን የተለያዩ ሱሶች እየጎተቱት በመሆኑ ይህን በመቅረፍ ለሀገሩና ለዲኑ ውጤታማ ሥራ እንዲሠራ ማድረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት ነው" ማለታቸው ይታወሳል።
በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ "እስላማዊ የአመራር ክህሎትን በማጎልበት ሥራ ፈጣሪ ትዉልድን ማፍራት" በሚል መሪ ቃል ለሁለት ቀናት በተለያዩ ርዕሶች ላይ ምሁራን ሥልጠና ሰጥተዋል።
በምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ ሥልጠና ላይ ከሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች የሴቶችና የወጣቶች ዘርፍ ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።
በሥልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ዋና ሥራ አስኪያጁ ሐጂ ከማል ሐሩን እና የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ ኃላፊዋ ዑስታዛ ፋጡማ ሁሴን ለሠልጣኞች የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል።
******
ሻዕባን 8፣ 1445 ዓ.ሒ

የሐጅ የምዝገባ ጣቢያዎችን ቁጥር በማሳደግ ፈ ጣን የምዝገባ አ ገልግሎ እየሰጠ መሆኑን የኦሮሚያ መጅሊስ ገለፀ።
የካቲት 12/16 (ፊንፊኔ)የሐጅ የምዝገባ ጣቢያዎችን አምና ከ ነበረዉ 5 የምዝገባ ጣቢያዎች ወደ 12በማሳደግ ፈጣንና የምዝገባ አ ገልግሎ እየሰጠ መሆኑን የኦሮሚያ መጅሊስ ፕረዚዳንት ገለፁ።
የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕረዚዳንት ሼይኽ ጀማል ሙሳ እንደ ተናገሩት ከአመታት በፊት የሐጅ ምዝገባ በጠቅላይ ምክርቤቱ ብቻ በመሆኑ ዑማው ለከፋ እንግልትና ለከ ፍተኛ ወጪ ይዳረጋል እንደነበር ተናግረዋል።
በዘንድሮ አመት የአሏህን እንግዶችን እንግልት ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ስራ መጅሊሱ ሲሰራ መቆየቱን የ ተናገሩት ፕረዚዳንቱ አምና ከነበረዉ የምዝገባ ጣቢያዎች በጥናት ሰባት ተጨማሪ የሐጅ የምዝገባ ጣቢያዎችን በመክፈት ለሕብረተሰቡ ተደራሽ መሆን መቻሉን ፕረዚዳንቱ ተናግረዋል ።
የኦሮሚያ መጅሊስ የሐጅና ዑምራ ዳይሬክተር ዑስታዝ ጀማል አሊ በዘንድሮውን ሐጅ መስተንግዶ የአላህን እንግዶችን መስተንግዶ ለማቀላጠፍ መጅሊሱ የአንድ ማ ዕከል አገልግሎት እየሠጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በዚህም የተመዝጋቢዎችን እርካታ ከፍ ማድረግ መቻሉን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የዘንድሮ የሐጅ ምዝገባ ቀድሞ መጀመሩ ን ዳይሬክተሩ ተናግረው በዘንድሮ አመት ሐጅ የማድረግ ኒያ ያላቸው የአላህ እንግዶች ከወዲሁ በአቅራቢያቸው የሐጅ የምዝገባ ጣቢያ ቀድሞ በመመዝገብ በመጨረሻ ሊገጥማቸው ከሚችል እንግልት እራሳቸው ሊጠብቁ እንደመገባ አሳስበዋል።
የመጅሊሱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሙሐመድ ጋሊ አባፊጣ ጥር 25/16 ዓ.ል ረጀብ 22/1445 የሐጅ ምዝገባ በኦሮሚያ መጅሊስ ስር በሚገኙ 12 የሐጅ የምዝገባ ጣቢያዎች መጀመሩን ገልፀዋል።
ለሐጅ ምዝገባ የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን አሟልቶ የመጣ አንድ ሐጅ ከአምስት እስከ አስር ደቂቃ ምዝገባውን ማጠናቀቅ እንደሚችል ተናግረዋል ።
የመጠቀሚያ ግዜያቸው የተጠናቀቀ አሊያም የጉዞ ሰነድ (ፖስፖርት ) የሌላቸው የአላህ እንግዶች ከኢሚግሬሽን የዜግነት ጉዳዮች ጋር በመተባበር መስተናገድ የሚችሉበት ስርዐት መጅሊሱ ማመቻቸቱን ዋና ስራ አስኪጅ ሙሐመድ ጋሊ ተናግረዋል።
የዘንድሮውን ሐጅ " የዘመነ መስተንግዶ ለአሏህ እንግዶች " በሚል መሪ ቃል መሰየሙ ይታወቃል።

የሐጅ ምዝገባን በአምስት ደቂቃ እየሰጠ መሆኑን የአዲስ አበባ መጅሊስ አሳወቀ።
የካቲት 14፣ 2016 (አዲስ አበባ) - አስፈላጊውን መረጃ ይዞ ለሐጅ ምዝገባ የቀረበ የአላህ እንግዳ (ሐጃጅ) በአምስት ደቂቃ የምዝገባ ሥርዓቱን የሚያጠናቅቅበት የአሠራር ሥርዐት መዘርጋቱን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሱልጧን አማን ተናገሩ።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከአሁን በፊት የሐጅ ማጣሪያ አገልግሎት ብቻ ይሰጥ እንደነበር ፕሬዚዳንቱ አስታዉሰዋል።
በዘንድሮ ዓመት የሐጅ ምዝገባ ሂደት ሙሉ በሙሉ በመጅሊሱ የሚካሄድ በመሆኑ ለተከሩ ለአሏህ እንግዶች ፈጣን ፣ ግልፅ መሰተንግዶ ለመስጠት ሰፊ ዝግጅት ሲያደረግ መቆየቱን ፕረዚዳንቱ ገልፀዋል።
የ1445/2016 የሐጅ ምዝገባ የሳውዲ አረቢያ ሐጅ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት ጥር 25/16 ( ረጀብ 22/1445 ምዝገባ ተጀምሮ የካቲት 27/16(ሻዕባን 25፣1445 ዓ.ሒ) ምዝገባዉ እንዲጠናቀቅ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ፕረዚዳንቱ
ተናግረዋል።
የምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ክፍል ኅላፊ ሐሺም አ ብደላ በምክር ቤቱ ምዝገባ ከተጀመረ ከጥር 25/16(ረጀብ 22/1445 ) የተከበሩ የአሏህ እንግዶች ምዝገባ መጀመራቸውን ተናግረዋል።
በምክር ቤቱ ምንም እንኳን የሐጅ ምዝገባን ሙሉ በሙሉ በዘንድሮ አመት የጀመረ ቢሆንም የምዝገባ ስርዐቱ ቀልጣፋ እንዲሆን በቂ ባለሙያ :ምቹ የቢሮ ዝግጅትና የቁሳቁስ ዝግጅት ከቀድሞ በመጠናቀቁ በአሁኑ ሰ ዓት አ ንድ ሐጅ የምዝገባ ስርዐቱን በአማካይ በአምስት ደቂቃ መስተናገድ መቻሉን ሐሺም አብደላ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ መጅሊስ የሐጅ ምዝገባ ጣቢያ የሐጅ ኒያ ያደረጉ የአሏህ እንግዳን ሲያስመዘግቡ ያገኘናቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክርቤት ምክትል ፕረዚዳንት ሼይኽ አብዱልሐብ ሼይኽ በድረዲን የዘንድሮ የሐጅ ምዝገባ ቀድሞ በመጀመሩ ምክንያት መዘናጋት ስለሚኖሮ ሐጅ የሚወጅባቸውን ሑጃጆችን የምዝገባ ቀኑ ከመጠናቀቁ በፊት መመዝገብ እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።
******
ሻዕባን 12፣ 1445 ዓ.ሒ
******
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/e
የሐጅ ምዝገባን በአምስት ደቂቃ እየሰጠ መሆኑን የአዲስ አበባ መጅሊስ አሳወቀ።
የካቲት 14፣ 2016 (አዲስ አበባ) - አስፈላጊውን መረጃ ይዞ ለሐጅ ምዝገባ የቀረበ የአላህ እንግዳ (ሐጃጅ) በአምስት ደቂቃ የምዝገባ ሥርዓቱን የሚያጠናቅቅበት የአሠራር ሥርዐት መዘርጋቱን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሱልጧን አማን ተናገሩ።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከአሁን በፊት የሐጅ ማጣሪያ አገልግሎት ብቻ ይሰጥ እንደነበር ፕሬዚዳንቱ አስታዉሰዋል።
በዘንድሮ ዓመት የሐጅ ምዝገባ ሂደት ሙሉ በሙሉ በመጅሊሱ የሚካሄድ በመሆኑ ለተከሩ ለአሏህ እንግዶች ፈጣን ፣ ግልፅ መሰተንግዶ ለመስጠት ሰፊ ዝግጅት ሲያደረግ መቆየቱን ፕረዚዳንቱ ገልፀዋል።
የ1445/2016 የሐጅ ምዝገባ የሳውዲ አረቢያ ሐጅ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት ጥር 25/16 ( ረጀብ 22/1445 ምዝገባ ተጀምሮ የካቲት 27/16(ሻዕባን 25፣1445 ዓ.ሒ) ምዝገባዉ እንዲጠናቀቅ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ፕረዚዳንቱ
ተናግረዋል።
የምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ክፍል ኅላፊ ሐሺም አ ብደላ በምክር ቤቱ ምዝገባ ከተጀመረ ከጥር 25/16(ረጀብ 22/1445 ) የተከበሩ የአሏህ እንግዶች ምዝገባ መጀመራቸውን ተናግረዋል።
በምክር ቤቱ ምንም እንኳን የሐጅ ምዝገባን ሙሉ በሙሉ በዘንድሮ አመት የጀመረ ቢሆንም የምዝገባ ስርዐቱ ቀልጣፋ እንዲሆን በቂ ባለሙያ :ምቹ የቢሮ ዝግጅትና የቁሳቁስ ዝግጅት ከቀድሞ በመጠናቀቁ በአሁኑ ሰ ዓት አ ንድ ሐጅ የምዝገባ ስርዐቱን በአማካይ በአምስት ደቂቃ መስተናገድ መቻሉን ሐሺም አብደላ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ መጅሊስ የሐጅ ምዝገባ ጣቢያ የሐጅ ኒያ ያደረጉ የአሏህ እንግዳን ሲያስመዘግቡ ያገኘናቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክርቤት ምክትል ፕረዚዳንት ሼይኽ አብዱልሐብ ሼይኽ በድረዲን የዘንድሮ የሐጅ ምዝገባ ቀድሞ በመጀመሩ ምክንያት መዘናጋት ስለሚኖሮ ሐጅ የሚወጅባቸውን ሑጃጆችን የምዝገባ ቀኑ ከመጠናቀቁ በፊት መመዝገብ እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።
******
ሻዕባን 12፣ 1445 ዓ.ሒ
******
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/e
Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት በዓሊሞች ፎረም ላይ ለመሳተፍ አልጀርስ ገቡ።
የካቲት 16፣ 2016 (አዲስ አበባ) - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ በነገው ዕለት በአልጄሪያ በሚካሄደው የዓልጄሪያ ሙስሊሞች ፎረም ላይ ለመሳተፍ አልጀርስ ገቡ።
ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ወደ አልጀርስ የተጓዙት ነገ በሚጀመረው የአልጄሪያ ሙስሊሞች ፎረም ጉባዔ ላይ በክብር እንግድነት እንዲገኙ ከአልጄሪያ የሙስሊሞች መሪ በሆኑት ሼይኽ ሙሐመድ አል መሙን ሙስጠፋ በተደረገላቸው ጥሪ መሠረት ነው።
የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም አልጀርስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በአልጄሪያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ነቢያት ጌታቸውና የአልጄሪያ ሙስሊሞች ዓሚር ሼይኽ ሙሐመድ አል መሙን ሙስጠፋ አቀባበል እድርጎላቸዋል።
የክቡር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም በአልጀርስ በ ሚመረቀው ትልቁ መስጂድ ላይም በ ክብር እንግድነት እንደሚገኙ በቦታው የሚገኘው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ቃል አቀባይ ገልጿል።
****
ሻዕባን 15፣ 1445ዓ.ሒ

ጠቅላይ ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ፌስቲቫል ላይ ተሳተፈ
የካቲት 16፣ 2016 (አዲስ አበባ) - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የባህልና ቅርስ ዘርፍ ከየካቲት15- 17 በግዮን ሆቴል በሚካሄደው 'የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ፌስቲቫል' ላይ የካሊግራፊ (calligraphy) ጥበብን በማቅረብ እየተሳተፈ ይገኛል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የባህልና ቅርስ ዘርፍ ኃላፊና የሥራ አመራር ሸይኽ መሐመድ አሚን ሰዒድ የፌስቲቫሉን አስፈላጊነት ሲገልፁ፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ እስላማዊ ጥበባት እና ታሪካዊ ቅርሶች ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኙ ይጥራል ብለዋል።
በአረብኛ ፊደላት ላይ የተመሠረተው ካሊግራፊ በእስላማዊ የጥበብ ታሪክ ውስጥ የራሱ ታሪክ እና ቦታ ያለው፣ የእጅ ጽሑፍ ጥበብ መኾኑን ሸይኽ መሐመድ አሚን ተናግረዋል።
እስልምና በየትኛውም ዘርፍ የራሱ ማንነትና መገለጫ እንዳለው የጠቀሱት ሸይኽ መሐመድ አሚን፣ በካሊግራፊ እስላማዊ አስተምህሮት ጥበባዊና ዐይነ ግቡ በሆነ መልኩ እንደሚቀርብ ጠቁመዋል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ በእስልምና ባህል፣ ታሪክ፣ ጥበብ እና ቅርስ ታሪክ ዙሪያ የሚሠሩትን ያበረታታል፤ ተባብሮም ይሠራል ብለዋል።
በዚህ የኪነ ጥበብ ፌስቲቫል ላይ የካሊግራፊ ሥራዎቹን ያቀረበዉ አቶ ባህሩ ጀማል ይህን መድረክ በምክር ቤቱ አማካኝነት እንዳገኘው ገልጾ፣ የካሊግራፊ ጥበብ በሙስሊሙ ዓለም ውስጥ ጠቃሚ የኪነ ጥበብ ዘዴ እንደኾነ ተናግሯል።
ካሊግራፊ በአረብኛ ፊደላት ላይ የተመሠረተ እስላማዊ የአጻፃፍ ጥበብ መኾኑን የጠቀሰው ባህሩ ጀማል፣ በዚህ ጥበብ ለማኅበረሰብ እስላማዊ መልዕክትን ማስተላለፍ እንደሚቻል ተናግሯል።
ማኅበረሰቡ ዳዕዋን በጥበባዊ መንገድ እንዲያገኝ ያስችላል ያለው ባህሩ፣ ስነ-ህንፃ ከማስዋብ ባሻገር ሃይማኖታዊ ተልዕኮን ለመወጣት ያስችላል ብሏል።
ከአቶ ባህሩ በተጨማሪ፣ ተማሪ አረቢ አብዱልዋሲጥ እና ተማሪ ሀይደር ሰባህም
በፌስቲቫሉ ላይ የካሊግራፊ ሥራቸውን አቅርበዋል።
እስላማዊ ካሊግራፊ መልዕክትን ምስላዊ አድርጎ የሚያስውብ፣ የቁርኣን አናቅፅ በጥበብ የሚገለጹበት በመሆኑ፣ በሙስሊሙ ዓለም ትኩረት ይሰጠዋል ሲሉ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ባዘጋጀው በዚህ 'የጥበብ ፌስቲቫል' ላይ የመውሊድ እና የሀሪማዎችን እሴቶች የሚያሳዩ ባህላዊ ቁሶችም ለዕይታ ቀርበዋል።
*****
ሻዕባን 15፣ 1445 ዓ.ሒ
****
የጠ/ምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ

ፕሬዚደንቱ በአልጄሪያ የጀምዓተል ጀዛኢር የመስጂድ ምርቃት ላይ በመገኘት ንግግር አደረጉ።
የካቲት 17፣ 2016 (አዲስ አበባ) - በአልጄሪያ የዓሊሞች ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ አልጀርስ ያቀኑት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የጀምዓተል ጀዛኢር የመስጂድ ምርቃት ላይ ተገኝተው ንግግር አደረጉ።
ሸይኽ ሐጂ በንግግራቸው ዛሬ በአልጀርስ ከተማ በውቡ የጀምዓተል ጀዛኢር መስጂድ ምርቃት ላይ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ በራሳቸውና በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም ገልፀዋል።
ፕሬዚደንቱ አክለውም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በፍትኃዊዉ ንጉሥ አስሃመተል ነጃሺ ስም በአፍሪካ ሕብረት ዋና መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት ደረጃውን የጠበቀ መስጂድ ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት ላይ መኾኑን ተናግረዋል፡፡
የመስጂደል ጀዛኢር መስጂድ በአልጀሪያው ፕሬዚደንት አብዱልነጂብ ቲቦኒ ተመርቋል፡፡
ፕሬዚደንት አብዱልነጂብ በዚሁ ጊዜ ባደረጉት ንግግር መሃል ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ለክቡር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም እና ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶክተር) የክብር ሰላምታቸውን አቅርበዋል።
ዛሬ በአልጀርስ በድምቀት የተመረቀዉ መስጂደል ጀዛኢር በስፋቱ ከመካ እና ከመዲና ቀጥሎ የሦስተኝነት ደረጃ እንደሚኖረው ተነግሯል።
የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ የአልጄሪያ የሙስሊሞች አሚር በሆኑት ሸይኽ ሙሐመድ አል መሙን ሙስጠፋ አል ቃሲሚ በተደረገላቸው ጥሪ መሠረት በጉባዔዉ ተሳታፊ ኾነዋል።
የመስጂደል ጀዛኢር የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ ከመላው ዓለም የተጋበዙ ዓሊሞች መታደማቸውን በቦታው የተገኘው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ቃል አቀባይ ለክፍላችን የላከው መረጃ ያመላክታል።
****
ሻዕባን 16፣ 1445 ዓ.ሒ

ፕሬዚደንቱ በአልጀርሱ የዓሊሞች ፎረም ላይ በመገኘት ንግግር አደረጉ።
የካቲት 18፣ 2016 (አዲስ አበባ) - በአልጄሪያ የዓሊሞች ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ አልጀርስ ያቀኑት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በፎረሙ ላይ ንግግር አድርገዋል።
ሸይኽ ሐጂ በንግግራቸው በአልጄሪያ የዓሊሞች ፎረም ላይ ተገኝተው ንግግር ለማድረግ በመቻላቸው ለፈጣሪያቸው ለአላህ (ሱ.ወ.) ምሥጋናቸውን በማቅረብ ፎረሙን ላዘጋጁት አካላት በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም ምሥጋና አቅርበዋል።
በንግግራቸውም፣ እስልምና መዲና ከመግባቱ በፊት ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን አውስተዋል።
በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ ለእስልምና ብርሃን መስፋፋት ባለውለታ ሀገር መሆኗን፣ የቢላል ኢብኑ ረባህ፣ የዑሙ ዐይመን እና የፍትኃዊዉ ንጉሥ የአስሐመተል ነጃሺን ታሪክ በአብነት ጠቅሰዋል።
አስልምና ለእስላማዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ከፍተኛ ቦታ እንደሚሰጥ የተናገሩት ፕሬዚደንቱ፣ በዑማው ላይ ሊደርስ የሚችለውን ችግርና መከራ አንድነታችንን በመጠበቅ መቀነስ እንደሚቻል ተናግረዋል።
ሰላም ለሰው ዘር ሁሉ አስፈላጊ እንደኾነ የጠቀሱት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም፣ በሰላም እጦት ምክንያት እምነታቸዉን በነፃነት ማምለክ ላልቻሉት የፍልስጥኤም፣ የአዘርባጃን እና የኢስቶኒያ ሕዝቦች ዓለም ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።
በዛሬዉ የፎረሙ ውሎ በአወያይነት ከተሰየሙ የአምስት ሀገራት ዓሊሞች ውስጥ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ አንዱ ሆነዋል።
ከአፍሪካ ትልቁና ከዓለም በትልቅነቱ ሦስተኛ ይኾናል በተባለው የመስጂድ አል ጀዛኢር ምርቃት ትላንት የተጀመረው የአልጀርሱ የዓሊሞች ፎረም በዛሬው ውሎው በተለያዩ ዲናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ተጠናቅቋል።
በአልጄሪያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ነቢያት ጌታቸውና የኤምባሲው ሠራተኞች ለሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ክብር በዛሬው ዕለት የእራት ግብዣ እንዳደረጉላቸው ከፕሬዚደንቱ ጋር አብሮ የተጓዘው የመጅሊሱ ቃል አቀባይ ገልጿል።
****
ሻዕባን 17፣ 1445 ዓ.ሒ
****
የሕዝብ ግንኙነት ክፍል

ቀልጣፋ የሐጅ ምዝገባ በአዲስ አበባ መጅሊስ እየተካሄደ ነው።
የካቲት 19፣ 2016 (አዲስ አበባ) - ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለዘመናት የሕብረተሰቡ የቅሬታ መንስዔ የነበረውን የሐጅ ምዝገባ በማዘመን ፈጣን አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚደንት ተናገሩ።
በጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚደንትና የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ አብዱልአዚዝ ሸይኽ አብዱልዋሊ የተመራው ልዑክ የአዲስ አበባ መጅሊስ የሐጅ ምዝገባ ጣቢያን የሥራ ሂደትን ጎብኝቷል።
"የዘመነ አገልግሎት ለአልረህማን እንግዶች" በሚል መሪ ቃል የ1445/2016 የሐጅ ምዝገባ የሐጅ ኒያ ላላቸው ተመዝጋቢዎች ቀልጣፋ፣ ምቹ እና ግልፅ የምዝገባ ሥርዐት በመዘርጋት በዘንድሮ በተከፈቱ 27 የምዝገባ ጣቢያዎች እየተሰጡ መኾኑን ሸይኽ አብዱልአዚዝ ተናግረዋል።
ዛሬ በተጎበኘው የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች የሐጅ የምዝገባ ጣቢያ እየተሰጠ ባለው የምዝገባ ሂደት የተመዝጋቢውን እንግልት የቀነሰ መሆኑን እንደተመለከቱ ሸይኽ አብዱልአዚዝ ተናግረዋል።
የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ አብዱልፈታህ ሙሐመድ ናስር የሳዑዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ባወጣዉ መመሪያ መሠረት የዘንድሮ ዓመት የሐጅ ምዝገባ ቀድሞ የጀመረ ቢሆንም፣ ለሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች ለሐጅ ምዝገባ ሠራተኞች ሥልጠና የዌብ ሲስተም ዝርጋታና የሐጅ ምዝገባ ሶፍትዌርን አጠቃቀም ሲሰጥ መቆየቱን እና ጥር 25/16 (ረጀብ 22፣ 1445) ምዝገባ መጀመሩን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከኢምግሬሽን የዜግነት ጉዳዮች ባለው መልካም ግንኙነት የጉዞ ሰነዳቸው (ፓስፖርት) ያገልግሎት ጊዜው የተጠናቀቀ ለማደስ አዲስ ማውጣት ለሚያስፈልጋቸው የአሏህ እንግዶን ጠቅላይ ምክር ቤቱ በሚፅፈው የድጋፍ ደብዳቤ መሰረት እየተስተናገዱ መኾናቸውን ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስኪያጅ ሪያድ ጀማል ከአሁን በፊት የአዲስ አበባ መጅሊስ ለሐጅ ተመዝጋቢዎች የእስልምና ማረጋገጫ ሰነድ ብቻ በመስጠት የምዝገባ ሒደቱ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ብቻ በመሰጠት ምክንያት ሰፊ የኅብረተሰብ ቅሬታ እንደነበር አስታውሰዋል።
ሥራ አሥኪያጁ፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በአሁኑ ሰዓት እየተጠቀመ ባለው ያልተማከለ የአሠራር ሥርዓት መሠረት መጅሊሱ ራሱን ችሎ መሥራት በመቻሉ፣ የምዝገባ ሥርዓቱ ቀልጣፋ እንዲሆን ዓይነተኛ ሚና መጫወቱን ተናግረዋል።
በ1445/2016 የትውልደ ኢትዮጵያ የአላህ እንግዶች ምዝገባን በተመለከተ ለሳዑዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስቴር ተደጋጋሚ ደብዳቤዎች ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ቢፃፍም፣ እስካሁን አዎንታዊ ምላሽ ማግኘት አለመቻሉን ለማወቅ ተችሏል።
****
ሻዕባን 18፣ 1445 ዓ.ሒ

ቢላሉል ሐበሺ የልማትና መረዳጃ ማኅበረሰብ የመጀመሪያውን የቢላል የክብር እውቅና መሰናዶ አካሄደ።
የካቲት 19፣ 2016 (አዲስ አበባ) - ቢላሉል ሐበሺ የልማትና መረዳጃ ማኅበረሰብ የመጀመሪያውን የቢላል የክብር እውቅና መሰናዶ ትናንት በሸራተን አዲስ አካሄደ።
ቀጣይ እንደሚኾን በተነገረው በዚህ የክብር እውቅና መስጫ መሰናዶ፣ በትላንትናው ዝግጅት አራት ግለሰቦች እና አንድ ትውልድ የክብር እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
"መልካም ሠሪዎችን ማመሥገን፣ መልካም ሠሪዎችን ይወልዳል" በሚል መርኅ የተካሄደው ይህ የክብር እውቅና መርኃ ግብር፣ ቢላሉል ሐበሺ በቋሚነት እንደሚያካሂደው የዝግጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ሐጅ መሐመድኑር ሙሐመድሳኒ ተናግረዋል።
1ኛ/ የአባድር ትምህርት ቤት መሥራች አባት ሐጅ አቡበከር ኢብራሂም ሸሪፍ፣
2ኛ/ ፕሮፌሰር ሑሴን አሕመድ (የኢትዮጵያ እስልምና የታሪክ ጥናት አባት)
3ኛ/ ፕሮፌሰር ላጵሶ ጌ. ድሌቦ (የኢትዮጵያ እስልምና ታሪክን በማጥናት ምሁራዊ አበርክቶ ያደረጉ)
4ኛ/ በንጉሡ ዘመን ለሙስሊሞች የእኩልነትና የዜግነት ክብር የታገለው ቀዳሚ ትውልድ
5ኛ/ ዳግማዊ አባ ጂፋር
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ ከአምስቱ የክብር እውቅና ተጎናጻፊዎች አንዱ ለኾኑት ለታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ላጵሶ ጌ. ድሌቦ፣ የክብር እውቅናውን ሰጥተዋል።
የመጀመሪያው የቢላል የክብር እውቅና በአብዛኛው በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በማኅበራዊ ንቅናቄ፣ ፖለቲካዊ ተጋድሎ እና ምሁራዊ አርበኝነት ላይ ተሳትፎ በማድረግ እንቅስቃሴ ያደረጉ ሰዎች ላይ ያተኮረ ነው።
በመርኃ ግብሩ ላይ የክብር እውቅና የተሰጣቸው ግለሰቦች የሠሩትን ሥራ የሚያሳይ ከፊል ዘጋቢ ፊልም ለዕይታ ቀርቧል።
በዝግጅቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ፣ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸኽ ሡልጣን አማን ኤባ እና ጥሪ የተደረገላቸው የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።