የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.67K subscribers
9.62K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
41 ቤተ ክርስቲያናት የተሳተፉበት ናሽናል ዩዝ ኮንፍረንሥ በኦክላሆማ ዩኒቨርስቲ መካሄዱ ተገለጸ።

73ኛ ብሔራዊ የወጣቶች ኮንፍረንስ ከ400 በላይ ወጣቶች እና 100 ጎልማሶች የተገኙበት ሲሆን በያዝነው የፈረንጆች አመትም በኦክላሆማ ተካሂዷል። ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ሲሥታፉም በባለፈው አምስት አመታት ውስጥ ይሄ ከፍተኛው ቁጥር ነው።

በ16 ግዛቶች ከሚገኙ 41 ቤተ ክርስቲያኖች የተወጣጡ ወጣቶች በኮንፍራንሱ ላይ የተገኙ ሲሆን ኮንፍረንሱም አምልኮን፣ ጨዋታዎችን እንዲሁም መንፈሳዊ መዋቅር የተደረገበት ነበሩ።

የኦክላሆማ ግዛት ሴናተር የሆኑት ኒኪ ናይስ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ፕሮግራሙን የከፈቱት ሲሆን ወጣቶች በእምነታቸው ጠንካራ እንዲሆኑና ወደ ነበሩበት ማህበረሰብ ሲመለሱም እውነተኛ ክርስቲያናዊ ማንነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል።

የኮንፍረንሱ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት ራሞን ሆህሪጅ በተለያዩ ቤተ እምነቶች መካከል ጠንካራ የሆነ ግንኙነት ሊኖር እንደሚገባ ተናግረዋል።

በከሰዓት በነበሩት ፕሮግራሞች ላይ ብዙ ወጣቶች መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲታደስ ወደ መድረክ ሲመጡ የተስተዋሉ ሲሆን “ወጣት እንዴት ልቡን ይጠብቃል?” የተሰኘው ዝማሬ በተደጋጋሜ እንደተዘመረ ተገልጿል።

መረጃውን ከክርስቲያን ክሮኒክልስ ድረ ገጽ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ
7
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ከቀደምት አገልጋዮች አንዱ የሆኑት ፓሰተር ፍቃዱ ኦፍጋ ከዚህ አለም ድካም አረፉ።

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ከቀደምት አገልጋዮች አንዱ የሆኑት እና በቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተክርስትያን ሲያገለግሉ የነበሩት ፓሰተር ፍቃዱ ኦፍጋ ከዚህ አለም ድካም አርፈዋል።

መጋቢ ፍቃዱ ግማሽ ክፍለ ዘመን የዘለቀው አገልግሎታቸው የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ ከምስረታዋ ጀምሮ አስከ ዛሬ ድረስ በጸሎት ፤ በወንጌል ሰባኪነት ፤ በመጋቢነት በማግልገል ከብዙዎች ጋር ስለወንጌል ዋጋ የከፈሉ የወንጌል አርበኛ ነበሩ።

ነሐሴ 12፣ 2017 ዓ.ም የአስክሬን ሽኝት ስነስርዓት በቀጣና ሁለት ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተክርስትያን የተከናወነ ሲሆን የቀብር ስነ ስርዓቱም በዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን መካነ መቃብር ተከናውኗል።

ኢቫንጃሊካል ቴሌቪዥን በመጋቢ ፍቃዱ ዜና እረፍት የተሰማውን ሃዘን እየገለጸ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል።
5🙏3
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ክልሎች ጠቅላላ ጉባኤዎቻቸውን አካሄዱ።

በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የወንጂና አካባቢው ጊዜያዊ ክልል፣ አዋሽ ሸለቆ ክልል፣ የደቡብና ሰሜን አዳማ ክልሎች እንዲሁም የምስራቅ ኢትዮጵያ ክልል ከነሃሴ 9-11/2017 ዓ.ም የክልል ጠቅላላ ጉባኤዎችን አካሂደዋል።

በክልሎቹ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ከዋናው ቢሮ በተወከሉ ኃላፊዎች በ2016 ዓ.ም በተሻሻለው ውስጠ ደንብ ላይ ገለጻ ሲደረግ የ2017 ዓ.ም ሪፖርትና የ2018 ዓ.ም እቅድ በክልሎቹ ዋና ጸሐፊዎች ቀርቧል። እንዲሁም የክልል ዋና ጸሐፊና አስተዳደር መሪዎች ምርጫ ተከናውኗል።

መረጃው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው።
11