ዛሬ ነሐሴ 15/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ አንድነት በክርስቶስ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት 7ተኛ ጠቃላላ ጉባኤውን ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ የክብር እንግዶች ፣ የካውንስሉ አመራሮች ፣ የአብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚደንቶች እንዲሁም የህብረቱ አባላት በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ በጉዲና ቱምሳ ሁለንታናዊ የስልጠና ማዕከል አካሂዷል።
መርሃ ግብሩን ፓስተር አስፋው በጸሎት ካስጀመሩ በኋላ አምልኮተ እግዚአብሔር ተከናውኗል። በመቀጠልም በሲዳማ ክልል ወንጌል ለዓለም ፍጥረታት ቤተ ክርስቲያን ባለ ራዕይ እና ፕሬዚደንት እንዲሁም የእምነት አባት የሆኑት ሐዋሪያ ዳኒሶ ሉምቤ በሲዳመኛ ቋንቋ መልዕክታቸው አስተላልፈው ኅብረቱን ባርከዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ምክትል ፕሬዚደንት የሆኑት ሐዋሪያ ዩሃንስ ግርማ የእግዚአብሔር ቃል አካፍለዋል።
የኢትዮጵያ አንድነት በክርስቶስ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያን ኅብረት ሰብሳቢ እና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ስራ አስፈጻሚ አመራር ሐዋሪያ እዩኤል አብርሃም ጠቅላላ ጉባኤውን አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግግር አድርገዋል። በመቀጠልም የኅብረቱ ፕሬዚደንት ታምሩ ዋቸጎ እንዲሁም የህብረት ጠቅላይ ጸሐፊ ሐዋሪያ ተሰማ ሀብተወልድ ለህብረቱ አባላት እና ተጋባዝ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ እንዲሁም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመቀጠልም የህብረቱ ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር አማኑኤል አብርሃም የተገኙ የክብር እንግዶችን ለህብረቱ አባላት መልዕክት እንዲያስተላልፉ ጋብዘዋል።
የኅብረቱ ዋና ሰብሳቢ እና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ስራ አስፈጻሚ አመራር የሆኑት ሐዋሪያ እዩኤል አብርሃም በንግግራቸው ለተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም ለህብረቱ አካላት እንኳን አደርሳችሁ ብለው በዛሬው ጉባኤ ኅብረቱ ለ5 አመታት የሚጠቀምበትን ስትራቴጂ ካለፉት ሪፖርቶች በመነሳት እንዳጸደቁ እንዲሁም ለሁለት አመታት የተስሩቱ የክንውን ሪፖርት እንደሚቀርብ ተናግረው እግዚአብሄር እንዲሁም የተገኙ የክብር እንግዶችን አመስግነዋል።
የህብረቱ ምክትል ፕሬዚድንት የሆኑት ዶከተር አማኑኤል አብርሃም የዛሬውን ጉባኤ አስመልክቶ ኅብረቱ እየሰራ ስለሚገኝባቸው ዘርፎች ተናግረው በዝግጅቱ ላይ የተገኙ አካላትን አመስግነዋል።
የኅብረቱ ጠቅላይ ጸሃፊ የሆንቱ ሐዋሪያው ተሰማ ሀብተወልድ በእለቱ ትልልቅ ውሳኔዎችን እንዳሳለፉ ተናግረዋል።

❤1