በአምፕሊፋይ 2025 በተዘጋጀው የጀማ የወንጌል ስብከት ፕሮግራም አማካኝነት ከ1,200 በላይ ሰዎች ጌታን እንደግል አዳኛቸው አድርገው መቀበላቸው ተገለጸ።
በአሜሪካ ፣ አርካንሳስ ግዛት ፣ ሳሊን አውራጃ በአምፕሊፋይ 2025 የተዘጋጀው የክርስቲያኖች የሙዚቃ ፌስቲቫል ላይ ከ45,000 በላይ ሰዎች ተገኝተዋል። ይህም የአምፕሊፋይ የክርስቲያን የሙዚቃ ፌስቲቫልን በሀገሪቱ ከሚደረጉ መንፈሳዊ የሙዚቃ ፌስቲቫሎች በግዝፈት አቻ የማይገኝለት ያደርገዋል።
በፐልስ ኢቫንጀሊዝም የተዘጋጀው እና በወንጌላዊ ኒክ ሆል የተመራው የሁለት ቀን ፕሮግራም ፤ አምልኮን፣ የእግዚአብሔር ቃል ስብከትን እንዲሁም የወንጌል ስርጭትን ያካተተ ሲሆን በወጣቱ ትውልድ ላይ መንፈሳዊ መነቃቃትን ለመፍጠር ያለመ ነው።
ፕሮግራሙን በቀጥታ ስርጭት በተለያዩ አማራጮች የተከታተሉትን ሰዎች ጨምሮ አጠቃላይ ፕሮግራሙን የተከታተሉ ሰዎች ከ67,000 በላይ እንደሆነ የሚገመት ሲሆን ይህም በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካውያን ዘንድ ለመንፈሳዊ ነገር ያለውን ረሃብ የሚያሳይ እንደሆነ ተጠቅሷል።
ያሳደረው መንፈሳዊ ተጽዕኖም የማይካድ እንደሆነ የተነሳ ሲሆን ከ1200 በላይ ሰዎች በሁለቱ ቀን ፕሮግራሞች ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛቸው አድርገው ለመቀበል ወስነዋል። የፕሮግራሙ አዘጋጆችም የፕሮግራሙ ዓላማ “ኢየሱስን በብዙዎች ዘንድ ማሳወቅ” እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን ወጣቶችን እና መሪዎችን በጸሎት ፣ በእቅበተ እምነት እና በወንጌል ስርጭት ለማስታጠቅ ያለመ እንደሆነም ተናግረዋል።
አምፕሊፋይ 2025 ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በአብዛኛው የተገኙት ወጣቶች መሆናቸውም የአሜሪካ ወጣቶች ለቤተ ክርስቲያን ያላቸው አመለካከት እየተለወጠ ለመምጣቱ መርሃ ግብሩ አስተዋጽዖ እንዳደረገ ማሳያ ነው ተብሎለታል። የፕሮግራሙ አዘጋጅ ኒክ ሆልም ‘ይሄ ትውልድ ከኢየሱስ የሚሸሽ ሳይሆን ወደ ኢየሱስ የሜሮጥ ነው።” በማለት ተናግረዋል።
መረጃውን ከሲቢኤን ኒውስ አገኘነው
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ

🔥2❤1
41 ቤተ ክርስቲያናት የተሳተፉበት ናሽናል ዩዝ ኮንፍረንሥ በኦክላሆማ ዩኒቨርስቲ መካሄዱ ተገለጸ።
73ኛ ብሔራዊ የወጣቶች ኮንፍረንስ ከ400 በላይ ወጣቶች እና 100 ጎልማሶች የተገኙበት ሲሆን በያዝነው የፈረንጆች አመትም በኦክላሆማ ተካሂዷል። ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ሲሥታፉም በባለፈው አምስት አመታት ውስጥ ይሄ ከፍተኛው ቁጥር ነው።
በ16 ግዛቶች ከሚገኙ 41 ቤተ ክርስቲያኖች የተወጣጡ ወጣቶች በኮንፍራንሱ ላይ የተገኙ ሲሆን ኮንፍረንሱም አምልኮን፣ ጨዋታዎችን እንዲሁም መንፈሳዊ መዋቅር የተደረገበት ነበሩ።
የኦክላሆማ ግዛት ሴናተር የሆኑት ኒኪ ናይስ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ፕሮግራሙን የከፈቱት ሲሆን ወጣቶች በእምነታቸው ጠንካራ እንዲሆኑና ወደ ነበሩበት ማህበረሰብ ሲመለሱም እውነተኛ ክርስቲያናዊ ማንነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል።
የኮንፍረንሱ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት ራሞን ሆህሪጅ በተለያዩ ቤተ እምነቶች መካከል ጠንካራ የሆነ ግንኙነት ሊኖር እንደሚገባ ተናግረዋል።
በከሰዓት በነበሩት ፕሮግራሞች ላይ ብዙ ወጣቶች መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲታደስ ወደ መድረክ ሲመጡ የተስተዋሉ ሲሆን “ወጣት እንዴት ልቡን ይጠብቃል?” የተሰኘው ዝማሬ በተደጋጋሜ እንደተዘመረ ተገልጿል።
መረጃውን ከክርስቲያን ክሮኒክልስ ድረ ገጽ አገኘነው።

❤7
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ከቀደምት አገልጋዮች አንዱ የሆኑት ፓሰተር ፍቃዱ ኦፍጋ ከዚህ አለም ድካም አረፉ።
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ከቀደምት አገልጋዮች አንዱ የሆኑት እና በቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተክርስትያን ሲያገለግሉ የነበሩት ፓሰተር ፍቃዱ ኦፍጋ ከዚህ አለም ድካም አርፈዋል።
መጋቢ ፍቃዱ ግማሽ ክፍለ ዘመን የዘለቀው አገልግሎታቸው የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ ከምስረታዋ ጀምሮ አስከ ዛሬ ድረስ በጸሎት ፤ በወንጌል ሰባኪነት ፤ በመጋቢነት በማግልገል ከብዙዎች ጋር ስለወንጌል ዋጋ የከፈሉ የወንጌል አርበኛ ነበሩ።
ነሐሴ 12፣ 2017 ዓ.ም የአስክሬን ሽኝት ስነስርዓት በቀጣና ሁለት ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተክርስትያን የተከናወነ ሲሆን የቀብር ስነ ስርዓቱም በዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን መካነ መቃብር ተከናውኗል።
ኢቫንጃሊካል ቴሌቪዥን በመጋቢ ፍቃዱ ዜና እረፍት የተሰማውን ሃዘን እየገለጸ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል።

❤4🙏3
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ክልሎች ጠቅላላ ጉባኤዎቻቸውን አካሄዱ።
በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የወንጂና አካባቢው ጊዜያዊ ክልል፣ አዋሽ ሸለቆ ክልል፣ የደቡብና ሰሜን አዳማ ክልሎች እንዲሁም የምስራቅ ኢትዮጵያ ክልል ከነሃሴ 9-11/2017 ዓ.ም የክልል ጠቅላላ ጉባኤዎችን አካሂደዋል።
በክልሎቹ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ከዋናው ቢሮ በተወከሉ ኃላፊዎች በ2016 ዓ.ም በተሻሻለው ውስጠ ደንብ ላይ ገለጻ ሲደረግ የ2017 ዓ.ም ሪፖርትና የ2018 ዓ.ም እቅድ በክልሎቹ ዋና ጸሐፊዎች ቀርቧል። እንዲሁም የክልል ዋና ጸሐፊና አስተዳደር መሪዎች ምርጫ ተከናውኗል።
መረጃው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው።

❤10