EECMY Youth Ministry
1.83K subscribers
3.51K photos
8 videos
269 links
Fellowship - Discipleship - Evangelism

1Thimothy 4:12

This is the official telegram channel of EECMY Head Office - Youth Ministry
Download Telegram
የልጆች እና የወጣቶች ማስተማርያ መጽሐፍት ማዳረስ- በደቡብ ሲኖዶስ- ዲላ
===
''የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።'' 2ጢሞቴዎስ 3:16-17

-ልጆችን እና ወጣቶችን በሁለንተናዊ መልኩ ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጁ መጽሐፍት
-ልጆች እና ወጣቶች በእግዚአብሔር ቃል እውቀት እንዲያድጉ: ከስህተት ትምህርት እንዲጠበቁ: በጥሩ ስነ ምግባር እንዲታነጹ: በውስጣቸው ያለውን ዕምቅ ችሎታ እና ጸጋ አውቀው; አሳድገው ለትውልድ በረከት እንዲሆኑ የሚረዱ የተለያዩ መጽሐፍትን የማዳረስ ስራ በቤተክርስቲያኒቱ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ እና በቤተክርስቲያናችን የምስራች ድምጽ የመገናኛ ዘዴዎች በጋራ በመሆን በየሲኖዶሱ በሚደረጉት የስልጠና እና የኮንፈረንስ ፕሮግራሞች እያዳረሱ ይገኛሉ።
👉የልጆች ማስተማርያ መጽሐፍት (ከ4-12ዓመት)
👉በተለያዩ ርዕሶች የተዘጋጁ ለወጣቶች አገልግሎት የሚሆኑ
👉በአጠቃላይ ለአገልጋዮች እና ለአገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ መጽሐፍትን መጽሐፍትን በመካነ ኢየሱስ ዋና ጽ/ቤት እና በተለያዩ የምስራች ድምፅ መጽሐፍት መደብር ማግኘት ይችላሉ::

(በፎቶው የምታየው: የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት ክፍል ከየምስራች ድምጽ እና የመገናኛ ዘዴዎች ጋር በመተባበር በዲላ ከተማ (በደቡብ ሲኖዶስ) የልጆች ማስተማርያ መጽሐፍትን: ለወጣቶች አገልግሎት ጠቃሚ መጽሐፍትን እና ሌሎች ተጨማሪ የተለያዩ መጽሐፍቶችን ወደ እያንዳንዱ ማ/ም የማዳረስ ስራ ሲሰራ ነው:: ይሄ እንቅስቃሴ በየሲኖዶሶች ተጠናክሮ ይቀጥላል።)
👇👇👇
መጽሐፎቹን ለማግኘት እና
ለበለጠ መረጃ:
0911424091/0911249368 የምስራች ድምጽ

@eecmyyouthministry
ልጆች እና ወጣቶች ላይ መስራት በዛሬዋና በነገዋ ቤ/ክ ላይ መስራት ነው!
The SundayService@EECMY; #Dilla Congregation
===
"ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም" እንደሚለው የእግዚአብሔር ቃል (ምሳሌ 22:6): ልጆችን በትክክለኛው እና በእውነተኛው የዕድገት አቅጣጫ ለመምራት የልጆች አገልግሎትን በሚገባ ማደራጀት: የልጆች መምህራንን መደገፍ: እንዲሁም ቤተሰብን በአገልግሎቱ ማሳተፍ አስፈላጊ እና ወሳኝ ነው::

-ልጆች እና ወጣቶች የዛሬ/የአሁን እና የነገ/የወደፊት ቤተክርስቲያን ናቸው::
-ልጆች እና ወጣቶች የሌሉባት ቤተ ክርስቲያን የሞተች ናት::
-ነባሩን እና የሚመጣውን ውስብስብ ዓለም (ዘመናዊነት) እንዲቋቋሙ እና እንዲያልፉ በጊዜው በቃሉ እውነት ማስታጠቅ አስፈላጊ ነው::
-ልጆች ከአዋቂዎች የበለጠ በቀላሉ የሚነኩበት የልጅነት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት በጣም አስፈላጊ ስለሆኑ ትኩረት ሰጥቶ: ቀድሞ በእነርሱ ላይ መስራት አስፈላጊ ነው::

"ልጆች ሆይ፥ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ፥ ይህ የሚገባ ነውና።መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር፤ እርስዋም የተስፋ ቃል ያላት ፊተኛይቱ ትእዛዝ ናት። እናንተም አባቶች ሆይ፥ ልጆቻችሁን በጌታ ምክርና በተግሣጽ አሳድጉአቸው እንጂ አታስቆጡአቸው።" ኤፌ. 6:1-4

Equipping Family in a Holistic Way (Children, Youth & Parents)

📷: EECMY Dilla Congregation Media

#EECMY #SouthSynod #Dilla #Leadership #Training #Children #Youth #Family
''መጽሐፍ ቅዱስ ካልሰጣችሁን አታልፉም...''

'KITAABA QULQULLUU YOO NUUF KENNITANE MALEE HIN DABARTANU...'

@eecmyyouthministry