EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
135K subscribers
18.8K photos
160 videos
79 files
10.4K links
Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)
Download Telegram
የሠራተኛው ትግል ከኢንዱስትሪ አብዮት እስከ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ስጋት
*************

ኢንዱስትሪ እየተስፋፋ የነበረበት 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሠራተኛው በርካታ የመብት ጥያቄዎችን ያነሳ የነበረበት ጊዜ ነበር፡፡ ከነዚህ ጥያቄዎች መካከልም የተመጣጣኝ ከፍያ፣ የሥራ ሰዓት፣ የመደራጀት እና ሌሎች ይገኛሉ፡፡

በሥራ ላይ በሚደርስ አደጋ ሕይወትን ማጣት፣ አካል መጉደል፣ ለዘላቂ የጤና ችግር መዳረግ እና ሌሎች ለሰው ልጆች ምቹ ያልሆኑ ሁኔታዎች ጥያቄው መሰረታዊ እንዲሆን ማድረጋቸውን የሠራተኛውን ትግል የሚያወሱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ሠራተኞች ትግላቸውን ቀጥለው ምቹ ባልሆነ የሥራ አካባቢ ከ10 እስከ 16 ሰዓታት የነበረው የሥራ ሰዓት 8 ሰዓት ብቻ ሆኖ የሙሉ ቀን ደመወዝ እንዲከፈላቸው መጠየቅ ቢጀምሩም፣ የዘመኑ አሠሪዎቻቸው ግን ለጥያቄው ምላሽ መስጠት አልፈለጉም ነበር፡፡

ይህ የከበርቴዎች ለሠራተኛው ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት ግን ሠራተኞች የበለጠ ተደራጅተው ጥያቄያቸውን እንዲገፉበት አደረጋቸው:: ነገር ግን ቀጣሪዎቹ በማይመች አካባቢ እና የአየር ሁኔታ ውስጥ በቀን ለረዥም ሰዓታት በማሠራት ከፍተኛ ትርፍ ማጋበስ የለመዱ በመሆናቸው በቀላሉ ጥያቄዎቹን ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡

በሠራተኛው እንቅስቃሴ የተበሳጩት እና መጪው ሁኔታ ያሳሰባቸው አሠሪዎች “አድማ ቀስቅሳችኋል፤ ምርታማ መሆን አልቻላችሁም፤ እኛ በምንፈልጋችሁ ሁኔታ እየሠራችሁ ስላልሆነ አንፈልጋችሁም” በማለት በርካታ ሠራተኞችን ከሥራ ማሰናበት ጀመሩ::
https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=6587
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለመላው ኢትዮጵያውያን የኩራት ምንጭ የሆነ ታላቅ ተቋም ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
****************

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ የአስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ቡድን በኢፌዴሪ አየር ኃይል ጉብኝት አድርጓል።

በጉብኝቱ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ አየር ኃይል በላቀ የስራ ትጋትና ጥራት እንደ ሀገር ያለንን ሀብት ተጠቅሞ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል አንዱ ማሳያ የሆነ ተቋም ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በተለይም ከተጣለበት ሀገራዊ ተልዕኮ ባሻገር በግብርናው ልማት በኩል ቀድሞ አላግባብ ጥቅም አልባ ተደርጎ የነበረውን የተቋሙን መሬት ወደ ልማት በመቀየር ያስመዘገበው ታላቅ ስኬት በሀገር ደረጃም አርዓያነት ያለው አኩሪ ስራ መሆኑን ተናግረዋል።

በሰላም ወጥቶ ለመግባትም ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገር ለተያዘው የልማት ጉዞ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ያፀናው ሰላም ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለመላው ኢትዮጵያውያን የኩራት ምንጭ የሆነ ታላቅ ተቋም ነው ብለዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0WkygJR84sG8g9meW4pH2SJkmQF9fWrTVtq95ScQECGqUT73LrUQnJp96qtyMHWf6l
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ በአከራይም ሆነ በተከራይ ላይ ጫና በማይፈጥር መልኩ ወደ መሬት እንዲወርድ እንሰራለን፡- ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ
******************

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መጋቢት 24 ቀን የጸደቀው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ መጽደቁን ተከትሎ ለተግባራዊነቱ እየተሰራ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ገለጸ።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ከኢቲቪ 57 ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ የዜጎችን መሰረታዊ የመኖሪያ ቤት ችግር ዘላቂ በሆነ መልኩ ለመፍታት በተጠናከረ መልኩ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ነገር ግን ዜጎች ከገጠር ወደ ከተማ የሚያደርጉት ፍልሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ የመኖሪያ ቤት ፍላጎትም ጨምሯል ብለዋል።
https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=6588
የትግራይ ክልል ክለቦች ከ2017 ጀምሮ ከጦርነቱ በፊት ወደነበሩበት ሊግ ተመልሰው እንዲወዳደሩ ውሳኔ ተላለፈ
********************

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ፥ የትግራይ ክልል ክለቦች ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ከጦርነቱ በፊት ሲወዳደሩበት ወደነበረው ሊግ ተመልሰው እንዲወዳደሩ ውሳኔ አሳልፏል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለሚመለከታቸው አካላት በደብዳቤ ያሳወቀ ሲሆን፤ ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ/ማ በተላከው ደብዳቤም ሊጉ በ2017 የወድድር ዘመን በ19 ቡድኖች መካከል ተደርጎ 5 ቡድኖች ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲወርዱ በማድረግ በ2018 ከዚህ ቀደም ወደነበነረበት 16 ክለቦች እንዲመለስ አቅጣጫ መቀመጡን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
https://www.facebook.com/EBCSPORT/posts/pfbid02anFTwKycGrc3J2U321yvXynymXDvW95D52mgPdTbMS8mabEMydbhAKR5DsKYFPwLl
Live stream finished (1 day)
አፍሪካ እና አውሮፓ በባቡር ትራንስፖርት ሊገናኙ ነው
***********************

ለ2030ው የዓለም ዋንጫ አፍሪካ እና አውሮፓ በባቡር ትራንስፖርት ሊገናኙ መሆኑ ተገለጸ።

በስፔን ፖርቹጋል እና ሞሮኮ አስተናጋጅነት እንደሚካሄድ በሚጠበቀው የ2030ው ዓለም ዋንጫ አፍሪካ እና አውሮፓ በባቡር ትራንስፖርት ለማገናኘት ታቅዷል ተብሏል።

ሞሮኮ እና ስፔን በጋራ የባቡር ትራንስፖርት መስመሩን ለመገንባት ጥረት መጀመራቸው ተገልጿል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02VZjmZwMtgvQ63PE94kQ2osY6bijbeac2EcEh4FoAbWFnHU4scpy9C6h6cuaLwCm7l
የዕለቱ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ
ለትንሳኤ በዓል ወደ ሀገር እየገቡ ላሉ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን አቀባበል እየተደረገላቸው ነው
****************

ለትንሳኤ በዓል ወደ ሀገር እየገቡ ላሉ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት አቀባበል እየተደረገላቸው ነው።

በአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ላይ የቱሪዝም ሚንስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

"ባክ ቱ ዩር ኦሪጅንስ" የሚል ስያሜ የተሰጠው እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በውጭ ለሚኖሩ የ2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ያቀረቡት ጥሪ በሦስት ዙሮች የሚካሄድ ነው።

በዚህም ከታህሳስ 20 እስከ ጥር 30 በመጀመሪያው ዙር "ከብዝኀ ባህል መሰረትዎ ጋር ይገናኙ" በሚል በተሰየመው መርሐ-ግብር ወደ ሀገራቸው ገብተው እንደነበር ይታወሳል።

አሁን ደግሞ "ታሪካዊ መሰረትዎን ይወቁ" በሚል በተሰየመው መርሐ-ግብር በሁለተኛ ዙር ወደ ሀገር እየገቡ ይገኛሉ።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid03Bva9RaBMiwPmCskX4VC7U1KvpFCChEdEe37qxTEv7Hhpym46yhZrtfpRmt3QwGwl
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ለ1 ሺህ 455 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ
******************

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 455 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፥ መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ የክልሉ መንግሥት የይቅርታ አዋጁን መስፈርት ላሟሉ 1 ሺህ 455 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት፥ ይቅርታ የተደረገላቸው የሕግ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ሥነ-ምግባር ያሳዩ እና በሕግ የተደነገገውን የይቅርታ መስፈርት ማሟላታቸው በክልሉ የይቅርታ ቦርድ ተጣርቶ የቀረቡ ናቸው።

https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=6595
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የ'ገበታ ለሀገር' ፕሮጀክቶችን ለየክልሉ አስረከበ
********************

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለተከናወኑት የ'ገበታ ለሀገር' ፕሮጀክቶች ዛሬ አንድ ሌላ ምዕራፍ ተከናውኗል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዛሬ ባዘጋጀው መርሃ ግብር ፕሮጀክቶቹን ለአማራ፣ ለኦሮሚያ እና ለደቡብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስረክቧል።

በተጨማሪም በገበታ ለሀገር የተገነቡ ሎጆችን ስራ የማስኬድ ተግባርን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስካይ ላይት ሆቴል ተቋሙ በኩል እንዲወጣ የስምምነት ፊርማ ሥነሥርዓት ተካሂዷል።

ከአራቱ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ሶስቱ (ሃላላ ኬላ ሎጅ፣ ጨበራ ጩርጩራ የዝሆን ዳና ሎጅ እና ወንጪ ኢኮ ሎጅ) በቅርቡ መመረቃቸው የሚታወስ ሲሆን፤ የጎርጎራ ፕሮጀክት ስራም በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

በጠቅላይ ሚኒስሩ ከፍተኛ ትኩረት እና አመራር የተከናወነው የ’ገበታ ለሀገር’ ስራ የብሔራዊው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አንዱ ማዕዘን የሆነውን ቱሪዝምን የማሳደግ ዓላማ ያለው ነው።

እነዚህ ፕሮጀክቶች በመጀመሪያው ፋይናንስ የማሰባሰብ ምዕራፍ የኅብረተሰቡን ድጋፍ በሰፊው ያሰባሰቡ፣ በግንባታቸው ምዕራፍ ግዙፍ የስራ ዕድል የፈጠሩ ብሎም ታላላቅ የመሰረተ ልማት ስራዎች እንዲከናወኑ በር የከፈቱ ናቸው።

በፈጠራ የተሞላ የፕሮጀክት ስራ እና አስተዳደር እና ፈጣን አፈፃፀም ምን ሊመስል እንደሚችል ማሳያም ሆነዋል።

ቀጣይ የስራ ማስኬድ እና ማስተዳደር ተግባሩ ለብሔራዊ ሰንደቅ ተሸካሚው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሃላፊነት መሰጠቱም የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ከማስቻሉም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻነት ትውውቅ ከፍ ያለ ዕድል እንደሚፈጥር ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።