EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
136K subscribers
20.4K photos
168 videos
79 files
10.6K links
Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ255 ሺህ የመዲናዋ ነዋሪዎች ማዕድ አጋራ
***************

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ255 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች እና በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የመዲናዋ ነዋሪዎች ማዕድ አጋርቷል።

የማዕድ ማጋራቱ የተከናወነው በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት በኩል ሲሆን፤ ዓላማውም ነዋሪዎቹ በዓሉን በፍሰሐ እንዲያሳልፉት መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

ሰርተው ካገኙት ለወገኖቻቸው ማካፈልን ባሕል ላደረጉ የከተማዋ ልበ ቀና ባለሀብቶች እና በጎ ፈቃደኞች ከንቲባ አዳነች በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባህርዳር ገቡ
******************

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ ባህርዳር ገብተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባህርዳር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ካቢኒያቸው እንዲሁም የከተማዋ ከንቲባ እና ህዝብ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ በባህርዳር ለተደረገላቸው የሞቀ አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል።
ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የትንሣኤ በዓል ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖች ማዕድ አጋሩ
*************

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የ2016 ዓ.ም የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ለሚኖሩ አቅመ ደካሞችና በዝቅተኛ ኑሮ ላይ ለሚገኙ ወገኖች ማዕድ አጋርተዋል።

ፕሬዚዳንቷ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው፤ መደጋገፍ የዕለት ተለት ተግባር መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

መጪውን የትንሳኤ በዓል ከአቅመ ደካማ ወገኖች ጋር አብሮ ማሳለፍ እንደሚገባም መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ድጋፍ የተደረገላቸው የወረዳው ነዋሪዎች በበኩላቸው የትንሳኤ በዓልን ተደስተው እንዲውሉ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ላደረጉላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።
• “በወተት እና የወተት ተዋፅኦ ምርቶች ላይ ያለው የዋጋ ጭማሪ ቢታይልን”- የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

• “የምርቶቹን ዋጋ ማረጋጋት ቀጣይ የቤት ስራዬ ነው“- የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ
**********************

የበዓል ወቅት መድረሱን ተከትሎ ኢቢሲ በተመረጡ የመዲናዋ ገበያዎች የመሰረታዊ ሸቀጦች የዋጋ ቅኝት አድርጓል፡፡

በቅኝቱ ወቅት ያነጋገራቸው ሸማቾች በአትክልት እና ፍራፍሬ ላይ የታየው የዋጋ መረጋጋት ቀጣይነት እንዲኖረው ጠይቀዋል፡፡

በአንጻሩ የወተት እና የወተት ተዋፅኦ ምርቶች ላይ ያለው የዋጋ ጭማሪ መፍትሔ እንዲበጅለትም አሳስበዋል፡፡

ኢቢሲ ሳይበር በቅኝቱ፤ ቅቤ በአማካኝ 950 ብር፣ ቆጮ በኪሎ 130 ብር፣ የፈረንጅ እንቁላል 8 ብር፣ የሐበሻ እንቁላል 14 ብር፣ አይብ ከ550 ብር ጀምሮ፣ የሐበሻ ዶሮ ከ1 ሺህ ብር ጀምሮ፣ የፈረንጅ ዶሮ ከ500 ብር ጀምሮ እንዲሁም በግ ከ8 ሺህ ብር ጀምሮ በመሸጥ ላይ መሆናቸውን ተመልክቷል፡፡https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0jBSMXtPV18jSwy8yKJxq5pwLqeYY5WSwYK5RPAZ9t3SEZj5CFf2tZAi4hrWFNYVVl