EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
136K subscribers
20.5K photos
169 videos
79 files
10.6K links
Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)
Download Telegram
"በደቡብ ወሎ ዞን በወረኢሉ ወረዳ በ620 ሄክታር ላይ የለማው ስንዴ አመርቂ ውጤት አሳይቷል።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ከነዋሪዎች ጋር በቅርበት የሚሰራ የፖሊስ ተቋም ለማደራጀት የጀመርነው ስራ ዉጤታማ መሆኑን ተመልክተናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
***************

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ፖሊስ እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርምና የተቋም ግንባታ ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ከንቲባዋ ይህን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ በዛሬ ጉብኝታችን የከተማችንን ቁመና የሚመጥን በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂ እና በሎጀስቲክ የተደራጀ፤ ከነዋሪዎች ጋር በቅርበት የሚሰራ የፖሊስ ተቋም ለማደራጀት የጀመርነው ስራ ዉጤታማ መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል።

እስካሁን ለተገኘው ውጤት ምስጋና ያቀረቡት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ በቀጣይም የሪፎርም ስራው እስከታችኛው መዋቅር እንዲደርስ እና የአገልጋይ ፖሊስ ዲሲፕሊን እየተጠናከረ እንዲሄድ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
በአምስተርዳም ማራቶን አትሌት የዓለምዘርፍ የኋላው ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈች
***************

በአምስተርዳም ማራቶን አትሌት የዓለምዘርፍ የኋላው የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፋለች።

አትሌቷ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ50 ሴኮንድ በማጠናቀቅ በአትሌት አልማዝ አያና ተይዞ የነበረውን የቦታውን ክብረወሰን አሻሽላለች።

በሌላ በኩል በወንዶች ማራቶን አትሌት ፀጋዬ ጌታቸው ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቋል፡፡

አትሌት ፀጋዬ ርቀቱን 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ37 ሴኮንድ በመግባት ነው ማሸነፍ የቻለው፡፡