ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹
2.84K subscribers
2.46K photos
76 videos
2 files
342 links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል

DW AMHARIC NEWS IS A GLOBAL NEWS AND INFORMATION CHANNEL FROM A GERMAN INTERNATIONAL BROADCASTER DEUTSCHE WELLE (DW)
Download Telegram
በሐረሪ ክልልና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ፦

- በሐረሪ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዟ የተረጋገጠው የሀኪም ወረዳ ነዋሪ የሆነች የ37 ዓመት ሴት ስትሆነን በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረች ናት።

- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኮቪድ-19 የተያዘው ግለሰብ ከአዲስ አበባ ወደ አሶሳ በተደረገው በረራ በአሶሳ ህዳሴ ኤርፖርት በተወሰደው የናሙና ምርመራ የተገኘ ሲሆን ግለሰቡ የጉዞ ታሪክም ሆነ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለሌው ነው።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
በኬንያ 72 የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል!

በኬንያ እስካሁን በትንሹ 72 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የሀገሪቱን የጤና ሚኒስቴር ጠቅሶ ሲጂቲኤን /CGTN/ ዘግቧል፡፡

የጤና ዋና አስተዳዳሪ ጸኃፊ ዶክተር ረሺድ አማን በግንባር ቀደምነት ሲሳተፉ የነበሩ 72 የጤና ባለሙያዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አስታውቀዋል፡፡

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል አስራ ዘጠኙ በተለያዩ የህክምና መስጫ ተቋማት ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ዶክተር ረሺድ አማን ተናግረዋል።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
የኢትዮጵያ የአስር ዓመት መሪ የልማት እቅድ ይፋ ሆኗል!

የአስር ዓመቱ መሪ የልማት እቅድ ዛሬ ለሚኒስትሮችና ለክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ፍፁም አሰፋ በአገሪቱ የሥራ አጥ ቁጥር ምጣኔን ከዘጠኝ በመቶ በታች ማድረስ የዕቅዱ ዋነኛ ዓላማ ነው ብለዋል፡፡

ኮሚሽነሯ አክለውም በየዓመቱ አንድ ነጥብ 3 ሚሊዮን ለሚሆኑ ሰዎች አዳዲስ ሥራ በመፍጠር ምርታማነትን በመጨመር የዋጋ ንረትን ለመቀነስ መታሰቡን አመልክተዋል፡፡ መሪ እቅዱም ከክልሎችና የተለያዩ ሴክተሮች ከፕላንና ልማት ኮሚሽን ጋር እንዲናበቡ ተደርጎ መዘጋጀቱንም ኮሚሽነር ፍፁም ተናግረዋል፡፡

በውይይት መድረኩ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሚቀጥሉት አስር ዓመት የኢትዮጵያን የነፍስ ወከፍ ገቢ በማሳደግ ኢትየጵያን አስተማማኝና መካከለኛ የኢኮኖሚ ገቢ ያላት አገር ለማድረግ የአስር ዓመት የብልጽግና ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡

መሪ እቅዱ አቅምን በማሳደግ በተለይ በሰው የልማት ሀይል ጥራት ተኮር የሆኑ ሥራዎች ላይ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት እንደሚያስችልና ከአገር የኢኮኖሚ አቅም ባሻገር ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
27k ቻናል super best view
ፊት ለፊት መግዛት የሚፈልግ በዚህ @dwamharicnewsbot ያናግሩን
ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹 pinned «27k ቻናል super best view ፊት ለፊት መግዛት የሚፈልግ በዚህ @dwamharicnewsbot ያናግሩን»
#DrLiaTadesse

በሀገራችን የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ታማሚ ከተገኘ ዛሬ ሶስተኛ (3) ወሩን አስቆጥሯል።

በመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ብዛት 250 የነበረ ሲሆን ባለፈው አንድ ወር ብቻ 2,420 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ይህም ማለት ባለፈው 1 ወር ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ጋር ሲነፃፀር በ10 እጥፍ ጨምሯል።

በመሆኑም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኙ መስፋፋት ግምት ወስጥ በማስገባት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባናል።

መከላከል ከመታከም ይቀላል ፣ ቤት መቆየትም ሆስፒታል ከመተኛት ይሻላል ፣ የአፍና የአፍንጫን መሸፈኛ አድርጎ መተንፈስ በማሽን ከመተንፈስ ይልቃል።

ስለሆነም እነዚህን አንዲሁም ሌሎችን የቫይረሱን መከላከያ መንገዶች ሳንዘናጋ በመተግበር እራሳችንንና የምንወዳቸውን ከኮሮና ቫይረስ በሽታ እንጠብቅ።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
250 ኢትዮጵያዊያን ከኩዌት ወደ አገራቸው ተመለሱ!

250 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ዛሬ ሰኔ 4 ቀን 2012 ዓም ከኩዌት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል። ዜጎቻችን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከውጭ ጉዳይ እና ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል። ባሳለፍነው ማክሰኞ 259 ዜጎች ከኩዌት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል፡፡

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
እየተካሄደ ባለው ድርድር ግብጽ አራት ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጣለች ተባለ!

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ ከማክሰኞ ጀምሮ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይ ዳግም ከሥምምነት ለመድረስ አሜሪካን፣ የዓለም ባንክን እና ደቡብ አፍሪካን በታዛቢነት አስቀምጠው ድርድር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ዛሬ #AlharamOnline የግብጽ የመስኖ ሚኒስቴር ቃል አቀባይን ጠቅሶ እንደዘገበው በዚህ ድርድር ላይ ግብጽ አራት ቅድመ ሁኔታዎችን እንዳስቀመጠች ገልጸዋል፡፡

1. በድርድሩ ስምምነት እስኪገኝ ድረስ ኢትዮጵያ በግሏ ውሳኔ የውኃ ሙሌቱ ላይ ምንም እንቅስቃሴ እንደማታደርግ ማረጋገጫ እንድሰጥ ግብጽ ትፈልጋለች፣

2. ድርድሩ በተገደበ የገዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቅ ግብጽ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጣለች፡፡ በዚህም ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 6 ድረስ በግድቡ የውሃ ሙሌት እና ዓመታዊ የውሃ አለቃቀቅ ላይ መስማማትን እንደ ሁለተኛ ቅድመ ሀኔታ አስቀምጣለች፣

3. ውይይቱ በዋሽንግተኑ የውይይት ኃሳቦች ላይ መሰረት ያደረገ እንዲሆን ግብጽ ጽኑ ፍላጎቷን እየገለጸች ነው፡፡ ይህንንም እንደ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጣለች፣

4. በድርድሩ በታዛቢነት የተኙት አካላት ሚናቸው ከታዛቢነት ወደ ከአደራዳሪነት ከፍ እንዲል ግብጽ ትሻለች፡፡

የኢትዮጵያ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ግብጽ የግድቡን ጉዳይ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የጸጥታው ምክርቤት በመውሰድ ውጫዊ የዲፕሎማሲ ጫና ለማሳደር እየሞከረች ነው ብሏል።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
ፈረንሳይ ባዘጋጀችው 1000 የአፍሪካ ስራ ፈጣሪዎች ውድድር 11 ኢትዮጵያውያን አሸነፉ

ውድድሩ በአፍሪካ-ፈረንሳይ ጉባዔ 2020 ዋና ጸሃፊ እና ዲጂታል አፍሪካ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን በመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን፣በኢነርጂ ልማት እና በሌሎችም ዘርፎች የተሰማሩ በርካታ አፍሪካዊ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ተሳትፈውበታል፡፡

ስራ ፈጣሪዎቹ ከአህጉሪቱ 53 ሃገራት የተውጣጡ ሲሆኑ ውድድሩን ካሸነፉ 1 ሺ ስራ ፈጣሪዎች መካከል 11ዱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውንም የፈረንሳይ ኤምባሲ የውድድሩን አዘጋጆች ጠቅሶ አስታውቋል፡፡ አሸናፊዎቹ ገንዘብን ጨምሮ የተለያዩ የሙያና የስልጠና ድጋፎችን ያገኛሉ እንደ አዘጋጆቹ ገለጻ፡፡

28ኛው የአፍሪካ-ፈረንሳይ ጉባዔ ባሳለፍነው ሳምንት በፈረንሳይ ቦርዶ ከተማ ሊዘጋጅ እቅድ ተይዞለት የውድድሩ አሸናፊዎች ጉባዔውን እንዲታደሙ ግብዣ ተደርጎላቸውም ነበር፡፡ ሆኖም በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

#AlAin
@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 245 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
#BREAKING

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 245 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,709 የላብራቶሪ ምርመራ 245 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2,915 ደርሷል።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 47 ደረሰ!

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሰባት (7) ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸውና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 47 ደርሷል።

ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ75 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

2. የ70 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው።

3. የ80 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው።

4. የ29 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት።

5. የ48 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት።

6. የ85 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው።

7. የ21 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
በደቡብ ክልል ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች፦

ታማሚ 1 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን ቡራ ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌለው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው።

ታማሚ 2 - የ18 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌለው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው።

ታማሚ 3 - የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌለው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው።

ታማሚ 4 - የ21 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን ቡራ ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌላቸው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው።

ዛሬ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከተረጋገጠው አራቱ (4) ሰዎች ይርጋለም ህክምና ማዕከል እንዲቆዩ ተደርገዋል።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
#TIGRAY

በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሰባት (107) ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 182 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው አስራ አምስት (15) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

ከአስራ አምስቱ (15) መካከል አስሩ (10) የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ፣ ሶስት (3) ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት (ንክኪ) ያላቸው እንዲሁም ሁለት (2) የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ናቸው።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
#AMHARA

በአማራ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ስልሳ ሰባት (167) ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 246 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው ሶስት (3) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

በዛሬው ዕለት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ፦

- አንድ (1) ሰው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታልና አንድ (1) ሰው በደሴ ከተማ በሚገኘው የግል የህክምና ማዕከል አገልግሎት ለማግኘት በሄዱበት ወቅት ናሙና ሲወሰድላቸው ኮቪድ-19 የተገኘባቸው።

- አንድ (1) ሰው ደግሞ በጎንደር ጎሃ ለይቶ ማቆያ ማዕከላት ክትትል ሲደረግላት የነበረች ሴት ናት።

ከፆታ አኳያ ሲታዩ አንድ (1) ወንድ እና ሁለት (2) ሴቶች ሲሆኑ ከ22 እስከ 60 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ይገኛሉ።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot