ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹
2.84K subscribers
2.46K photos
76 videos
2 files
342 links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል

DW AMHARIC NEWS IS A GLOBAL NEWS AND INFORMATION CHANNEL FROM A GERMAN INTERNATIONAL BROADCASTER DEUTSCHE WELLE (DW)
Download Telegram
እየተካሄደ ባለው ድርድር ግብጽ አራት ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጣለች ተባለ!

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ ከማክሰኞ ጀምሮ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይ ዳግም ከሥምምነት ለመድረስ አሜሪካን፣ የዓለም ባንክን እና ደቡብ አፍሪካን በታዛቢነት አስቀምጠው ድርድር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ዛሬ #AlharamOnline የግብጽ የመስኖ ሚኒስቴር ቃል አቀባይን ጠቅሶ እንደዘገበው በዚህ ድርድር ላይ ግብጽ አራት ቅድመ ሁኔታዎችን እንዳስቀመጠች ገልጸዋል፡፡

1. በድርድሩ ስምምነት እስኪገኝ ድረስ ኢትዮጵያ በግሏ ውሳኔ የውኃ ሙሌቱ ላይ ምንም እንቅስቃሴ እንደማታደርግ ማረጋገጫ እንድሰጥ ግብጽ ትፈልጋለች፣

2. ድርድሩ በተገደበ የገዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቅ ግብጽ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጣለች፡፡ በዚህም ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 6 ድረስ በግድቡ የውሃ ሙሌት እና ዓመታዊ የውሃ አለቃቀቅ ላይ መስማማትን እንደ ሁለተኛ ቅድመ ሀኔታ አስቀምጣለች፣

3. ውይይቱ በዋሽንግተኑ የውይይት ኃሳቦች ላይ መሰረት ያደረገ እንዲሆን ግብጽ ጽኑ ፍላጎቷን እየገለጸች ነው፡፡ ይህንንም እንደ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጣለች፣

4. በድርድሩ በታዛቢነት የተኙት አካላት ሚናቸው ከታዛቢነት ወደ ከአደራዳሪነት ከፍ እንዲል ግብጽ ትሻለች፡፡

የኢትዮጵያ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ግብጽ የግድቡን ጉዳይ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የጸጥታው ምክርቤት በመውሰድ ውጫዊ የዲፕሎማሲ ጫና ለማሳደር እየሞከረች ነው ብሏል።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot