DW Amharic
42.7K subscribers
3.21K photos
746 videos
69 files
13.2K links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
በኤች አይቪ ሳቢያ ለህልፈተ ህይወት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ምጥቷል ተባለ
በዓለም ላይ በኤች አይቪ ሳቢያ ለህልፈተ ህይወት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ምጥቷል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለፀ።ድርጅቱ ዛሬ ይፋ ባደረገዉ መረጃ መሰረት በጎርጎሮሳዊዉ 2018 ዓ/ም ከኤች አይ,ቪ ጋር በተያያዘ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 770 ሺህ ነዉ።ይህ የሞት መጠን ከዘጠኝ ዓመት በፊት ከነበረዉ ጋር ሲነፃፀር በአንድ ሦስተኛ መቀነሱን ነዉ የተመለከተዉ። ለዚህም የፀረ-ኤች አይቪ ህክምና ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣት ለሚከሰተዉ ሞት መቀነስ በምክንያትነት ተጠቅሷል።በአንፃሩ ግን በገንዘብ ድጋፍ ማጣት የተነሳ ኤች አይቪ ኤድስን ለመከላከልና በበሽታዉ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ የሚደረገዉ ጥረት አናሳ እየሆነ መምጣቱን ነዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የገለፀዉ።
በዓለም ላይ 38 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ከኤች አይቪ ጋር የሚኖሩ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ ከ23 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የፀረ-ኤች አይቪ ህክምና ይወስዳሉ።
የማክሰኞ ሐምሌ 9 ቀን 2011 የዓለም ዜና

- የጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት የክልሉ ሰባት ቢሮ ኃላፊዎችን ሹመት ዛሬ አጸደቀ። ምክር ቤቱ የክልሉን መገናኛ ብዙሃን እና የመንገዶች ባለስልጣን በዋና ዳይሬክተርነት የሚመሩ ግለሰቦችንም ሾሟል።

- በማዕከላዊ ናይጄሪያ ባለ ሦስት ፎቅ የመኖሪያ ህንጻ ተደርምሶ 13 ሰዎች መሞታቸውን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አስታወቁ። ህንጻው የተደረመሰው በአካባቢው ዶፍ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ ነው።

- አስር የቱርክ መርከበኞች በናይጄሪያ የባህር ጠረፍ በታጣቂዎች መታገታቸው ተነገረ። መርከበኞቹ የታገቱት ከካሜሮን ወደ አይቬሪኮስት በመጓዝ ላይ እንዳሉ ነበር።

- ከኤች. አይ. ቪ ጋር በተያያዘ የሚከሰት ሞት ከዘጠኝ ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጻር በአንድ ሦስተኛ መቀነሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። በሽታውን ለማጥፋት የሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት የገንዘብ ድጋፍ በመጥፋቱ ምክንያት መዳከሙንም ገልጿል።

-የየመን ተፋላሚ ወገኖች አዳጊዎችን አስገድደው ወታደር እንደሚያደርጓቸው አንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አጋለጠ። ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት እንደገለጸው በየመን የእርስ በእርስ ጦርነት ከአንድ ሺህ የሚልቁ አዳጊዎች ተሳትፈዋል።

- ዮርዳኖስ ከሁለት ዓመት በኋላ በኳታር አዲስ አምባሳደር ዛሬ ሾመች። ሹመቱ የሻከረውን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማደስ ያለመ እርምጃ ነው ተብሎለታል።

📻 የዕለቱን ዜና ለማድመጥ ይህንን ማገናኛ (ሊንክ) ይጫኑ 👉 https://p.dw.com/p/3MAVa?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

👉🏾 @dwamharicbot
የፎን ዴር ላየንን የምርጫ ውዝግብ

የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ፎን ዴር ላየን፣ ሳይጠበቅ እና ከተለመደው አሰራር በተለየ ለአዉሮጳ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚደንትነት መታጨታቸው ሲያወዛግብ ከርሟል። ለኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት የታጩት ጀርመናዊት ፎን ዴር ላየን በብቃትም ሆነ በልምዳቸው ለቦታው የሚመጥኑ ስለ መሆናቸው መሪዎቹም ሆኑ ሌሎች አስተያየት ሰጭዎችም ይስማማሉ። ሆኖም ለሃላፊነቱ የተወዳደሩትን እና ያሸነፉትን ወደ ጎን ትተው እርሳቸው በምርጫ ሳይወዳደሩ ለቦታው መታጨታቸው የህብረቱን ዴሞክራሲያዊ አሠራር የሚፃረር አድርገው የሚተቹ ጥቂት አይደሉም።

ከአንጌላ ሜርክል ፓርቲ ከጀርመኑ የክርስቲያን ዴሞክራቶች ህብረት ጋር ተጣምሮ ጀርመንን የሚመራው የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ የርሳቸውን እጩነት አለመቀበሉ ሌላው ችግር ነበር። ፎን ዴርላየን የአውሮጳ ህብረት አባል ሃገራት መሪዎችን ሙሉ ይሁንታ አግኝተው ቢመረጡም ሜርክል ግን የመንግሥታቸው ተጣማሪ ፓርቲ SPD ባለመስማማቱ ድምጽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ሜርክል SPD ከጎናቸው አለመቆሙ ሁኔታውን እንዳከበደባቸው ተናግረው ነበር።

https://p.dw.com/p/3MATk?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

👉🏾 @dwamharicbot
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰኔ 15፣ 2011 ዓም በአዲስ አበባ እና በባህርዳር የተፈጸሙትን ግድያዎች ዛሬ ባወጣው የአቋም መግለጫ አወገዘ። የጋራ ምክር ቤቱ በመግለጫው ችግሮች ሳይባባሱ መፍትሔ መፈለግ ሲቻል መንግሥት ቸልተኝነት አሳይቷል ሲልም ወቅሷል።

https://p.dw.com/p/3MAXB?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

👉🏾 @dwamharicbot
በደቡብ ክልል ለተነሱ የክልል መዋቅር ጥያቄዎች በጥናት የተደገፈ ምላሽ እንደሚሰጥ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) አስታውቋል። ንቅናቄው ይህን ያስታወቀው የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ያካሄደውን ልዩ ስብሰባ ትናንት ሲያጠናቅቅ ባወጣው የአቋም መግለጫ ነው። የንቅናቄውን መግለጫ ተከትሎ አዎንታዊም፣ አሉታዊም አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/3MAXZ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

👉🏾 @dwamharicbot
በበርካታ ሚሊየኖች የሚገመቱ ሰዎችን የሚያስቸግር የማይጋባ ህመም መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፤ ኢፕሊፕሲ ወይም በዘልማድ የሚጥል በሽታ በሚል የሚታወቀውን የጤና እክል። ታማሚዎቹ የሃኪሞች ያላሰለሰ ምክር እንደሚያስፈልጋቸውም ይመክራሉ። ኢፕሊፕሲ ህክምና ሊረዳው የሚችለው የጤና እክል ነው ወይስ የርኩስ መንፈስ ሥራ? ሃኪሞች ምን ይላሉ?

https://p.dw.com/p/3MAYI?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
ድጋፍ እና ስጋት በእጩ ርዕሰ መስተዳድሩ ላይ

ለአማራ ክልል በእጩ ርዕሰ መስተዳድርነት የቀረቡት አቶ ተመስገን ጥሩነህ በስራ ያልተፈተኑ፣ ብቃታቸው አጠራጣሪ እና አካባቢውን በመሩበት ጊዜም አንድም ቀን ህዝብን ያላወያዩ እንደሆኑና ክልሉን በብቃት ይመራሉ የሚል እምነት እንደሌላቸው አስተያየት ሰጪዎች ተናገሩ። የግለሰቡን አቅም ወደፊት የምናየው ይሆናል ያሉም አሉ።

https://p.dw.com/p/3MAbK?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የአውሮጳ ህብረት አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከኢራን ጋር በተደረገው የኒውክለር ስምምነት ቀጣይነት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው ውሳኔዎችን አሳልፈዋል። በውይይቱ አጀንዳ ውስጥ ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ እና ሱዳንም ተካተው ነበር። የህብረቱ የውጭ ጉዳዮች ሃላፊ ፌደሪካ ሞጎሮኒ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።

https://p.dw.com/p/3MAcJ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የሱዳን ተቃዋሚዎች እና የሽግግር ምክር ቤቱን የሚመሩ ወታደራዊ ሹማምንት ሥልጣን ለመጋራት ስምምነት ተፈራረሙ። የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ሊቀ-መንበር ሉቴናንት ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ስምምነቱን ታሪካዊ ብለውታል።
ዳጋሎ ስምምነቱን ከፈረሙ በኋላ «በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እና በታላቁ የሱዳን አብዮት መሪዎች መካከል አዲስ እና ተስፋ ሰጪ ምዕራፍ ከፍቷል» ሲሉ አወድሰዋል። ከተቃውሞ መሪዎች አንዱ የሆኑት ኢብራሒም አል-አሚን በበኩላቸው ፖለቲካዊ ሥምምነቱ መጠናቀቁን አረጋግጠዋል።
ለሱዳን መፃኢ እጣ-ፈንታ ጉል ህ ሚና ይኖረዋል የተባለውን የሥልጣን መጋራት ስምምነት ያቀረቡት የአፍሪካ ኅብረት እና ኢትዮጵያ ናቸው። የአፍሪካ ኅብረት ዋና አደራዳሪ መሐመድ ኢል ሐሲን ሌባት «ወታደራዊው የሽግግር ምክር ቤት እና ጥምረት ለነፃነት እና ለውጥ የተባለው ኃይል ወደ አጠቃላይ ዕርቅ የሚመራ እጅግ ጠቃሚ ስምምነት ላይ ደርሰዋል» ሲሉ ተናግረዋል።
በስምምነቱ መሰረት ሱዳን ምርጫ ከማከናወኗ በፊት ለሶስት አመት ከሶስት ወር የሚያስተዳድር እና 11 አባላት የሚኖሩት ሉዓላዊ ምክር ቤት ይቋቋማል። አምስቱ የምክር ቤት አባላት ከጦሩ ቀሪዎቹ ስድስት አባላት ከሲቪል ዜጎች ይመረጣሉ። ምክር ቤቱን ለመጀመሪያዎቹ 21 ወራት የሚመሩት የጦሩ ተወካዮች ይሆናሉ። ኦማር ሐሰን አል በሽር ከሥልጣን ከተወገዱ ወዲህ በሱዳን የሆነው ሁሉ በገለልተኛ ኮሚሽን እንዲጣራ ሁለቱ ወገኖች ከስምምነት ደርሰዋል።
የዎላይታ ዞን ምክር ቤት ክልል ለመሆን ያሳለፈውን ውሳኔ ደኢሕዴን ለደቡብ ክልል ምክር ቤት እንዳይቀርብ አዘግይቷል ሲል የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን) ወቀሰ። ድርጊቱ «ኢ-ዴሞክራሲያዊ፣ ኢ-ፍትሐዊ እና ኢ-ሞራላዊ» ነው ያለው ንቅናቄው «የዎላይታ ብሔር ጥያቄ በአስቸኳይ ለክልሉ ምክር ቤት ቀርቦ ሕዝበ-ውሳኔ እንዲያደራጅ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲያስተላልፍ» በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።
ይኸ ካልሆነ ግን የዎላይታ ዞን ምክር ቤት በሕገ-መንግሥቱን የተቀመጠውን የጊዜ ገደብ ጠብቆ ውሳኔውን በራሱ ለማስፈፀም እንዲዘጋጅ ዎብን አሳስቧል። ዎብን እንዳለው የዞኑ ምክር ቤት ዎላይታ ራሱን የቻለ ክልል እንዲሆን ውሳኔ አስተላልፎ ሕዝበ-ውሳኔ እንዲዘጋጅ ለደቡብ ክልል ምክር ቤት የላከው ታኅሳስ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ነበር። https://www.facebook.com/dw.amharic/posts/2642979259068487
በመቐለ ሮማናት የተባለ አካባቢ የመኖሪያ ቤቶች ፈረሱ
በመቐለ ዙርያ ሮማናት ተብሎ የሚታወቅ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ 300 ገደማ ዜጎች መንግስት ሕጋዊ ሰነድ ያላቸው ቤቶቻች እያፈረሰ ነው ሲሉ ቅሬታቸው አቀረቡ። ያነጋገርናቸው ቅሬታ አቅራቢዎች በትላንትናው ዕለት ብቻ ከ200 በላይ የሚገመቱ ቤቶች "ሕጋዊ አይደሉም" ተብለው ፈርሰዋል ብለዋል፡፡ በዚህም ከፍተኛ የሀብት ውድመት እንደገጠማቸው ቅሬታ አቅራቢዎቹ ለዶይቼ ቬለ DW ተናግረዋል፡፡ ቤቶቹ የፈረሱበት አካባቢ አስተዳደር ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
የቪዲዮ ዘገባ፦ ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ https://www.facebook.com/dw.amharic/videos/444265266128989/
በኢትዮጵያ ከቢሾፍቱ አቅራቢያ በደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ቤተሰቦቹን ያጣው ፖል ኒጆርጌይ ኩባንያው ለአውሮፕላኖቹ ራሱ የበረራ ደሕንነት ማረጋገጫ እየሰጠ ጥፋት ፈጽሟል ሲል በዛሬው ዕለት በአሜሪካ ምክር ቤት ወቀሰ።

ቦይንግ በበኩሉ ከዚህ ቀደም ካዘጋጀው 100 ሚሊዮን ዶላር ግማሹን በኢትዮጵያ እና በኢንዶኔዥያ በደረሱ የ737 ማክስ አውሮፕላን የመከስከስ አደጋዎች ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች ድጋፍ እንደሚያውል አስታወቋል።

በኢትዮጵያ በደረሰው አደጋ ባለቤቱን፣ ሶስት ልጆቹን እና የባለቤቱን እናት ያጣው ካናዳዊው ፖል በአሜሪካ ምክር ቤት በበረራ ደህንነት ላይ በተጀመረ ምርመራ በምስክርነት ከቀረቡ መካከል አንዱ ነው።

ፖል ልጆቹ እና ቤተሰቦቹ አደጋው በደረሰበት የመጨረሻ ቅጽበት ያለፉበትን አሰቃቂ ኩነት እያሰላሰለ ዛሬም በከፍተኛ ሐዘን ውስጥ እንደሚገኝ ለምክር ቤቱ አባላት አስረድቷል። የቤተሰቦቼ ሥጋ ከኢትዮጵያ አፈር ተቀላቅሎ ቀርቷል ያለው ፖል አደጋው ሲደርስ አብሪያቸው በሆንኩ ኖሮ ሲል ምኞቱን በከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ሆኖ ገልጿል። በቦይንግ ኩባንያ ላይ የሰላ ትችት ያቀረበው ፖል የአውሮፕላኖችን ደኅንነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ አሳስቧል። የአሜሪካ ፌድራል የበረራ አስተዳደር ባለስልጣን አመራሮች ተቀይረው የደኅንነት መኃንዲሶች ኃላፊነቱን እንዲረከቡ ጥሪ አቅርቧል።

ቦይንግ በበኩሉ ከዚህ ቀደም ካዘጋጀው 100 ሚሊዮን ዶላር ግማሹን በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች ቤተሰቦች እንደሚሰጥ አስታውቋል። ቦይንግ ሒደቱን እንዲመሩ የቀጠራቸው የካሳ ክፍያ ባለሙያ ኬን ፋይንበርግ በዛሬው ዕለት እንደተናገሩት ቀሪው 50 ሚሊዮን ዶላር በመንግሥታት እና በማኅበረሰቦች ለሚመሩ ዕቅዶች የተዘጋጀ ነው ብለዋል። ፋይንበርግ የካሳ ክፍያ ለሚገባቸው የመጠየቂያ ረቂቅ ሰነድ ዝግጅት በፍጥነት ይጀመራል ብለዋል።👉🏾 @dwamharicbot
በኢትዮጵያው ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ቤተሰባቸውን ያጡ አንድ ግለሰብ ቦይንግ ስህተት የተሞላበት ባህርይ ያለው ኩባንያ ነው ሲሉ ከሰሱ። ዛሬ ስለ ጉዳዩ ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ንዑስ ኮሚቴ የተናገሩት ሦስት ልጆቻቸውን ባለቤታቸውን እና አማቻቸውን በአደጋው ያጡት ፖል ንጆርጌ የተባሉት እኚሁ ግለሰብ የኩባንያውን አውሮፕላን ብቃት የማረጋገጡ ሂደት መጠናከር አለበት ብለዋል።ኒጆርጌ የራሱ ፖሊስ ሆኖ እንዲሰራ ተለቋል ያሉት ቦይንግ፣ለማክስ አውሮፕላኑ እንደ አዲስ አውሮፕላን፣የማረጋጋጫ ሰርተፊኬት ሳያገኝ እንዲሸጥ መፈቀዱን ተናግረዋል።የአሜሪካ ፌደራል አቭየሽን አስተዳደር እንዲቀየር ፣የአውሮፕላን ደህንነትን የሚያረጋግጡ መሀንዲሶች ሥራውን በሃላፊነት እንዲያከናውኑ እና የአሜሪካን ምክር ቤትም የበጀት ጭማሪ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
ወይዘሮ አነግሬት ክራምፕ ካረንባወር ዛሬ በይፋ የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሰየሙ። ካረንባወር ሹመቱ የተሰጣቸው ትናንት የአውሮጳ ህብረት የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ኡርዙላ ፎን ዴር ላየንን የህብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት አድርጎ ከመረጠ በኋላ ነበር። ለካረንባወር ዛሬ የሹመት ደብዳቤያቸውን የሰጧቸው በእረፍት ላይ የሚገኙትን የጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየርን የተኩት የበርሊን ከንቲባ ሚሻኤል ሙለር ናቸው። በዚሁ ወቅት ባሰሙት ንግግርም ካረንባወር የጀርመንን ደህንነት የማስከበር ከባድ ሃላፊነት የተጣለበትን መሥሪያ ቤት ሃላፊነት ተረክበዋል ብለዋል። በዚሁ ሥነ-ስርዓት ላይ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና ፎን ዴር ላየን ተገኝተዋል። ካረንባወር በወቅቱ ባሰሙት ንግግር በወታደሮች ደህንነት ላይ ይበልጥ ለማተኮር ቃል ገብተዋል። የጀርመን ክርስቲያን ዴሞክራት ህብረት ፓርቲ ሊቀመንበር ወይዘሮ ካረንባወር የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ኃላፊነት ከመውሰድ ይልቅ፣ በፓርቲያቸው ጉዳይ ላይ ይበልጥ ማተኮር እንደሚፈልጉ ከዚህ ቀደም ተናግረው ስለነበረ የመከላከያ ሚኒስትርነትን ሃላፊነትን መቀበላቸው አስገርሟል።
በጠባብ ልዩነት ትናንት ማምሻውን የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ኡርዙላ ፎንዴር ላየን የመልካም ምኞት መግለጫዎች እየጎረፉላቸው ነው።እንኳን ደስ አለዎ ካሏቸው የአውሮጳ ሃገራት መሪዎች አንዷ የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ናቸው።ሜርክል በቃል አቀባያቸው በኩል በትዊተር ባስተላለፉት መልዕክት ፎን ዴር ላየን የመጀመሪያዋ ሴት የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት እና ከ50 ዓመትት በላይ በኋላ ለአውሮጳ ሥራ አስፈጻሚነት የበቁ የመጀመሪያዋ ጀርመናዊት ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸውላቸል።«ምንም እንኳን ለረዥም ጊዜ በሚኒስትርነት ያገለገሉትን ፎን ዴር ላየንን ባጣቸውም በብራሰልስ አዲሷ አጋሬ ይሆናሉ»ም ብለዋል።ፎን ዴር ላየን ለህብረቱ ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ እንዲበቁ ቁልፍ ሚና የተጫወቱት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑዌል ማክሮም በትዊተር «ዛሬ አውሮጳ ርስዎን አግኝቷል።እርሱም አብሮ መስራትን ትልቅ ዓላማ እና እድገት ነው።በአውሮPa መኩራት እንችላለን።»ሲሉ አወድሰዋቸዋል።ውጤቱን በደስታ ከተቀበሉት መካከል የግሪክ የኦስትርያ የፖላንድ እና የቤልጂግ መንግሥታትም ይገኙበታል።ብራሰልስ የተወለዱት ፎን ዴር ላየን የሚተኳቸው äዦን ክሎድ ዩንከር «ሥራው ከባድ ሃላፊነት ያለበት እና ፈታኝም ቢሆን ታላቅ ፕሬዝዳንት እንደሚሆኑ እርግጠኛ ነኝ፣እንኳን ወደ ቤትዎ ተመለሱ ብለዋቸዋል። የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንም በእንኳን ደስ አለዎ መልዕክታቸው የአውሮጳ እና የሩስያ አጋርነት በእኩልነት እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ያደርጋሉ ብለው እንደሚተማመኑባቸው ገልጸዋል። የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ቃል ኪዳን ድርጅት ናቶ ዋና ጸሐፊ የንስ ሽቶትንበርግ ደግሞ የርሳቸው የጠለቀ የመከላከያ ህብረት እውቀት የአውሮጳ እና የሰሜን አሜሪካን ትብብር ለማጠናከር ይረዳናል ሲሉ ተናግረዋል።ሳይታሰብ ለኮሚሽኑ ፕሬዝዳንትነት በታጩት በፎንዴር ላየን ሹመት ላይ ድምጻቸውን ከሰጡት 747 የአውሮጳ ህብረት የህዝብ እንደራሴዎች፣ 383 ቱ ነበሩ ይሁንታቸውን የሰጡዋቸው። የጀርመን ተጣማሪ መንግሥት አካል የሆነው የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ በምህጻሩ SPD ግን ድጋፉን ነፍጓቸዋል የፓርቲው አባል እና የጀርመን ምክትል መራሄ መንግሥት ኦላፍ ሹልዝ ግን እንኳን ደስ አለዎ ብለዋቸዋል።በህብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ለአምስት ዓመታት የሚያገለግሉት ፎን ዴር ላየን ትልቁ ሃላፊነታቸው ህብረቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ፖለቲካዊ ጉዳዮች መቅረጽ ነው።በስራቸውም ከ32ሺህ በላይ ሠራተኞችን ያስተዳድራሉ።
ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች በደቡብ ሱዳንዋ በአብዬ ግዛት አንድ የተመድ ሰላም አስከባሪ እና አምስት ሰላማዊ ሰዎች መግደላቸው ተነገረ። የተመድ ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የተገደለው ሰላም አስከባሪ፣ ኢትዮጵያዊ ወታደር ነው። ሌሎች 5 ሰላማዊ ሰዎችም በጥቃቱ ተገድለዋል። አንድ ደግሞ ቆስሏል። በተመድ መግለጫ መሠረት ግድያው የተፈጸመው ሰላም አስከባሪዎቹ መደበኛ ቅኝት በማድረግ ላይ ሳሉ ነው። የአብዬ አስተዳዳሪ እንዳሉት ትናንት ከአብዬ በስተሰሜን በሚገኝ የገበያ ቦታ በተፈጸመው በዚሁ ጥቃት ከሞቱት መካከል አንድ ህጻን ይገኝበታል። በአወዛጋቢዋ በአብዬ ግዛት ከደቡብ ሱዳን ጋር መቀላቀል በሚፈልጉ እና ከሰሜንዋ ሱዳን ጋር መሆን በሚሹ መካከል ግጭት ሲካሄድባት ቆይቷል። ከጎርጎሮሳዊው 2011 አንስቶ የተመድ «ለአብዬ ጊዜያዊ የፀጥታ ኅይል» በምህጻሩ «UNISFA» የተባለ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ አሰማርቷል።